84 ዓመት
መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሀና 84 ዓመት ቀንና ለሊት በፆምና በፀሎት፣ እለት እለት እያገለገለች ከቤተመቅደስ አትለይም ነበር ይላል። "እለት እለት" ሊያውም ቀንና ለሊት። ይሄ ሁሉ ዓመት ፈተና ሳይኖር ቀርቶ አይደለም።
እኛ አንድ ግዜ እንመጣለን አንዴ እንቀራለን፣ ቀላል በሆኑ ምክንያቶች ወደኋላ እንቀራለን።
ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በመኖሯ ምን አመጣላት እኛስ ብንኖር ምን እናገኛለን ለሚለው መልስ - እመቤታችን ጌታን ይዛው በ40 ቀኑ ወደ ቤተመቅደስ ሲመጣ ሀና እሱን ለማየት በቃች። በዚያች ቅፅበት የሌለ ሰው እኮ አያገኘውም።
ሚል 3 - የምትጠባበቁት ጌታ ድንገት በመቅደሱ ይገለጣል ይላል። መቅደሱ እኮ ሁሌም ቤቱ ነው ድንገት ይገለጣል ማለት ፀጋ የሚሰጥበት፣ ክብር፣ ኃይል የሚያድልበት፣ እለተ በረከት አለው።
ስንመኘው የነበረው፣ እግዚአብሔርን ስንለምነው የነበረውን ነገር ሊሰጠን ሲመጣ እኛ ደግሞ ከቤቱ እንዳንጠፋ። በትጋታችን ልክ ዋጋ እንቀበላለን።
በክርስትያን ህይወት ከሁሉ ከሁሉ ምን ይቀድማል? የሚቀድመው ቤ/ክ መምጣት ነው! ሳይመጡ መማር የለም፣ ሳይመጡ ማወቅ የለም፣ ሳይመጡ ንስሃ የለም፣ ሳይመጡ ቁርባን የለም፣ ሳይመጡ መለወጥ የለም። የአንድ ክርስቲያን የመጀመሪያው ስራው ወደ ቤ/ክ መምጣት ነው። ከመጡ ነው ማወቅ መሻሻል ያለው።
@KaleEgziabeher