Latest Posts from "ቃለ እግዚአብሔር " (@kaleegziabeher) on Telegram

"ቃለ እግዚአብሔር " Telegram Posts

"ቃለ እግዚአብሔር "
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።
7,919 Subscribers
652 Photos
22 Videos
Last Updated 28.02.2025 18:30

The latest content shared by "ቃለ እግዚአብሔር " on Telegram


ጌታችን ለአቡነ መብዓ ጽዮን የወርቅ በትር ሰጥቷቸው በእርሷ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጡባት ነበር፡፡ መቋሚያዋም እሳቸው ካረፉ በኋላ የሚሞተውን ሰው እየለየች ትናገር ነበር፡፡ አባታችን እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም በመልአክ ተጥቀው ተወስደው የሥላሴን መንበር ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር አጥነዋል፡፡ ጌታችን ከተረገመችና ከተወገዘች ዕፅ ጋር በተገናኘ ለአቡነ ዘርዐ ቡሩክና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ልዩ ምሥጢር እንደነገራቸው በሁለቱም ቅዱሳን ገድላት ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡

አቡነ መብዓ ጽዮን በይበልጥ የሚታወቁት ሁልጊዜ ወር በገባ በሃያ ሰባት መድኃኔዓለምን አብልጠው በመዘከራቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት "እንደ አንተም በየወሩ በሃያ ሰባት የሞቴ መታሰቢያ ለሚያደርግ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣለታለሁ" የሚል ድንቅ ቃልኪዳን ከጌታችን ተቀብለውበታል፡፡ ይኸውም የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ሲነግራቸው ነው፡፡ ቅዱስ አባታችን "ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ! በዓልህን አደርግ ዘንድ አንተ የምትወደውን ግለጥልኝ" ብለው ጌታችንን ሲጠይቁት እርሱም "የሞቴን መታሰቢያ ያደረገ እንደ እኔ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ "በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ይሠራል፣ ከዚያም የበለጠ ይሠራል" ብዬ በወንጌሌ እንደተናገርሁ" አላቸው"፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ለልጆቻቸው እንዲህ ብለው መከሯቸው፡- "ክርስቲያኖች ሁሉ የፈጣሪያችንን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን የመታሰቢያ በዓሉን እናድርግ፡፡ የአባቶቻችን የሐዋርያት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የመላእክት መታሰቢያቸው ባረፉበት በተሾሙበት ቀን ይከበራል፡፡ እነርሱን የፈጠራቸው እርሱ መድኃኔዓለም ነው፣ ያከበራቸው፣ ከፍ ከፍ ያደረጋቸው፣ ስማቸውን ለጠራ መታሰቢያቸውን ያደረገ እንደሚድን ቃልኪዳን የሰጣቸው እርሱ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ ያደረገ ግን የተኮነኑ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ በሞቱም ጊዜ ሥቃይን አያያትም"፡፡

የአቡነ መብዓ ጽዮን በዓለ ዕረፍታቸውም እጅግ አብዝተው በሚዘክሩበትና ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ታስቦ በሚውለው በመድኃኔዓለም ቀን ጥቅምት ሃያ ሰባት ነው፡፡ ከአባታችን አቡነ መብዓ ጽዮን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!።

+ + +
አቡነ ጽጌ ድንግል፡- ደራሲና ማኅሌታዊ ሲሆኑ የላመ የጣፈጠ ከመብላት ተቆጥበው ጥሬ ቆርጥመው 9 ዓመት ከቆዩ በኋላ የእመቤታችንን ስደት በጣም በጥልቀት የሚተርከውን "ማኅሌተ ጽጌን" የደረሱ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ውኃም በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነበር የሚጠጡት፡፡

አቡነ ጽጌ ድንግል ከደብረ ሐንታው ከአቡነ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰቱን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር በአንድነት አግልግለዋል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡-
አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥተው ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አቡነ ጽጌ ድንግል ከገዳማቸው ከደብረ ብሥራት ተነሥተው ወደ ደብረ ሐንታ ሄደው እንዲሁ እንደ አቡነ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አግልግለው ይመለሳሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን እንደዚህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ ሌላኛው ገዳም እየሄዱ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና አብረው እመቤታችንን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ ይኸውም በራሳቸው በአቡነ ገብረ ማርያም ገድል ላይ እና በአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ገጽ 72-73 ላይ በሰፊው ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ የሁለቱ ድርሰታቸው የሆነው "ማኅሌተ ጽጌ" ድርሰት የእመቤታችንንና የልጇን የጌታችንን ሥጋዊ ስደት የሚገልጽ ሲሆን በጨማሪም ስደት የማይገባው አምላካችን ወደ አህጉራችን አፍሪካ ተሰዶ የሠራቸውን ድንቅ ድንቅ ተአምራትና የእመቤታችንን ንጽሕናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷን የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

አባ ጽጌ ድንግል ከማኅሌተ ጽጌ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ አስደናቂ ድርሰቶችን ደርሰዋል፡፡ የጻድቁ ቅዱስ ዐፅማቸው፣ ታቦታቸውና የደረሷቸው በርካታ ድርሰቶች በገዳማቸው ደብረ ጽጌ ውስጥ በክብር ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡ አምሃራ ሳይንት ቦረና ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከተሄደ በኋላ የሚገኘው ገዳማቸው "ደብረ ጽጌ" ከአንድ ወጥ ዓለት ተፈልፍሎ የተሠራው ሲሆን አሠራሩም እጅግ ድንቅ ነው፡፡

የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ጋር የሚያገናኘው "የእግዜር ድልድይ" የተባለ አስገራሚ ታሪክ ያለው ድልድይ አለው፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በመንፈስ ተጠራርተው ለመገናኘት ቢያስቡም የወለቃ ወንዝ ሞልቶ በአካል ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ በዚህም በጣም አዝነው ከወንዙ ወዲያና ወዲህ ሆነው ተላቅሰው አፈር ተራጭተው ወደየገዳማቸው ቢመለሱም ያ ተላቅሰው የተራጩት አፈር በተአምር ትልቅ ድልድይ ሆነ፡፡ ድልድዩን ሁለቱም በበዓታቸው ሆነው በመንፈስ አዩት፡፡ የበጎ ነገር ጠላት ሰይጣንም ይህንን ሲመለከት ድልድዩን
በትልቅ ሹል ድንጋይ በስቶ ሊያፈርሰው ሲል አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመንፈስ አዩትና ከጋስጫ ተነሥተው በደመና ተጭነው በመሄድ ሰይጣኑን በግዘፈ ሥጋ ገዝተው ያንን ድልድዩን አፈርስበታለሁ ያለውን ትልቅ ሹል ድንጋይ አሸክመውት በዓታቸው ጋስጫ ድረስ ወስደውታል፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬ በጋስጫ አቡነ ጊዮርጊስ ገዳም ለመነኮሳቱ ደወል ሆኖ እያገለገለ ይኛል፡፡ ድልድዩም እስከ አሁን ድረስ ለአካባቢው ኢስላም ማኅበረሰብ ብቸኛው የወለቃ ወንዝ መሻገሪያቸው ሆኖ እያገለገላቸው ነው፡፡
ከአባታች አቡነ ጽጌ ድንግል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ይሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን! ምንጭ፦ገድለ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ መዝገበ ቅዱሳን።

+ + +
አባ መቃርስ ዘሀገረ ቃው፡- ለዚህም ቅዱስ የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ ያልሔደ በኃጢአተኞችም ጎዳና ያልተጓዘ በዘባቾችም መቀመጫ ያልተቀመጠ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል።

ይህም አባ መቃርስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ በመክሊት ነግዶ ዕጥፍ አድርጎ አትርፎአልና እግዚአብሔርም በእጆቹ ያደረጋቸውን ታላላቆች ድንቆች ተአምራት ስንቱን እናገራለን። ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ በአገረ ቃው ተሾሞ በወንበር ተቀምጦ ሕዝቡን በሚያስተምራቸው ጊዜ ዘወትር ያለቅሳል ከደቀ መዛሙርቶቻቸውም አንዱ በእግዚአብሔር ስም ካማላቸው በኋላ ለምን ሁልጊዜ እንደሚያለቅሱ በመሐላው አምሎ ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ስለመሐላቸው ፈርተው ነገሩት "ዘይት በብርሌ ውስጥ ጎልቶ እንደሚታይ

የወገኖቼም ኃጢአት እንዲሁ በታየኝ ጊዜ አለቅሳለሁ" አሉት፡፡ በሌላም ጊዜ ጌታችን በመሠዊያው ላይ ሆኖ ተገልጦላቸው የእያንዳንዱን ሰው ኃጢአት መላእክት ሲያቀርቡለት አሳያቸው፡፡ ቀጥሎም "ሕዝቡን አስተምረህ ከክፋታቸው መልሳቸው" አላቸው፡፡ እሳቸውም "አይሰሙኝም" ቢሉት ጌታችንም "አስተምረሃቸው ከክፋታቸው ባይመለሱ ደማቸው በራሳቸው ላይ ይሆናል" አላቸው፡፡

መናፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስና ተከታዮቹ ክብር ይግባውና ጌታችንን "ሁለት ባሕርይ" በማለታቸው ጉባዔ ሠርተው አባቶች ሲሰበሰቡ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አባ መቃርስን አስከትሎ በጉባዔው ተገኘ፡፡ አባ ዲዮስቆሮስና አባ መቃርስም ሁለት ባሕርይ ባዮችን አስተምረዋቸው እምቢ ቢሏቸው አውግዘውና እረግመው ከቤተ ክርስቲያን ለዩአቸው፡፡ ለመከራም የተዘጋጁ ሆነው ራሳቸውን አሳልፈው ሰጧቸው፡፡ ከሃዲው ንጉሥም ወደ ጋግራ ደሴት አጋዛቸው፡፡ አባ ዲዮስቆሮስም ለአባ መቃርስ "አንተ በእስክንድርያ ሀገር ሰማዕትነት ትቀበላለህ" በማለት ትንቢት ነግረዋቸው ከአንድ ነጋዴ ጋር ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡ እዚያም ሲደርሱ መናፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስ አባ መቃርስን ይዞ ብዙ ካሠቃያቸው በኋላ ኩላሊታቸውን ብሎ ገደላቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ጥቅምት 27 ቀን ሆነ፡፡ ክርስቲያኖችም ሥጋቸውን ወስደው ከነቢዩ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ መቃርስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት27 ስንክሳርና መዝገበ ቅዱሳን።

+ + +
የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም። ወገብረ መድኃኒት በማእከለ ምድር። አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ"። መዝ73፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ27፥20-57።

+ + +
የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ተሣለኒ እግዝኦ እስመ ኬደኒ ሰብእ። ወኵሎ አሚረ አሥርሐኒ ቀትል። ወኬዱኒ ፀርየ ኵሎ ዓሚረ በኑኀ ዕለት"። መዝ55፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 1 ኛቆሮ 12፥20-28፣ 1ኛ 2፥20-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 5፥12-17። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ3፥11-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ በዓል፣ የአባ ጽጌ ድንግልና የአቡነ መብዓ ጽዮን የዕረፍታቸው በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
መልካም። ቀን

#ክፉ_አሳብ

ልጆቼ! ከመጀመሪያውኑ ክፉ አሳብ ባታስቡ መልካም ነው፡፡ ካሰባችሁ ግን ቢያንስ አትናገሩት፡፡ በዚያው በሕሊናችሁ ውስጥ እያለ ዝም አሰኙት፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም ወዳለመኖር ይኼዳል፡፡

እኛ ሰዎች ነን፡፡ በመኾኑም ብዙውን ጊዜ ክፉ፣ ያልተገቡና ጸያፍ ነገሮችን እናስባለን፡፡ ነገር ግን ቢያንስ እነዚህን አሳቦች አንናገራቸው፤ ቢያንስ ወደ ቃል አንለውጣቸው፡፡ ወደ ውጭ እንዳይወጡ አምቀን እንያዛቸው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እየከሰሙና እየደከሙ እየጠፉም ይኼዳሉ፡፡ አንድን እንስሳ ወደ ጉድጓድ ብትጥሉትና ጉድጓዱንም በመክደኛ ብትከድኑት ያ ወደ ጕድጓድ የጣላችሁት እንስሳ የሚተነፍሰውን አየር አጥቶ ይሞታል፡፡ ምናልባት ጥቂት ቀዳዳ ካገኘ ግን በዚያች ቀዳዳ በምትገባው አየር በሕይወት መቆየት ይችላል፡፡ ሲጨንቀውም እናንተን ክፉኛ ለመጉዳት ይዝታል፤ ከወጣም በኋላ ይጎዳችኋል፡፡ ልክ እንደዚሁ እናንተም በልቡናችሁ የተመላለሰውን ኩላሊታችሁ ያጤሰውን ክፉ አሳብ መውጫ ቀዳዳ እንዳይኖረው አድርጋችሁ ብትከድኑት (ብታፍኑት) ይሞታል፤ ከመኖር ወዳለመኖር ይለወጣል፡፡ በአንደበታችሁ በመናገር ጥቂት ቀዳዳ ከከፈታችሁለትና እንደ እንስሳው እንዲተነፍስ ከፈቀዳችሁለት ግን ክፉው አሳብ ክፉ ግብርን ይወልዳል፡፡ ያቆጠቁጣል፡፡ በአሳብ ሳለ ከጎዳችሁ በላይም በገቢር ተወልዶና ተለውጦ ክፉኛ ይጎዳችኋል፡፡

(#የክርስቲያኖች_መከራ #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ገጽ 7➛በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

https://youtu.be/rG7MzbsAT5k?si=1USv56raU4l5d4Pg

ወዳጄ ሆይ! ኃጢአተኛ ከኾንህ በደልህን ትናዘዝ ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ጻድቅም ከኾንህ ከጽድቅ (ጎዳና) እንዳትወድቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ቤተ ክርስቲያን የኃጥኡም የጻድቁም ወደብ ናትና፡፡

ኃጢአተኛ ነህን? ተስፋ አትቁረጥ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሐ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡

እስኪ ንገረኝ! “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ ምን ውጣ ውረድ፣ ምን ዓይነት የሕይወት መርሕ፣ ምንስ መከራ አለው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት (ኃጢአት ሠርተህ ሳለ) በደለኛ አይደለሁም የምትል ከኾነ ዲያብሎስም አንተን አይወቅስህም፡፡ (በድያለሁ ብለህ ንስሐ የምትገባ ከኾነ ግን) ይህን (ዲያብሎስ ሊወቅስህ እንደሚችል) አስቀድመህ አስብ፡፡ …

ስለዚህ ክብርህን እንዳይወስድብህ ለምን አትከለክለውም? ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?

ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” ብለህ ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም፡- “ንግር አንተ ኃጣውኢከ ቅድመ ከመ ትጽደቅ - ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡

ይህን ለማድረግ ውጣ ውረድ የለውም፤ ዙሪያ ጥምጥም የቃላት ድርደራም አያሻህም፤ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፤ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፡፡ አንዲት ቃል ተናገር፤ በደልህን በአንቃዕድዎ አስባት፤ “በድያለሁ” ብለህም ተናዘዛት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

​በፃድቁ ቀን ስራ አልገባም!!

ቢሮ ውስጥ አንዲት እህት የአብነ አረጋዊ ቀን ስራ አልሰራም ገዳማቸው ሄጄ ቁጭ ማለት ነው የምፈልገው አለችኝ ምነው በሰላም አልኩ እኔም ምክንያቷን ማወቅ ፈልጌ
ይገረመሀል ፍጼ በልጅነቴ በድንገት አይኔ ማየት ያቆማል ግንባሬ በጣም ማበጥ ጀመረ እናቴ ያለ እንቅልፍ ለብዙ ጊዜያት በለቅሶ ቆየች ታዲያ ባንደኝው ቀን አንድ የኔ ቢጤ በየቤቱ እየዞሩ ፍርፋሪ የሚለምኑ አባት የእናቴን ለቅሶ ዘወትር ያስተውሉ ነበርና እናቴን አይዞሽ አታልቅሽ ለእንደዚህ መዳኒት የሆነ ጸበል ይዥልሽ እመጣለው ማን ያውቃል እግዚአብሔር በፀበሉ ላይ አድሮ ሊፈውሳት ይችላል አሉ እንዳሉትም አልቀሩ በንጋታው በለሊቱ 10:00ላይ የአብነ አረጋዊ ጸበል ነው ብለው ለእናቴ ሰጧት አለችኝ ወሬውን ላፍታም እንድታቋርጠው አልፈለኩም ታምናለህ ፍጽም የመጀመሪያውን ጸበል ፊቴላይ ስታረገው አይቼው የማላውቀው ስሜት ነው የተሰማኝ ቀኑን ሙሉ በከባድ ህመም ቆየው ፊቴን በጣም ያሳክከኝ ነበር በሁለተኝ ቀን ጸበሉ ሲደረግ ከአበጠው ፊቴ ላይ መግል እና ደም ይፈስ ጀመር በሦስተኝው ቀን ፀበሉ ሲደረግልኝ ከ አይኔ ላይ ትል ይወድቅ ጀመር አለችኝ ታሪኳ ልቤን ወስዶታል ለካ አይኔን የጋረደው የአጋንንት ስራ ነው እግዚአብሔር ይመስገን በጻድቁ ጸበል እግዚአብሔር አደነኝ አለች እንባዎን መቆጣጠር እያቃታት ።እውነት ነው "የጻድቅ ሰው ጸሎት በስራዋ እጅግ ሀይል ታደርጋለች" ያዕ 5:16 የጻድቁ በረከት በሁላችን ይደር።
እኔም ጻድቁ ፈቅደውልኝ ከመልካም ሰው ጋር ዋል መልካም ታገኝለህ በሚለው መሠረት በመልካም ወንድሞች ትጋት እነዚያን በትግራይ ላይ የሚገኙ ድንቅ ገዳማት እና አድባራት ለመሳለም በቃን ።ቀላል የመሰለኝ የደብረ ዳሞ ተራራን በጭንቅ ወጣሁት ከደረሱ ብኃላ ደሞ ሌላ ዓለም የሚደንቅ ምስጢር ።

@KaleEgziabeher

​በፃድቁ ቀን ስራ አልገባም!!

ቢሮ ውስጥ አንዲት እህት የአብነ አረጋዊ ቀን ስራ አልሰራም ገዳማቸው ሄጄ ቁጭ ማለት ነው የምፈልገው አለችኝ ምነው በሰላም አልኩ እኔም ምክንያቷን ማወቅ ፈልጌ
ይገረመሀል ፍጼ በልጅነቴ በድንገት አይኔ ማየት ያቆማል ግንባሬ በጣም ማበጥ ጀመረ እናቴ ያለ እንቅልፍ ለብዙ ጊዜያት በለቅሶ ቆየች ታዲያ ባንደኝው ቀን አንድ የኔ ቢጤ በየቤቱ እየዞሩ ፍርፋሪ የሚለምኑ አባት የእናቴን ለቅሶ ዘወትር ያስተውሉ ነበርና እናቴን አይዞሽ አታልቅሽ ለእንደዚህ መዳኒት የሆነ ጸበል ይዥልሽ እመጣለው ማን ያውቃል እግዚአብሔር በፀበሉ ላይ አድሮ ሊፈውሳት ይችላል አሉ እንዳሉትም አልቀሩ በንጋታው በለሊቱ 10:00ላይ የአብነ አረጋዊ ጸበል ነው ብለው ለእናቴ ሰጧት አለችኝ ወሬውን ላፍታም እንድታቋርጠው አልፈለኩም ታምናለህ ፍጽም የመጀመሪያውን ጸበል ፊቴላይ ስታረገው አይቼው የማላውቀው ስሜት ነው የተሰማኝ ቀኑን ሙሉ በከባድ ህመም ቆየው ፊቴን በጣም ያሳክከኝ ነበር በሁለተኝ ቀን ጸበሉ ሲደረግ ከአበጠው ፊቴ ላይ መግል እና ደም ይፈስ ጀመር በሦስተኝው ቀን ፀበሉ ሲደረግልኝ ከ አይኔ ላይ ትል ይወድቅ ጀመር አለችኝ ታሪኳ ልቤን ወስዶታል ለካ አይኔን የጋረደው የአጋንንት ስራ ነው እግዚአብሔር ይመስገን በጻድቁ ጸበል እግዚአብሔር አደነኝ አለች እንባዎን መቆጣጠር እያቃታት ።እውነት ነው "የጻድቅ ሰው ጸሎት በስራዋ እጅግ ሀይል ታደርጋለች" ያዕ 5:16 የጻድቁ በረከት በሁላችን ይደር።
እኔም ጻድቁ ፈቅደውልኝ ከመልካም ሰው ጋር ዋል መልካም ታገኝለህ በሚለው መሠረት በመልካም ወንድሞች ትጋት እነዚያን በትግራይ ላይ የሚገኙ ድንቅ ገዳማት እና አድባራት ለመሳለም በቃን ።ቀላል የመሰለኝ የደብረ ዳሞ ተራራን በጭንቅ ወጣሁት ከደረሱ ብኃላ ደሞ ሌላ ዓለም የሚደንቅ ምስጢር ።

@KaleEgziabeher

ላመለጣችሁ ሰዎች ይኸው...

https://youtu.be/ys3rV6L5r_c?si=oswwLYP-OaNKn-HO

ብዙ ታተርፉበታላችሁ፣ ቀሲስ ህብረት የሺጥላ በወጣቶች ዙርያ ብዙ ያስተማሩ እጅግ ጥዑም አንደበት ያላቸው በእውነት ታላቅ መምህር ናቸው። ዘወትር ሰኞ በማህበረ ቅዱሳን ቲቪ ማታ 2 ሰአት ህይወተ ወራዙት (የወጣቶች ህይወት) በሚል ርእስ ሊያስተምሩን ነው እንከታተል ትምህርቱን። ስለ ትዳር፣ ስለ ወጣቶች ፈተና፣ ስለ ብዙ የጊዜው ፈተና... ስለ ህይወት ሊያስተምሩን ነው እንከታተል። ለሌሎችም ሼር አድርጉ አደራ።