Y4C @youth4christ Channel on Telegram

Y4C

@youth4christ


#ተወዳጁና_የመጀመሪያው_የክርስቲያን_የቴሌግራም_ቻናል
የተለያዩ
#ዝማሬዎችን
#መንፈሳዊ_ፅሁፎችን
#ኢየሱስ_ኢየሱስ_የሚሸቱ_ፕሮግራሞችን_የሚያቀርብ
ይህ ቻናል የእርስዎ ድምፅ ነው ያሎትን ሃሳብና አስተያየት ያድርሱን
በ @CbarokT ና
በ @CnahomT ላይ ያናግሩን

https://youtube.com/channel/UCuLK7iURoPACbDnIq4mdNpQ

@Christian_Mezmur ይቀላቀሉን

Y4C (Amharic)

የቴሌግራም ቻናል Y4C እናመሠረታለን! ይህ ቻናል በተወዳጁና የመጀመሪያው ክርስቲያን እና ቴሌግራም ያሉትን ዝማሬዎችን እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ይሰጡ። ኢየሱስ የሚሸቱ ፕሮግራሞችን እስከመቀላቀል የቴሌግራም ቻናልም መታየት እንችላለን። በY4C ቴሌግራም ቻናለው የእርስዎ ድምፅ እንደተለያዩ ሃሳብና አስተያየት ያድርሱን። የቴሌግራም ምርጥ ተጨማሪ ፕሮግራምንና የቴሌግራም ፊልምን ይቀላቀሉ ከመሆኑ። የY4C ቴሌግራም ቻናል በ@CbarokT እና @CnahomT ላይ ሊያናግሩን እንዴት ይችላሉ። አንድ ገላፊዎችም በቴሌግራም የምናገኘውን ድምፅ በ@Christian_Mezmur ላይ ይቀላቀሉ። የY4C ቴሌግራም ቻናል ከአዳምጡ በኋላ የመረጡን ዝማሬዎችን ይጠብቁ!

Y4C

19 Sep, 20:06


በዘማሪት #ሀና የተዘመረ! ርዕስ - #እውነተኛ!
ሙሉውን ለማዳመጥ 👇
https://youtube.com/watch?v=yhR8PRrs_24&si=-eTGCHXynED0xd2x

Y4C

11 Jul, 08:12


Omnipotent movement presents

Omnipotent charity day 2023

Hebrew 13:16
And do not forget to do good and to share with others, for with such sacrifices God is pleased.

Donate trousers for men and other items
We are donating at Win souls for God, for 42 boys in the orphanage.
1 donation would mean a lot for us🙌.

Call us on 0909322576 or 0924451666 or 0974424774

Win souls for God
📍shiromeda

Y4C

21 Jun, 05:08


“ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል...።”
  — 2ኛ ቆሮ 6፥10


"ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።"

ዕንባቆም 3:17-18

@Youth4Christ

Y4C

16 Jun, 15:38


ተለቀቀ 🔥 በዘማሪ ብንያም ዮናስ ይሰማ በአለም
ሊንኩን ተጭነው ያድምጡ 👇👇👇
👉 https://youtu.be/lDJvdvCgyuk

Y4C

16 Jun, 14:14


“በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥21
“For after that in the wisdom of God the world by wisdom knew not God, it pleased God by the foolishness of preaching to save them that believe.”
— 1 Corinthians 1:21 (KJV)

Y4C

16 Jun, 05:08


#ይሰማ_በዓለም #በዘማሪ_ቢንያም_ዮናስ 🎶
   ዛሬ ማታ 12 ሰዓት ላይ ይለቀቃል!
እስከዛ YouTubeን Subscribe አድርጉ!
#Share ይደረግ! #ሼር ይደረግ!
👉  https://youtu.be/aqG7UNBfBJ0

Y4C

16 Jun, 05:01


🎶 ዛሬ ማታ 12 ሰዓት ላይ ይለቀቃል!
#ይሰማ_በዓለም #በዘማሪ_ቢንያም_ዮናስ
እስከዛ YouTubeን Subscribe እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ
👉  https://youtu.be/aqG7UNBfBJ0

Y4C

12 Jun, 05:14


“አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን?”
  — መዝሙር 39፥7

@Youth4Christ

Y4C

11 Jun, 18:39


“አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።”
— መዝሙር 46፥1


@Youth4Christ

Y4C

11 Jun, 04:47


★★★    ክፍል 3    ★★★
★★★★የመጨረሻ ክፍል★★★★ እነሆ

@Youth4Christ
@Youth4Christ

ያለፉትን ክፍሎች ከፍ ብለው ያንብቡ

ከትናንት የቀጠለ 👇👇👇👇

....... ‹‹አንዳንድ ወንዶች ልጆች ይሳሳማሉ፤ እኔ ግን ይደብረኛል፤ ደግሞ ይተሻሻሉ›› አለኝ፡፡ ከገጽታው የመቅፈፍ ስሜት አየሁበት፡፡ ይህንን ስሜት ስመለከት ወደ ችግሩ ውስጥ ዘልቆ እንዳልገባበት ተረዳሁ፡፡ እኔ የማዝነው በባህላችን ተከብሮ የኖረውን የወንድም ለወንድም፣ የእኅት ለእኅት ግንኙነት ግብረ ሰዶማዊነት እያጠፋብን በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ከአክስቶቼ ልጆች ጋር አብሬ እየተጫወትኩ፣ አብሬ እየተኛሁ ነው ያደግኩት፡፡ ልጆቻችን ግን እንዲህ ማድረግ ላይችሉ ነው፡፡
@Youth4Christ
ከአጎታችን፣ ከአክስታችን ጋር መተኛት ለኛ ደስታችን ነበር፡፡ ዛሬ ግን ዘመዶች በዘመዶች ላይ እንዲህ የሚፈጽሙ ከሆነ ዝምድናችን ሊጠፋብን ነው፡፡ መምህሮቻችንን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የቤት ሠራተኞችን፣ የጥበቃ ሠራተኞችን እየተጠራጠርን ልንኖር ነው፡፡ ግብረ ሰዶምነት ባህላችንን እጅግ አድርጎ ነው የሚያበላሸው፤ ማኅበራዊ ግንኙነቶቻችንን ነው የሚበጣጥሰው፤ እንዴት ያለ ችግር ውስጥ ነው የገባነው በእግዚአብሔር?
@Youth4Christ
በኋላ ከአንዳንድ የሕክምና ባለሞያዎች ጋር ስንነጋገር ብዙ ነገር ሰማሁ፡፡ በከተማችን ውስጥ የግብረ ሰዶማውያን ማዘውተሪያዎች የታወቁ ናቸው፡፡ የራሳቸው የመግባቢያ ‹ቋንቋም› አላቸው፡፡ ትልልቆቹ ግብረ ሰዶማውያን ድራግ በመውሰድ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ለሕፃናቱ ድራጉን በከረሚላ መልክ ይሰጧቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ለመደበቅ ሲሉ ልጆቹ ግለኛነትን ይመርጣሉ፡፡ ከሌሎች ልጆች ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ከመጨዋት ይልቅ ከጌምና ከቴሌቭዥን ጋር ብቻ መሆንን ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ፌስ ቡክን በሚገባ ለዚህ አስተሳሰብ ማራመጃ ይጠቀሙበታል፡፡ ወላጆች ኢንተርኔትን ልጆቻችን ያለ እድሜያቸው እንዳይጠቀሙበት ማድረግ አለብን፡፡
ስለ ኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ስለ ጥቅምና ጉዳቱ ሳንነግራቸው ነው የምንፈቅድላቸው፡፡ ይኼኔ ከበጎው ይልቅ ክፉውን የመያዝ ዕድላቸው ይሰፋል፡፡ በቤታችን ውስጥ ያስገባናቸውን የቴሌቭዥን ቻነሎችንም መቆጣጠር አለብን፡፡ ልጆቻችን ክፉውንም ደጉንም ዝም ብለው እንዲያዩ ማድረግ የለብንም፡፡ ግብረ ሰዶምን የሚያበረታቱ ቻነሎች አሉ፡፡
@Youth4Christ
‹አሁን ልጅዎ ከችግሩ በሚገባ ወጥቶልዎታል?›› አልኳቸው፡፡
‹‹ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ወጥቷል ማለት አልችልም፤ አሁንም እጠራጠራለሁ፡፡ ፍርሃቱ ገና አልለቀቀኝም፡፡ ነገር ግን ክትትሌን አላቆምኩም፤ ከልጄ ጋር ያለኝን ቀረቤታም ጨምሬያለሁ፤ ስለ ብዙ ነገሮችም እንነጋገራለን፤ የሃይማኖት ትምህርት እንዲማርም እያደረግኩ ነው፡፡ አንድ የማውቀው የሥነ ልቡና ባለሞያ ስለ ግረ ሰዶም ጉዳት በሚገባ ነግሮታል፡፡ በተለይ በዚህ ክረምት የተለየ ነገር ለማድረግ እየሞከርኩ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶቻችንን ግን ከትምህርት ጥራትና ከክፍያቸው ባለፈ ወላጆች መከታተል አለብን፤ ልጆቻችንም የተለየ ነገር ሲያዩ እንዲነግሩን ማሳሰብ ይገባል፡፡ ዘመኑ ወላጅነት ከባድ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡
እግዚአብሔር  ኢትዮጵያን ይባርካት ይጠብቃት፡፡ 🙏🙏🙏

ይህንን ፅሁፍ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ለወዳጅ ዘመዶዎ በየግሩፑ @Youth4Christ share ማድረግ  አይርሱ፡፡

ጥያቄ አስተያየት ካላችሁ @CbarokT ላይ ያናግሩን::


👇👇👇👇👇👇
@Youth4Christ @Youth4Christ
@Youth4Christ @Youth4Christ
@Youth4Christ @Youth4Christ
@Youth4Christ @Youth4Christ
@Youth4Christ @Youth4Christ
@Youth4Christ @Youth4Christ
@Youth4Christ @Youth4Christ
@Youth4Christ @Youth4Christ

Y4C

10 Jun, 07:20


ክፍል  ፪ ሁለት 2

ለወዳጅ ፣ ጓደኛ ፣ ቤተሰብ  share ማድረግ አይርሱ 👉 @Youth4Christ

ከትላንቱ የቀጠለ 👉
.......፤ እንዲያውም ‹I am a gay› የሚል ልብስ የሚለብሱ እንዳሉ ነገርኩት ግራ ሳይገባው አልቀረም፡፡ ስለ እርሱ እንደምናገር ገምቷል፡፡ ስጨርስ ‹‹የኔ ልጅ አንተ ግን እንደዚህ አታደርግም አይደል?›› አልኩት፡፡ ምንም አላለኝም፡፡ ዝም አለኝ፡፡ መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡ ‹‹ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ እንዴ›› አልኩት፡፡ ዝም አለ፡፡ ‹‹አደራህን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልጆች ሌሎች ልጆችን ሳያውቁት ወደዚህ ነገር እያስገቧቸው ነውና ተጠንቀቅ›› አልኩት፡፡
@Youth4Christ
እሺም እምቢም አላለኝም፡፡ ‹‹አንተ ይህንን ስታደርግ ካየሁ፤ እኔ ወዲያው ነው የምሞተው›› ስለው ተስፈንጥሮ መጥቶ ጭኔ ላይ ተደፋ፡፡ ሲያለቅስ ይሰማኛል፡፡ ዕንባውም እግሬን ሲያሞቀው ይታወቀኛል፡፡ እኔም እያለቀስኩ ነበር፡፡
ከብዙ የዝምታ ልቅሶ በኋላ ‹‹እማዬ እኔኮ ጌይ ሆኛለሁ›› አለኝ፡፡ ቀድሜ ባውቅም ያ ሰዓት ግን መብረቅ የመታኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከልጄ አንደበት ይህንን ስሰማ ኩምሽሽ ብዬ ትንሽ የሆንኩ መሰለኝ፡፡ የማደርገው ጨነቀኝ፤ ምን ልመልስለት? ምን ልበለው? ግራ ተጋባሁ፡፡ ‹‹ለምን ልጄ? ለምን?›› አልኩት፡፡ ከእኛ ራቅ ብለው የሚያዩን ሰዎች ሁኔታዬ ግራ አጋብቷቸው ሁሉም እኔን ያያሉ፡፡
‹‹እኛ ትምህርት ቤትኮ ብዙ ልጆች አሉ›› አለኝ፡፡
@Youth4Christ
‹‹ምን ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት
‹‹ሽቱ ተቀብተው ይመጣሉ፤ ደግሞ አንድ ዓይነት ማስቲካ ነው የምንበላው፤ ‹I am a gay› የሚል ቲሸርት እንለብሳለን›› አለኝ፡፡
‹‹ቲሸርቱን ማን ነው የሰጣችሁ?›› አልኩት
‹‹አንድ ልጅ ነው ያመጣልን፤ ለሁላችን ሰጠን፡፡ ግን ከዩኒፎርማችን ሥር እንድንለብሰው ነግሮናል››
‹‹ሌላስ?››
‹‹ደግሞ አንድ ልጅ የጌይ ፊልም በዕረፍት ጊዜ ያሳየናል››
‹‹የት ነው የሚያሳያችሁ?››
‹‹በኪሱ የሚያመጣው ሞባይል አለ፡፡ እናቴ ናት የምትጭንልኝ ብሏል››
የምሰማውን እንዴት ልመነው?
‹‹እርሱኮ [የልጁን ስም እየነገረኝ] አባቱ ትምህርት ቤት ሲሸኘው ሁልጊዜ ከንፈሩን ይስመዋል›› አለኝ፡፡ ይኼኔ ነቃሁ፡፡ አስታወስኩ፡፡ ሰውዬውንም ዐወቅኩት፡፡ እኔም ደስ አይለኝም ነበር፡፡ አባት ወንድ ልጁን፣ እናትም ሴት ልጇን ከንፈራቸውን መሳም እዚህ ትምህርት ቤት የማየው ነገር ነው፡፡ ይህ ነገር ልጆቻችን ይህንን መሰሉን ተግባር ከዕድሜ ቀድመው እንዲለምዱት ያደርጋል፡፡ ከዚያም አልፎ ነገ ሌሎች ግብረ ሰዶማውያን በልጆቹ ላይ ይህንን መሰል ተግባር ሲፈጽሙባቸው ምንም እንዳይመስላቸውና የፍቅር መግለጫ አድርገው እንዲወስዱት ያደርጋቸዋል፡፡ ከባህላችን ያፈነገጡ ነገሮችን በልጆቻችን ላይ ማድረግ እነዚህ ነገሮች በልጆቻችን ላይ በሌሎች አካላት ሲደረጉባቸው እንዳያስተውሉት እንዳይጸየፉትም ያደርጋቸዋል፡፡
‹‹ለመሆኑ አብራችሁ ስትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት፡፡
‹‹አንዳንድ ወንዶች ልጆች ይሳሳማሉ፤ እኔ ግን ይደብረኛል፤ ደግሞ ይተሻሻሉ›› አለኝ፡፡ ከገጽታው የመቅፈፍ ስሜት
አየሁበት፡፡ ይህንን ስሜት ስመለከት ወደ.... ክፍል 3 ነገ  ይቀጥላል...

@Youth4Christ
@Youth4Christ

አስተያየት  ጥያቄ  ካለ @CbarokT ላይ ያናግሩን

Y4C

09 Jun, 04:59


እውነተኛ ታሪክ በአዲስ አበባ
ከ #የዳንኤልክብረት ፅሁፍ የተወሰደ፡፡

‹‹ግብረ ሰዶማዊነት›› ስር ስለመስደዱ እጅግ በጣም አሳዛኝና አስገራሚ ታሪክ ነግሮናል፡፡
ግብረ ሰዶማዊነት በሀይማኖት የተወገዘ ፤ በባህል የተፀየፈ ፤ በህሊና የተጠላ ፤ በሀገርም የተነወረ እጅግ አፀያፊ ድርጊት ነው፡፡ @Youth4Christ
እባካችሁ አንብባችሁ ስትጨርሱ ለየግሩፑ ሼር አድርጉት ፤ በቤት ውስጥ በስራቦታም ብቻ የትም ይሁን ሰብሰብ ስትሉ ተወያዩበት - ትውልድ ገዳይ ድርጊት ነውና፡፡

( #ዳንኤል ክብረት )
ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት!?@Youth4Christ
@Youth4Christ
ይቀላቀሉን 👆👆👆

ባለፈው ሰሞን አንዲት እናት ወደ ቢሮዬ መጥተው እንዲህ አወጉኝ፡፡
‹‹ልጄ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅና የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የማይበት ጠባይ ግራ የሚያጋባኝ እየሆነ ተቸግሬ ነበር፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የእኔን ሽቱ ይቀባል፡፡ እኔም ይህን ሳይ የልጅ ነገር አድርጌ ትቼው ነበር፡፡ በኋላ ግን ከሌላው ነገር ጋር ሲደረብብኝ ነው ግራ የተጋባሁት፡፡ ፀጉሩን እንደ ሴቶች ማስተኛት ይፈልጋል፡፡ ጥብቅ ያለ ሱሪ ካልገዛሽልኝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት አድርሼው መኪናዬን አዙሬ ልመለስ ስል ከኋላ ያለውን መኪና እንዳልነካው ዞር አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ያየሁትን ነገር ዓይኔ ሊያምን አልቻለም ነበር፡፡ ከአንድ ሌላ ወንድ ልጅ ጋር #ከንፈርለከንፈር ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ከኋላዬ የነበረው መኪና በጡሩንባ እየጮኸብኝ እንኳን የማየውን ተጠራጥሬ ለረዥም ሰዓት ፈዝዤ ነበር፡፡
@Youth4Christ
@Youth4Christ
ሥራ ከገባሁ በኋላ እጅግ ፈዝዤ ነበር፡፡ የቢሮ ሰዎች ሁሉ እየደጋገሙ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ግን ለማን ምን ብዬ ልንገረው? ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ወደ አንዲት ጓደኛዬ ባለቤት ጋር ደወልኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነበርና ምናልባት ከረዳኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ በስልክ አነጋገሬ አደጋ የደረሰብኝ ይመስል ስለነበር እየከነፈ ቢሮዬ መጣ፡፡ ከእርሱ ጋር ተያይዘን ወጣንና አንድ ቦታ ቁጭ አልን፡፡ በልጄ ላይ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኩት፡፡ እርሱም ከሌሎች የሰማቸውን የባሱ ነገሮች እየነገረ አጽናናኝ፡፡ ከዚያም የበለጠ ርግጠኛ ለመሆንና ችግሩንም በሚገባ ለመረዳት ልጄ በማይኖርበት ሰዓት የልጄን ዕቃዎች እንድፈትሻቸው ነገረኝ፡፡
@Youth4Christ
ለማስታወቂያ ነው 😁 ቻናሉን በየመሃሉ ምለቀው Join ያድርጉ
@Youth4Christ
አንድ ቀን አባቱ ወደ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደው ነገርኩትና እኔ ዕቃዎቹን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ ያኔ ነው የልጄን ጉዳይ በጥልቀት የተረዳሁት፡፡ እኔ ያልገዛሁለት አንድ ቀይ ቲሸርት አገኘሁ፡፡ ቲሸርቱ ላይ በእንግሊዝኛ ‹I am a gay› የሚል ተጽፎበታል፡፡ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋው ላይ ተቀምጬ ለረዥም ጊዜ አለቀስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ልጄን እንዳጣሁት ገባኝ፤ ልጄን እንደማላውቀው ገባኝ፤ ልጄና እኔ በተለያዩ መንገዶች እየተጓዝን መሆኑ ገባኝ፡፡
የጓደኛዬ ባለቤት በጉዳዩ ላይ እንዴት ከልጄ ጋር ልወያይ እንደምችል መንገዶችን አመላከተኝ፡፡ አንድ ቀን ከልጄ ጋር ከአዲስ አበባ ወጣ አልን፡፡ አብሬው ስጫወት ዋልኩና ለሻሂ ዐረፍ ስንል አንድ ስልክ አነሣሁ፡፡ እንደ ደነገጠ ሰው ሆኜ ነበር የማወራው፡፡ ልጄም ድምፄን እየሰማና ሁኔታዬን እያየ ተደናገጠ፡፡ ስጨርስ ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ፡፡ ‹‹አንዲት ጓደኛዬ ከባድ ነገር እንደ ደረሰባት፡፡ ልጇ ግብረ ሰዶማዊ እንደሆነባት፡፡ በዚህም ምክንያት በሕግ ሊጠየቅ መሆኑን›› ነገርኩት፡፡ እጅግ ደነገጠ፡፡ ‹‹የእኔ ልጅ መቼም እንዲህ ያለ ነገር አያደርግም›› ብዬ ተውኩት፡፡ አፍጥጦ ዓይን ዓይኔን ያየኝ ነበር፡፡ ‹‹በጣም ከባድ ነገር ነው የገጠማት፤ ግብረ ሰዶማዊ ማለትኮ በሃይማኖታችንም ትክክል አይደለም፤ እግዚአብሔር ግብረ ሰዶማውያንን አጥፍቷቸዋል፡፡ ከዚያም በላይ ግብረ ሰዶማውያን በኅሊናቸውም ሆነ በማኅበራዊ ኑሮአቸው ላይ ችግር እንደሚገጥማቸው፤ ከሕዝቡም እንደሚገለሉ፤ አኗኗራቸውም ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ እንደሆነ፤ ወንድ ከሴት ጋር ሴትም ከወንድ ጋር እንጂ ወንድ ከወንድ፣ ሴትም ከሴት ጋር የሚደረገው ግንኙነት እንስሳት እንኳን የማይፈጽሙት መሆኑን፡፡ የወሲብ ግንኙነት ማንኛውም ወንድ ከ ተፈቀደለት ሴት ጋር ብቻ፣ ባህሉና እምነቱ፣ ሕጉም በሚፈቅደው እድሜና ሁኔታ የሚፈጸም መሆኑን›› እየዘረዘርኩ መግለጥ ጀመርኩ፡፡ ዝም ብሎ ነበር የሚያዳምጠኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ልጆቻቸውን ግብረ ሰዶማውያን እንደሚያደርጓቸው፤ እነዚህ ልጆችም ሌሎችን ልጆች አባብለው ወደዚህ እንደሚያስገቧቸው፤ እንዲያውም ‹I am a Gay የሚል ልብስ የሚለብሱ እንዳሉ ነገርኩት............ ይቀጥላል

ክፍል ፪ ነገ ቅዳሜ ማታ ይቀጥላል  

ቻናላችንን ለመቀላቀል ይህንን ሊንክ ይጫኑ


👇👇👇👇👇👇👇
👉 @Youth4Christ
       @Youth4Christ
👉 @Youth4Christ

Y4C

09 Jun, 04:57


Y4C pinned «ከአመታት በፊት በአዲስ አበባ ውስጥ ስለተከሰተ ትውልድ ገዳይ ስለሆነው ስለ ግብረ ሰዶማዊነት አንድ ጽሁፍ አጋርተናችሁ ነበር። ዛሬ ላይ ይህ በሽታ በሀገራችን በተለያዩ ከተሞች እጅግ በጣም በመበራከቱ ሁላችንም እንድንነቃና እንድንጸልይ በድጋሚ ጽሁፉን ልናጋራችሁ ወደድን! እባካችሁ ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አድርጉት። @Youth4Christ»

Y4C

09 Jun, 04:57


ከአመታት በፊት በአዲስ አበባ ውስጥ ስለተከሰተ ትውልድ ገዳይ ስለሆነው ስለ ግብረ ሰዶማዊነት አንድ ጽሁፍ አጋርተናችሁ ነበር።
ዛሬ ላይ ይህ በሽታ በሀገራችን በተለያዩ ከተሞች እጅግ በጣም በመበራከቱ ሁላችንም እንድንነቃና እንድንጸልይ በድጋሚ ጽሁፉን ልናጋራችሁ ወደድን!

እባካችሁ ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አድርጉት።

@Youth4Christ

Y4C

03 Jun, 10:29


አይዟችሁ !!!

ነገሮች ግራ የገቧችሁ . . . በሰው የተጎዳችሁ . . . ያዘናችሁ . . . ተስፋ የቆረጣችሁ . . . ነገሮች የጨለሙባችሁ . . . ያልተጠበቀ ነገር የደረሰባችሁ . . . አይዟችሁ!

እግዚአብሔር አለ!!

@Youth4Christ

Y4C

29 May, 07:26


"እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።”
— 2 ዜና 15፥2

@Youth4Christ

Y4C

28 May, 05:35


"እግዚአብሔርን ደጅ እጠናለሁ፤ ነፍሴም በትዕግሥት ትጠብቀዋለች፤ በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ።ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።"

መዝሙር 130:5-6 (አዲሱ መ.ት)

@Youth4Christ

Y4C

27 May, 04:16


"እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ ሐሳቤ ለዐጒል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም። ነገር ግን ነፍሴን ጸጥዝም አሰኘኋት፤ ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች። እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።"

መዝሙር 131: 1-3  (አዲሱ መ.ት)

@Youth4Christ

Y4C

26 May, 18:06


Watch "Ante GetaNeh (አንተ ጌታ ነህ) | Ayda Abraham | Live 2023" on YouTube
https://youtu.be/C9lnrK8vkPY