Remedial students @remedialstudent2017 Channel on Telegram

Remedial students

@remedialstudent2017


Remedial students (English)

Are you a student struggling with your studies? Do you feel like you need extra help to catch up with your peers? Look no further than the Telegram channel 'Remedial students'! This channel, with the username @remedialstudent2017, is dedicated to providing support and resources for students who need a little extra help in their academic journey. Whether you're facing challenges in math, science, language arts, or any other subject, this channel is here to support you

Who is it for? 'Remedial students' is for students of all ages who are looking to improve their academic performance and reach their full potential. Whether you're in elementary school, high school, or even college, this channel is for you if you need that extra push to succeed

What is it? 'Remedial students' is a community of like-minded individuals who are dedicated to helping each other succeed. The channel offers study tips, resources, practice materials, and even virtual tutoring sessions to help students overcome their academic challenges. With a supportive community of fellow students and educators, you'll never feel alone in your academic journey again

Don't let your struggles hold you back from reaching your goals. Join 'Remedial students' today and take the first step towards academic success!

Remedial students

01 Dec, 16:57


ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 36 የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 'አክሰስ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስኮላርሺፕ ፕሮግራም' ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት አካሒዷል።

ፕሮግራሙ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ነፃ የትምህርት ዕድል ሲሆን፤ ከስድስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 18 ሴት እና 18 ወንድ በድምሩ 36 የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

ፕሮግራሙ (English Access Scholarship Program) የተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት በማሻሻል የወደፊት የሥራ ዕድላቸውን ማሳደግ የሚያስችል ነው ተብሏል።

Remedial students

18 Nov, 19:36


#ጥቆማ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች ነው።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት እንደሚፈልግ ገልጿል።

በመሆኑም ፦

- የእንግሊዘኛ፣
- የፈረንሳይኛ
- የዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የሚችሉ እና ዕድሚያቸው ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ምዝገባው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ነው የሚከናወነው።

ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲመጡ የትምህርት ማስረጃቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው እንዲቀርቡ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ " የአገራት መሪዎች፣ የዓለምአቀፍና ቀጠናዊ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሚሳተፉበት የአህጉራችን ትልቁ ጉባዔ ላይ በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል በመሆን የዚህ ታሪክ አካል ሆናችሁ አገራችሁን ያለ ክፍያ በኩራት እንድታገለግሉ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

Remedial students

12 Nov, 17:10


Raya University

ለ2017 የትምህርት ዘመን ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

Remedial students

10 Nov, 18:11


#BuleHoraUniversity

በ2016 ዓ.ም እና በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ወስዳችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የሚያስፈልጋችሁን ሙሉ መረጃ በመያዝ ከጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት (15) የሥራ ቀናት ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

በቅድሚያ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ማስላክ ይኖርባችኋል ተብሏል።

የድኅረ-ምረቃ የትምህርት መስኮች፦
1.Gadaa and Peace Studies (MA)
2.Gadaa and Governance Studies(PhD)

የምዝገባ ቦታ፦
ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንጻ ቢሮ ቁ. 59

Remedial students

10 Nov, 08:40


#ArbaMinchUniversity

በ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በ2016 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ተማሪዎች ቅበላ ቅዳሜና እሁድ ህዳር 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ምዝገባ ሰኞ እና ማክሰኞ ኅዳር 9 እና 10 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀምረው ረቡዕ ኀዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በዚህ መሠረት የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A እስከ Q የሆናችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣ እንዲሁም የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ R እስከ Z የሆናችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጂስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች እየቀረባችሁ በተጠቀሰው ቀን ሪፖርት እንድታደርጉና ምዝገባ እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡

Remedial students

09 Nov, 21:17


#UniversityOfGondar

ለ2017 የትምህርት ዘመን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ 2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የነበራችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 12 እና 13/ 2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የመጀመሪያ ቀን ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 16/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

Remedial students

09 Nov, 07:58


DambiDollo University

ለደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 ዓ.ም ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችዉ እና በ2016 ዓ.ም የሪሜዲያል ፕሮግራም (የአቅም መሻሻያ ትምህርት) በመደበኝነት ወስዳቹ ያለፋችዉ (50% ከዚያ በላይ) የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የትምህርት ምዝገባ የሚከናወነዉ ህዳር 11 እና 12/2016 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን ስትመጡ ከዚ በታች የተገለፁትን ማለትም፣

1. የ8-12 ክፍል ትራኒስክርብት ኦርጅናልና ኮፒ፣

2. የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሰርተፍኬት ኦርጅናልና ኮፒ፣

3. 3 በ 4 የሆነ በቅርብ ጊዜ የተነሳችሁትን አራት(4) ጉርድ ፎቶ፣

4. እንዲሁም ለግል መገልገያ የሚሆኑ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አሉሙናይ ዳይሬክቶሬት በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡
ከተገለፀዉ ጊዜ ቀድሞም ሆነ ዘግይተዉ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳዉቃለን፡፡

በ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ተማሪዎች የመግብያ ቀን ወደፊት የምናሳዉቅ ይሆናል፡፡

Remedial students

09 Nov, 07:20


https://t.me/MAKIBA33







We Provide for our Customers original and VIB products from all over the world
Tops, dresses, jeans, shoes, bags, accessories ለሴቶች and others 👗👚👠👡👜

Contact me @Makiba66
ለወዳጅ ዘመዶቻቹ ያጋሩ ለሁለም በሁሉም ባታ እናደርሳለን ይዘዙን፦ከታማኝነት ጋር እናመስግናለን🙏🙏
https:@Makiba0

Remedial students

08 Nov, 16:30


በ2017 ዓ.ም  ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ  ለተመደባችሁ የ1ኛ ዓመት (FRESHMAN) ተማሪዎችሙሉ

በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አድስ የተመደባችሁ የ1ኛ ዓመት (FRESHMAN) እንድሁም በ2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (REMEDIAL) ፕሮግራም ተከታትላችሁ ማለፊያ ዉጤት 50% እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደዉ ህዳር 09 – 10/2017 ዓ.ም ስለሆነ በተጠቀሰዉ ቀን ብቻ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳዉቃለን፡፡

Remedial students

08 Nov, 14:59


ለ2017 የመጀመርያ ዓመት የፍሬሽማን ተማሪዎቻቸውን የጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች

1. Addis Ababa University

2. Adama ST University

3. Addis Ababa ST University

4. Salale University - ጥቅምት 21 እና 22/2017

5. Kebri dehar University - ጥቅምት 25,26/2017

6. Mizan Tepi University - ህዳር 2 እና 3/2017

7. Hawassa University - ህዳር 9 እና 10/2017

8. Haramaya University - ህዳር 9,10,11/2017

9. Raya University - ህዳር 2 እና 3/2017

10. Oda Bultum University - ህዳር 4,5/2017

11. Jigjiga university - ህዳር 7,8,9,/2017

12. Dire Dawa University - 16 እና 17/2017

13. Kotebe University - ህዳር 4 እና 5 /2017

14. Ambo University - ህዳር 09 እና 10/2017

15. Wollega University -  ህዳር 4 እና 5/2017

16. Aksum University - ህዳር 9 እና 10/2017

17. Borana University - ህዳር 12 እና 13/2017

18. Woldia University - ህዳር 18 እና 19/2017

N.B: ራያ ዩኒቨርሲቲ አራዝሟል

Remedial students

08 Nov, 09:01


BoranaUniversity

በቦረና ዩኒቨርሲቲ :-

👉አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ እና Remedial ተማሪዎች ፣
👉በ 2016 በሬሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ እንዲሁም
👉 በ 2016 ከ 1ኛ አመት Withdraw የሞላችሁ ተማሪዎች የሁሉም ምዝገባ ቀን ህዳር 13 እና 14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀምረው  ህዳር 17/2017 ነው ተብሏል፡፡

Remedial students

05 Nov, 09:00


በ2017 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የማጠናከሪያ ትምህርት (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ህዳር 9/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል

Remedial students

04 Nov, 19:23


ማስታወቂያ
*****
ጥቅምት 25/2017 ዓም

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች   የምዝገባ  ጊዜ ኀዳር 09-10/2017 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
• የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
• የማህበራዊ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
• የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
• የስፖርት ትጥቅ

ማሳሰቢያ:-

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
     
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

                    ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
                    ሁሌም ለልህቀት!

Remedial students

04 Nov, 17:47


https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=uU9RYqhk this is the second project of the dogs .if you do not start yet now ,begin your journey,click the link that i provided you and start counting your paws

Remedial students

04 Nov, 17:37


የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ምደባችሁን ለማየት

በድረ ገጽ፦
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም፦
https://t.me/moestudentbot

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

Remedial students

30 Oct, 04:33


t.me/seed_coin_bot/app?startapp=5432420056 make sure to use your opportunity.seed listing day is in the coming November so if you don't start working it ,hurry up 🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀ to begin your journey. Who knows you will get an amazing reward.

Remedial students

24 Oct, 20:31


Remedial

Remedial students

24 Oct, 12:42


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

Remedial students

19 Oct, 17:09


#dmu

Remedial students

15 Oct, 12:56


#Update

ትምህርት ሚኒስቴር መስማት ለተሳናቸው የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው ተሸፍኖ) የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት እንደሚከተለው ይሆናል፦

► የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ 192
► የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186
በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224
► በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

Remedial students

12 Oct, 13:14


ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ላገኛችሁ የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የወጣ የቅበላ እና ምዝገባ ማስታወቂያ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 የትምህርት ዓመት በመደበኛው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚኒስቴርና በዩኒቨርሲቲው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ መስፈርት መሠረት ቅበላ ላገኛችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6 2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ

1.የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ኮፒ፣
2. አራት ጉርድ ፎቶግራፎች፣
3. የማደሪያ ምድብ (Dormitory) ለተሰጣችሁ ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ ያስታውቃል፡፡
• ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል UAI በተፈተናችሁበት ሀG ቁጥር በመጠቀም ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን
https://portal.aau.edu.et/NewStudent/DormitoryPlacement
ያሳውቃል፡፡
• በተጠቀሱት ቀናት (ጥቅምት 5 እና 6) ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ
ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና
መናኸሪያዎች ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን
እንገልጻለን፡፡
• ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ ሆኖ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome.www.aau.edu.et
• ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ስለ ዩኒቨርስቲዉ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡
• የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን • የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያዉ ሰሚስተር ትምህርት የሚጀመረዉ ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡
• ስለምዝገባ ሂደቶች በተመለከተ እና ተጨማሪ መረጃ ከታች ካሉት ሊንኮች ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን::
https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome
www.aau.edu.et
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር

Remedial students

12 Oct, 07:50


ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾች የምዝገባ ጊዜን እስከ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም አራዝሟል።

ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ በተጠቀሰው ጊዜ ማመልከት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

Remedial students

11 Oct, 15:36


ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መሸጥ እንደሚጀምር አስታወቀ

ግዙፉና መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻዉን ለህዝብ መሸጥ እንደሚጀምር ተሰምቷል ።

በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የነበረዉን የቴሌኮም ዘርፍ ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ለግል ባለሃብቱ በይፋ መሸጥ እንደሚጀምር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።

Source: capital Ethiopia

Remedial students

11 Oct, 10:04


I am so excited to launch the Productive Habesha Journal📔.  it always helps me to live intentional life and of course besides God, planning is the second most significant factor in my success.

What is the Productive Habesha Journal?
A 394-page guided journal designed to help Ethiopian youth and diaspora live a balanced, intentional life by improving spiritual, mental, physical, and social well-being.

What makes it different?
It blends Ethiopian values with practical life strategies, offering prompts for spiritual growth, mental health check-ins, and goal-setting, created specifically for the Habesha community.

What's inside?
Yearly Calendar: For long-term planning.
Monthly Prompts: For goal reflection and well-being.
Daily Planner: Keeps you productive.
Custom Design: Fits the Ethiopian youth lifestyle.

How does it help productivity?
It helps set and review goals, promotes mindfulness, and keeps you organized and motivated.

Price - birr 1000 (Fixed)
dm- @MBAM27

Remedial students

11 Oct, 09:41


#BahirDarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አውጥቶት የነበረውን ማስታወቂያ "በተመዝጋቢዎች ተደጋጋሚ ጥያቄ" እስከ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም አራዝሟል።

መስፈርቱን የምታሟሉና መማር የምትፈልጉ አዲስ አመልካቾች በኦንላይን https://studentportal.bdu.edu.et ወይም በአካል በመገኘት ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። ካልቻሉ ደግሞ በኢሜይል አድራሻ [email protected] ማመልከት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

አመልካቾች ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባችሀኋል።

Remedial students

10 Oct, 12:51


ተራዝሟል

የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ እንድትሞሉ መባሉ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ "አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻቸውን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ መሙላት በመቸገራቸው" የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫ መሙያ ጊዜው እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

Remedial students

10 Oct, 07:03


ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ለመከታተል የአመልካቾች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

በዚህም የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ መስከረም 30/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

https://application.haramaya.edu.et በመጠቀም የማመልከቻ ቅፁን ኦንላይን መሙላት ይቻላል ተብሏል።

አመልካቾች ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፋችሁና በሚያመለክቱበት ትምህርት ክፍል የሚሰጥን ፈተና ማለፍ ይጠበቅባችሀኋል።

Remedial students

09 Oct, 17:02


#MaddaWalabuUniversity

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

የሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው በኦንላይን http://estudent.mwu.edu.et/auth/login ሲሆን፤ ትምህርታችሁን በምትከታተሉባቸው ካምፓሶች በአካል በመገኘት መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ የነበራችሁና በ2017 ዓ.ም አዲስ በትምህርት ሚኒስቴር ለምትመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ ጊዜ ወደ ፊት ይገለፃል ተብሏል።

Remedial students

08 Oct, 16:11


#MoE
#Placement

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደምትችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

Remedial students

29 Sep, 07:56


በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሐምሌ መግለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የ2017 ትምህርት ዘመን መጀመርንም ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ቀድሞ በነበረው የበጀት አሰራር ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ ይገኛሉ።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፣ የተሻሻለው አዲስ የበጀት አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ብለዋል።

"ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አንድ አይነት የሜኑ በጀት ይሁን ወይስ በየአካባቢው የሚገኘውን ሀብት መሠረት ያደረገ በጀት ይሁን" በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ የተሻሻለው አዲስ የሜኑ አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህም የአንድ ተማሪ የቀን ወጪ ከ100 ብር በላይ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡

የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ጥናቶች "እስከ ነሐሴ 2016 ዓ.ም ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ የመረጃ ምንጬን ለመቀላቀል https://t.me/Dolarcoinsbot?start=r01741121864

Remedial students

28 Sep, 16:55


በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሐምሌ መግለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የ2017 ትምህርት ዘመን መጀመርንም ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ቀድሞ በነበረው የበጀት አሰራር ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ ይገኛሉ።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፣ የተሻሻለው አዲስ የበጀት አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ብለዋል።

"ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አንድ አይነት የሜኑ በጀት ይሁን ወይስ በየአካባቢው የሚገኘውን ሀብት መሠረት ያደረገ በጀት ይሁን" በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ የተሻሻለው አዲስ የሜኑ አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህም የአንድ ተማሪ የቀን ወጪ ከ100 ብር በላይ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡

የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ጥናቶች "እስከ ነሐሴ 2016 ዓ.ም ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ https://t.me/remedialstudent2017

Remedial students

28 Sep, 14:30


በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሐምሌ መግለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የ2017 ትምህርት ዘመን መጀመርንም ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ቀድሞ በነበረው የበጀት አሰራር ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ ይገኛሉ።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፣ የተሻሻለው አዲስ የበጀት አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ብለዋል።

"ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አንድ አይነት የሜኑ በጀት ይሁን ወይስ በየአካባቢው የሚገኘውን ሀብት መሠረት ያደረገ በጀት ይሁን" በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ የተሻሻለው አዲስ የሜኑ አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህም የአንድ ተማሪ የቀን ወጪ ከ100 ብር በላይ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡

የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ጥናቶች "እስከ ነሐሴ 2016 ዓ.ም ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

Remedial students

28 Sep, 12:58


https://t.me/Dolarcoinsbot?start=r01741121864

Remedial students

26 Sep, 17:32


#SalaleUniversity

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፤ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከታወቀ በኋላ የሚገለፅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

1ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ቀናት ከዚህ በፊት በተገለፀው መሰረት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
https://t.me/remedialstudent2017

Remedial students

26 Sep, 17:32


https://t.me/remedialstudent2017

Remedial students

21 Sep, 18:20


MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት በተቋሙ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል። ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀምራል።

አዲስ ገቢ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የ NGAT ውጤት ከተገለፀ በኋላ ይከናወናል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣቹ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡ ተማሪዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።