School of Indiana(Alembank Branch) @schoolofindiana Channel on Telegram

School of Indiana(Alembank Branch)

@schoolofindiana


Education is a key of success!!
Dear parents, Click on grade level of your child to get all the necessary materials.

School of Indiana(Alembank Branch) (English)

Welcome to the School of Indiana, Alembank Branch! Education is the key to success, and we are dedicated to providing quality learning resources for your child. Our Telegram channel, @schoolofindiana, is here to support parents in helping their children excel academically. Whether your child is in elementary school, middle school, or high school, we have all the necessary materials to aid in their education. Simply click on the grade level of your child to access a wide range of resources, including practice worksheets, educational videos, study guides, and more. Our team of experienced educators is committed to ensuring that your child receives the best education possible, both inside and outside the classroom. Join our Telegram channel today and give your child the tools they need to succeed!

School of Indiana(Alembank Branch)

18 Feb, 09:44


ለውድ ወላጆች በሙሉ
የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን የተወሰኑ ወላጆች የወላጅ-መምህር ግንኙነት መፅሓፍን (Communication Book) በተመለከተ በሰጣችሁን አስተያየት  መሠረት ከደብተር እና ከት/ቤቱ ሲስተም(Online) በተጨማሪ ት/ቤቱ ባለፉት ዓመታት ይጠቀምበት የነበረውን ኮሚኒኬሽን መፅሓፍ መጠቀም የምቻልበት ሁኔታ ቢፈጠር በመባሉ ከዚህ መልዕክት ጋር አያይዘን ሶፍት ኮፒውን ስላስቀመጥን ኘሪንት በማድረግ አስጠርዛችሁ በልጆቻችሁ በኩል ለክፍል ኃላፊ መምህራን በመላክ ከሁለተኛ ሴሚስቴር(3ኛ ሩብ ዓመት) ጀምራችሁ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
                        ት/ቤቱ

School of Indiana(Alembank Branch)

13 Feb, 11:28


ሠላም ውድ ወላጆች(አሳዳጊዎች) ከላይ ያሉትን ቃላት(Spelling) ባሉት የእረፍት ቀናት ልጆቻችሁን አስጠንታችሁ ለስፔሊንግ ቢ ውድድር(Spelling bee computation) ዝግጁ እድታደርጉ ስንል መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን። ት/ ቤቱ

School of Indiana(Alembank Branch)

03 Feb, 15:24


ማስታወሻ
ነገ የሰድስተኛ ክፍል እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ትምህርታዊ ጉዞ እንዳላቸዉ ቀደም ብለን በላክነዉ መልዕክት ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡
በ መሆኑም ሁሉም የጉዞዉ ተሳታፊ ተማሪዎች 1፡30 ላይ ትምህርት ቤት ግቢ እንዲገኙ እንዲሁም ተገቢዉን የድንብ ልብስ እና ምግብ ይዘዉ እንዲመጡ እናሳስባለን፡፡
ለ ነገዉ ጉዞ ከ ተማሪዎች ጋር የሚሄዱ መምህራን
1. መ/ር ሮቤል ደቻሳ 0910214766
2. መ/ርት ሃና ሽመልስ 0912388392
3. መ/ርት አባነሽ ካሳ 0912002063
4. መ/ር ነጋሽ 0982767465
5. መ/ር ጥላነህ 0955084140
6. መ/ርት የኔነሽ 0954452299
7. መ/ር በላይነህ 0915259588

School of Indiana(Alembank Branch)

24 Jan, 15:41


መልዕክት ለ ወላጆች
በ ነገዉ ዕለት በ 17/05/2017 ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል ማጠናከሪያ ትምህርት የማይኖር መሆኑን እያሳወቅን ተማሪዎች ሰኞ ለሚጀመረዉ የማጠቃለያ ፈተና በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የተለመደዉ ክትትሎ እንዳይለይ ለማስታወስ እንወዳለን፡፡

School of Indiana(Alembank Branch)

16 Jan, 10:31


Well done

School of Indiana(Alembank Branch)

16 Jan, 08:39


ትምህርት ቤታችን በ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በተለይም በአቅመ ደካማ ወገኖቻችን ቤት እድሳት ላይ ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡ በ ያዝነው የ2017 የትምህርት ዓመትም ይህን ተግባሩን አጠናክሮ በ መቀጠል አጠቃላይ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ በማስተባበር አቅም የመፍጠር ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡
በ07/05/2017 ዕለትም በይፋ የእናታችንን ቤት የማደስ ስራዎችን አስጀምረናል፡፡ ለዚህም ስራ መሳካት ድጋፍ ያደረጋችሁልንን እያመሰገንን አጠቃላይ ዕድሳቱ እስከሚጠናቀቅ ከጎናችን እንደምትሆኑ እንተማመናለን፡፡
በ ቀጣይም የተሰሩ ስራዎችን እንደምናሳውቃችሁ እንገልፃለን፡፡

School of Indiana(Alembank Branch)

16 Jan, 08:29


በአቃቂ ቃሊቲ ክፋለ ከተማ ወረዳ1 አስተዳደር እና ስኩል ኦፍ ኢንዲያና ትምህርት ቤት በጋራ በመሆን በወረዳ 01 አስተዳደር የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት አስጀመሩ፡፡

ጥር 7/2017 የአቃቂ ወረዳ 01 ኮሙኒኬሽን

በአቃቂ ቃሊቲ ክፋለ ከተማ ወረዳ1 አስተዳደር እና ስኩል ኦፍ ኢንዲያና ትምህርት ቤት በጋራ በመሆን በወረዳ 01 አስተዳደር የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ቀጠና 5/1 የሚኖሩ የአንድ አረጋዊት እናት ቤት እድሳት ዛሬ አስጀምረዋል፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፋለ ከተማ ወረዳ 1 ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ወልዴ እንደገለፁት አቅመ ደካሞችን መርዳትና ማገዝ ለአእምሮ ሰላምና ደስታ የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ ማንኛውም የተሻለ አቅም ያለው ምንም ለሌለው አቅም በመሆን ለሰዎች ደስታ በመፍጠር ሰው ተኮር የሆኑ የበጎ ፍቃድ ሥራዎቻችንን በመተባበር ማስቀጠል ይገባል ያሉ ሲሆን በዚህ የበጎ ሥራ የተሰማሩትን ተቋማት በሙሉ አመስግነው፤ ሌሎችም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተመሳሳይ እገዛና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አቅመደካሞችና አረጋውያንን በቻልነው አቅም ሁሉ በመደገፍ በጎ የመስራት ባህላችንን ማሳደግ ይገባናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ቤታቸው የሚታደስላቸው አረጋዊት እናትም የሚረዳቸው ተማሪዎችና ትምህርት ቤት አቅም የሌላቸው በመሆናቸው ለሚደረግላቸው በጎ ተግባር አመስግነዋል፡፡

#አቃቂ_በለውጥና_በውጤት_ጎዳና!

School of Indiana(Alembank Branch)

07 Jan, 17:01


የማክበር ሠላምታችንን እያቀረብን የሁለተኛ ሩብ ዓመት እና የጥር ወር የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ያላጠናቀቃችሁ ወላጆች በዚህ ሳምንት እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን።
ትምህርት ቤቱ

School of Indiana(Alembank Branch)

02 Jan, 13:53


Great we are proud of you

School of Indiana(Alembank Branch)

27 Dec, 14:20


መልዕክት ለ 12 ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች
እንደሚታወቀዉ ተማሪዎች ለ ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት የማጠናከሪያ ትምህርት እየወሰዱ ይገኛል፡፡ ይህን መርሀግብር በተሻለ መልኩ ለማካሄድ እንዲሁም ተማሪዎች በቂ የጥናት ጊዜ በ ቤታቸዉ እና በ ቤተመፀህፍት እንዲኖራቻዉ በ ማሰብ የ ማክሰኞ እና የሀሙስ መርሀግብር በ ማስቀረት በ ቅዳሜ ግማሽ ቀን እንዲቀየር ተወስኖል በ መሆኑም ከ ነገ 19/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ የማጠናከሪያ ትምህርቱ የሚጀምር መሆኑን እያሳወቅን ተገቢዉን ክትትል እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡

School of Indiana(Alembank Branch)

24 Dec, 15:33


መልዕክት ለ ሁለተኛ ደረጃ ወላጆች
ከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ግቢ ከ ገቡ በኃላ በተለያዩ ምክንያቶች ለ ወላጅ እያስደዉሉ የመመለስ ባህሪያቶችን አስተዉለናል፡፡
በ መሆኑም ይህን ተግባር የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ከገመገመ በኃላ የሚከተሉትን ዉሳኔዎች አስተሳልፎል
1. ማንኛዉም ተማሪ በህክምና ክፍል የተረጋገጠ ድንገተኛ ህመም ካላጋጠመዉ በስተቀር ከ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ መዉጣት እንደማይችል
2. በተለያዩ ሁኔታዎች ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ግቢ የሚወጡበት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወላጆች በ አካል በ መምጣት ብቻ ተማሪዎቹ መዉጣት እንደሚችሉ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

School of Indiana(Alembank Branch)

23 Nov, 06:59


ለ2ኛ ደረጃ ተማሪ ወላጆች
የመጻሕፍት ክፍያ የምትፈጽሙት ለሁሉም መጻሕፍት መሆን እንዳለበት ለማሳሰብ እንወዳለን። መጻሕፍት ለይቶ በምርጫ መግዛት የማይፈቀድ መሆኑን እናሳስባለን።
ከሠላምታ ጋር

School of Indiana(Alembank Branch)

12 Nov, 08:04


School payment code for students.

School of Indiana(Alembank Branch)

11 Nov, 06:55


Ok

School of Indiana(Alembank Branch)

11 Nov, 06:52


የተከበራችሁ የስኩል ኦፍ ኢንዲያና ወላጆች የ2ኛው ሩብ አመት የትምህርት አገልግሎት ክፍያ የተጀመረ ሲሆን የክፍያ ወቅቱ ከህዳር 1 - 20 መሆኑን አዉቃችሁ ከወዲሁ እንድትከፍሉ እየጠየቅን ወቅቱ ካለፈ በቀን 20 ብር ቅጣት የሚኖር መሆኑን ከአክብሮት ጋር እናሳስባለን ::

School of Indiana(Alembank Branch)

31 Oct, 13:55


መልዕክት ለ ወላጆች
የ2016 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ዉጤት ወረቀት ስለመጣ ተማሪዎች ከነገ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በ አካል በመምጣት ከ መረጃ ዴስክ ዉጤታችሁን መዉሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

School of Indiana(Alembank Branch)

29 Oct, 08:29


Students login manual.pdf

School of Indiana(Alembank Branch)

25 Oct, 17:49


https://schoolofindianaofficial.com/register/

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:57


https://t.me/SOIAlembankGr12N

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:57


https://t.me/SOIAlembankGr11

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:57


https://t.me/SOIAlembankGr10

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:56


https://t.me/SOIAlembankGr9

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:56


https://t.me/SOIAlembamkG8

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:56


https://t.me/SOIAlembamkG7

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:56


https://t.me/SOIAlembamkG6

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:56


https://t.me/SOIAlembamkG5

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:56


https://t.me/SOIAlembankKG3

School of Indiana(Alembank Branch)

19 Sep, 07:56


https://t.me/SOIAlembankKG2