ኢትዮጵያ ቡና ሰኔ 30/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል ሆኖም በጨዋታው ላይ በርካታ ድራማዊ ክስተቶች ተፈጥረው ተመልክተናል። በጨዋታው ላይ የነበሩ የዳኝነትም ሆነ የደጋፊዎችን ችግር አስመልክቶ እግርኳስ ፌዴሬሽኑ መርምሮ ውሳኔ ይሰጥበታል ብለንም እናምናለን።
ኢትዮጵያ ቡና የበደልን ብዛት ግፍን ተቋቁሞ ከንጋት ኮከብ እስከ ኢትዮጵያ ቡና አልወድቅም ብሎ ፀንቶ የቆሞ ለእውነተኛ ፍትህ እና ለንፁህ እግርኳስ የሚታገል ግንባር ቀደም ስፖርት ክለብ ነው።
ኢትዮጵያ ቡና በዘር በጎሳ በአካባቢ ያልተደራጀ በውብ እግርኳሱ የሁሉንም የሃገሪቱ ክፍል ነዋሪዎች ልብ ያሸፈተ በብሄራቸው በዘራቸው በአካባቢያቸው የተቋቋሙ በርካታ ክለቦች እያሉ የሚኖሩበት ርቀት ሳይገድባቸው ልባቸውን ውብ እግርኳስ ለሚጫወተው እና ለዘመናት በበደል በግፍ በሴራ በርካታ ዋንጫዎችን ለተነጠቀው ሁሌም ለመልካም የስፖርት አስተዳደር ለሚታትረው ኢትዮጵያ ቡና አስረክበዋል!!
ከእሁዱ የጨዋታ መጠናቀቅ በሁዋላ አንዳንድ የወላይታ ደጋፊዎች እና ሌሎች የተለየ አላማ ያላቸው ግለሰቦች የክለባችንን ስም በማጉደፍ ላይ ይገኛሉ እኛም ነገሩን ተመልክተን እግርኳስ ስሜታዊ የሚያደርግ ስፖርት ስለሆነ ከዛ ስሜታቸው ሲወጡ ነገሩን ይተውታል ወይም አስተውለው ያስብቡታል ብለን ዝምታን መርጠን ቆይተናል።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ እንደ ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ አፀያፊ ስድቦችን የተሰደበ ደጋፊ የለም እኛ ግን ነገሩን ጎትተን ወደ ሌላ አቅጣጫ ወስደነው አናውቅም!! የወላይታ ዲቻውን ግብ ጠባቂ የተወሰኑ ደጋፊዎች ሊስትሮ አሉት ብሎ የነገሩን አቅጣጫ ወደ ዘረኝነት መጎተት ለምን እንደተፈለገ ግልፅ ባይሆንልንም ሊስትሮ የሚለው ቃል የስራ እንጂ አንድን ብሄር አሳንሶ የሚያሳይ ወይም የሚያንቋሽሽ አይደለም!! በዚህ ሙያ ውስጥ ደግሞ በርካታ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች ሰርተው አልፈዋል እየሰሩም ይገኛሉ ቃሉ የወላይታን ማህበረሰብ ብቻ የሚወክልም አይደለም።
ሌላው ነገር ለምን በረኛው ብቻ ተሰደበ ሌሎቹ የወላይታ ተወላጅ የሆኑ የዲቻ ተጫዋቾች ለምን አልተሰደቡም? ነገሩ የዘረኝነት ከሆነ ማለት ነው ነገር ግን ቢኒያም ደጋፊው ላይ ላደረገው ነገር ብቻ ደጋፊው ምላሽ ሰጥቶታል እንጂ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ለሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ትልቅ አክብሮት ያለው በስታዲየም ውስጥ ከሚደረጉ ብሽሽቆች በዘለለ ሌላ አላማ የሌለው የማንም መጠቀሚያ ያልሆነ ንፁህ እግርኳስን ብቻ ብሎ የመጣ ስርአት ያለው እግርኳስ ተመልካች ነው።
#ኢትዮጵያ_ቡና_ለዘለዓለም_ይኑር 👆