Últimas publicaciones de Roha Tv/ሮሃ ቴቪ (@rohatv1) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ
ትኩስ ወቅታዊና ታአማኒ መረጃዎችን የሚያገኙበት
ሮሃ ቴቪ የሀገሬው
8,730 Suscriptores
727 Fotos
95 Videos
Última Actualización 06.03.2025 17:16

El contenido más reciente compartido por Roha Tv/ሮሃ ቴቪ en Telegram

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 14:07

2,257

⁠6. ይህንኑ⁠ በመረዳት፣ ድርድርም ባይሆን፣ በቅርቡ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ተወካዮች ጋር ተነጋግረናል በሚል ያሳወቁት ቡድኖችም ሆኑ ሁሉም የፋኖ ኃይሎች፣ የዐማራውን የህልውና ጥያቄ ለመፍታት፣ ሥርዓታዊ ለውጥ ማረጋገጥን ባላቀፈ እና አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ባላሟላ፣ አካታችም ባልሆነ፣ በማንኛውም ዓይነት ይፋዊም ሆነ ምስጢራዊ ውይይት ወይም ድርድር እንደማይሳተፉ የማያወላውል ማረጋገጫ እንዲሰጡ አጥብቀን
እንጠይቃለን::

7. ከዚህም ጋር ተያይዞ፣ ሁሉም የፋኖ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን አቻችለው፣ ከግለሰብ ወይም የቡድን ፍላጎት በላይ የሕዝባቸውን ህልውና በማስቀደም፣ በአስቸኳይ ኅብረት ለመመሥረት የሚያስችል ውይይት እንዲያደርጉ አጥብቀን እንጠይቃለን:: በዚህ ረገድ፣ የዐማራ ዲያስፖራ ግሎባል ፎረም እስካሁን ሲያደርግ የቆዬውን ያላሰለሰ ጥረት እንደሚቀጥልና ወደፊትም የሚጠየቀውን ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነቱን የሚገልጸው በታላቅ ቁርጠኝነት ነው::

8. በዓለም ዙሪያ የሚኖሩት የዐማራው ሕዝብ የህልውና ትግል ደጋፊ ዲያስፖራ አባሎች፣ ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ የተደረሰበት እድገት ተጨናግፎ፣ የዐማራ ሕዝብ ሰቆቃ እንዳይቀጥል፣ ማንኛውንም ከፋፋይ እርምጃ አንዲቃወሙ፤ ከመሳተፍም እንዲቆጠቡ፤ አጥብቀን እናሳስባለን። ይልቁንም፣ በአንድ ጃንጥላ ሥር ተሰባስበው፣ የፋኖ አደረጃጀቶችም በህበረት ተናብበው ትግሉን እንዲያራምዱ፣ የሚያስፈልግውን የገንዘብ፣ የቁሳቁስ፣ የዲፕሎማሲ እና የገንቢ ሃሳብ ድጋፍ በማድረግ፣ ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን።

የዐማራ የህልውና ትግል ያሸንፋል!
ድል ለፋኖ!
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 14:06

2,361

ውይይትና ድርድርን በተመለከተ የዐማራ ዲያስፖራ ዓለም ዓቀፈረ ፎረም የአቋም መግለጫ!

የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም.

ሰሞኑን በተለያዩ መድረኮች ላይ እንደተገለጸው፣ አንዳንድ የፋኖ ቡድኖች፤ ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ከኢጋድ
(IGAD)፣ እና ከአሜሪካ መንግሥት ተወካዮች ጋር በወሎ ዳውንት ውስጥ ግንኙነት አድርገው እንደነበር ለመረዳት
ተችሏል። ግንኙነቱም ድርድር ወይም የድርድር ቅድመ-ዝግጅት ይሆናል በሚል ግንዛቤ ከተለያዩ አቅጣጫዎችም ስጋት
ተገልጿል።

ለዚህም ፍራቻ እንደ ተጨማሪ ጠቋሚነት የሚቀርበው፣ በግንኙነቱ የአፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ ተወካዮች ተሳታፊ መሆናቸው ነው:: ሆኖም፣ ግንኙነቱን ያደረገው ቡድን መሪዎች በዲፕሎማሲና ሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ የተደረገ ውይይት እንጂ ምንም አይነት የድርድር ሥራ እንዳልተካሄደ በመግለጽ አስተባብለዋል:: የሆነው ሆኖ፣ የዐማራው ሕዝብ የተደቀነበትን ሥርዐታዊ የህልውና አደጋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገርስሶ ለመጣል ከፍተኛ
መሥዋዕትነት እየከፈለ በሚዋደቅበት በአሁኑ ወሳኝ ወቅት፣ ማንኛውም ወቅቱን ያልጠበቀና ምስጢራዊ ድርድር ወይም የቅድመ ድርድር እንቅስቃሴ፣ ትግሉን አደናቅፎ የዐማራውን ሕዝብ ለዘለዓለም ባርነት የሚያጋልጥ መሆኑ ሊካድ የማይችል ሐቅ ነው።

ስለሆነም፣ ውይይትንም ሆነ ድርድርን በተመለከተ የማያሻማና ብዥታ የሌለው፣ ጥርት ያለ አቋም በሁሉም የዐማራውን የህልውና ትግል እመራለሁ በሚል ቡድንም ሆነ በሚደግፍ ወገን ዘንድ መያዙ አስፈላጊ ነው።

የአገዛዙ ጦር የሞራል እና የውጊያ አቅሙ ተዳክሞ፣ የፀረ ዐማራው ሥርዐት በውድቀት አፋፍ ላይ እያቃሰተ በሚገኝበት ሰዐት፣ ወንጀለኛው መንግሥት ከዚህ ውድቀቱ ተንሰራርቶ ወደ ተለመደው የዐማራን ዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመመለስ ከሚጠቀምባቸው ስልቶች ዋናው መንገድ፣ የተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶችን ከፋፍሎ፣ በድርድር እና በውይይት ስም አዘናግቶ ማኮላሸት እንደሆነ ካለፉት የቅርብ ጊዜ የክህደት ታሪኮቹ መረዳት አዳጋች አይሆንም።

የድርድር ዓለማቀፍ ተሞክሮም ቢሆን የሚያሳየው፣ አገዛዞች አንድ ሆኖ ከቀረበ ተደራዳሪ መካከልም እንኳን በጥቅም፣
በድብቅ ፍላጎት ወይም በሥልጣን ሽሚያ የተለያዩ ፍላጎቶች ያሏቸው ተለይተው፣ ተደራዳሪውን በመከፋፈል የድርድር አቅምን ለማሳጣት እና የእነሱን ፍላጎት ለመጫን፣ በስኬት የሚጠቀሙበት የከፋፍለህ ምታ ስትራቴጂ ዋናው መሣሪያቸው
መሆኑን ነው። የታላላቆቹ መንግሥታት ተቋማት ደግሞ በዚህ የመቶ ዐመታት ልምድ ያካበቱና፣ ሚዛኑ በእጅጉ ወደ እነሱ ያጋደለ ነው። በዚህ መሠረት፣ ገና ከወዲሁ ተነጣጥሎ ለዚህ ጥቃት ተጋላጭ መሆን፣ በፋኖ እና በዐማራው ትግል ላይ የሚያስከትለውን አደጋ መገንዘብ ያስፈልጋል።

የዐማራ ዲያስፖራ ግሎባል ፎረም በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደገለጸው፣ የዐማራውን ህልውና የማረጋጥንም ሆነ፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የሥርዐት ለውጥ የማምጣትን ጥያቄ የማይመልስ፤ የፋሺስታዊዉን አገዛዝ ዕድሜ የሚያራዝምና በጥገናዊ ለውጥ
የዘረኛውን ሥርዐት በማስቀጠል ዐማራውን ለከፋ ዕልቂት፣ አገሪቷንም ጨርሶ ለመፍረስ የሚዳርግ ድርድር ወይም ውይይት፣ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም:: በመሆኑም፣ ዘላቂ ውጤት ሊገኝ የሚችለው፣ መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው፣ በተለይም የዐማራ ህልውና ትግል መሪዎች የሆኑትን የፋኖ አደረጃጀቶች አንድነት ተከትሎ፣ በግልፅ መርህና የኃይል የበላይነት ላይ ተመርኩዞ ሲከናወን ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ፣ በይበልጥም የፋኖን አንድነትና ጥንካሬ አደጋ ላይ
ሊጥል በሚችልና፣ ከስር-ነቀል ሥርዐታዊ ለውጥ ማምጣት ዉጪ፤ የጥቂቶችን የስልጣን ፍላጎት ለማርካት፣ ወይም በውጭ ኃይሎች ግፊት ጊዜያዊ እፎይታን ለማምጣት የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ በጥብቅ ሊወገዝ ይገባል:: ከዚህም አኳያ፣
ፎረሙ ከዚህ በታች የተገለፀውን አቋም ለፋኖ መሪዎችም ሆነ ለመላው የዐማራ ሕዝብና የትግሉ ደጋፊዎች ሁሉ ይገልጻል::

1. የዐማራ ሕዝብ ባለፉት ብዙ አስርት ዓመታት በተለያዩ መንግሥታት ያጋጠመው የህልውና አደጋ የሚወገደው፣ በሥርዐት ለውጥ እንጂ፣ በክልልም ሆነ በብሔራዊ ደረጃ በሚደረግ የስልጣን ክፍፍል ሂደት፣ ወይም በአጠቃላይ በአገሪቱ የጥገና ለውጥ በማድረግ አይሆንም:: በስልጣን ላይ የሚገኘው የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ መንግሥት፣ የዐማራን ሕዝብ በግልፅ ለማጥፋት ወስኖ በመነሳት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ አረመኔአዊ ጦርነት ከፍቶ፣ በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መጠን በዐማራ ሕዝብ ላይ የዓለም አቀፍ ሕግጋትን የጣሰ ወንጀል እየፈፀመ ይታያል::

2. ⁠በአንጻሩ የዐማራ ሕዝብ እያካሄደ በሚገኘው ራስን የመከላከል ጦርነት አገዛዙን ድል እየመታ፣ ኃይሉን እያጠናከረ በመገስገስ ላይ ይገኛል:: በዚህ ሁኔታ፣ አገዛዙ ወደ ድርድር ለመግባት ፈቃደኛ መስሎ ቢቀርብም፣ ዋናው ዓላማው ፋኖን በመከፋፈል፣ እንቅስቃሴውን ማዳከምና በትናንሽ መደለያዎች ማኮላሸት እንጂ፣ የችግሩ ሁሉ ምንጭ የሆነውን የጎሳ-ጥላቻ ሥርዐት በውዴታ ከሥር መሰረቱ ቀይሮና ስልጣኑን አስረክቦ፣ የዐማራውን መብትና ክብር ተቀብሎ እኩልነትን፣ ዲሞክራሲንና ፍትህን በአገሪቱ ለማስፈን አይደለም::

3. ⁠ምንም⁠ እንኳን ግጭቶችን በሰላምና በድርድር ለመፍታት መጣር ተመራጭና ተጨማሪ የሕይወት መስዋዕትነትና
ውድመት እንዳይኖር የሚረዳ ቢሆንም፣ በስልጣን ላይ ያለው ወንጀለኛ መንግሥት እስካሁን በተግባር ያረጋገጠው ምግባር፣ ሸፍጥ እና ተንኮልን የተጎናፀፈና፣ በባህርዩም ለችግሩ መሠረታዊ መፍትሄ ለማግኘት የፈቃደኝነት ዝንባሌ በፍፁም የማይታይበት ነው። ስለዚህ፣ የግጭቱን መሠረታዊ ምክንያቶች የማያስወግድ፤ በመንግሥት መዋቅር ተደግፎ በዐማራው ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃትና፣ ባለፉት ስድስት ዐመታት ለተፈፀመው የሰብአዊ መብት
ጥስት ወንጀል ሙሉ ተጠያቂነትን የማያረጋግጥ እና፤ በአንድነት የተሰለፉ የፋኖ ኃይሎች በትጥቅ ትግል በተገኘ
የበላይነት ላይ ተመርኩዘው የማይመሩት፣ ማንኛውም የሰላምና የድርድር ተግባር ስኬታማ ሊሆን አይችልም:: ይልቁንም በተቃራኒው የዐማራን የህልውና ትግል አጨናግፎ፣ ሕዝቡንም ለባሰ ሰቆቃና ስቃይ የሚያጋልጥ ይሆናል::

4. በዚህም⁠ መሠረት፣ የዐማራውን ሕዝብ የህልውና ትግል የሚያደናቅፍ፣ ወይም ዘረኛውን ፀረ -ዐማራ ሥርዓት ለማቆየት የሚደረግ፣ ማንኛውንም በሽግግር ወይም በለውጥ ስም የሚካሄድ ውይይትን ወይም ድርድርን፣ የዐማራ ዲያስፖራ ግሎባል ፎረም አጥብቆ ይቃወማል:: የዐማራው የህልውና ትግል መሠረታዊ ምክንያቶች በሥር-ነቀል ለውጥ ተፈትተው፣ ወንጀለኞች ለፍትህ እንዲቀርቡ መደረግ፣ የፋኖ ኃይሎች እና የዐማራ ሕዝብ ወደ ኋላ ሊሉ የማይችሉበት አቋም እንደሆነም ያምናል::

5. የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም ከከፋፋይ አድራጎቶች ተቆጥቦ፣ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ጥረት እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ማሳሰብ ግዴታ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ እንደተደረገው የፕሪቶሪያ ዓይነት የችኮላ፣ የማግለልና የቆረጣ ስምምነት፣ ከዘላቂ መፍትሄ ይልቅ ችግሩን አባብሶ፣ የሕዝቡን መከራ ከማራዘም በስተቀር ፋይዳ ያለው ውጤት እንደማያስገኝ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 12:36

2,498

በወሎ የተመረቀው ግዙፍ ጦር

የአማራ ፋኖ በወሎ ( ቤተ አማራ) ከአንድነት ማግስት ግዙፍ ጦር አስመረቀ
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የልጅ እያሱ ኮር ቤተ አማራ ክፍለጦር ለበርካታ ወራት ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ፋኖዎችን አስመርቋል፡፡
ከአምባሰል ተራራ ስር በተንጣለለ ሜዳ ላይ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ጦር የብልጽግናን አገዛዝ ከቀጠናው የሚያስወጣ እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡
በምረቃ ዝግጅቱ ላይ አርበኛ ድርሳል ብርሃኔን ጨምሮ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ አርበኛ ሰለሞን አሊ በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት “ አገዛዙ የአማራ ህዝብ ላይ የህልውና አደጋ የደቀነ የዘር ማጥፋት እያካሄደ መሆኑ ለትግላችን መነሻ ነው” ብሏል፡፡
ከዘላለም ባርነት የነጻነት ሞት የበለጠ ክብር ስላለው ሁላችንም ተባብረን አገዛዙን ልንጥለው ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡
ይህን ምረቃ ልዩ የሚያደርገውም ወደ አንድ ከመጣን በኋላ መሆኑ ነው ሲል ገለጿል፡፡
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 10:48

2,644

አብይ አህመድ በኤርትራ የተወረሱ የጦር መሳሪያዎችን ለማስለቀቅ ያላደረገው ሙከራ እና ልመና የለም። የብልፅግናው ቡድን ስለ ጉዳዩ በብዙሃን መገናኛ ከማስትባበሉ በተጨማሪ በአምባሳደሮች፣ በውጭ ዲፕሎማቶች እና በተለያዩ መንገዶች ለማግባባት እና ለማባበል ሞክሯል፤

ኤርትራ ግን ብልፅግናን ከትግራይ ጋር ጦርነት በምታደርግበት ግዜ የተበደርከኝን የጦር መሳሪያ ባለመመለስህ ለዚህ ማካካሻ ይሆነኛል ብላለች።

ልብ በሉ ቀይ-ባህርን አስመልሳለሁ እያለ ሲፎክር የነበረው ብልፅግና ሌላ የጦር መሳሪያውንም አስረክቧል።

ምክንያቱም አብይ አህመድ እና አገዛዙ ፈሪ ነው። ፈሪ ስለሆነም የፈሪ ዱላውን የሚያሳርፈው ንፁሃኖች ላይ ነው።

ብልፅግና የታጠቁ ኃይሎችን አይገጥምም‼️
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 07:53

2,745

https://youtu.be/vh0EGF5Q4nQ?si=YsK009s2tC_-OMU7
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

02 Feb, 17:07

2,276

በሰላም እረፍ!
በዶክተር Gashu Kindu የተፃፈ!

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው በትናትናው እለት በአብይ አህመድ የብልፅግና ሰራዊት በግፍ ተገድሏል። ይህ ለ50 ሆስፒታሎች፣ 509 ጤና ጣቢያወች፣ 1850 ጤና ኬላወች፣ ከ350 በላይ አንቡላሶች፣ 338 የጤና መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መዘረፍ፣ ስራ ማቆም እና መቋረጥ ምክንያት የሆነዉ የጥቁር ናዚ ስርዓት ዛሬም እንደ ትናነቱ የህክምና ባለሙያወች ላይ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት አድርሷል፤ ህይወታቸውን ቀጥፏል፤ እንዲሁም ብዙ የህክምና ባለሙያዎችን ፋኖን አክማችሗል በማለት በየማጎሪያ ቤቱ አስሮ ቶርች እያደረጋቸው ይገኛል።

እንደ ሲዲሲ፣ ሜሊንዳ ጌትስ ፋዉንዴሽን፤ ግሎባል ፈንድ እና ከመሳሰሉ አለም አቀፍ ተቋማት የሚያገኘዉን የጤና ፕሮግራም የፋይናንስ ድጋፍ ከታለመዉ አላማ ዉጭ ለሚኒሻ፣ አድማ ብተናና የመረጃ ሰራተኞች ደሞዝ እና የዉሎ አበል እያፈሰሰ የሚገኘዉ ይህ ስርዓት፤ ለጤናዉ ስርዓት መጠናከር የጀርባ አጥንት የሆነዉን የፋይናንስ ሀብትና እና የተማረ የሰዉ ሀይል ለብልሹ አሰራር፣ ለእስር፣ ለግድያና ለስደት በመዳረግ የክልሉን የጤና አገልግሎት እያዳከመዉ ይገኛል።

Rest in peace!

Dr. Andualem Dagne, a surgeon and a liver, pancreas and bile duct sub-specialist at Bahir Dar University College of Medicine and Health Sciences, was brutally murdered by Abiy Ahmed’s Prosperity Army on the night before. Ahmed's prosperity army has led to the looting, shutdown and interruption of 50 hospitals, 509 health centers, 1850 health posts, more than 350 ambulances, and 338 health infrastructure projects in the Amhara region of Ethiopia. This 'Black Nazi Regime,' which has caused physical and psychological harm to thousands of medical professionals, has taken their lives and is also imprisoning many medical professionals in concentration camps, claiming that they have treated injured Fano Freedom Fighters.

This regime, which is spending the foreign financial support of the health programs received from organizations such as the CDC, Melinda Gates Foundation, and the Global Fund on salaries and allowances of militia and intelligence personnel, is weakening the delivery of the health services in the region by mismanaging financial resources and deporting the educated and skilled workforce that is the backbone of the health system.
©Asres Mare Damtie
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

02 Feb, 15:46

2,020

#የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ለስድስት ወራት ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ልዩ ምልምል የኮማንዶ ሰልጣኞችን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ

የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ቢትወደድ  መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ለስድስት ወራት ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ልዩ ኮማንዶ ምልምል ሰልጣኞችን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።

በዚህ የምረቃ ስነ ስርአት ላይ የተከኙት የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ግሩም ምሳሌ ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ስለሺ ከበደ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም የውጭና ዲያስፖራ ጉዳዮች ም/ኃላፊ አርበኛ ኃይለሚካኤል ባዬ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ሰብሳቢ አርበኛ ዘመን ተሻለ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ክፍለ ጦር ም/ሰብሳቢ አርበኛ ጌራ ወርቁ፣ እንዲሁም የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ አሌ ባይህ በቦታው ታድመዋል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረገው አርበኛ ስለሺ ከበደ የሚከተለውን መልዕክት ለተመራቂዎቹ አስተላልፏል ።

የአማራ ህዝብ ለበርካታ አስርት ዓመታት ፍትህን ከገዥወቹ ሲለምን የኖረበት ሂደት ተጠናቆ ይህ ትውልድ መብቱን በክንዱ ሊያስከብር በቁርጠኝነት በተነሳበት ዘመን ላይ ላይ በመሆናችሁ የዚህ ዘመን ልዩ ትውልዶች እና እድለኞች መሆናቸውን፤

ትግሉ የተጀመረውም ሆነ የተቀጣጠለው ለተራ የስልጣን ጥያቄ ሳይሆን እንደ ሰው ተፈጥሮ ትውልድን የማስቀጠል ህልውና ሙሉ በሙሉ የመጥፋት ጥቃትን የመከላከል፣ ትውልድን ሳይጠፋ የማስቀጠል
ትግል በሆነበት ወቅት ላይ መቀላቀላቸው ልዩ ያደረጋችኃል።


ትግሉ ከአማራ ህዝብ ነፃነት አልፎ አጠቃላይ የምስራቅ አፍሪካን መልክዓ-ፖለቲካ ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ትግል ሲሆን በይዘቱም አለም አቀፋዊ አጀንዳዉ እና የሃይሎች አሰላለፍ ከ50 እና 60
ዓመት በኋላ በተፋጠጠበት ወሳኝ ወቅት ላይ በመሆኑ
ሃገራዊም አህጉራዊም ጭምር በሆበት የታሪክ መታጠፊያ ላይ መቀላቀላቸውን  ልዩ ያደረጋችኃል።

ትግሉ በታሪክ እደታየ እንዳለፈው ጥቂት  ጊዜ የመላው ህዝብ ትግል ጭምር የሆነበት ወቅት መቀላቀላቸው ልዩ ያደረጋችኃል።

ትግሉ አድማሱን እያሰፋ ከክልል ወደ ሃገር ፤ከሃገር ወደ አፍሪካ ቀንድ ቀጥሎም አህጉራዊና አለም አቀፋዊ አሰላለፍንና ፍጥጫን ተወዳድሮ አሸንፎ   በሚወጣበት ወሳኝ ወቅት መሆኑን ልዩ ያደርጋችኃል።


ከትግሉ ፍጥነትና ከሁኔታወች ተለዋዋጭነት አንፃር ትግሉን ከሚሸረሽሩ ሰብአዊ ድክመት ራስን መጠበቅ፤  ከቁሳዊ ፍላጎቶች እራስን በማራቅ ቅዱስ የሆነውን አላማ በፅናት ማስቀጠል፤ በተለያዬ መልክ በየጊዜው የሚመጡ ግላዊም ሆነ ቡድናዊ ስሜቶች ራስን በማራቅ በአላማ ፅናት ትግሉን ማስቀጠል የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሰጥበት ውቅት ላይ  መመረቃችሁ ልዩ ያደረጋችኃል።
ትግሉ በተለያዩ አመርቂ ድሎች እየተመዘገበ ባለበት የማሸነፍ የሞራል ስብእና በተላበስንበት የድል ወቅት ላይ የተቀላቀሉ መሆናቸው  ልዩ ያደርጋችኃል።

ትግሉ በሰው ሃይል፤በመሳሪያ፤ በቁሳቁስ፤ በእውቀትና በአስተሳሰብ የተዳረጀበትና በጥሩ ቁመና ላይ መቀላቀላቸው  እና ትግሉ እዚህ እንዲደርስ   መስእዋትነት የከፈሉ ወንድሞቻቸው  አላማቸውን ዳር የማድረስ የመተካት ሀላፊነት እንዳለባችሁ አውቃችሁ። ታጋይ ይሞታል ትግሉ በድል ይቀጥላል። እነሱን እያሰቡ መቆዘም ሳይሆን የሞቱለትን አላማ ዳር በማድረስ ዘላለማዊነታቸው ማፅናት እንደሚገባችሁ  ለዚህ ልዩ ትውልድ ማሳሰብ እፈልጋለሁ።

የፖለቲካው  ወርቃማ ቃል ቋሚ ጥቅም እንጅ ቋሚ ወዳጅም ሆነ ቋሚ ጠላት የለም የሚል ነው።  ለብሄራዊ ጥቅምህ፣ ለትግልህ ስትራቴጅካዊ ግብና ዓላማ መሳካት የሚጠቅምህ እስከሆነ ድረስ ከማናቸውም ኃይል ጋር ትተባበራለህ። ይሁንም እንጅ የግንኙነቱ ተገዳዳሪ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ውስብስብ ስለሚሆኑ ከማን ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ይኑር? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ጥልቀት እና ጥራት ያለ ስሌት ያስፈልጋል።።


. በህልውና  ላይ መደራደር አይቻልም ። በህልውና ላይ እደራደራለሁ የሚል ካለ እሱ ከጠላት ወገን ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ይህ ትዉልድ ያለው አማራጭ  ህልውናውን በክንዳችን ማሰጠበቅ ብቻና ብቻ  ነው።

የዚህ ትውልድ አካል ሆኖ ለርስቱ፣ ለማንነቱ፣ ለህዝቡ፣ ለሀገሩ ፣ለሚስቱና ለልጆቹን፣ ለቤተሰቡ እና ለወገኑ ከዚህ ወራሪ ሀይል  ከጥቃት መከላከል የማይችለው ፈሪ እና ባንዳ ነው። እናንተ የዚህ ዘመን  የአማራ ህዝብ የህልውና  ታጋዩች በመሆናችሁ የጀግና ጀግና መሆናችሁን መግለፅ እፈለጋለሁ።

"ለቤትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ  በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም /በባህር ማዶ/ ያላችሁ የዳንግላና አከባቢ ተወላጆች በሙሉ ለምታድርጉልን ድጋፍ ላቅ ያለምስጋና ይገባችኋል።ቀጣይም ድጋፋችሁ አይለየን እንላለን።

የአማራ ፋኖ የህልውና ትግል አሁን ያለንበት ሁኔታ ስናየው መታጠፊያ ላይ ያለንበት ዘመን ነው። ይህን ዘመን ለመሻገረ ደግሞ ትግሉ ያለበትን ሁኔታ መገምገም  ያስፈልጋል ብዙ የትግል ጭልፊቶች  በሚያገኙት የትግል አጋጣሜ  ሁሉ  ትግሉን ለመጥለፍ አሰፍስፈውዋል።ካልቻሉም ትግሉ ለጠላት አሳልፎ ለመስጠጥ እየሰሩ ይገኛሉ።


ትውልዱ ዋጋ የሚከፍልበት ተጋድሎ በሚከፍለው መስዋዕትነት ልክ ውጤት ይኖረው ዘንድ አንድ አማራዊ ድርጅት ወይም የጋራ አመራር መፍጠር ግዜ የማይሰጥ ጉዳይ ነው። እስካሁን ባለው ሂደት የአንድነት ሂደቱ መሰረት እየተገነባ ነው። መሪወቻችን መሰረት የጣሉለት ቤታችንን በቅርቡ ጣሪያ እና ግድግዳውን ገንብተው ሁነኛ ቤት እንደሚገነቡልን አልጠራጠርም።

የአማራ የህልውና ጥያቄ የወረረንን ሰራዊት በማሸነፍ ብቻ የሚቆም አይደለም። ዘላቂ ሰላም፣ ዘላቂ ፍትህ የሚያስፍን ማህበራዊ ውል እስኪፈጠር ድረስ ተጋድሎው ይቀጥላል። ለዚህ ስኬት ደግሞ ያልተቋረጠ እና ጥራቱን የጠበቀ የኃይል ግንባታ ተግባር  ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ስድስት ወራት በላይ የፈጀ ወታደራዊ ስልጠና የተሰጣቸው ኮማንዶወቻችን የዚህ ፕሮጀክት አካል ናችሁ።
ደማቅ ታሪክ እየፃፈ በአማራ ፋኖ ጎጃም  የሚደረገውን ተጋድሎ የኃይል ሚዛን እያስጠበቀ ያለውን ብርጌዳችሁን በመቀላቀላችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።

አሻራ ሚዲያ በቦታው በመገኘት  የሚዲያ ሽፋን የሰጠ ሲሆን  ሙሉ ዝግጅቱን በመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና በአሻራ ዩትዩብ ቻነል ይዘን እንቀርባለን ።

ይጠብቁን

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

02 Feb, 15:31

1,931

https://youtu.be/ipJQ2ms0icc?si=dpTegVJOvzYUWlC-
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

02 Feb, 11:45

2,392

የግፍ ጥግ በሜጫ ወረዳ
በቀን 23_05_2017 ዓ/ም የፅንፈኛው የአብይ ወራሪ ሠራዊት  በሰሜን ጎጃም ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ ገሸር ጎጥ በርካታ ንፁሃኖችን ከቤታቸው እያወጡ ከ10በላይ ግለሰቦችን አረሽነዋል
በርካቶችን በጥይት ቁስለኛ አድርገው ደብድበው በሞትና ሽረት ውስጥ ይገኛሉ። ሌላው በትናንትናው ዕለት የቀብር ሥነሥርዓታቸው ላይ የተገኙ ከባህርዳር ለለቅሶ የተገኙ ቤተሠቦች መካከልም አንድ ንፁሃንን በጥይት ደብድበው ገለዋል።
ከእነዚህ  ንፀሃን ውስጥ በጥቂቱ
1ኛ ተመሥገን አለሙ
2ኛ ጥሩዬ ፀጋ
3ኛ ምሥጌፈጠነ
4ኛ በቃሉ ዘመነ
ገሸር ላይ የተቀበሩ ሢሆን ሌሎችን አሥከሬናቸውን ይዞ አልሰጥም ሢል
ድብደባና በቁሥለኛ ያሉ ደግሞ
1ኛ በላይ ቄስመንጌ
2ኛ ምትኬ ጥሌ
3ኛ ፀጋ ሞላ
4ኛ አትርሣው ተፈራ
5ኛ ሙሉ ፈጠነ  የተባሉ ንፁሃን በሞት አፋፍ ላይ የሚገኙ ናቸው
በተመሣሣይ  ሙገር ከተማ ላይ የተደበደቡ ቁስለኞች አክመሻል በሚል አንድ የጤና ባለሙያ አፍነው ወደ መሸንቲ ከወሠዷት በሗላ እስካሁን አድራሻዋ አልተገኘም።
  የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ህ/ግንኙነት  ሄኖክ አሸብር
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

01 Feb, 18:33

2,638

https://youtu.be/ME_YcUU4zlU?si=GDa-_61kIVI053N6