#ኾራ_አታ_ኾንሶ ዘንድሮ ይከበራል።
ዘንድሮ በወርሃ ግንቦት "ኾራ አታ ኾንሶ" እንደምከበር 𝑷𝒓𝒐𝒎𝒐𝒕𝒆 𝑲𝒐𝒏𝒔𝒐 ከታማኝ ምንጮች ያገኜው መረጃ ያመላክታል።
"ኾራ አታ ኾንሶ" የኮንሶ ዓመታዊ የባህል ክብረ በዓል ማለት ነው። ይህ ዝክረ በዓል በዋናነት የሚከበረው የኮንሶ ባህላዊ መልከአ ምድር በዓለም ቅርስ የተመዘገበበትን ቀን በማሰብ ነው።
የኾራ ዓመታዊ የምክክር መድረክ ነው። ከባለፈው ወራት መነሻነት የቀጣይ ጊዜ ምክረ ሀሳብ የሚቀርብበት ትልቅ የባህል ሥርዓት ነው።
ኾራ ሥርዓት ሁሉም ይሳተፍበታል። የሚያጠፋ ይመከራል ጠንካራ ይበረታታል ህዝባዊ ውሳኔዎች በአደባባይ በይፋ ለህዝቡ ይተላለፋሉ።
በፕሮግራሙ
1. ዝክረ ቅርስ:- የኮንሶ ባህላዊ መልከአ ምድር በዓለም ቅርስ የተመዘገበበት ቀን ይታወሳል። ቅርስን መዘከር ለቅርሱ ህልውና የራሱ ሚና ይኖረዋል።
2. የኮንሶ ህዝብ የ100 ዓመት ታርክ በፎቶ አውዴ ሪዕይ ይቀርባል። የጠፉ ባህላዊ ክዋኔዎች በፎቶ ይቀርባሉ። ልጠፉ ያሉ ባህሎች ህይወት ዘርተው ይታያሉ።
3. በጉምቱ የኮንሶ ሙሁራን ጥናታዊ ፅፎች ይቀርባሉ። በተለያዩ ሪዕሶች ዙሪያ ሙጉት ይኖራል።
4. የኮንሶ ባህላዊ ጭፈራዎች #ኦሶማታ_ቱሮ፣ #ታንሳ፣ #ህማሻ፣ # ኦይሌ፣#ኩሬታ፣#ሻባላ፣ #ኩራይላ፣ #ሌኦታ #ቱታ እና #ሆፓ ይቀርባሉ።
5. የኮንሶ ብቻ ይሆኑ የከበሩ እና ውድ ምግቦችን #ሀይዳ ፣#ቲንፋ፣#ሱፓ፣#ጮራ ይቀርባሉ።
6. ለትውልዱ አደራ ይሰጣል:- የቅድሜ አያቶቻችን ድንቅ ዕውቀት በዓለም ቅርስ የተመዘገበው በቀደምት አያቶች ፍፁም ታታሪነት ነው። ታዲያ አሁን ያለው ትውልድ የታርክ ተወቃሽ እንዳይሆን የአባቶች ቅርስ የመጠበቅ የማስቀጠል አደራ ይሰጠዋል።
➦𝑭𝒐𝒓 𝒎𝒐𝒓𝒆 𝑨𝒃𝒐𝒖𝒕 𝒌𝒐𝒏𝒔𝒐 ...
➤ 𝑭𝒂𝒄𝒆𝑩𝒐𝒐𝒌 𝑷𝒂𝒈𝒆-https://www.facebook.com/promotekonso
➤ 𝒀𝒐𝒖𝑻𝒖𝒃𝒆 ፦https://youtube.com/@promotekonso985
➤ 𝑭𝒂𝒄𝒆𝑩𝒐𝒐𝒌 𝑮𝒓𝒐𝒖𝒑-https://facebook.com/groups/367936341826141/
➤ 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 ፦https://t.me/promotekonso
➦ 𝑻𝒊𝒌𝒕𝒐𝒌- tiktok.com/@promotekonso
➦ 𝑰𝒏𝒔𝒕𝒂𝒈𝒓𝒂𝒎-https://instagram.com/promotekonso?igshid=YmMyMTA2M2Y=
𝓣𝓱𝓪𝓷𝓴 𝔂𝓸𝓾 𝓯𝓸𝓻 𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀𝓲𝓷𝓰 𝓾𝓼!