(ምሁራን)
====
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለአገራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለመወጣት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር አልሞ እየሰራ ነው።
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለመደገፍና ለተጣሉ ግቦች ስኬት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አዳዲስ ምርምሮችን ማድረግ የሚያስችለውን የፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ አደረጃጀት፣ ተልዕኮ ቀረጻና ትግበራና ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ ላይ ያተኮረ ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር አድርጓል።
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከዩኒቨርስቲው ጋር በመተባበር በኢኖቬሽንና ምርምር ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ምርምርና የኢኖቬሽን አሰራርና ድጋፍ አተገባበር የሚመራበትን አውድ በመፈተሽ ሰነድ አዘጋጅቶ የማረጋገጫ አውደ ጥናት አድርጓል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የኢኖቬሽን ልማትና ምርምር ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒኤችዲ) አውደ ጥናቱን ሲከፍቱ ፤ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፉን ለመምራት የተሰጡትን ተልዕኮዎች በመወጣት አገር ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር ባይሳ አክለውም፥ የዘርፉን አገራዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ መርሃ ግብሮች እና የማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀትና የዘርፉን ተልዕኮዎች ከዐለም አቀፍ ተሞክሮ ጋር ተጣጥመው እንዲመሩ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የማስተባበርና የመደገፍ ስራ እየሰራ ነው።
https://t.me/ethiopian_ministry_of_education