Natnale Mekonen @natnaelmekonenethio Channel on Telegram

Natnale Mekonen

@natnaelmekonenethio


natnaelmekonenethio (English)

Are you interested in exploring the vibrant culture and rich history of Ethiopia? Look no further than the Natnale Mekonen Telegram channel! This channel, managed by the knowledgeable and passionate Natnale Mekonen, is dedicated to sharing insights, stories, and facts about Ethiopia that will leave you in awe. Natnale Mekonen is a respected expert in Ethiopian history and culture, with years of experience in research and exploration. Joining this channel will give you access to daily updates on Ethiopian traditions, folklore, cuisine, and so much more. Natnale Mekonen takes pride in curating content that is both educational and engaging, making it the perfect platform for anyone who wants to delve deeper into the beauty of Ethiopia. Whether you are a history buff, a foodie, or simply someone who appreciates learning about different cultures, this channel has something for everyone. What sets Natnale Mekonen apart from other channels is the personal touch that he adds to each post. You will feel like you are embarking on a journey through Ethiopia with a close friend who is eager to share the wonders of the country with you. From stunning photos of Ethiopian landscapes to intriguing historical anecdotes, every piece of content is carefully selected to provide you with a comprehensive understanding of Ethiopia. So, if you are ready to immerse yourself in the rich tapestry of Ethiopian culture, don't hesitate to join the Natnale Mekonen Telegram channel today. With a community of like-minded individuals who share your passion for Ethiopia, you will have the opportunity to engage in lively discussions, ask questions, and connect with others who appreciate this extraordinary country. Join us on this exciting adventure and let Natnale Mekonen be your guide to the wonders of Ethiopia.

Natnale Mekonen

09 Sep, 22:28


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 7 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

Natnale Mekonen

19 Aug, 02:05


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 29 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

Natnale Mekonen

27 Sep, 13:18


#Ethiopia : መልካም በዓል

Natnale Mekonen

27 Sep, 13:18


የሱዳን መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአወዛጋቢው አዋሳኝ የድንበር አካባቢ ጥቃት ሰነዘሩብኝ ሲል ከሰሰ።

ከሱዳን ጦር የወጣው መግለጫ፤ ከኢትዮጵያ በኩል የተሰነዘረውን "ጥቃት መመከት" መቻሉን አመልክቷል።የኢትዮጵያ መንግሥት ከሱዳን በኩል ለቀረበበት ክስ አስካሁን በይፋ የሰጠው ምላሽ የለም።የሱዳን ጦር ተሰነዘረብኝ ስላለው ጥቃት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳብራራው ክስተቱ ያጋጠመው ኡማ ናራኪት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ብሏል።

የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበርና ጦር አዛዥ ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሐን ከኢትዮጵያ በኩል ጥቃት የተሰነዘረብን ቅዳሜ ዕለት ነበር ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።ጄነራሉ በቅርቡ ሱዳን ውስጥ ተሞክሮ ከሸፈ የተበላውን መፈንቅለ መንግሥት በማስታወስ፤ ክሰተቱ ጦሩ ሱዳንን እየጠበቀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት በጉዳዩ ላይ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም፤ አል-ጀዚራ የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን በመጥቀስ እንደዘገበው በሱዳን ደንበር አካባቢ የኢትዮጵያ ጦር ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረገም፤ የተባለው ጥቃትም አልተፈጸምም።

በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው በሁለቱ አገራት መካከል በድንበር ይገባኛል ምክንያት የተከሰተውን አለመግባባት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

Via BBC

Natnale Mekonen

27 Sep, 11:07


#Ethiopia : በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች በጅማ ኤርፖርት ፍንዳታ እንደደረሰና በረራም እንደቆመ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ሐሰት መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን። በአሁኑ ሰዓት በጅማ መደበኛ የኤርፖርት እና የበረራ ስራዎቻችን በተለመደው መልኩ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

Via የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Natnale Mekonen

27 Sep, 07:42


#Ethiopia : ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ÷የመስቀል ደመራ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለምታከብሩ ሁሉ መልካም ምኞቴ ይድረስ ብለዋል።

በዓሉ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ ሲሉም አስፍረዋል።

Natnale Mekonen

27 Sep, 07:42


ከአባቶቻችን የተረከብነውን የመስቀል በዓልም ሃይማኖታዊ እሴቱን በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሰተላለፍ እንደሚገባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሰዉ ገለጹ፡፡

#Ethiopia : ሚኒስትሯ የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት በአዲስ አበባ መሰቀል አደባባይ ባድረጉት ንግግር፥ በዓሉን ስናከበር የተሰጠንን ሃላፊነት በብቃት በመወጣት ሰላምና ፍቅርን በማስተማር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የምንወዳትን ታላቅ ሃገር ልዕልናዋን አስጠብቆ ለማቆየት በትጋት መስራት ይገባናል ሲሉም ሚኒስተሯ ተናግረዋል፡፡

በአዲሱ ዓመት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሃላፊነታቸውን በብቃት በመወጣት፣ ፍቅርን በመስበክ እና ጥላቻን በማሰወገድ በሁሉም ዘርፍ ሊንቀሳቀሱ አንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከአባቶቻችን የተረከብነውን የመስቀል በዓልም ሃይማኖታዊ እሴቱን በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሰተላለፍ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በዓሉ በሰላም አንዲከበር ላደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅረበዋል ፡፡

Natnale Mekonen

26 Sep, 16:41


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከህንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብህራህማን ጃይሻንካር ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን÷ የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ገንቢ ሃሳቦች ተለዋውጠዋል።

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ህንድ ያደረገችውን ድጋፍ አቶ ደመቀ አድንቀዋል።

አቶ ደመቀ በዚህ ወሳኝ ጊዜ በምክር ቤቱ ውስጥ ህንድ የነበራትን የፀና አቋም እና ድጋፍ በማመስገን፤ በሌሎች የጋራ ፍላጎቶች እና ጠቃሚ መስኮች ዙሪያ ቅንጅታችንን ማጠናከር ይገባናል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Natnale Mekonen

26 Sep, 16:41


‹‹ሳሮ ጊዶ(ሰላም ይሁን)፣ ሲጋ ጊዶ(እርቅ ይሁን)፣ ካሎ ጊዶ ( ጥጋብ ይሁን)››

የዎላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። ግፋታ በወላይታ ዘመን አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ሲሆን በኩር ማለት ነው፡፡

ግፋታ የሚከበርበት ቦታ ‹በጋሮ› በንጉሱ ቤተ-መንግስት ፣ ‹በጉተራ› በህዝብ መሰብሰቢያ አደባባይ ፣ እንዲሁም በማህበረሰቡ መሰብሰቢያ ቦታ እና በየደጃፉ ነው፡፡

ለዚህም በዓል ከሰኔ ወር የመጨረሻ ሳምንት ጀምሮ ዝግጅት ይካሄዳል፡፡ ይህም ወጣቶች ለጉልያ( ለበዓሉ የሚነደው/ ደመራ) በዓባቶች መሪነት ይሰበስባሉ፡፡

ጉልያ የሚቃጠለው በዛው በዓሉ በሚከበርበት ዕለት ሲሆን ከእርዱ ስነ-ሥርዓት በኋላ የሚከናወን ነው፡፡ ጉልያው እስኪወድቅ ከወጣት እስከ ሽማግሌ ጭፈራው ይቀጥላል፡፡ የጉልያው ምሰሶ የወደቀበት አቅጣጫ ለአዲሱ ዓመት ትርጉም ይኖረዋል፡፡

ግፋታ የጥጋብ በዓል በመሆኑ እንኳን ሰው ከብቱ እንዳይራብ ለበዓሉ ሳር ተከልሎ ይቀመጥለታል፡፡ ንጉሱም በበዓሉ ለተገኙት ጸሎትና ቡራኬ ይሰጣል እንዲህም ብሎ ይመርቃል፡፡

‹‹ ሳሮ ጊዶ(ሰላም ይሁን) ፣ ሲጋ ጊዶ(እርቅ ይሁን) ፣ ካሎ ጊዶ ( ጥጋብ ይሁን) ›› ብሎ ይመርቃል፡፡

በማግስቱ ‹ታማ ሳይኖ› ይባላል፡፡ የእሳት ሰኞ እንደማለት ነው፡፡ ይህም ማታ የጉልያ እሳት ሳይጠፋ የሚያድር በመሆኑ ታማሳይኖ ይባላል፡፡ ማክሰኞ ደግሞ ‹ጭሻ ማስቃይኖ› የአበባ ማክሰኞ ይባላል፡፡

ዘመድ አዝማድ ወዳጅ ቤት ነጭ አበባ ተይዞ ግፋታ ዮዮ እያሉ የአዲስ አመት ብስራት የሚገለጽበት ሲሆነ ለአንድ ወር ይከበራል፡፡

ወላይታዎች እንዲህ በጥጋብ በደስታ የተቀበሉትን አዲስ ዓመት በጠነከረ የስራ መንፈስ ወደ ስራ ለመመለስ ግፋታን ሸኝተው ጸደይን ይቀበላሉ፡፡

#ዮዮግፋታ
📸 wolaitaTimes

Natnale Mekonen

26 Sep, 13:55


<<በማንም አገር የውስጥ ጉዳይ ላይ ገብተን እንደማናቀው ሁሉ እናተም በውስጥ ጉዳያችን እንድትገቡ አንፈቅድላችሁም። ፈተና በገጠማችሁ ወቅት ኢትዮጵያ ከጎናችሁ እንደነበረችው ዛሬም እናንተ ከጎኗ ልትሆኑ ይገባል።

#Ethiopia : ኢትዮጵያ ወንጀለኛው ቡድን ላይ እየወሰደች የምትገኘውን እርምጃ መደገፍ የአፍሪካ ቀንድን ሠላም ማረጋገጥ ነው።
እንደጠላቶቻችን ሃሳብና ዕቅድ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ አይደለም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድም በነበር አይዘልቅም ነበረ ፤
ኢትዮጵያ ዛሬም እንደሁልግዜ ሁሉ የነጻነትና አሸናፊነት ምልክት ናት። የህዳሴውን ግድብ በመገንባት ሌሎች ሀገራት በራስ አቅም የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶችን እንዲገነቡ መነሳሳት እንደሆንላቸው ተስፋ እናደርጋለን። ከገዛ ውኃችን ስለጠጣን በዓለም መድረክ ተቃውሞ እና ዛቻ ደርሶብናል። በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ያለን በራስ-መተማመን መሰረቱ እውነት፣ እውቀት እና ፍትኃዊነት ናቸው>>

አቶ ደመቀ መኮንን (ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ የተናገሩት

Natnale Mekonen

26 Sep, 13:54


በበርሊን ማራቶን አትሌት ጉዬ አዶላ አንደኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል:: ቀነኒሳ በቀለ በሶስተኝነት አጠናቋል

Natnale Mekonen

26 Sep, 13:54


የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በደማቅ ስነስርአት እየተከበረ ይገኛል ።

Natnale Mekonen

25 Sep, 17:39


የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንደኛውን ክንፍ ሲመሩ የነበሩት አራርሶ ቢቂላ ዛሬ በተመሰረተው አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ካቢኔ ውስጥ ተሾሙ❗️

በዛሬው የኦሮሚያ የካቢኔ ሹመት የተቃዋሚው ኦነግ አንደኛው ክንፍ ሲመሩ የቆዩት አቶ አራርሳ ቢቂላ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ተደርገው ተሹመዋል።

የዛሬው የካቢኔ አባላት ሹመት በጨፌው 12 ተቃውሞ እና 13 አባላት ድምፀ ከመስጠት ታቅበዋል።

Natnale Mekonen

25 Sep, 17:39


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
******************************

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

ስለ መስቀል በዓል ስናነሣ አንድ መታሰብ ያለበት ጉዳይ አለ። ከፈተና በኋላ ድል፣ ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከመውደቅ በኋላ መነሣት እንደሚኖር። የጠፋ ሁሉ ጠፍቶ እንደማይቀር፤ የመስቀሉ ታሪክ ያስተምረናል።

ባለፉት ሦስት ዐሠርት ዓመታት የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከልባችን ላይ እንዲፋቅና ስለ ሀገር ያለን ፍቅር ከውስጣችን እንዲጠፋ በብዙ መልኩ ሤራ ተሠርቷል። እርስ በእርስ በጥርጣሬ እንድንተያይ ብዙ ተንኮል ተጎንጉኗል። በደስታም ሆነ በኀዘናችን፣ በድልም ሆነ በችግራችን አንድነትና ኅብረታችንን እንዳናስቀድም ተደርገናል። ምኞትና ፍላጎታችን በክልልና በብሔር ዙሪያ ብቻ ታጥሮ ትልቁን ሀገራዊ ምስል እንዳናስተውል ተሞክሯል። ሳይወዷት የመሯት ጠላቶቿ፣ ኢትዮጵያ በትንሽ በትንሹ እየፈረሰች እንደሆነ እያሰቡ ይደሰቱ ነበር። "አሁን ያለችው ኢትዮጵያ እኛ ብቻ እንድናስተዳደራት የተሠራች ናት፤ እኛ እስከፈቀድን ድረስ የምትኖር፣ በሌላ እጅ ከገባች በቀላሉ የምትፈርስ ናት" እያሉ በዕብሪት አፋቸውን ሞልተው ይናገሩ ነበር። ሕዝባዊ አንድነታችን ላልቶ እንደተበጠሰና እነርሱ በፈለጉ ጊዜ ሀገራችንን በቀላሉ ሊያፈርሷት እንደሚችሉ ደጋግመው ዝተዋል። ዳሩ ግን ሁሉም ነገር እንደተናገሩት አልሆነም። ኢትዮጵያዊነት እንደ ክርስቲያኖች መስቀል የመለያየት አፈር የተጫነው ቢመስልም አልጠፋም። አንድነታችን የሰለለ ቢመስልም አልተበጠሰም። ለሀገር ያለን ቀናዒነት የተዳፈነ ቢመስልም አልቀዘቀዘም ነበር።

ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በክርስቲያኖች ዘንድ የፈውስና የኃይል ምንጭ ተደርጎ ይታመናል። ለሕመማቸው ፈውስን፣ ለመከራቸው ጊዜ ጽናትን፣ በተሰበሩ ጊዜ ብርታትን፣ በተበታተኑ ጊዜ ኅብረትን አምጥቶላቸዋል። ይኽ ሁኔታ ያላስደሰታቸው የዚያን ዘመን ጨቋኞች ሤራ ሲያስቡ ዋና ትኩረታቸውን ያደረጉት የመስቀሉን ደብዛ ለማጥፋት ነበር። ከሰው ደብቀው ቀበሩት። ቦታውንም የቆሻሻ መጣያ እንዲሆን አዘዙ። ለ300 ዓመታት ከየነዋሪው ቤትና ከየሰው ግቢ ተጠርጎ የሚወጣ ቆሻሻ እየተጣለበት ቆይቶ ግዙፍ ተራሮችን መሰለ። ነገር ግን ክፉዎች እንዲህ ለክፋት መትጋታቸው በመስቀሉ ቤዛነት የሚያምኑትን አላሸነፈም። ተራራ ንደው፣ ቁልሉን ደርምሰው፣ አቧራውን ጠርገው፣ መስቀሉን ከማግኘት አላገዳቸውም።

ባሳለፍነው ዓመት አሸባሪው ጁንታና የኢትዮጵያ ጠላቶች በሐሰት ፕሮፓጋንዳቸው የሀገራችንን ስም ሊቀብሩ ተባብረው ሲሠሩ ነበር። በውሸት የተቀመሙ ዜናዎቻቸውን በሚያሠራጩባቸው ሚዲያዎች አማካኝነት ያልተፈጠረውን ተፈጠረ፣ ያልሆነውን ሆነ እያሉ፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ኢትዮጵያ ቀና ብላ እንዳትታይ ዐቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ አድርገዋል። ዓላማቸው ግልጽ ነው። የእነርሱ ጥቅም የሚከበረው በእኛ መሸነፍ ውስጥ እንደሆነ ያውቃሉ። በውንጀላዎቻቸው ተሸንፈን ጉልበታችን ሲብረከረክ በቀላሉ እጅ እንሰጣለን፤ ለእኩይ ፍላጎታቸው ተገዥ እንሆናለን ብለው አስበዋል። በተሸናፊነት ሥነ ልቡና ውስጥ ገብተን ዳግም በእግራችን መቆም ካልቻልን፣ ያኔ እስከመጨረሻው የእነርሱ ጥቅም ባሪያዎች ሆነን እንደምንቀር ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለዚህም የቻሉትን ያህል የውሸት ቆሻሻ ሰብስበው፣ የእኛን እውነት የሚጋርድ ግዙፍ ተራራ መፍጠር ችለዋል።

መስቀሉን አርቀው የቀበሩ ሰዎች መስቀሉ ለዘላለም እንደተቀበረ የሚቀር መስሏቸው ነበር። መስቀሉ አፈር ተጭኖት ስለተከለለ ትውስታው ከምድረ ገጽ እንደሚሰረዝ፣ እምነቱ ከክርስቲያኖች ልብ ተፍቆ እንደሚጠፋ አስበዋል። ነገር ግን ሐሳባቸው እውነት የመሰለው እንደ ንግሥት እሌኒ ያሉ ብርቱዎች መስቀሉን ፍለጋ እስኪነሡ ድረስ ብቻ ነው። የእነርሱ ዓላማ ስኬት የተመሠረተው በሌሎች ስንፍና ላይ በመሆኑ፣ ብርቱ ፈላጊዎች ቆርጠው በተነሡ ጊዜ፣ የመስቀሉ መጥፋት ጉዳይ ያከትምለት ጀመር። “ጠፋ”ጠፋ የሚለው ዜና “ተገኘ” በሚለው ዜና ተተካ። እንደተተካም ቀረ።
ንግሥት እሌኒ መስቀሉን ለመፈለግ በተነሣች ጊዜ፣ ነገር ሁሉ አልጋ በአልጋ ሆኖ አልጠበቃትም። መስቀሉ ስለመቀበሩ እንጂ የት እንደተቀበረ እንኳን አታውቅም ነበር። በዙሪያዋ የነበሩ ሰዎችም መንገድ ከመጠቆም ይልቅ ተስፋ በማስቆረጥ የተጠመዱ ነበሩ። የመስቀሉ ጉዳይ ያበቃ ያከተመለት ጉዳይ እንደሆነ ነበር የሚነግሯት። እሷ ግን እጇን አጣጥፋ ከመቀመጥ ይልቅ እምነትና ተስፋዋን ይዛ በመፈለጉ ጸናች። ተስፋ አስቆራጮች የሚናገሩትን ትታ እምነት የጣለችበትን የዕጣን ጢስ ተከተለች። ተከትላም አልቀረች። ጢሱም መስቀሉ የተቀበረበትን ትክክለኛ ቦታ መጠቆም ብቻ ሳይሆን፣ ከብዙ ድካምና ልፋት ታደጋት። የዕጣኑ ጢስ ወደ እውነተኛው ቦታ የሚያደርስ ምልክት ሆናት።

ለዘመናት በሤረኞች ተንኮል ደብዝዞ የጠፋ የመሰለው አንድነትና ኢትዮጵያዊነታችን ወደ ቦታው እየተመለሰ ነው። ይሄንን የሚያሳዩ ምልክቶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መታየት ጀምረዋል። እንደ እሌኒ ያሉ ጀግኖች፣ ሤረኞች የቀበሩት የመሰላቸውን ኢትዮጵያዊነት እያወጡት ነው። ከመላ ኢትዮጵያ፣ አያሌ እሌኒዎች መጥተው ታሪክ እየሠሩ ነው። ድሮ በክልሎች መካከል የነበሩ መሥመር የሳቱ ፉክክሮች አሁን በትብብር ተለውጠዋል። “አትምጣብኝ አልምጣብህ” የሚሉ ክፉ ንግግሮች “ለችግርህ ደራሽ እኔ ነኝ” በሚል ተተክተዋል። በየጓዳችን ተወሽቀን ስለ ጓዳችን ብቻ አብዝተን መጨነቃችን ቀርቶ ዛሬ ሀገራዊ ጥቅማችንን ላለማስነካት በዓለም ፊት በአንድ ድምፅ መናገር ጀምረናል። ኢትዮጵያዊ ማንነታችን በእርግጥም በደማችን ውስጥ ስለመኖሩ አሁን በግልጽ ይታያል። ኅብርነታችን መለያያችን ሳይሆን የአንድነት ጌጣችን መሆኑን እንደ መስቀሉ ከፍ አድርገን አሳይተናል።

አሁን ኢትዮጵያ በየተሠማሩበት መስክ ሉዓላዊነቷን ላለማስደፈር የሚባትሉ ልጆቿ ጥቂቶች አለመሆናቸውን እያየች ነው። ከጠላት ጋር አብረው ከጀርባ የሚወጓት ክፉ ልጆችዋ ዕለት በዕለት ቀን ሲጨልምባቸው፣ ወደ አመድነት ሲለወጡ፤ በተቃራኒው ለክብሯ ለሚጨነቁ ደጋግ ልጆችዋ ፈተናው እየቀለለ፣ የድል ውጋጋን በመታየት ላይ ነው። የጨለማው ጊዜ ተወግዶ ብርሃኑን፣ የፈተና ጊዜ አልፎ ድሉን የምናይበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን አልጠራጠርም። የሤረኞች ምንቸት ወጥቶ፣ የኢትዮጵያዊነት ምንቸት እየገባ ነው።

የመስቀልን በዓል ስናከብር ግዛታዊ አንድነታችንን ለማስጠበቅ በዱር በገደሉ የሚወድቁ እኅቶቻችንንና ወንድሞቻችንን እያሰብን መሆን አለበት። እነርሱ እንደ ደመራው አንድ ሆነው ለኢትዮጵያ የሚሠው ህያዋን ችቦዎች ናቸው። ዛሬ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ተጠብቆ ያለው እነርሱ በሚከሰክሱት አጥንትና በሚያፈሱት ደም ነው። በተመሳሳይ በጁንታው ጥቃት የተጎዱ ዜጎቻችንን አለሁ ልንላቸው፣ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል። የከፈሉት ዋጋ ለኢትዮጵያ የተከፈለ ዋጋ ነው። የታመሙት የሁላችንን ሕመም ነው። ከቤት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን መልሶ የማቋቋም፣ የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን የመገንባትና የወደሙ ጤና ተቋማትን በምትካቸው የመሥራት ኃላፊነት በእያንዳንዳችን ትከሻ ላይ የወደቀ ነው። ይሄንን ዐውቀን ከአሁኑ ወገባችን አሥረን መነሣት አለብን። ካላጎነበሳችሁ አንረዳችሁም የሚሉ ወገኞች ይኖሩ ይሆናል። ለኢትዮጵያ ሲባል ሐሞትና ከርቤ ለመጠጣት እንገደድ ይሆናል። ጥርሳችን ነክሰንና አንጀታችን አሥረን እንጋፈጠዋለን። ተጋፍጠንም እናሸንፈዋለን።

Natnale Mekonen

25 Sep, 17:39


በዓሉ የሰላም፣ የመረዳዳትና የመተጋገዝ እንዲሆን እመኛለሁ።
በድጋሚ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 15፣ 2014 ዓ.ም

Natnale Mekonen

25 Sep, 14:41


ጨፌ ኦሮሚያ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱራህማንን የጨፌው አፈጉባኤ አድርጎ መረጠ!

ጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ እያካሄደው ባለው 6ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ የምስረታ ጉባኤው ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱራህማንን የጨፌው አፈጉባኤ አድርጎ መርጧል።በተጨማሪም ጨፌው አቶ ኤሊያስ ኡመታን ምክትል አፈጉባኤው አድርጎ መርጧል።ወ/ሮ ሰዓዳ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በተለያዩ የመንግስት አደረጃቶች ያገለገሉ ሲሆን አቶ ኤሊያስ ደግሞ በምስራቅ ወለጋ በተለያዩ ዞኖች በአመራርነት አገልግለዋል።

Natnale Mekonen

25 Sep, 14:41


የኦሮሞ ህዝብን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሻገር ለውጡን ለማስቀጠል ዳግም ቃሌን አድሳለሁ ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ።

በጨፌ ኦሮሚያ በድጋሜ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ዛሬ የተሾሙት አቶ ሽመልስ ባደረጉት ንግግር በ2013 ዓ.ም ትላልቅ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በውስብስብ ችግር ውስጥ ሆነን ሀገራችንን ለማፍረስ የቋመጡ የውስጥና የውጭ ሃይሎችን ያሳፈረና ተስፋቸውን ያስቆረጠ ምርጫ በማካሄድ ዳግም ታሪክ ማደስ ችለናል ነው ያሉት።

ምርጫው ተሳክቶ ዛሬ ለደረስንበት ስኬት ላበቃን ህዝባችንንና ባለድርሻ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

አሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሃትን ማፅዳት የክልሉንም ሆነ የሀገሪቱ ሰላም አስተማማኝ ማድረግ ቀዳሚ ተግባራችን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድ።

የክልሉ ወጣቶች እኛ እያለን ሀገራችን አትፈርስም በማለት መከላከያና ልዩ ሃይሉን መቀላቀላቸውን አድንቀው ይሄው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

“ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊ ማንነት ለማራቅና የተሸናፊነት አባዜ ውስጥ እንዲቆይ ያደረገውን አሸባሪ ሃይል አከርካሪውን በመስበር የበለፀገች አሮሚያና ኢትዮጵያን ለትውልድ እናስረክባለን” ነው ያሉት።

“በዚህም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን ሌት ተቀን እየተረባረብን አፋጣኝ ውጤት እናስመዘግባለን” ብለዋል።

“የጥንካሬያችን ማዕከል ኦሮሞነት ነው፣ ማንነታችን የበለፀገች፣ አንገቷን ቀና ያደረገች ኢትዮጵያን መፍጠር ነው” ሲሉ አቶ ሽመልስ አስታውቀዋል።

በተለይ የግብርና፣ የቴክኖሎጂና ሜካናይዜሽን አገልግሎት በማስፋት የአጠቃላይ ሰብል ልማትና የስንዴ መስኖ ልማት፣ የእንስሳት ሀብት፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የኑሮ ውድነት ማቃለል፣ትምህርት፣ ጤና፣የመንገድ ልማት፣ የከተሞች ሴክተር ልማትና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ቀዳሚ ተግባር መሆኑንም አመላክተዋል።

የወጣቶችና ሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ ሌብነትና የመልካም አስተዳደር እጦት ችግርን ማቃላል የትኩረት አቅጣጫችን ነው ብለዋል።

ከአጎራባች ክልሎች ጋር ወንድማማችነትን ይበልጥ ለማጠናከር አብሮ መልማትና ማደግ ላይ በትብብር እንደሚሰራም ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት በነበረው አካሄድ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ እንደማይቻል አውስተው፤ አሁን የመጣውን ለውጥ በመጠቀም በገቢ አቅም ማሳደግ፣ የህዝቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተሳትፎ ይበልጥ ማጠናከር አለብን ብለዋል።

የኦሮሞ ቄሮና ቀሬ አሸባሪውን ህወሃት በማስወገድ ዛሬ ለደረስንበት ደረጃ አብቅታችሁናል ያሉት
ርዕሰ መስተዳድሩ አሁንም ትልቁ ጠላታችን የሆነውን ድህነት ማሸነፍ አለብን ብለዋል።

መላው የክልሉ ህዝብ፣ የኦሮሞ ምሁራን ለሁሉን አቀፍ ልማት በገንዘብ፣ ጉልበትና ዕውቀት ማገዝ እንደሚገባቸው አመልክተዋል።

የውስጥና ውጭ ጠላት ለመቅበር የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በመሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት መቆም አለብን ነው ያሉት።

የክልሉ መንግስት ሠራተኞች ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንክረን መስራት አለብን፤ የዲያስፖራ አባላት የክልሉን ልማት በማገዝ ሀገራችንን በጋራ ሆነን ማሻገር አለብን ሲሉ አቶ ሽመልስ ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።