Kesis Getnet Aytenew @kesisgetnetaytenew Channel on Telegram

Kesis Getnet Aytenew

@kesisgetnetaytenew


Kesis Getnet Aytenew (Amharic)

ከሰላም በተለመኑ እና ጥሩ በትምህርት የሚጠቅመው እስከ ስለሆነ በተጠበቀ ድንገተኛ ታላቅ የመፅሐፍ መረጃ፣ አማርኛ ድምጽ እና የመጻሕፍት ፍላጎት ግማሽ የትምህርት ፕሮግራም እንዲሆኑ እንደተነጠቀ ት/ቤት እንዲሆኑ በከማቹ ማኅበረሰብ ጥራት ማጣሪያ ፕሾፌት ዮምፒንግ ርቀት ላይ መጻሕፍት ያልታወቁ ቺትሶማፐት ጽሁፍ ስኬልና ብልት ጠቃሚ እና ሁኔታ እንዲሆኑ እንደትምህርት ዜና አጫቢ እና መምርያ ይጠቁማል።

Kesis Getnet Aytenew

12 Jan, 11:28


➾ ሐዋርያ
➾ ወንጌላዊ
➾ ነባቤ መለኮት
➾ አቡቀለምሲስ
➾ ታኦሎጐስ
➾ ባለ ራእይ
➾ ዘንሥር
➾ ሰማዕት እንበለ ደም
➾ ፍቊረ እግዚእ
➾ ዘረፈቀ ውስተ ሕፅኑ ለእግዚእ
➾ ወልደ ነጐድጓድ
➾ ወልዱ ለዘብዴዎስ
➾ እኅወ ያዕቆብ ሐዋርያ
➾ ቊጹረ ገጽ

➥ ቅዱስ ዮሐንስ

የከበረች በረከቱ ትድረሰን። ለዘለዓለሙ አሜን።

Kesis Getnet Aytenew

11 Jan, 14:30


✞ የልደት መጀመሪያ ሳምንት ✞
❖ መዝሙር:- "ሃሌ ሃሌ ሉያ ይሠርቅ ኮከብ እምያዕቆብ ወየዓትት ኃጢአተ እም፳ኤል ወአነሂ በኲርየ እሬስዮ። ልዑል ውእቱ እምነገሥተ ምድር። ወይከውን ምስማከ ለኲሉ ምድር:......."

• የዕለቱ የቅዳሴ መልእክታት፣ ምስባክና ወንጌል

✞ መልእክታት:-
➊. ሮሜ ፲፩ : ፳፭ - ፍ:ም (11 : 25-ፍ:ም)
➋. ፩ኛ ዮሐንስ ፬ : ፩ - ፱ (4 : 1-9)
➌. የሐዋ/ሥራ ፯ : ፲፮-፳፫ (7-16-23)
.
✞ ምስባክ
ወአነሂ በኲርየ እሬስዮ።
ወልዑል ውእቱ እምነገሥተ ምድር።
ወለዓለም አዐቅብ ሎቱ ሣህልየ።
ትርጉም:-
እኔም ደግሞ አባቴ አደርገዋለሁ።
ከምድር ነገሥታት ከፍ ይላል።
ለዘለዓለም ምሕረቴን ለእርሱ እጠብቃለሁ።
(መዝ ፹፰:፳፮ /88:26)

✞ ወንጌል
ማቴዎስ ፪ : ፩ - ፲፪ /2 : 1-12
፩-፪
ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል። የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤

የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።
፭-፮
እነርሱም። አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ
ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።

ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥

ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ። ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።

እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።

ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።
፲፩
ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።

✞ ቅዳሴ = ዘዲዮስቆሮስ (እምቅድመ ዓለም) - በዕዝል ዜማ
...................................................
+ ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/kesisgetnetaytenew

+ ቴሌግራም መወያያ፦
https://t.me/gitsawie

Kesis Getnet Aytenew

11 Jan, 14:15


<<ወሀለውነ ዘበጽድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ ውእቱ ዘበአማን እግዚአብሔር ወብነ ሕይወት ዘለዓለም - እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።>>

[ ፩ኛ ዮሐንስ ፭ ፥ ፳ ]

ብዘገይም፦ እንኳን አደረሳችሁ።

Kesis Getnet Aytenew

04 Jan, 08:09


• • • ግጻዌ ዘኖላዊ • • •
ከብርሃን ቀጥሎ ያለው የጾመ ነቢያት የመጨረሻ (ከበዓለ ልደት በፊት የምናገኘው) ሳምንት "ኖላዊ" ይባላል። ትርጉሙም "እረኛ" ማለት ሲሆን የክርስቶስ ቸርነት፣ እረኝነትና ጠባቂነት ይነገርበታል። ይሰበክበታል።

✞ መዝሙር:- «ኖላዊ ዘመጽአ ውስተ ዓለም ወልዱ ወቃሉ ለእግዚአብሔር ዘወረደ እምላዕሉ በዓቅሙ ክርስቶስ። እስመ ውእቱ እግዚአ ለሰንበት። ይቤሎ አብ ለወልዱ ወልድየ ንበር በየማንየ።»

❖ የዕለቱ የቅዳሴ መልእክታት፣ ምስባክና ወንጌል

#መልእክታት
➊☞ ዕብራውያን ፲፫ : ፲፮ - ፍ:ም /13:16-ፍ:ም
፲፮
ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።
፲፯
ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ።
፲፰
ጸልዩልን፤ በነገር ሁሉ በመልካም እንድንኖር ወደን፥ መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናልና።
፲፱
ይልቁንም ፈጥኜ እንድመለስላችሁ ይህን ታደርጉ ዘንድ አጥብቄ እለምናችኋለሁ።

በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ #እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥
፳፩
በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
፳፪
ወንድሞች ሆይ፥ የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ፥ በጥቂት ቃል ጽፌላችኋለሁና።
፳፫
ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ እወቁ፥ ቶሎ ብሎም ቢመጣ ከእርሱ ጋር አያችኋለሁ።
፳፬
ለዋኖቻችሁ ሁሉና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣልያ የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
፳፭
ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

➋☞፩ኛ ጴጥሮስ ፪ : ፳፩-ፍ:ም /2:21-ፍ:ም
፳፩
የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
፳፪
እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
፳፫
ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
፳፬
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤
፳፭
በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ #እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።

➌☞የሐዋርያት ሥራ ፲፩ : ፳፪-ፍ:ም /
11:22-ፍ:ም
፳፪
ወሬውም በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ስለ እነርሱ ተሰማ፥ በርናባስንም ወደ አንጾኪያ ላኩት፤
፳፫
እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፥ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው፤
፳፬
ደግ ሰውና መንፈስ ቅዱስ እምነትም የሞላበት ነበረና። ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።
፳፭
በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ መጣ፤
፳፮
ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
፳፯
በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤
፳፰
ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።
፳፱
ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤

እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት።


✞ ምስባክ
ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል አጽምዕ፤
ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ፥
ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ።
ትርጉም፦
የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፤
ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ተገለጥ።
(መዝ ፸፱ : ፩ /79 : 1)

፨ ወንጌል
ዮሐንስ ፲ : ፩ - ፳፪ /10:1-22/

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤

በበሩ የሚገባ ግን የበጎች #እረኛ ነው።

ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።

የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤

ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።

ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም።

ኢየሱስም ደግሞ አላቸው። እውነት እውነት
እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።

ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።

በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
፲፩
መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
፲፪
እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል።
፲፫
ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።
፲፬-፲፭
መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብ እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።
፲፮
ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።
፲፯
ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።
፲፰
እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም
አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
፲፱
እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ።

ከእነርሱም ብዙዎች። ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ።
፳፩
ሌሎችም። ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።

✞ ቅዳሴ - ዘእግዚእነ (ነአኲተከ) - በዕዝል ዜማ

እንቅልፍ የሌለበት ትጉሕ፣ ጭካኔ የማይስማማው ቸር፣ ምንደኝነት የማይሻ መልካም እረኛ አምላካችን መድኃኔ ዓለም ጥበቃው አይለየን። ቸርነቱና ምሕረቱም ትብዛልን! አሜን።

Kesis Getnet Aytenew

14 Dec, 15:34


የማይማሩ የማያስተምሩ የማይጠይቁ የማይጠየቁ ባዶ ማድጋዎች መልተዋል።

እንነሣ !!

Kesis Getnet Aytenew

14 Dec, 14:22


🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ስርአተ ማህሌት ዘታህሳስ አርሴማ
☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሉ አለም፤በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አርሴማኒ ተወፈየ ሠለስተ ለቤተክርስቲያን ሃይማኖት ወተስፋ ወፍቅር ሃይማኖት ዲበ አብ ወተስፋ ዲበ ወልድ ተፈጻሜተ ፍቅር ዘመንፈስ ቅዱስ፤እንዘ ይብል አሐዱ እግዚአብሔር፤አንሰ አስተብቋዕክዎ
@EOTCmahlet
ዚቅ ዓዲ
፩ዱ አብ ቅዱስ ፩ዱ ወልድ ቅዱስ፤፩ዱ ዉእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘአድኃኖሙ ለሰማዕት።

@EOTCmahlet
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለአዕጋሪከ በክነፈ ነፋስ እለ ይረውፃ፤አብያተ ግፉአን የሐውፃ፤ሚካኤል የዋህ ወኅሩም እምነ ዓመፃ፤ተኖለው አዕጋርየ ለፍኖተ ስህተት እምዳኅፃ፤ወኀበ ምድረ ጽድቅ ምርሐኒ ከመ እብላዕ ሠርፃ
@EOTCmahlet
ዚቅ
ይሔውፅዋ መላእክት አንተ በሰማያት፤ይሔውፅዋ መላእክት እስመ ማኅደረ መለኮተ ዖድክዋ ዖድክዋ ዖድክዋ ወርኢኩ ስነ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምስእል ወምስጋድ፤ወምለት ሥራየ ኀጢአት ይዕቲ ቅድስት ደብተራ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
አክሊሎሙ አንተ ለሰማዕት ሠያሜሆሙ ለካህናት ወልደ እግዚአብሔር
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ፦
ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ዕጔለ አንበሳ ዕጔለ አንበሳ በከርሥኪ ፆርኪ፤እምአንስት ቡርክት አንቲ፤ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር፤አንቲ ዉእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር፤ዘኃረያ ፀባዖት አማኑኤል።
@EOTCmahlet
መልክአ አርሴማ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ በሰንዱነ ኪዳን ጥብሉል፤ወለስዕርትኪ ሰላም ዘፅርየተ ሕብሩ ፅዱል፤ሥርጉት ትዕግሥት አርሴማ ወዑፅፍተ ሐዲስ ገድል፤ይጸሐፍ በልሳንየ ወዘበእንቲአየ ቃለ፤መፆር ትርጓሜ ረቂቅ ኃይልኪ ፊደል
@EOTCmahlet
ዚቅ
አርሴማ እምነ በሀ፤ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርጉት በስብሐት፤ዓረፋቲሃ ዘመረግድ ሥርጉት በስብሐት፤ወማኅፈዲሃ  ዘቢረሌ  ሥርጉት በስብሐት፤ እምስነ ገድሎሙ ለሰማዕት ሥርጉት በስብሐት፤ታቦተ ሕጉ  ለንጉሥ ዐቢይ ሥርጉት በስብሐት፤እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፤ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ፡፡
@EOTCmahlet

ወረብ፦
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ ፀሐየ ጽድቅ/፪/
ታቦተ ሕጉ  ለንጉሥ ዐቢይ አርሴማ ሰማዕት/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ አርሴማ
ሰላም ለአዕጋርኪ...

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ቤተክርስቲያን መርዓቱ ለአልፋ ታቦቱ መኃትዊሃ ፯ቱ ከዋክብቲሃ ሰማዕታት እሙንቱ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ቤተክርስቲያን መርዓቱ ለአልፋ ታቦቱ ቤተክርስቲያን/፪/
መኃትዊሃ ሰብዓቱ ከዋክብቲሃ ሰማዕታት እሙንቱ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ አርሴማ
ሰላም ለበድነ ሥጋኪ ዘተሠርገወ ብናሴ፤ወለግንዘትኪ ዘኮነ በእደ መላእክት ሕዝበ ቅዳሴ፤አርሴማ ቅድስት በስብሐት ወበዉዳሴ፤ለፀላእትየ በባሕረ እሙቅ ድምሳሴ፤ያስጥሞሙ ኪዳንኪ ወኃይልኪ ሙሴ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
በሐ በልዋ ተሳለምዋ፤ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ፤ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ፤እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ወተቀደሰት በደሙ፤ወተአትበት በዕጸ መስቀሉ፤ጌሡ ኃቤሃ እስመ ሃይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
"በሐ በልዋ"/፪/ ተሳለምዋ/፪/
ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ ደዩ ልበክሙ ውስተ ሃይላ ለቤተክርስቲያን/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ አርሴማ
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ በቃለ ፈጣሪ ዘተቀደሰ፤ወንብረተ ዝንቱ ዓለም እንተ ኢኀሠሠ፤አርሴማ ብፅዕት ከመ ኢይርአይ ተፅናሰ፤ሴስይኒ እመዝገብኪ እስመ ኢይክል ሐሪሰ፤ወእስእለኪ ተሀብኒ ሐፍሰ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ብፅዕት ከርሥ እንተ ፆረትኪ፤ወብፁዓት አጥባት እለ ሐፀናኪ፤ ተክዕወ ሞገስ እምከናፍሪኪ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ብፅዕት ከርሥ ብፅዕት ከርሥ እንተ ፆረተኪ አርሴማ ቅድስት/፪/
ወብፁዓት አጥባት እለ ሐፀናኪ ተክዕወ ሞገስ እምከናፍሪኪ/፪/
@EOTCmahlet
ምልጣን
አርሴማ ቅድስት ሥርጉት በሃይማኖት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት ከመ ቂርቆስ ሕጻን ኢያፍርኃ ነበልባለ እሳት እስመ አጽንዓ ኃይለ አማኑኤል ጸባዖት
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
እስመ አጽንዓ ኃይለ አማኑኤል እስመ አጽንዓ/፪/
ኃይለ አማኑኤል ጸባዖት/፬/
@EOTCmahlet
ወረብ፦
አርሴማ ቅድስት ሥርጉት በሃይማኖት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት/፪/
ከመ ቂርቆስ ሕጻን ኢያፍርኃ ነበልባለ እሳት/፪/
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም ዘሰንበት
ይቤ ዳዊት በመዝሙር ፤መሠረታቲሀ ውስተ አድባረ ቅዱሳን፤ወካዕበ ይቤ ቀደሰ ማህደሮ ልዑል ፤ ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረክዋ፤ ማ፦ እግዚአ ለሠንበት በከርሣ ተፀውረ ፤ሰማየ ወምድር ዘውእቱ ፈጠረ
@EOTCmahlet
🍀🍀🍀
መዝሙር
🌺🌺🌺
ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ለእለ በሰማይ ወለእለ በምድር ለእለ በባሕር ወለእለ በየብስ ፣ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ለአበዊነ ነቢያት ወለሐዋርያት ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ለጳጳሳት ወለቀሳውስት ለዲያቆን ወለመነኮሳት ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ለጻድቃን ወለኃጥአን ለሙታን ወለሕያዋን ሠርዓ ሰንበት ለሰበእ ዕረፍተ፤ሰንበቱሰ ለክርስቶስ ይእቲ ወማኅደረ ስሙ ለልዑል

👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    # Join & share #

Kesis Getnet Aytenew

12 Dec, 06:41


+++ ዐዲሲቷ መቅደስ ወደ ቤተ-መቅደስ +++

ዓመተ ኲነኔ [ዓመተ ፍዳ] ሊፈጸም፣ ዓመተ ምሕረት ሊተካ ፲፭ ዓመት ሲቀረው ግንቦት ፩ ቀን በሊባኖስ ተራራ ተወለደች። ከእናት ከአባቷ ጋር አልከራረመችም።

የስእለት ልጅ ናትና ኢያቄምና ሐና "ሆዷ ዘመድ ሳይወድ፥ አፏ ምግብ ሳይለምድ ወደ ቤተ መቅደስ እናስገባት" ተባብለው ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሲሆናት ቤተ መቅደስ አስገቧት።

ለመለኮት ማኅደር ልትሆን የተገባት አማናዊቷ ቤተ መቅደስ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባች። ወደ ቤተ መቅደስ የገባችው ፫ ዓመት ከመንፈቅ ሲሆናት ነው።

ምነው በ፫ ዓመት አይደለምን ቢሉ፦ የጎደለውን ሞልቶ፥ የተረፈውን ትቶ መናገር የመጻሕፍት ልማድ ስለሆነ ነው እንጅ የገባችስ ፫ ዓመት ከመንፈቅ ሲሆናት ነው። ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ወደ ሰማዕትነት ዐደባባይ ብቅ ያለው በ፪ ዓመት ከ፱ ወር ነበር። ፫ ዓመት ብለው እንደጻፉልን ያለ ነው።

ክቡር ዳዊት አስቀድሞ፦ "ርሥዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ፤ እስመ ፈተወ ንጉሥ ሥነኪ - ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሽ። ንጉሥ ውበትሽን ወድዷልና። [መዝ ፵፬፥፲] ብሎ እንደተናገረላት የአባቷን ቤት ልትረሳ የተገባት ሆነ።

ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት ምክንያት ልትሆን በአምላክ ኅሊና ታስባ የኖረች ድንግል ማርያም ታኅሣሥ ፫ ቀን ለቤተ እግዚአብሔር መባዕ ሆና ተሰጠች። "እበውዕ ቤተከ ምስለ መባዕየ። ወእሁብ ብፅዓትየ ዘነበቡ በአፉየ። ዘእቤ በከናፍርየ አመ ምንዳቤየ - መባዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ። በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርኩትን÷ በከንፈሮቼም ያልሁትን ስእለቴን ለአንተ እሰጣለሁ።" እንዲል [መዝ ፷፭፥፲፫]

በዚያ በቤተ መቅደስም መልአኩ ሰማያዊ ምግብ እየተመገበች ፲፪ ዓመት ኖረች። በዚህ ዕድሜዋ ከእናት ከአባቷ ፍቅር መለየት ምን ዓይነት ድንቅ ነው። እንዴት ያለስ አሳዛኝ ነገር ነው። መልአኩ ሰማያዊ ምግብና ሰማያዊ ሲመግባት ደግሞ የደስታችን ጽዋዕ ይመላዋል።
"የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና፤
ወያሥተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልኅቀትኪ በቅድስና፤
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሤስየኪ መና፤
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና።" እንዲል ሊቁ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ።

የሀገረ ብሕንሳው ሊቅ አባ ሕርያቆስ፦
"ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ" ሲል ያደንቃል። (ቅዳሴ ማርያም)

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አማናዊት ቤተ መቅደስ መሆኗን ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ "መቅደስ ዘይኬልልዋ ኪሩቤል እለ ሥዑላን በሥዕለ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር የተሣሉ ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ አንቺ ነሽ።" (ውዳሴ ማርያም ዘእሑድ)

የእመቤታችን የእመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ረድኤት በረከት አይለየን። ምልጃዋ አይራቀን። አሜን።

© ቀሲስ ጌትነት ዐይተነው (ክንፈ ገብርኤል)
[ በድጋሜ የተለጠፈ ]

Kesis Getnet Aytenew

12 Dec, 06:41


እንኳን አደረሳችሁ...

Kesis Getnet Aytenew

12 Dec, 06:40


ውድ ወዳጆቼ እንዴት ከረማችሁ?

ከእኛ ዘንድ ኢንተርኔት ዝግ ስለሆነ ነው የጠፋሁ። የደወላችሁልኝ፣ የጻፋችሁልኝ በሙሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

እግዚአብሔር ይመስገን እኔ በቸርነቱ ደኅና ነኝ።

ቸሩ በሰላም ያገናኘን። በደኅና ቆዩኝ!

Kesis Getnet Aytenew

18 Aug, 11:16


ድርሳነ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ፦
• የገጽ ብዛት፦ 158
• የሕትመት ዘመን፦ 2016 ዓ.ም
• ባለ ገበታ (Hard cover)
• የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል) ክብር በሰፊው የተዳሰሰበት ደገኛ መጽሐፍ፦

መጽሐፉ የሥላሴን ዙፋን ዘወትር የሚጥኑ የሰማይ ካህናት (ሰማያውያን መላእክት) ክብራቸው የሚታወስበት ድርሳን ነው። በውስጡም በርካታ ምክርና እዝናትን የያዘ ሸጋ መጽሐፍ ነውና ሁሉም አማኝ ገዝቶ ቢያነበው መልካም ነው ስንል እንመክራለን።

በተለይም የመጋቢት እና የሚያዚያው ድርሳን ካህናትን እየገሠፀ ክብረ ክህነት እያጐላ ያስተምራል። ከግንቦት ድርሳን ጀምሮ ደግሞ ነገረ ድኅነት በሰፊው ተተርኮበታል። መልክዐ ፳ወ፬ቱ ካህናተ ሰማይ እና መልክዐ ፬ቱ እንስሳ'ም ተካትተውበታል። ቢነበብ ደግ ነው!

=> መጽሐፉን ለማግኘት፦ በየመጻሕፍት መደብሩ መጠየቅ ወይም በ0915551515 ወይም 0915551525 መደወል ይችላሉ።

Kesis Getnet Aytenew

18 Aug, 10:01


እንኳን አደረሳችሁ! <ነሐሴ ፲፫/13>
[በዓለ ደብረ ታቦር ወልደቱ ለሙሴ ወብንያም ወጋልዮን መስተጋድል]

=> የዕለቱ ግጻዌ

ምስባክ ዘነግህ
ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል።
ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉዓን።
ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ።
ትርጉም፦
የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው።
የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ?
እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ ይህን ተራራ ወደደው።
(መዝ ፷፯ : ፲፭ - ፲፮ /67:15-16)

+ ወንጌል ዘነግህ
የማቴዎስ ወንጌል ፲፯ : ፩ - ፲፬ /17:1-14

ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።

በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።

እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።

ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡— ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ፡ አለ።

እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፡— በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፡ የሚል ድምፅ መጣ።

ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።

ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡— ተነሡ አትፍሩም፡ አላቸው።

ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።

ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ፡— የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ፡ ብሎ አዘዛቸው።

ደቀ መዛሙርቱም፡— እንግዲህ ጻፎች፡— ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።
፲፩
ኢየሱስም መልሶ፡— ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
፲፪
ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው፡ አላቸው።
፲፫
በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።

+ መልእክታት:-
1. ወደ ዕብራውያን ፲፩ : ፳፫ - ፴ /11:23-30
2. ፪ኛ ጴጥሮስ ፩ : ፲፭ -ፍጻሜ /1:15-ፍጻሜ
3. ግብረ ሐዋርያት ፯ : ፵፬ - ፶፩ /7:44-51

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ።
መዝራእትከ ምስለ ኃይል።
ትርጉም፦
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል።
ስምህንም ያመሰግናሉ።
ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፤
(መዝ ፹፰ : ፲፪ - ፲፫/88:12-13)

+ ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ፱ : ፳፰ - ፴፰ /9:28-38
፳፰
ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
፳፱
ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤
፴፩
በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።
፴፪
ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።
፴፫
ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።
፴፬
ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
፴፭
ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
፴፮
ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ። ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።
፴፯
በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ / ዘዲዮስቆሮስ {በዕዝል ዜማ ቀድስ}

በቅዱሱ ተራራ መለኮታዊ ክብሩን የገለጸ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ዕውቀቱን ጥበቡን ማስተዋሉን ያድለን። በመንግሥቱም ያስበን። የክብርት እናቱ ምልጃም አይለየን።

፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠
❀❀❀✿❀❀✿ ❀❀❀
________
+ ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/kesisgetnetaytenew

+ ቴሌግራም መወያያ፦
https://t.me/gitsawie

Kesis Getnet Aytenew

08 Aug, 16:19


የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን ፋና ማጣሪያ አረጋግጧል፡፡

ተጨማሪ በጀቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤትም ሆነ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባልጸደቀበት ሁኔታ መሰል ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱ ተገቢ እንዳልሆነ ተመላክቷል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ በሚል የተሰራጨው እና ከታች በምስል የተያያዘው መረጃ ሃሰተኛ እና አሳሳች መሆኑም ተረጋግጧል፡፡

© Fana

Kesis Getnet Aytenew

08 Aug, 15:51


☞ ነሐሴ ፫ (ሦስት)
[ስምዖን ዘዐምድ ወቅድስት ሶፍያ]

✞ መልእክታት:-
፩. ፩ኛ ወደ ተሰሎንቄ ፫ : ፩ - ፍጻሜ
፪. ፩ኛ ጴጥሮስ ፫ : ፲ - ፲፭
፫. የሐዋርያት ሥራ ፲፬ : ፳ - ፍጻሜ

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ።
ወለገጽኪይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር።
ኲሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን።
ትርጉም:-
የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል።
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትህ ይማለላሉ።
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤
(መዝ ፵፬ : ፲፪-፲፫ /44:12-13)

✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ፲፰ : ፱ - ፲፰ /18:9-18

ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥

እንዲህ ሲል። ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።
፲፩
ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ። እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤
፲፪
በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።
፲፫
ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን። አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።
፲፬
እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።
፲፭
እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ደግሞ ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ዐይተው ገሠጹአቸው።
፲፮
ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠርቶ። ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው አትከልክሉአቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።
፲፯
እውነት እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አለ።

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) ~ (በግዕዝ ዜማ)
...................................................
+ ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/kesisgetnetaytenew

+ ቴሌግራም መወያያ፦
https://t.me/gitsawie

Kesis Getnet Aytenew

07 Aug, 17:24


• ነሐሴ ፪ (ሁለት) •
[አትናስያ ቅድስት ወደሚና ሰማዕት ወአኃዊሁ ወኢዮጰራቅስያ ብፅዕት]

+ መልእክታት
፩ኛ ጢሞቴዎስ ፪ : ፰ - ፲፭ /2:8-15/
፩ኛ ጴጥሮስ ፫ : ፩ - ፯ /3:1-7/
የሐዋ/ሥራ ፲፮ : ፲፫ - ፲፱ /16:13-19/

+ ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ።
ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ።
ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት።
ትርጉም:-
በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፥
ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፤
በደስታና በሐሴት ይወስዱአቸዋል፥
(መዝ ፵፭ : ፲፬ - ፲፭)

.
+ ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ፰ : ፬ - ፲፪ /8:4-12

መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።

ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።

የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤

መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።

ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።

ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።
፲፩
እርስዋም። ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም። እኔም አልፈርድብሽም፤ ሒጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።
፲፪
ደግሞም ኢየሱስ። እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ (ጎሥዐ) ~ (በግዕዝ ዜማ)
................................................
+ ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/kesisgetnetaytenew

+ ቴሌግራም መወያያ፦
https://t.me/gitsawie

Kesis Getnet Aytenew

07 Aug, 07:45


=> ነሐሴ ፩ (1)

✞ የቅዳሴ መልእክታት:-
➊. ፩ኛ ጢሞቴዎስ ፭ : ፩ - ፲፩ (5:1-11)
➋. ፩ኛ ዮሐንስ ፭ : ፩ - ፮ (5:1-6)
➌. የሐዋ/ሥራ ፭ : ፳፮ - ፴፬ (5:26-34)

✞ የቅዳሴ ምስባክ
ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኀፈር።
ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀረኩ ጥቀ።
ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ።
ትርጒም፦
በነገሥታት ፊት ምስክርነትህን እናገራለሁ። አላፍርም።
እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።
እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣሁ።
( መዝ ፻፲፰ : ፵፮ /118:46 )

+ የቅዳሴ ወንጌል
የዮሐንስ ወንጌል ፲፱ : ፴፰ - ፍጻሜ (19:38-ፍጻሜ)
፴፰
ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።
፴፱
ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ።

የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።
፵፩
በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።
፵፪
ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት።

+ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ /ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ/ (በግዕዝ ዜማ)
........................................................
+ ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/kesisgetnetaytenew

+ ቴሌግራም መወያያ፦
https://t.me/gitsawie

Kesis Getnet Aytenew

06 Aug, 17:36


ዱባዮች በነጭ ጎርፍ እየጎረፉ ነው።

በእውነቱ [ሥርዓት ከመጠበቅ ጋር] በዚሁ በርቱልን!

Kesis Getnet Aytenew

06 Aug, 16:46


እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ።

የበረከት ጾም ያድርግልን።

Kesis Getnet Aytenew

05 Aug, 18:57


"ከተጋባን ጀምሮ በስሕተት እንኳ ክፉ ነገር ተነጋግረን አናውቅም" የሚሉ ባለትዳሮችን ግን እንመናቸው? 🤔😊

Kesis Getnet Aytenew

05 Aug, 15:44


የምሥራቅ ጐጃም ሀገረ ስብከት የአጫብር ጾመ ድጓውን አሳትሞ አስመርቋል።

Kesis Getnet Aytenew

05 Aug, 15:13


መጣች ያቺ ጾመ ፍልሰታ
የሁላችን ደስታ

የበረከት ጾም ያድርግልን።

Kesis Getnet Aytenew

04 Aug, 11:24


እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር፦
ከዚህ ቀደም ስናደርግ እንደነበረው ጉባኤ ቤቶችን ወደ ማገዝ እንመለሳለን።

የጉባኤ ቤት ፍቅር ያገበራችሁ ወዳጆቼ ተዘጋጁ!