Latest Posts from "ቃለ እግዚአብሔር " (@kaleegziabeher) on Telegram

"ቃለ እግዚአብሔር " Telegram Posts

"ቃለ እግዚአብሔር "
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።
7,919 Subscribers
652 Photos
22 Videos
Last Updated 28.02.2025 18:30

The latest content shared by "ቃለ እግዚአብሔር " on Telegram


👏👏👏👏👏👏👏ቅበላ👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
               ቅበላ   ቅበላ_
መቼም ቅበላ የሚለው ቃልን ስንሰማ ሁላችንም ጀሮ ላይ አንድ ነገር ያቃጭላል እሱም ፆም ከመግባቱ በፊት የምናደርገው ተግባር ነው።
በመሰረቱ ቅበላ ማለት በእንግድነት ለሚመጣው እንግዳ ለእንግዳው የሚመጥነውን ያህል ክብር ለመስጠት አዘጋጅቶና ተዘጋጅቶ መቀበል ነው::
ስለዚህ ለአንድ ነገር ቅበላ ስናደርግ ያንን የምንቀበለውን ነገር በሚመጥን መልኩ መሆን አለበት። ለምሳሌ አንድ መንፈሳዊ መነኩሴ ወደ ቤታችን በእንግድነት ቢመጣ ለመነኩሴው ቅበላ የምናደርግለት እሱን ሊመጥን በሚችል መልኩ ነው የፀሎት ቤት አዘጋጅተን እግሩን አጥበን ጉልበት ስመን መኝታ ክፍሉ ውስጥ ቅዱሳት ስዕላትን ወይም መፅሐፍ ቅዱስ አስቀምጠን.  .  . የመሳሰሉትን ነገሮች እንደ እኛ አቅም አዘጋጅተን ልንቀበለው እንችላለን። አልያ ደግሞ አንድ ህፃን ልጅ ወደ ጎጆአችን በእንግድነት ቢመጣ መኝታ ክፍል አዘጋጅተን የተረት መፃሕፍቶችን አሰናድተን የህፃናት ፊልም ከፍተን የህፃናት መጫወቻ አወጋጅተን ቅበላ ልናደርግለት እንችላለን።
ልክ እንደዚሁ ሁሉ ፆምንም ስንቀበል ከፆም ጋር የሚስማማ ነገር ማድረግ አለብን እንጅ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ተግባር ማድረግ ትልቅ ስህተት ነው። ፆም ሊገባ ነው ብለን ሆዳችን እስኪተረተር የምንበላ ጨንጓራችን እስኪላጥ የምንጠጣ ዝሙት የምንፈፅም በየ ጭፈራ ቤቱ የምንዞር ከሆነ ይህ የፆም ቅበላ ይባላልን? በጭራሽ አይባልም።እንደውም ይህ የሚያሳየው ፆሙን ሳንፈልግ እንደምንቀበለው ነው።
"ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይን ዋጋ ይወስዳል" ማቴ 10:41 እንዳለ ጌታችን ፆምን ስንቀበል በፆም ስም በፆም ተግባር መሆን አለበት።
እንደውም አንዳንድ የበቁ አባቶች የአብይ ፆም ሊገባ ሲል ፆሙን በፆም ይቀበሉታል።በእርግጥ ይህ ለእኛ ሊከብደን ይችላል ቢሆንም ፆሙን በፆም መቀበል ቢያቅተን እንኳን ፆሙን ከፆም ጋር በሚስማሙ መልካም ተግባራት መቀበል እንችላለን።
ፆም ከመግባቱ በፊት ንስሐ መግባት ፣ የበደሉንን ይቅር ማለት ፣ የበደልናቸውን ይቅርታ መጠየቅ ፣ የተጣላናቸውን መታረቅ ፣ መመፅወት ፣ ፆሙ የበረከት እንዲሆንልን መፀለይ ፣ መንፈሳዊ ምግባራትን መላበስ ፣ ከመጠን ያለፈ ደስታን ከራስ ማራቅና የመሳሰሉትን ከእኛ ጋር የሚስማሙትን መንፈሳዊ ተግባራት ከንስሐ አባታችን ጋር ተመካክረን ተግባራዊ በማድረግ ቅበላ ማድረግ ይኖርብናል።
በዚህ መሰረት የሚፈፀም ቅበላ ፆሙ ከመግባቱ በፊት መንፈሳችን እንዲዘጋጅ ከማድረጉም ባለፈ እግዚአብሔር ከፆሙ በፊት አስቀድሞ እንዲባርከን ያደርጋል።
ወዳጄ ሆይ የአንተ ቅበላ ከየትኛው ነው? መቼም በስካር በከርስ መሙላት በጭፈራና በዝሙት ቅዱሱን እንግዳ #ፆምን እንደማትቀበል ተስፋ አደርጋለሁ።
አበው "ከምግብ ብቻ በመከልከል እንጾማለን አትበሉ .. ከክፉ ግብር መራቅ ጾማችንን ትክክል ታደርጋለች" ይላሉ::
በዚህም የአባቶቻችን ልጆች እንባላለን አባቶቻችን የወረሷትን መንግስት በእውነት እንወርሳለን::
.
.
.
ኦ ጌታ ሆይ! ቸሩ አምላኬ ሆይ ሀጢያቴ እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝቶ በደሌ ስፍር መለኪያ ጠፍቶለት ክፉዋ ምላሴ ፤ የተበረዘው ጭንቅላቴ ፤ የደነደነው ልቤ ሳያሰለችህ ሳያስቀይምህ ቀናትን በሳምንታት ሳምንታትን በወራት ወራትን በአመታት ተክተህ ለዚህች ቀን ስላደረስከኝ በደካማ አንደበቴ አመሰግንሀለሁ።
እንደ እውነቱ ዘመኑ ዓመተ ምህረት ባይሆን ኑሮ እኔ ገና ድሮ ነበር የምቀሰፍ! ገና ድሮ ነበር የምጠፋ! ግን አምላኬ ሆይ አንተ እንደ ሰው ስላልሆንክ ለፍርድ አልቸኮልክም በፍቅር ታገስከኝ በስስት ዓይንም ተመለከትከኝ።
ኦ አምላኬ ሆይ! እኔዋ ደካማይት ልጅህ ያለፈውን ፆም በቅጡ ሳልጠቀምበት ፍቃድህን ሳልፈፅም ደካሞችን ሳልረዳ የደከሙትን ሳልጎበኝ ያዘኑትን ሳላፅናና የሰጠህኝን ቅዱስ ቀናት እንዲሁ በከንቱ አሳለፍኩ።
ጌታ ሆይ እኔ ደካማ እንደሆንኩ ታውቃለህ አንተ እኮ የልብና የኩላሊትን የምትመረምር ቅዱስ አምላክ ነህ። እናም ድካሜን ታውቃለህ ስንፍናዬን ታውቃለህ አምላኬ ሆይ ታዲያ እንደዚህ ደካማ ሰው ሁኜ ፆምህን እንዴት ልፆም እችላለሁ? እንዴት 40 የፆም ቀናት በፍቃድህ ላሳልፍ እችላለሁ?
የድንግል ልጅ አማኑኤል ሆይ አንተ ካልረዳኸኝ አንተ ካልደገፍከኝ ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ልወጣው እችላለሁ? አንተ እኮ መቅደላዊት ማርያምን ወደ ቅድስትነት ሙሴ ፀሊምን ከገዳይነት ወደ ባህታዊነት ሳኦልን ወደ ሰባኪነት ለውጠሀል። ጌታዬ ሆይ ታዲያ እኔን አንተ ካላገዝከኝ በእኔ አቅምማ እንዴት ይሆናል?
የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእናትህ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በቅዱሳን መላዕክት አማላጅነት በፃድቃን ሰማዕታት ፀሎትና ምልጃ እያመንኩና እየተማፀንኩ ከሰይጣን ፍላፃዎች ሁሉ እንድትታደገኝና ለደካማዋ ልጅህ ትደርስላት ዘንድ በሀጢያት በተዳደፌ አንደበቴ እለምንሀለሁ!
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ፆሙ የበረከትና የፍሬ እንዲሆንልን ከወዲሁ እመኛለሁ!

መንፈሳዊ ጉባኤ:
❖ ❖ ❖ ኪዳነ ምህረት (የካቲት 16) ❖ ❖ ❖
               ❖ ❖ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ❖
   ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችም እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄዘንድ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ  እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጸውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡
   ሌላው በላዔ ሰብ በአማርኛ ሰው በላ ማለት ነው፤ ትክክለኛ ስሙ ግን ስምዖን ይባላል ቅምር በሚባል አገር የሚኖር እጅግ ባለጸጋ ነበር፤ እንደ አብርሃም እንግዶችን እየተቀበለ ድሆችን እየመገበ የሚኖር ጻድቅ ነበር፤ ሰይጣን በዚህ ስራው ቀናበት ሊፈትነውም በሦስት አረጋዊ ሽማግሌዎች ሥላሴ ነን ብሎ ተገለጠለት ልክ እንደ አብርሃም፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል እንዳለ፤ እርሱም ሥላሴ መስለውት ተቀበላቸው ተንከባከባቸውም፤ ምግብ አቀረበላቸው ምግብ አንበላም የምንጠይቅህን ግን ትፈጽምልን ዘንድ ቃል ግባልን አሉት ቃል ገባላቸው እንግዲያውስ የምትወደን ከሆነ አንድያ ልጅህን ሰዋልን አሉት፤ መጀመሪያ ደነገጠ ኃላ አብርሃም ልጁን ሊሰዋ አልነበረምን እኔንም ሊፈትኑኝ ይሆናል ብሎ ለማረድ ተዘጋጀ፤ ተው የሚለው ድምጽ አልሰማም፤ አረደው አወራረደው ይዞላቸው ቀረበ፤ መጀመሪያ ቅመስልን አሉት ቀመሰው ወዲያው እነዚያ ሰዎች ተሰወሩበት እርሱም አህምሮውን ሳተ ተቅበዘበዘ ከዚያ በኃላ ምግብ አላሰኘውም የሰው ስጋ እንጂ መጀመሪያ ቤተሰቦቹን በላ ከዚያም ጓደኞቹን ጦርና የውኃ መንቀል ይዞ ከቤቱ ወጣ ያገኘውን ሰው እየገደለ ይበላል የበላቸው ሰው ቁጥር 78 ደረሰ፤ በመንገድ ተቀምጦ የሚለምን በደዌ የተመታ አንድ ደሃ አገኘ ሊበላው ወደ እርሱ ተጠጋ ግን ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፤ ደሃውም “ስለ እግዚአብሔር ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ” አለው “ዝም በል ደሃ” ብሎት አለፈ፤ “አረ በውኃ ጥም ልሞት ነው ስለ ጻድቃን ስለ ቅዱሳን” አለው አሁንም ዝም ብሎት ሄደ ለሦስተኛ ጊዜ “ስለ አዛኝቷ ስለ ድንግል ማርያም” አለው፤ ሰውነቱን አንዳች ነገር ወረረው “አሁን የጠራከውን ስም እስኪ ድገመው ስለ ማን አልከኝ” አለው፤ ስለ አዛኝቷ ስለ እመቤቴ ማርያም አለው፤ ይህቺስ ደግ እንደሆነች በምልጃዋም ከሲኦል እንደምታወጣ ህጻን እያለው እናትና አባቴ ይነግሩኝ ነበር፤ በል እንካ አለው እጁን ዘረጋለት ጥርኝ ውኃ ጠብ አደረገለት ወደ ጉሮሮው አልወረደም የተሰነጠቀ እጁ ውስጥ ገባ እንጂ፤ በለዔ ሰብ ከዚያች ደቂቃ በኃላ አዕምሮው ተመለሰለት እንዲህም አለ “በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቼ ስለ ኃጢያቴ አለቅሳለሁ ስጋዬ ከአጥንቴ እስኪጣበቅ እጾማለሁ ወዮሊኝ ወዮታም አለብኝ አለ፤ ወደ ዋሻ ገባ ምግብ ሳይበላ ውኃም ሳይጠጣ 21 ቀን ኖሮ በርሃብ ሞተ ይላል ተአምረ ማርያም። ጨለማ የለበሱ ሰይጣናት እያስፈራሩ እያስደነገጡ ነፍሱን ወደ ሲኦል ሊወስዷት መጡ፤ እመቤታችን ፈጥና በመካከላቸው ተገኘች፤ ልጄ ወዳጄ ይህችን ነፍስ ማርሊኝ አለችው እናቴ ሆይ 78 ነፍሳትን የበላ እንዴት ይማራል አላት፤ የካቲት 16 ቀን በጎልጎታ የገባህልኝ ቃል ኪዳን አስብ ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገን እምርልሻለው ብለኸኝ የለምን አለችው፤ እርሱም እስኪ ይህቺን ነፍስ በሚዛን አስቀምጧት አለ ቢያስቀምጧት ጥርኝ ውኃው መዝኖ ተገኘ፤ ስላንቺ ስል ምሬታለው ሰባት ቀን ሲኦልን አስጎብኝታችሁ ወደ ገነት አግቧት አላቸው። ቦታሽ እዚህ ነበር እያሉ ሲኦልን አስጎብኝተው ወደ ገነት አገቧት። ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
በዕለቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚቀርበውን የምስጋና ቃል እንደሚከተለው አቅርበናል መልካም በዓል፡፡
           ❖ ❖ ❖ ዋዜማ ❖ ❖ ❖
ሃሌ ሉያ (፬) ርግብየ ይቤላ በእንተ የዋሃታ፤
በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ፤
እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
          ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖
እንዘ ዓመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
        እግዚአብሔር ነግሠ
        እንተ ክርስቶስ በግዕት እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ብሔር፤
        በቤተልሔም አስተብረከት ዕጓለ አንበሳ ግሩመ ወለደት፡፡
           ❖ ❖ ❖ ይትባረክ ❖ ❖ ❖
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤
ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፡፡
           ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖
ሃሌ ሉያ (3) ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋትሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤
የሐንፁ አሕዛብ አረፋተኪ በዕንቊ ክቡር፤
ወመሠረትኪ በወርቅ ንጹሕ ይሰግዱ ለኪ ውስተ ገጸ ምድር፤
በእንተ ዕበየ ክብርኪ አምላከ ፳ኤል ውእቱ ረዳኢኪ
ዘአድኀነኪ እምእደ ጸላዕትኪ፤
ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ፡፡
         ❖ ❖ ❖ መልክአ ሥላሴ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፡
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፡
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፡
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል
          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤
እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፤
ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤
ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤
ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ፤
ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
         ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ;
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪየኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኀኒት ለነፍስ ወሥጋ፤
እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ፤
ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዩ ፍኖተ፤
ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ መድኀኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ፡፡

❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤
አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤
አመ ይሰደድ እምገነት፡፡
          ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት በዓል ❖ ❖

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

''... ወደ ባሕር ጣሉኝ....''
የፈጣሪ ዓለማት መጋቢ ዓለማት የእግዚአብሔር ልጆች ሁላችሁ ኦርቶዶክሳውያን በአላችሁበት ሠላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ
ወገኖች  ከአባቶች እንደተማርን የችግሮቻችን ሁሉ መክፈቻው ቁልፍ እጃችን ላይ ነው እና እንበርታ ።
ተወዳጆች ሆይ ዛሬ ሀገር እና ቤተክርስቲያን ከገቡበት የመከራ ማጥ እንዲወጡ ሁላችን ራሳችን ልናይ ይገባል።
ወዳጆቼ መጪውን የነነዌ ፆም  እራሳችንን ልንፈትሽ ነብዩ ዮናስ  እኔን ወደ ብሀሩ ጣሉኝ እንዳለ።
ቤተክርስቲያን እና ሀገር አሁን ላሉበት ችግር መንስኤው እኔ ነኝ እኔ ንስሀ ብገባ ፣ የይቅርታ እና የፍቅር ሠው ብሆን የዓለም ማዕበል ጸጥ ይላል ምድሪቱም ታርፋለች  በሚል ታላቅ እምነት እራሳችንን በአምላክ ደጅ እንጣል  ነብዩ ዮናስ
“... ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው። ዮናስ 1፥12 እንዳለ የኢትዮጵያ ውጫዊ እና ወስጣዊ ችግር እንዲፈታ የችግሩ ባለቤ እኔ ነኝ  በማለት እራሳችን በካህኑ እግር ስር በመጣል ፆመ  ነነዌን በአግባብ በመጠቀም ለሀገራችን እና ለቤተ ክርስቲያናችን እረፍት እስኪሰጥልን ልንተጋ ይገባል እላለሁ ። እናንተስ ምን ትላላችሁ ?
አምላከ ዮናስ በጎውን ሁሉ ያሰማን።
አምላከ ነነዌ ስለ ሕጻናቱ ብሎ ሀገራችንን እና ቤተክርስቲያናችንን ያሳርፍልን።
ገ/ራጉኤል
አዲስ አበባ
30/5/2017ዓ.ም

https://youtu.be/JR-Oj0cVUHA?si=CQau8SpnXSk5tkg5

"#እባክህን_ከእሳቱ_ላይ_አትውረድ"
  
አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው።

ወዳጄ ሆይ ሕይወት ቀዝቅዛብሃለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሃልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ኃጢአቶች (ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወርሮ፣ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡

ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፥49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፥13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ንሳ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡

ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ (በመንፈሳዊ ተግባራት እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት (ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡

ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ፡፡ እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነት ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡

ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ፡፡

በኃጢአት "እጅ እጅ '' ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን!

(ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework

ጥር12
እንኳን  ቃና ዘገሊላ  ታላቅ ክብር በዓል በሰላም አደርሳችሁ አደርሰን አሜን

#ቃና ዘገሊላ ምንድነው?

ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት(ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡

በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጃ_ ወደ ወዳጃ_ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡ እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን አቆይተሃል›› አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል ፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23) በመሆኑም ጌታ አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡ ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡፡ ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡ ይህ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡፡
አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር  በእናቱ በቅድስት ድንግል አማላጅነት ወኃውን ወደ ወይን እንደ ቀየር ዛሬም የተመሰቃለብን  ህይወታችን  በእናቱ አማላጅነት  በመልካም ጎዳና ይቀርልን  ።
ከወላዲት አምላክ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን

https://youtu.be/lTxz6FfpduY?si=JAxRgAC2LdOKNlwt

[እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ጥምቀት ማለት ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውሃ ውስጥ ገብቶ መውጣት” ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ማለት አንድ ሰው አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በተጸለየበትና በተባረከ ውሃ ሦስት ጊዜ ጠልቆ ዳግመኛ ከሥላሴ ተወልዶ የቤተ ክርስቲያን አባል የእግዚአብሔር ሕዝብ ወገን የሚሆንበት ቅዱስ ምስጢር ነው (ማቴ 28፡19-20)፡፡

ምስጢረ ጥምቀት ምስጢር መባሉ ካህኑ ለጥምቀት የተመደበውን ጸሎት አድርሰው ለማጥመቅ የተዘጋጀውን ውሃ ሲባርኩት ውሃው ተለውጦ በዕለተ ዐርብ በመስቀል ላይ ከጌታ ጎን የፈሰሰውን ውሃ ስለሚሆንና ለተጠማቂው ሰው በሚፈጸምለት የሚታይ ሥርዐት የማይታይ የልጅነት ጸጋ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሚሰጥ ነው (ዮሐ 3፡5)፡፡

ምስጢረ ጥምቀትን የመሰረተልን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ሲመሰርትም በማዘዝ ብቻ ሳይሆን በሥራ በማሳየት ጭምር ነው (ማቴ 3፡17፤ ማር 1፡9፤ ሉቃ 3፡21፤ ዮሐ 1፡31)፡፡

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እከብር አይል ክቡር የባሕርይ አምላክ ሆኖ ሳለ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ (በፍጡሩ) በዮሐንስ የተጠመቀበት ምክንያት፦
1) አንድነቱን ሦስትነቱን ለመግለጽ
2) የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ
3) በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመቀደስ
4)ለጥምቀታችን ኀይልን ለመስጠት
5) ለአብነት ርሱ ተጠምቆ እናንተም ተጠመቁ ብሎ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በ30 ዘመኑ ጥር 11 ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት፤ ማግሰኞ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ እንደሚጠመቅና የዮርዳኖስ ወንዝ ጌታን ስታይ እንደምትሸሽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 113፡3-5 “ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ፤ ተራሮች እንደ ኮርማዎች፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ፤ አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ ምን ሆናችኋል?” በማለት ከ1000 ዓመት አስቀድሞ ትንቢት የተናገረ ሲሆን፤ ብዙ ምሳሌም አለው፨

ምስጢሩ ግን ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ መከራ አጸናባቸው፤ ከዚያም ለኔ የባርነት ስም ብትሰጡኝ መከራውን አቀልላችሁ ነበር አላቸው፤ እነሱም “አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ” (አዳም የዲያብሎስ ወንድ አገልጋይ ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው አሉ፤ ርሱም ይህንን በዕብነ ሩካም አድርጎ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል ጥሎት ነበርና፤ ጌታም በዮርኖስ ጥልቅ ወንዝ የተጣለውን የሰው ልጆች ሁሉ የዕዳ ደብዳቤ በጥምቀቱ ለማጥፋት ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡

ዮሐንስ ወደ ጌታችን መምጣት ሲገባው ጌታችን ወደ ዮሐንስ የሄደበት ምክንያት ትሕትናን ለማስተማር ሲሆን ሁለተኛው ለአብነት ለምሳሌ ነው፤ ይኸውም ዮሐንስ ሄዶ አጥምቆት ቢሆን ዛሬ ባለሥልጣናቱ ካህናትን ቤታችን ድረስ መጥታችሁ አጥምቁን ይሏቸው ነበርና ሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያን ተጠመቁ ለማለት ሄዷል።

ዮሐንስ ግን ወደርሱ በትሕትና የመጣው አምላኩ ክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ሲል ጌታችንም “ጽድቅን ልንፈጽም” ይገባናል ብሎ ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽም እንደመጣ ሲነግረው ዮሐንስ እሺ አለ።

ከዚያም ተያይዘው ወደ ዮርዳኖስ ሲወርዱ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት የዮርዳኖስ ወንዝ 40 ክንድ ወደ ኋላዋ ሸሽታለች በዚህም ዳዊት በመዝ 77፡16 ላይ “አቤቱ፥ ውኆች አዩህ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውኆችም ጮኹ” ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ።

ጌታችንም ተጠምቆ ከውሃው ከወጣ በኋላ አብ በሰማይ ኹኖ “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ” (በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው) ብሎ ሲመሰክር፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስም በጽንፈ ዮርዳኖስ ቁሞ ታየ፡፡

ይኸውም በምስጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደምንረዳው ከሰማይ ኾኖ የመሰከረው ክርስቶስ በቃልነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ያሉበት (ሕልው የኾኑበት) አብ ነው፤ ወርዶ በወልድ ራስ የተቀመጠው አብ በልቡናነት ክርስቶስ በቃልነት ሕልው የኾኑበት መንፈስ ቅዱስ ነው፤ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ የታየው አብ በልቡናነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ሕልው የኾኑበት አካላዊ ቃል ክርስቶስ ነው፤ እንዲኽ አድርገው የአካል ሦስትነታቸውን የፈቃድ አንድነታቸውን ለማስረዳት አብ በደመና ኾኖ መሰከረ፤ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ታየ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ ታየ።

በዚኽም የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሚገባ ሲታወቅ በተጨማሪም “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ እግዚአብሔር አብ በመመስከሩ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው በኋለኛው ዘመን ከእመቤታችን ያለ አባት በኅቱም ድንግልና የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ብቻ መኾኑ በሚገባ ተረጋግጧል፤ ዕለቱም በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋንያ ሲባል በግእዝ አስተርእዮ በዐማርኛም የመታየት የመገለጥ ጊዜ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን ስለ ነገረ ጥምቀት የሰማችው ከሌላው ዓለም አስቀድማ ጌታችን ባረገ በጥቂት ወራት (በ34 ዓ.ም) ነው (የሐዋ 8፥26-39)፤ ይህም በዐል ከዘጠኙ ዐበይት በዐላት አንደኛው ሲሆን ጌታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ስላመራ ይህንን ለማሰብ ታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ያመራሉ።

ሊቀ ትጉኃን ኃይለ ጊዮርጊስ በጻፉት የነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ ላይ በስፋት እንደጻፉት በኢትዮጵያ በዚህ መልኩ መከበር የተጀመረው ከ515-529 ዓ.ም ለ14 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በአጼ ገብረ መስቀል ዘመን ሲሆን በጊዜው ቅዱስ ያሬድ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ ከዝማሬው በመነሣት ታቦታቱ ጥር 11 ጠዋት ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አምርተው አመሻሹ ላይ ይመለሱ ነበር፡፡

ከዚያም ከ1157-1197 ዓ.ም ድረስ ለ40 ዓመት ኢትዮጵያን በመራው በታላቱ ጻድቅ ንጉሥ በላሊበላ ዘመን በአንድ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስትያናት ታቦታቱ ባንድ ላይ እንዲያከብሩ ንጉሥ ላሊበላ ታላቅ መንፈሳዊ ዐዋጅን አሳውጆ በአንድ አካባቢ፣ ወረዳ፣ ያሉ በአንድ ላይ ማክበር ጀመሩ፤ በርሱ ዘመን የነበሩት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በጎንደር፣ በሸዋ፣ በአንኮበር፣ በመርጡለ ማርያም እየሄዱ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡

በመቀጠልም ከ1245-1268 ዓ.ም ለ23 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በዐጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሳሳቢነት ታቦታቱ በባሕረ ጥምቀት ሲውሉ ምእመናን በታላቅ ድምቀት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንዲውሉ መንፈሳዊ ዐዋጅ አሳወጁ፡፡

በመቀጠል ከ1426-1460 ዓ.ም ለ34 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በታላቁ ንጉሥ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥትም ንጉሡ ከሊቃውንት ጋር በመወያየት የበዐሉን ታሪክ ተከትሎ ታቦታቱ ጥር 10 ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት እንዲወርዱና ጥር 11 እንዲመለሱ ተወሰነ።

+ከአእላፋት ማግስት+

''ይሄን ስእል እያመለክሽ ነው ሳታገቢ የቆየሽው በጌታ በእየሱስ ስም መንፈስሽን ወጋሁት''

እናቴ ናት በጠዋት እንዲህ የምትለው። አሁንማ ገና እየደረሰ በመሆኑ፥ አእላፋት ዝማሬ ብቻ ሆኗል ወሬው እሱ ይረብሻታል።

ስለ እናቴ ትንሽ ላውራቹህ...

ኤልሳ ትባላለች። ሲበዛ ተጫዋች፥ ረጅም፥ በጣም ቀይ፥ ስትስቅ ጥርሷ የሚያምር፥ በዛ ላይ ዲምፕል ያላት ውብ ናት። አባቴ ደግሞ ሱራፌል ይባላል፤ ዲያቆን ነበር። በእርግጥ እኔ 16 አመቴ እያለ ነው የሞተው። ሰዎች ስለ እርሱ አውርተው አይጠግቡም። ሰው ቀና ብሎ የማያይ፥ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፥ ጸሎተኛ ነበር ፤ መምህሩ ሲቀሩ እርሱ ነበር ጉባኤ ዘርግቶ የሚያስተምረው። ሁሉም ነበር የሚወደው። እኔን ራሱ ውዳሴ ማርያም፥ ዳዊት፥ ቅዳሴ፥ ሰዓታት አስተምሮብኛል። '

'ሰበኔ... ሴት ሆንሽብኝ እንጂ አንቺን ዲያቆን ነበር የማደርግሽ'' የሁል ጊዜ ንግግሩ ነበር።

እናቴ አባቴ በእግዚአብሔር ላይ ያለው መተማመን ይገርማታል። እኔ ልክ 15 አመት ሲሆነኝ አባቴ በጠና ታመመ። የሳንባ ካንሰር ያዘው። ከቤት መውጣት ከበደው፤ ቀኑን ሙሉ የሚያሳልፈው አልጋ ላይ መጽሐፈ መነኮሳትን እያነበበ ነበር። ትንሽ ህመሙ ባስ ሲልበት ደግሞ መጽሐፉን ደረቱ ላይ አድርጎ ለሰአታት መተንፈስ የከብደው ነበር። ከእርሱ ህመም በኋላ ቤታችን ውስጥ ሳቅ የሚባል ጠፋ። እናቴ ቀይ ፊቷን ማድያት ወረሰው።

.......የሆነ ማክሰኞ ቀን ጠዋት ላይ ''ኡኡኡኡኡኡኡኡ'' የሚል ጩኸት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ። እናቴ ነበረች። ብርድ ልብሱን ከራሴ ላይ በስርአት ሳላወልቅ ሮጥኩኝ። ኤልሲ አባቴን አቅፋ ፥-

"ጌታዬ ጉድ አታድረገኝ ባክህ ጉድ አታድርገኝ"

"እማ አባቴ ምን ሆነ?" ......እምባዬ ከየት እንደመጣ አላውቅም። ፊቴ ርሷል...

"የልጀነት ፍቅሬ ኧረ ተው" ትላለች።

"እማ አባቴ ምን ሆኗል?!"

"ጉድ አረከኝ! ብቻዬን ለማን ጥለከኝ! ኧረ ያላንተ አይሆንልኝም! ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ"

ጩኸታችንን የሰሙ ጎረቤቶቻችን ቤታችንን ሞሉት። በአንዴ ግማሹ ቲቪ ይሸፍናል፥ ግማሹ ስለ ድንኳን ያወራል......ራሴን ሳትኩ፤ ስነቃ ቀብር ሊሄዱ ህዝብ መጥቷል። ቤቱ ውጪው ግጥም ብሏል። ያ ሁሉ ህዝብ አንድ አባቴን አልሆን አለኝ.....

አባቴ ካረፈ ጊዜ ጀምሮ ቤታችን የማይቀሩ የማይቀሩ 3 ሰዎች ነበሩ። እነዚህ የእናቴ የስራ ባልደረቦች ታዲያ በመጡ ቁጥር ለእናቴ እንፀልይልሽ ብለዋት ነው የሚሄዱት፤ የሆነ ቀን ላይ ከታናናሾቼ ጋር ጸሎት እያደረግን "ከዛሬ ጀምሮ የዚህ ቤት ሃይማኖት ተቀይሯል!" አለችን።

"ወደምን?" አልን

"ጌታን ተቀብለናል! ነገ ትጠመቃላችሁ። አቁሙ አሁን!"

"እንዴ ኤልሲ! እኛ እኮ ልጅ እያለን ተጠምቀናል"

"አንቺ ልጅ! ተናገርኩ በቃ!"

"አልቀይርም! አባቴ ያስተማረኝ ያወረሰኝ ነው፤ አልቀይርም!" አልኩ።

ኤልሲም መልሳ "ነው? ከሆነ ከቤቴ ውጪ! እናንተም እንደዛ ነው?

ታናሽ እህቴም አዎ አለች።

"ውጡ! ችግር እና ረሃብ ሲፈራረቅባችሁ ትመጡ የለ!" አለችን በቁጣ።

ስልኬን አንስቼ ለአያቴ ደወልኩ። አያቴ ብቻዋን የምትኖር፥ በጣም ትልቅ ጊቢ ያላት፥ እሱ ላይ ወደ 20 ምናምን ቤት ሰርታ የምታከራይ ሴት ናት። ስደውል ኑ ኧረ ኑ አለች

......... እናቴ ሃይማኖቷን ቀየረች። ሁሉንም እኛ ክፍል የነበረ ስእለ አድኅኖ አውጥታ አቃጠለች። የአባቴን ግን ከበዳት። የእርሱን ዳዊት፥ የጸሎት መጻሕፍት፥ ሁሉን ነገሩን በአንድ ላይ አድርጋ አንድ ክፍል ውስጥ ቆለፈችበት። እኛም አያታችን ጋር መኖር ቀጠልን።

---------------------------------------------------

እናቴን ሃይማኖቷን ያስቀየሯት ሰዎች Theology እንድትማር አደረጉና ፓስተር ሆነች ።

ዛሬ...

"እሺ ባክሽ... አእላፋት ምናምን እያላችሁ ነው ደግሞ በነጭ ልብስ ጣኦት ልታመልኩ"

"ተይ እንጂ እማዬ... የማይሆን አትናገሪ። ለምን ዛሬ አብረን አንሄድም?"

"ማን? እኔ? ሆሆሆሆሆሆሆሆ... ሥራ አልፈታሁም"

"ምን ችግር አለው? ከደበረሽ ቶሎ እንወጣለን።"

"ቆይይይይይ እሄዳለው። የምሄደው ግን እንዴት ልክ እንዳልሆናችሁ ላሳይሽ ነው!"

ሁላችንም ለባብሰን ወጣን። በጊዜ ነበር የደረስነው፤ ቦሌ መድኃኔዓለም ሞልቷል። እንደምንም ብለን ፊት ተጠጋን። ዲያቆኑ "እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ" ይላል። ቁርጥ የአባቴን ድምፅ! ኤልሲ ደነገጠች። አባቴን ያየችው መስሏት ተንጠራርታ ፈለገችው፤ የለም። የሚፀየውን ጸሎት በግእዝም በአማርኛም ስታየው ቆየች። እምባዋ ይፈስ ጀመር። ጸሎቱ ተጠናቆ ነጫጭ የለበሱ ዘማሪያን መድረኩን ሞሉት። መዝሙር ቀጠለ። ቸሩ ሆይ የሚለው መዝሙር ዘማሪዎቹ መዘመር ጀመሩ። የአባቴ የሚወደው መዝሙር ነበር። የሲቃ ድምጽ አውጥታ አለቀሰች። አሳዘነችኝ ደስም አለኝ። መዝሙሩ አለቀ። በአባቶች ብራኬ ተጠናቀቀ። ኤልሲ ሙሉ ሰአት እያለቀሰች ነበር ።

"ኤልሲዬ በቃ አንቺ ሂጂ፥ እኛ እናስቀድሳለን።"

"ልምጣ?"

"የምርሽን ነው?"

"አዎ ልምጣ"

"ነይ" ድንጋጤዬ ያስታውቃል።

ማህሌቱ አልቆ፥ ቅዳሴው አልቆ፥ ቤት ገባን። እኛ ቤት ከመጣሁ 10 አመት አልፎኝ ነበር። ያው ነው፥ ምንም አልተቀየረም። እናቴ ሮጣ ጸሎት ቤት ገባች። ሁሉ ነገሩ አባቴን አባቴን ይላል። ትልቅ የእመቤታችን ምስለ ስዕል ፊት ወድቃ አለቀሰች።

"ሰበኔ አሁን ገባኝ! ልቤ ተሰብሬ ሲያገኙኝ ዓለም ገደል ስትሆንብኝ አግኝተውኝ ነው! ልጆቼ ይቅር በሉኝ! በጎደለኝ በኩል ሲቆሙ ወዳጆች መሰሉኝ ......"

ተቃቅፈን ተላቀስን። ምን ተረዳሁ መሰላችሁ? እግዚአብሔር ስራው Mysterious ነው። እንዲህ ነው ብለን Define የማይደረግ። ዛሬ ላይ ቤተሰቤ ሙሉ ሆኗል፤ እናቴም ወደ ክርስትና ለመመለስ ትምህርት ለመማር ከመምህሬ ጋር አገናኝቻለሁ። ከ 10 ዓመት ከብዙ ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ። እጆቼን ከፍ አድርጌ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ...

"የእኔን እምባ ያቆምክ እግዚአብሔር... እምባቸውን ለሚያወጡ ድረስ" ብዬ። "ሰላም ለናፈቁ ሁሉ ሰላም ስጥ። አባቴ የደከሙ ልቦችን አሳርፍ፥ ፈገግታን የናፈቁን ሁሉ ሳቅ አጥግብ፥ ለደስታ የተግደረደሩትን ሁሉ አላምዳቸው ...ባለቀሱበት ቦታ እንባቸውን አብስ። ሁሉን ቻይ ሆይ፥ የመዳናቸውን ቀን አታርቅ።"

ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው (Instagram: - @yohannes_getachew1
ጥር 1 / 2017
አዲስ አበባ

ቀዳማዊ ልደቱ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው የማይመረመር ስለሆነ ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለፅ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ እንደ ተወለደ ድኅረ ዓለምም ከእመቤታችን /እንበለ ዘርዓ ብዕሲ/ ያለ አባት ተወለደ፡፡ እሱም እመቤታችን ያለ አባት የወለደችው ፤ እግዚአብሔርም ያለ እናት የወለደው ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰባቱ መስተጻርራን /ተቃራኒ ነገሮች አንድ ሆነዋል ሕዝብና አሕዛብ ፤ በጠብና በክርክር ይፈላለጉ የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ በጌታችን ልደት ታርቀዋል
፡፡ ይኸውም ሊታወቅ ከዚህ አስቀድሞ ቤተ መቅደሱን ለማፍረስ ንዋየ ቅድሳቱን ለመዝረፍ ሕዝቡን ለመማረክ ምታ ነገሪት ብለው ይመጡ የነበሩ የሩቅ ምስራቅ /የፋርስ የባቢሎን ሰዎች በጌታችን ልደት ምክንያት ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ "አይቴ ሃሎ ዘተወልደ ንጉሠ አይሁድ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው" (ማቴ.2፥4) እያሉ መጥተው ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤ ገብረውለታል፡፡

  ነፍስና ሥጋ፡- በሲዖልና በመቃብር ተለያይተው የነበሩ ነፍስና ሥጋ ከእመቤታችን ከነፍሷ ነፍስ ከሥጋዋ ሥጋ ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው በሆነ ጊዜ ነፍስና ሥጋን አስታርቋል፡፡
ሰውና እግዚአብሔር፡- አባታችን አዳም አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስ በልቶ የሰውና የእግዚአብሔር የፍቅር ግንኙነት ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ተቋርጦ ነበርና ጌታችን የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ በተወለደ ጊዜ እርቀ ሰላም ተገኝቷል፡፡

ሰውና መላእክት፡- አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ጋር በተጣላ ጊዜ ቅዱሳን መላእክትም ስለተጣሉት በምትገለባበጥ ሰይፈ እሳት አስፈራርተው ከገነት ካስወጡት በኋላ ወደ ገነትም እንዳይገባ ገነትን ይጠብቁ ነበር፡፡ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አንድ ሆነው ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ይኸውም ዮም አሐደ መርኤተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብህዎ ለክርስቶስ እንዲል፡፡ ሰውና መላእክት ክርስቶስን ለማመስገን አንድ ሆኑ እንዳለ ሊቁ፡፡

  ቤተ ክርስቲያን ፤ ጌታችን የተወለደባት እና ሰባቱ መስተጻርራን አንድ የሆኑባት፤ ሰውና መላእክት የዘመሩባት የብርሃን ጎርፍ የጎረፈባት እንስሳት እስትንፋሳቸውን የገበሩባት ቤተልሔም በቤተ ክርስቲያን ትመሰላለች፡፡

  ቤተልሔም፡- ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ ፤ ሰውና እግዚአብሔር ፤ ነፍስና ሥጋ ፤ ሰውና መላእክት አንድ ሆነው በቤተልሔም እንደዘመሩ ዛሬም የፍቅር ተምሳሌትና የአማኞች ሁሉ እናት በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘር፣ በጎሣ፣ በጥቅም፣ በሥልጣን ሳንከፋፈል አንዲት ቤተ ክርስቲያንን በፍቅር እንድናገለግል በቤተልሔም የተደረገው የልደቱ ምሥጢር ይህን ያስተምረናል፡፡
ክርስቲያኖች የጌታን መወለድ የምናስበው በዚህ መንፈስ ነው፡፡
መልካም የልደት በዓል ይሁንልን አሜን !!!
      ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖❖ ❖ ❖
  💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫   
        ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖❖ ❖ ❖
❖ ❖ ❖ የልደት በዓል ማኅሌት  ❖ ❖ ❖
           ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላእክት ፤
ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ፡፡
ትርጉም፦ ቅድስት ድንግል ከሆነች ማርያም የተወለደውን እረኞች አዩት መላእክትም አመሰገኑት፤ እነሆ ዛሬ ሰማያዊው በበረት ተኛ፡፡
          ❖ ❖ ❖ ንግሥ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለልደትከ ኦ አማኑኤል፤
ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ብሉየ መዋዕል፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአብ ቃል፤
እፎ እፎ አግመረተከ ድንግል፤
ወእፎ እንዘ አምላክ ሰከብከ በጎል፡፡
ትርጉም፦ በዘመናት የሸመገልክ መጀመርያና መጨረሻ የሆንክ አማኑኤል ሆይ ለልደት ሰላም እላለሁ የአብ ቃል የሆንክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ድንግል እንዴት ተሸከመችህ? አምላክስ ስትሆን እንዴት በበረት ተኛህ?
          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ፤
እፎ ተሴሰየ ሐሊብ ከመ ሕፃናት፡፡
ትርጉም፦ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ፤ በድንግል ማኅፀንም አደረ፤ እንደ ሕፃናት ወተትን እንዴት ተመገበ?
        ❖ ❖ ❖ መልክአ ኢየሱስ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለአፅፋረ እዴከ ዘሕበሪሆን ጸዓዳ...
ትርጉም፦ቀለማቸው ነጭ ለሆኑት የእጆችህ ጥፍሮች ሰላም እላለሁ.....
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል ፤
አምኃሆሙ አምፅኡ መድምመ ፤
ረኪቦሙ ሕፃነ ዘተወልደ ለነ፡፡
ትርጉም፦ሰብአ ሰገል የተወለደልንን ሕፃን አገኙ በደስታም ዘለሉ ስጦታቸውንም አመጡ፡፡
        ❖ ❖ ❖ ምስባክ ❖ ❖ ❖
ዲያቆኑ በቅኔ ማኅሌቱ  "መዝ 71:10" ይሰብካል።
“ነገሥተ ተርሴስ ወደሴያት አምኃ ያበውዑ ፤ ነገስተ ሳባ ወዓረብ ጋዳ ያመፅኡ ፤
ወይሰግዱ ሎቱ ኩሎሙ ነገሥተ ምድር ፡፡ ትርጉም፦ የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ! ነገሥታት ኹሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ኹሉ ይገዙለታል፡፡
        ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖
መዘምራን (መሪጌቶች) መሪና ተመሪ ኾነው የሚዘምሩት ሲኾን በመቀጠልም ኹሉም በኅብረት እየደጋገመ የሚዘምረው ነው! እንዲህ ይላል.....
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ ፤
እም ቅድስት ድንግል ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤
ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤
አማን መንክር ስብሐተ ልደቱ፡፡
ትርጉም፦ እነሆ ዛሬ በክርስቶስ ልደት ምክንያት ደስታ ኾነ ከቅድስት ድንግል የተወለደው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለእርሱ ሰብአ ሰገል ሰገዱለት!
በእውነት የልደቱ ምስጋና ድንቅ ነው፡፡
          ❖ ❖ ❖ እስመ ለዓለም ❖ ❖ ❖
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም ዘይሁዳ፤
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ፤
ሰብአ ሰገል አምፅኡ ሎቱ ጋዳ፤
ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ ፡፡
ትርጉም፦ኢየሱስ በይሁዳ ቤተልሔም ተወለደ፤ የጢሮስ ሴቶች ልጆችም በዚያ ይሰግዱለታል፤ ሰብአ ሰገል እጅ መንሻን አመጡለት፤ የይሁዳ ሴቶች ልጆችም ደስ ይላቸዋል፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዑደት ❖ ❖ ❖
“ኹላችንም በልደቱን ብርሃን በማሰብና ጧፍ በማብራት "ሥዕለ አድኅኖ" ይዘው ከሚዞሩት ካህናት በስተኋላ ተሰልፈን እንዲኽ ይኼንን ዝማሬ እናቀርባለን!
“አማን በአማን አማን በአማን፤ መንክር ስብሐተ ልደቱ ፡፡
ትርጉም፦እውነት በእውነት እውነት በእውነት፤ የልደቱ ምስጋና ድንቅ ነው፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዕዝል ❖ ❖ ❖
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ፤
ዮም ተወልደ እግዚእ ወመድኅን ቤዛ ኩሉ ዓለም፡፡
ትርጉም፦ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ ፤ በድንግል ማኅፀን አደረ፤ የዓለም ኹሉ ቤዛ የኾነው ጌታና አዳኝ ዛሬ ተወለደ፡፡
        ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖
ተስሃልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤
ንሰብክ ወልደ እም ዘርዓ ዳዊት ዘመፅአ ወተወልደ በስጋ፤
ሰብእ እንዘ ኢየአርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ ስጋ ኮነ ወተወልደ፡፡
ትርጉም፦ ጌታ ሆይ ምድርህን ይቅር አልክ ሃሌ ሉያ ከዳዊት ዘር የመጣውንና በሥጋ የተወለደውን ወልድን እንሰብካለን ከምስጋናው ዙፋን የማይራቆት ሰው ነው! በድንግል ማኅፀን አደረ ሥጋ ኾኖም ተወለደ፡፡
የሚቀደሰው ቅዳሴ   ☞    "ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልእ"
የቅዳሴው ምስባክ   ☞ መዝ 71:15 ፤
የሚነበበው ወንጌል  ☞ ሉቃ2:1-21
    💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹