ኮራችን በተመሠረተ ውሥን ቀናት ውሥጥ ኮሩ በሚንቀሣቀሥባቸው መዳረሻዎች ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ድል እየተመዘገበ ነው የሚገኘው። ጦራችን በታላቁ እሥቴ ከቆማ እሥከ መካነ ኢዬሡሥ፣ ከሸምበቆች እሥከ ገና መምቻ፣ ከሾለክት እሥከ ደንጎልት፣ ከማጎት እሥከ ምክሬ፣ ከአጎና እሥከ ጉና፣ ከሊባኖሥ እሥከ ጥናፋ፣ ከልዋዬ እሥከ ግንዳ ጠመም፣ ከማሕደረ ማርያም እሥከ ልጫ፣ከጅብ አሥራ እሥከ ገላውዴዎሥ ከጋሣኝ እሥከ ደብረ ታቦር ከተማና መሠል መዳረሻዎች ላይ ለተከታታይ 4 ቀናት አውደ ውጊያ ማድረጉ ይታወቃል። ፈለገ ውባንተዎች ሀብት ንብረትን የናቁ፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የማያናውጧቸው፣ ለዳያሥፖራም ሆነ ለጠምዛዥ እጆች የማይምበረከኩ፣ ለአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አራዊት ሠራዊት የእግር እሣቶች፣ ጎጠኝነትን ተጠይፈው ፩ አምሐራነት ልዕልና ላይ የተቀመጡ ናቸው። ለአማራዊ አንድነት ሰናይ የሆነ ምልከታን ተላብሰው ለአንድነት በራቸውን ክፍት አድርገው ለሴረኞች ቤታቸውን ጠርቅመው የዘጉ ናቸው።
በዛሬው ዕለትም የካቲት 26/2017ዓ.ም የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር የሆኑት ጉና ክ/ጦር፣ ኢንጅነር ሥመኘው ክ/ጦር እና ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
አለም በር ከተማ ንጋት 10:30 የጀመረው አውደ ውጊያ አድማሡን አሥፍቶ አለም ሣጋ፣ ኮሶ ማርያም፣ አምቦ፣ አሞራ ገደል፣ ሱራይ ካምፕ፣ አለም በር፣ ወጂ፣ ሥንቆና ወርቅ ሜዳ ላይ ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎች ናቸው። ጠዋት 1:00 ላይ አለም በር ከተማን ከአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አካላቶች ነጻ ማድረግ ተችሏል። ጠላት ለወራት የሰራው ምሽግ በውቤ ልጆች ተደረማምሧል። ጥበበኛው የጥበብ ልጅ ታላቁ የአማራ ፋኖ መናበብን ሢከውን የሚያቆመው ኃይል እንደሌለ ከሰሞኑ እየተገኙ ያሉ ድሎች ምሥክር ናቸው።
✅ጋሳኝ
ጉና ክፍለ ጦር/መቅደላ አምባ ብርጌድ/ናደው ሻለቃ
ጋሳኝ ከተማ ንጋት 12:00 ጀምረው ከፍተኛ ትንቅንቅን በማድረግ የአገዛዙን አራዊት ሠራዊት ከጋሣኝ ከተማ አሥለቅቀው ከጋሳኝ ዙሪያ ባሉ መዳረሻዎች ውጊያ ሢያደርጉ አርፍደዋል።በዚህ ሠዓታትን የፈጀ አውደ ውጊያ ጠላት በቁሥም በአካልም ከፍተኛ የሆነ ኪሣራን አሥተናግዷል። ከጋሳኝ ወደ ደብረ ታቦር የአገዛዙ አገልግሎት ሠጪ አምቡላንሶች ቁሥለኞችን በማመላለሥ ተጨናንቀው አርፍደዋል። ጠላት ሊያደርገው የነበረው ትልቅ ራዕዩ ቅዠት ሆኖ እንዲቀር ተደርጎበታል። ከንጋት 12:00 እሥከ ቀኑ 6:00 በቆዬው አውደ ውጊያ ታጋዮች ጠላትን አምበርክከዋል፤ ረፍርፈዋል።
በድቅድቁ ጨለማ አብሪ ኮከብ የሆኑ የአማራ ፋኖዎች በብዛት እየተከሰቱ ነው። በዚህ ትግል ሻማ ሆነው እየቀለጡ ብርሐን እዬሠጡን፤ ክቡር መሥዋዕትነትን እየከፈሉና ለአማራነት ታምነው እየታገሉ እያለ አንዳንድ አዳፍኔዎች እና የፋኖነትን የተቀደሰ የትግል መንገድ ያልተረዱ አካላት የተሰሩ ድሎች ለሕዝብ አንዳይቀርቡ አለፍ ሢልም ባልዋሉበት ኩበት ለቀማን ሢከውኑ ይታያል። የአማራ ፋኖ መራራ ዕውነታን ይጋፈጣል። ያልሰራውን እንደሰራ አድርጎ አያቀርብም። ምክንያቱም ይህ ሠራዊት ለዕውነትና ለፍትሕ፣ ለታላቁ አማራ ሕዝብ ማንነትና ዘርፈ ብዙ ተጠዬቆች መልሥ ለመሥጠት እሥከ ሙሉ ቤተሰቡ ክቡር መሥዋዕትነትን የከፈለው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፈለግ ተከታይ የሆነ የታጋይ ሥብሥብ ነውና። በተጨማሪም ደግሞ ከሕዝብ በላይ ምሥክርነትን የሚሰጥ የለም። ማን እንደሚታገልለት ሕዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። ሕዝብ ዳኛ ነው ይመዝናል። በሕዝብ ቀልሎ ላለመገኘት የፋኖን የተቀደሰ የትግል መንገድ እንከተል። ሥለሆነም ለሕዝብ የወጣ አካል ሕዝባዊነትን ብቻ መሠረት አድርጎ መታገል እንዳለበት የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር አበክሮ ማሣሠብ ይፈልጋል። የፋኖነትን ዕንቁ የትግል መንገድም እንዲከተሉ ያሥገድዳል። አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፋኖነትን ምሽግ ላደረጉ አካላት ቅድሚያ ልክ አለመሆናቸውን ያሥገነዝባል፤ ካልተመለሱም ተገቢውን የማሥተካከያ ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል።
✅ትግላችን መራራ
✅መነሻችን መገፋት፤ መዳረሻችን ነጻነት
✅ድላችን በተባበረ አማራዊ ክንዳችን
፩ አምሐራ
አማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር