mensur abdulkeni official

@mensurabdulkeniofficia


mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:34


BisratSport Tuesday: Hamle 23, 2011

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:33


- የኒኮላ ፔፔ ዝውውር ጉዳይ
- ታላቁ ዳንኤሌ ዴ ሮሲ
(ልዩ ትንተና) የብስራት-ስፖርት የእሁድ ፕሮግራም

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:32


👉የጋርዝ ቤል ወደ ቻይናው Jiangsu Suning ክለብ ሊያደርገው የነበረውን ዝውውር በ ማድሪድ በኩል ተቋረጠ። በመሆኑም የስፔኑ ክለብ ንብረት ሆኖ ይቆያል።[BBC SPORT]

📌የቻይናው ክለብ ለ ቤል £1m ሳምንታዊ ክፍያ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል።
@bisratsport101 @bisratsport101

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:32


የሜሲ ወላጆች ልፋት
(ክፍል 1)
…ሆርጌ ሆራሲዮ ሜሲ ደስታ አሰከረው፡፡ በቻለው ፍጥነት ሁሉ ከብረታ ብረት ፋብሪካው ወደ ቤቱ ሮጠ፡፡ በአቧራማው መንገድ ላይ ለአላፊ አግዳሚው ሰላምታ እየሰጠ በእግሩ በረረ፡፡ ወንዙን አቋረጠ፡፡ ከፍጥነቱ የተነሳ እግሮቹ መሬት እንኳን የሚረግጡ አይመስሉም፡፡ በኤስታዶ እስራኤል ጎዳና የሚገኘው ቤቱ የቅርብ ሩቅ ሆነበት፡፡ እንደደረሰ የፊት ለፊቱን በር በኃይል ገፍትሮ ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡ በደስታ ይጮሃል፡፡ ባለቤቱና ሴት ልጁን ሲያገኝ ደግሞ በታላቅ ድምጽ ቤቱን አናወጠው፡፡
‘‘ገንዘቡን አገኘን! ገንዘቡን አገኘን!’’
የሊዮኔል ሜሲ አያት ሴሊያን ጨምሮ መላው የቤተሰቡ አባላት በምግብ ጠረጴዛው ዙሪያ ተቀምጠዋል፡፡ የራት ሰዓት ደርሷል፡፡ አባወራውን የህጻን ያህል ያስፈነጠዘው ነገር ምን ይሆን? ከምግብ ይልቅ የወሬው ረሃብ ቤተሰቡን አጣደፈው፡፡ ማቲያስ፣ ሮድሪጎ፣ ሊዮ እና ትንሹዋ ማሪያ በአንድ ወገን፣ አዋቂዎቹ ደግሞ በሌላ ወገን ተደርድረዋል፡፡
ሆርጌ ጉሮሮውን አጽድቶ ለማውራት ሲዘጋጅ አላስችል ያላት እናት ሴሊያ ‘‘ተናገረው! ተናገረው እንጂ! ምንድነው?’’ በማለት ባለቤቷ ፈጥኖ እንዲያወራ ወተወተችው፡፡፡
‘‘የማህበራዊ ደህንነት ፋውንዴሽኑ የወጪውን አካፋይ ሊሸፍን ተስማምቷል’’ እያለ በደስታ ሲቃ የምስራቹን ለቤተሰቡ አበሰረ፡፡ ሴሊያ ግን ለየምስራቹ ‘‘ምስር ብላ!’’ ከማለት ይልቅ ሌላ ጥያቄ አስከተለች፡፡
‘‘አካፋይ? የምን አካፋይ?... የቀረውን ክፍያስ ማን ይከፍልልናል?’’
‘‘ምነው ሴሊያ፣ አስጨርሺኝ እንጂ?!’’
‘‘የተቀረውን ደግሞ አሲዳር የብረታብረት ፋብሪካ ይሸፍንልናል፡፡’’

የሜሲ ቤተሰብ በእግር ኳስ ፍቅር ያበደውን ልጃቸውን ከመደገፍ ወደኋላ አላሉም፡፡ ትንሹን ሜሲ ያየ ሁሉ ስለተሰጥኦው መስክሮለታል፡፡ ተስፋው ብሩህ መሆኑን ያወቁት ወላጆች ግን ልጃቸው በተፈጥሮ የአካል ዕድገት ውስንነት እንዳለበት በምርመራ መረጋገጡ አስደንግጧቸዋል፡፡ በዘመኑ ህክምና የሆርሞን መርፌ መውሰድ እንዳለበት በሙያው በተከበረ ሐኪም ከተነገራቸው ጀምሮ የህክምናው ዋጋ ውድነት በብረታ ብረት ፋብሪካ ውስጥ በዝቅተኛ ተከፋይነት፣ ከእጅ ወደ አፍ ለሚኖረው ቤተሰብ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሆኗል፡፡ በመርፌ የሚሰጠው የዕድገት ሆርሞን ዋጋ ሲነገራቸው የሜሲ ወላጆች እንደተወጋ በሬ ደንዝዘው ቀርተዋል፡፡ ሆርጌ በደስታ ጨርቁን የጣለው በዚያ ሰሞን እንቅልፍ የነሳቸው ጉዳይ እስከወዲያኛው ዕልባት በማግኘቱ ነበር፡፡
ለጥያቄዋ አርኪ ማብራሪያ ካገኘች በኋላ የእመት ሴሊያ ልብ አረፈ፡፡ ዘና አለች፡፡ ደስታው ከሆርጌ ወደ ጠረጴዛው ዙሪያ ተላለፈ፡፡ ሊዮ ግን አልፈነጠዘም፣ አይኖቹን ጨፍኖ በዝምታ አምላኩን አመሰገነ፡፡
* * *
…. ሊዮኔል ሜሲ በሳሎኑ ድንክ መቀመጫ ላይ አረፍ ብሎ እግሩን መርፌ ሲወጋ ወንድሞቹ በጭንቀት ተመለከቱት፡፡ ትንሹ ወንድማቸው ጨከን ብሎ ራሱን በራሱ የማከም ግዴታ ውስጥ በመግባቱ አዝነውለታል፡፡
‘‘ሊዮ አንተ ግን እብድ ነገር ነህ፡፡ እኔ ብሆን ኖሮ አላደርገውም ነበር’’ አለ ሮድሪጎ፡፡
‘‘ቁመትህ ያድግልሃል ብትባል ኖሮ አንተም ታደርገው ነበር’’ አለው ሊዮ፣ ታላቅ ወንድሙን ቀና ብሎ ከተመለከተው በኋላ፡፡
‘‘ምን ይጠቅመኛል? እኔ ረጅም ነኝ፡፡’’
ሊዮ እንደመበሻጨት ብሎ ተሳድቦ መርፌውንና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎችን ሰብስቦ በቦርሳቸው ውስጥ አኖራቸው፡፡ ያን ጊዜ ሁለቱ ወንድሞቹ ‘‘በቃ! እዚያው ሜዳ ላይ እንገናኝ’’ ብለውት በፊተኛው በር ተከታትለው ወጡ፡፡
ሊዮ ሜሲ ህክምናውን ከጀመረ ገና አንድ ሳምንት መሆኑ ነው፡፡ ላለበት የአካል ዕድገት ውስንነት የታዘዘለትን መርፌ ጥርሱን ነክሶ፣ በየዕለቱ ራሱን በራሱ መውጋት ግዴታው ሆነ፡፡ በመጀመሪያ ዶክተሩ እንዴት መውጋት እንዳለበት አስተማረው፡፡ በኋላም የእርሱ ስራ መሆኑን ነገረው፡፡ ቁመቱ እስካደገ ድረስ መርፌው ወደ አካሉ ውስጥ ሲገባ የሚሰማው ዕለታዊ ህመም ምንም አልነበረም፡፡ በሚወደው እግር ኳስ የሚመኘው ደረጃ ላይ እንዲደርስ ተክለ ሰውነቱ በተፈላጊው ደረጃ ማደግ ስላለበት ይህ መሆኑ ግድ ነው፡፡
በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ሜሲ የኒዌልስ ኦልድ ቦይስ ታዳጊ ቡድንን ከአንድ ድል ወደ ሌላ ድል አሸጋገረው፡፡ ኒዌልስ በዋንጫ ላይ ዋንጫን እየደራረበ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
* * *
… የሆርሞኑን ህክምና ከጀመረ አንስቶ አድጎ እንደሁ በማለት ማልዶ እየተነሳ ቁመቱን መለካት ልማዱ ሆነ፡፡ በዚያች ማለዳ ግን ሜሲ አዲሱን ቀን በህመም ተቀበለው፡፡ ከእንቅልፉ ሲነቃ ጤናማ እንዳልሆነ ተሰማው፡፡ ከትምህርት ቤት ለመቅረት ሆን ብሎ አመመኝ የሚለው አይነት ህመም አልነበረም፡፡ ከአልጋ መነሳት እስኪያቅተው ድረስ ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጸጉሩ ድረስ ጠፍንጎ ያዘው፡፡
እናቱ ሴሊያ ቴርሞሜትር ይዛ ወደ ክፍሉ ገባች፡፡ ቃል ሳትናገር አፉ ውስጥ አኖረችው፡፡ ሰዓቱን ጠብቃ ስታወጣው 101 ዲግሪ ፋራናይት ይላል፡፡ ሰውነቱ በትኩሳት ግሏል፡፡
‘‘ዛሬ ከቤት አትወጣም፣ ታመሃል፡፡ ዕረፍት አድርግ፡፡ ሾርባ እሰራልሃለሁ’’ አለች ሴሊያ እንደመደንገጥ ብላ፡፡
‘‘እንዴ! እማዬ! ዛሬማ ቤት መቀመጥ አልችልም፡፡ መውጣት አለብኝ፡፡’’
ሴሊያ ጆሮዋን ማመን አልቻለችም፡፡ ዞር ብላ የእናትነትዋን መልስ ሰጠችው፡፡
‘‘ዛሬ ትምህርት ቤት ዝግ ነው ለካ፡፡ ቅዳሜ ስለሆነ ያ መከረኛ ጨዋታ አለኝ ልትለኝ ነው አይደል? በቃ ምንም ዓይነት በሽታ አያቆምህም ማለት ነው?’’
ሁልጊዜም ከልጆቿ ጋር ስትሟገት እንደምታደርገው ፊቷን ወደ እርሱ አዙራ እጁዋን አጣምራ ከፊት ለፊቱ ቆመች፡፡
‘‘የዛሬው ይለያል እኮ፡፡ ለዋንጫ ነው የምንጫወተው፡፡’’
ሙግቱን ልትረታ እንደምትችል ስታውቅ እጆቿን አጣምራ ተሟጋቹ ፊት መቆሟን መላ የቤተሰቡ አባላት ያውቃሉ፡፡
‘‘የዋንጫ?’’
እጆቿን በአየር ላይ ቀዝፋ ተስፋ በመቁረጥ ከክፍሉ ወጣች፡፡
ጥቂት ቆይቶ አሰልጣኝ ቬኪዮ ወደ ትንሹ ሜሲ ቤት መጡ፡፡ የኒዌልስ ኦልድ ቦይስ የታዳጊ ቡድን አሰልጣኝ ናቸው፡፡ በእርግጥም የዋንጫ ጨዋታ አለባቸው፡፡ ሜሲን ሲመለከቱት ጠውልጎ አገኙት፡፡
‘‘ምነው? ታመሃል እንዴ? ደህና አትመስልምኮ?’’ ቬኪዮ ጠየቁ፡፡ መዳፋቸውን በግንባሩ ላይ ጭነው ትኩሳት እንዳለው ተረዱ፡፡ ከባድ ውሳኔ ማሳለፍ ነበረባቸው፡፡ የዳሌያቸውን ታችኛውን ክፍል መታ መታ አድርገው ጥቂት ካሰቡ በኋላ ‘‘አዝናለሁ፡፡ ዛሬ ታመሃል’’ አሉት፡፡
ሜሲ በዋንጫው ጨዋታ ላይ ይሰለፍ ዘንድ እንዲፈቅዱለት ህመሙን መደበቅ ነበረበት፡፡
‘‘በእውነት ያን ያህል አልታመምኩምኮ፡፡ እውነቴን ነው፡፡’’ ቢልም ሳሉ ከንግግሩ ይቀድም ነበር፡፡ አሰልጣኙ ሳቅ ብለው ጀርባውን ቸብ ቸብ ካደረጉት በኋላ ‘‘አዝናለሁ፡፡ ለዛሬ አይቻልም’’ ሲሉ ቁርጡን ነገሩት፡፡
ሊዮ ሰማይ ተደፋበት፡፡ አቀርቅሮ እግር እግሮቹን እያየ መሬቱን በካልቾ ይነርት ጀመር፡፡ የአሰልጣኙንም ውሳኔ ቢቀበልም ወደ ሜዳ ሄዶ ጨዋታውን ለመመልከት ወሰነ፡፡
ጨዋታው ተጀምሮ በ10 ደቂቃ ውስጥ ኒዌልስ ጎል ተቆጠረበት፡፡ ቬኪዮ የሆነውን ባለማመን ጭንቅላታቸውን ሲነቀንቁ ተጠባባቂ ወንበር ላይ የተቀመጠው ሜሲ ቀና ብሎ ተመለከታቸው፡፡ 20 ደቂቃ ከመሙላቱ በፊት ኒዌልስ ሶስት ሙከራዎችን ሲያደርግ ኒዌልስ አንድ ጊዜ እንኳን በቅጡ ማጥቃት አልቻለም፡፡ አሰልጣኙ በቡድኑ ሁኔታ ተስፋ ሲያጡ ወደ ሜሲ ዞረው ‘‘ቁንጫው፣ አሁንስ እንዴት ነህ? ህመሙ መለስ አለልህ?’’ ሲሉ ጠየቁት፡፡ ሊዮም ለዚህ ጥያቄ ምን ዓይነት መልስ መስጠት እንዳለበት ያውቅ ነበር፡፡

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:32


‘‘አለቃ! ስላሳረፍከኝ አመሰግናለሁ፡፡ አሁን በጣም ደህና ነኝ፡፡’’
አሰልጣኝ ቬኪዮ ዓይናቸውን ከሜሲ ላይ ነቅለው ለአርቢትሩ ምልክት ሰጡ፡፡ የኒዌልስ አጥቂ ወጥቶ ሜሲ ወደ ሜዳ ገባ፡፡
(ረቡዕ ይቀጥላል)
(ቀጣይ ባለታሪክ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ)
@mensurabdulkeniofficia

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:32


Lio Messi


@mensurabdulkeniofficia

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:31


France Football Vote

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:31


My Vote

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:31


የባሎን ዶር ሽልማት አዘጋጁ ፍራንስ ፉትቦል መጽሔት የአፍሪካ የምንጊዜም ኮከብ ተጫዋቾችን ምርጫ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ እነሆ የምርጫው ዝርዝርና ምርጫዎቼ፡፡
የአጠቃላዩ የምንጊዜም የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች ምርጫ ውጤት
1. ጆርጅ ዌአህ
2. ሳሙኤል ኤቶ
3. ሮዤ ሚላ
4. ዲዲዬ ድሮግባ
5. አቤዲ ፔሌ
የእኔ ምርጫዎች (በቅደም ተከተል)
1. ጆርጅ ዌአህ
2. ሳሙኤል ኤቶ
3. ሮዤ ሚላ
4. አቤዲ ፔሌ
5. ዲዲዬ ድሮግባ

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:31


https://t.me/mensurabdulkeniofficia

ይሄን ሊንክ ለጓደኞቻቹ እና ወደ ግሩፕዎች ሼር በማድረግ ተባበሩን።

መልካም ሰንበት!!

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:31


ውድ የስፖርት ቤተሰቦች!
የሸገር ክለቦችን የወቅቱን ፈተናዎች የተመለከተው ትንተና አዘል አስተያየቴ ይኸውላችሁ።
http://liyusport.com/?p=800&lang=am

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:30


የዛሬ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ብስራት-ስፖርት፣ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ያደረግነው ቃለምልልስ እነሆ።

mensur abdulkeni official

19 Jan, 02:30


Channel created