እኔ ግን ዳንኩ
የሆነ ግዜ ሱስ ጀመርኩ ጫት ሲጋራ መጠጥ ፊቴን እስኪቀይረው ተከተብኩ አዬ መና ቀረ ተባልኩ
እኔ ግን ሱስ አቆምኩኝ ።
የሆነ ቀን ጓደኞቼ ሁሉ አልፈው እኔ አስረኛ ክፍል ወደኩ ሁሉም በጋራ አዘኑልኝ ብለን ነበረ አሉኝ ሰፈር ቀረ አሉኝ እኔ ግን ተመልሼ private ተፈትኜ አልፌ እስከሁለተኛ ድግሪ ድረስ ተማርኩ
የሆነ ግዜ እናቴ ለቆሶ ልቴድ ፈልጋ ነጠላ ስትበደር አይቻት እኔ ሳድግ አምስት ቅያሪ ነጠላ እገዛልሻለሁ አልኩኝ የሰሙ ሰዎች ሳቁብኝ ለምን እንደሳቁ አላቅም እኔ ግን ስራ ስይዝ አረ አምስት ነጠላ ምን ይሰራል እያሉኝ ጥለቱን እየቀያየርኩ ገዛው ....
ትላንት ብዙ አይሆንምን አልፌያለሁ ። ብዙ አበቃለትን ተሻግርያለሁ ፣ ነገ የተሻለ እንደሚሆን ትላንት ምስክሬ ነው!!
ተመስገን ነጋ ተነሱ🌤
@Yaletnka_Hasab🍂