Dernières publications de የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia (@ministryofindustry) sur Telegram

Publications du canal የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia ቴሌግራም ቻናል ነው፡፡
የኢፊዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የተመለከቱ መረጃዎችን
• ዜናዎች
• ሁነቶች
• የተለየያዩ ለአምራች ኢንዱስትሪ ማህበረሰብና ስለ ተቋሙ መረጃ የሚያገኝበት ቻናል ነው፡፡
https://t.me/+P0HOYJNw-wgyMmNk ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ፡፡
10,024 abonnés
5,606 photos
143 vidéos
Dernière mise à jour 11.03.2025 07:50

Le dernier contenu partagé par የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia sur Telegram

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

08 Nov, 06:21

774

ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

07 Nov, 13:12

975

ለግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፍ በቂ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደ ሚገባ ተገለጸ፡፡ (ፕሬዝዳንት አምባሰደር ታዬ አፅቀስላሴ)
=============================
ጥቅምት28/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌድሪ ፕሬዜዳንት አምባሰደር ታዬ አፅቀስላሴ ለሶስት ቀናት በተካሄደው ርሃብ አልባ ዓለምን መፍጠር ይቻላል ጉባኤ የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል፡፡

ክቡር ፕሬዜዳንቱ የጉባኤውን ዋና ዓላማ ለማሳካት ከሌላው ዘርፍ በተጨማሪ ለግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደ ሚገባ ገልጸዋል፡፡

ርሃብ አልባ ዓለምን ተግባራዊ ለማድረግ የአፍሪካ ሀገራት በቂ በጀት መመደብና ራሳቸውን በቴክኖሎጅ አጠቃቀም ረገድ ማብቃት እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡

የሀገራትን የምግብ ዋስትና እና የዘላቂ የልማት ግቦች ለማረጋገጥ ዓለም አቀፋዊ ትብብር ወሳኝ እንደሆነም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ረሃብን ከዓለም ለማስወገድ በአፋጣኝ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸውን ወሳኝ እርምጃዎች ዘርዝረዋል።

አንደኛው ጠንካራ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለሚከናወኑ ሥራዎች ህዝብን ለማስተባበርና ለማሳተፍ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።

ሌላኛው ወሳኝ ጉዳይ በቂ የሆነ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ነው ብለዋል።

ከሁሉ በላይ ከረሃብ ነፃ ዓለም ለመፍጠርና ተግባራዊ እርምጃዎችን ወደ ውጤት ለመቀየር ባለራዕይ መሪዎችን ማብዛትና ትርክትን መቀየር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የአፍሪካን እምቅ አቅም አሟጦ በመጠቀም አስከፊውን ረሃብ ለማስወገድ በአንድነት መነሳት ለነገ የማይባል መሆኑን ጠቅሰው ማንም በረሃብ እንዳይጎዳ አፋጣኝ የተቀናጀና ተግባራዊ እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

07 Nov, 12:43

534

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ’ዓለም ከረሃብ ነጻ’ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ ያደረጉት ንግግር
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

07 Nov, 11:01

621

ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የማህበረሰብ ንቅናቄ ረሃብን ለማጥፋት ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው:: (ፕሬዝዳንት አምባሰደር ታዬ አፅቀስላሴ)
======================================
ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ለተከታታይ ሦሥት ቀናት በአዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሲካሄድ የቆየው ከርሃብ ነፃ የሆነ ዓለም አለማቀፍ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከርሃብ ነፃ የሆነ አለምን ዕውን በማድረግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የማህበረሰብ ንቅናቄ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

07 Nov, 10:46

556

ኢትዮጵያ ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ያሰናዳችው ከርሃብ ነፃ የሆነ ዓለም (World with out hunger conference) አለማቀፍ ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

07 Nov, 09:28

589

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ በጋራ መስራት የማያስችላቸውን የመግባቢያ ሰምምነት ተፈራረሙ
===============================
ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የመግባቢያ ሰምምነቱን የተፈራረሙት የኢዱስትሪ ሚኒሰቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ከሰተ አድማሱ ናቸው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማስፋት ፣የኃይል መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት ፣የፋይናስ ዘርፉን በማዘመን፣ የውጭ ንግድ ሚዛንን በማሰጠበቅ አምራች ዘርፍ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን እንዲዘውር ማድረግ በ2030 እኤአ አትዮጵያን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንድትሆን ማስቻልን ራዕይ አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

የመግባቢያ ስምምነቱ ለሚኒስቴሩ ራዕይ ስኬታማነት ለፕሮጀክቶች ቴክኒካል ድገፍና ክትትል ለማድረግ እና የአፈፃፀም አቅምን ለማጎልበት ዓላማ ያደረገ ስለመሆኑ ተገልጿል ።

በጨርቃ ጨርቅ፣ በእርሻ ውጤቶች፣ በቆዳ ፣ በኬሚካል እና ኮንስትራክሽን፣ በቴክኖሎጂ፣ በፋርማሲ ውጤቶች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር በስምምነቱ እንደ አንድ ተግባር ተቀምጧል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

05 Nov, 13:54

616

A WORLD WITHOUT HUNGER CONFERENCE "ከረሀብ ነፃ ዓለም" ዓለም አቀፍ ጉባዔ
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

05 Nov, 12:58

741

የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ከምትሰራቸው ስራዎች አንዱ ነው ፡፡
===============================
ጥቅምት 26/2017 (ኢሚ) በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የምግብ ምርትን ለመጨመር ብቻ ሳይሆን ምግብን በተመጣጣኝ ዋጋ፣ ተደራሽ እና ለሁሉም የተመጣጠነ እንዲሆን ለማድረግ እንደ ሀገር እየተሰራ ነው ያሉት የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የምርት አቅርቦት ሰንሰለትን በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከምትሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱና ዋናው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፓርኮቹ ከጥሬ ዕቃ ማቀነባበሪያ እስከ ገበያ ስርጭት ድረስ ሁሉንም የግብርና ንግድ ዘርፎችን ይደግፋሉ ያሉት ሚኒስትሩ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው ገበሬዎችን ከኢንዱስትሪዎች ጋር በማገናኘት የግብርና ውጤቶችን ወደ ከፍተኛ ዋጋ ወደ ሚሰጡ ምርቶች በመቀየር፣ በምግብ ስርዓታችን ውስጥ ትስስር እንዲፈጠር በማድረግ ወሳኝ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡
ለሴቶች እና ለወጣቶች ቅድሚያ በመስጠት እነዚህ ፓርኮች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መናኸሪያ ብቻ ሳይሆኑ የማህበራዊ ማጎልበት ሞተሮች መሆናቸውን የገለፁት አቶ መላኩ ለሀገር ውስጥ ሀብታችን ተጨማሪ እሴት የሚያመጡ እና በአለም ገበያ ያለንን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ የተቀነባበሩ ምግቦችን እንደ ቡና፣ ማር እና ሌሎች ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ረሃብን ለማስወገድ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምትከተለው ተልዕኮ ከግሉ ሴክተር ጋር ጠንካራ ትብብር ማድረግ አስፈላጊ ነው ያሉት ሚኒስትሩ መንግሥት የአገር ውስጥ ሥራ ፈጣሪ ባለሀብቶችን የመደገፍ ተግባሩን አጠናክሮ እንደመሚቀል አስረድተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

05 Nov, 10:31

759

ከረሃብ ነፃ አለም ዓለማቀፍ ጉባኤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ለማጠናከር ወርቃማ እድል ነው፡፡( አቶ መላኩ አለበል)
==============================
ጥቅምት 26/2017 (ኢሚ) ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት አመታት የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፎችን በማጠናከር የምግብ ዋስትን ለማረጋገጥ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት እየሰራች መሆኑን የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል፡፡

ከባህላዊ የግብርና አሰራር ወደ አግሮ ፕሮሰሲንግ እና የግብርና ቢዝነስ ሞዴልነት መሸጋገር አስፈላጊ መሆኑን በገንዘብ እሴት የሚጨምር አምራች ኢንዱስትሪ መፍጠር ላይ መንግስት ትኩረት በማድረግ እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ጠንካራና ራሱን የቻለ ኢኮኖሚ ከማድረግ ባሻገር የግል ኢንቨስትመንትን የሚስብ እና የግብርና ውጤቶችን ወደ ከፍተኛ ዋጋ ወደ ሚሰጡ ምርቶች የሚቀይር ሀገራዊ ዕቅድ ለማሳካት ቁልፍ ሚና የሚጫወት ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ጉባኤው ረሃብን ለማስቆም እና በአለም አቀፍ ደረጃ ማህበረሰቦችን ለማገልገልና ዘላቂ የምግብ ዋስትናን እውን ለማድረግ የጋራ ቁርጠኝነታችንን ለማጠናከር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ረሃብን ለማስወገድ የቆረጡ አእምሮዎችን እና በድህነት ላይ የዘመቱ ልቦችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ ለመስራት በጋራ መምከር የአፍሪካን ቀጣይ እጣፋንታ የሚወስን ትልቅ የትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን በአፍሪካ ዘላቂ የማኑፋክቸሪንግ ልማትን በመገንባት ከረሃብ ነፃ አለምንእውን ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ በውጤታማነት በመተግበር አርአያ ለመሆን እንደምትሰራ አስረድተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

05 Nov, 09:35

676

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሰራች ያለውን ስራ አጠናክራ ትቀጥላለች (ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ )
==============================
ጥቅምት 26/2017(ኢሚ) ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰራች ያለው ስራ ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ባለው ከርሃብ ነጻ አለም ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የተፈጥሮ አደጋ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በአለም የሚስተዋሉ ግጭቶች ከርሃብ ነጻ አለምን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በታቀደው ልክ እንዳይሄድ እንዳደረጉት ተናግረዋል ።

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት አመታት ርሃብን በመዋጋት ተሞክሮ የሚወሰድበት ውጤት አስመዝግባለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ
የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረትና የግብርና ግብአት አቅርቦት እጥረት ፈተና መሆኑን ጠቁመዋል ።

ባለፉት  አመታት ኢትዮጵያ በግብርና ማሻሻያ ላይ ትኩረት ሰጥታ መስራቷንና ድርቅን መቋቋም የሚችሉ ሰብሎችን በመዝራት ምርታማነት ማሳደግ መቻሏን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ
አለምን የተፈታተኑ ታላላቅ ችግሮች ቢኖሩም ጥረትን በእጥፍ በመጨመርና ፈጠራ የታከለባቸውን ስራዎች በመተግበርና ዘመናዊ የግብርና ስራን በመተግበር ፈተናዎችን መቋቋም እንደተቻል ገልፀዋል።

በአረንጓዴ አሻር መርሀ ግብር ባለፉት አመታት 40 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል ለግብራናው ስራ አለም አቀፍ ፈተና የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖንን በመከላከል የተሰራው ስራ በግብራናው ላይ ምርታማነትን ለመጨመር ትልቅ ሚና እንዳለው የገለፁት ዶክተር ዐቢይ ኢትዮጵያ ረሃብን ለመግታታ በአለም አቀፍ ደረጃ ለተያዘው ዕቅድ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት የጀመረችውን ስራ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት