https://youtu.be/PGbzQh_H0PE?si=FCXLk96NNVE_-kWE
"ቃለ እግዚአብሔር " Telegram Posts

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16
"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ
በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

7,919 Subscribers
652 Photos
22 Videos
Last Updated 28.02.2025 18:30
Similar Channels

10,460 Subscribers

6,535 Subscribers

4,512 Subscribers
The latest content shared by "ቃለ እግዚአብሔር " on Telegram
የፆመ ነቢያት(የገና ፆም) ሳምንታት ልክ እንደ አቢይ ፆም ሳምንታት ስያሜ እንዳላቸው ያውቃሉ? ከታች በ3 ደቂቃ ስሜያቸውን ኆኅተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አዘጋጅቶልናል። በዛው ቻናሉን subscribe እያረጋችሁ ብዙ ትማሩበታላችሁ።
https://youtu.be/PGbzQh_H0PE?si=FCXLk96NNVE_-kWE
https://youtu.be/PGbzQh_H0PE?si=FCXLk96NNVE_-kWE
ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡
ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡
አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡
የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቀፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡
እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡
በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳ እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡
ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡
የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡
ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’
ብዬ ላመስግነው፡፡
ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡ አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡
የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ”
Deacon Henok Haile
#የብርሃን_እናት - ገፅ 305-308
@KaleEgziabeher

እንኳን ለገና ፆም በሰላም አደረሳችሁ። (ሁሌም በተመሳሳይ ቀን በህዳር 15 ነው የሚገባው።) የምግብ ለውጥ ብቻ እንዳይሆንብን ከፀሎት፣ ከስግደት፣ ከምፅዋት.. ከሌሎችም መንፈሳዊ ተግባራት ጋር ፆሙን አጅብን በረከት ለመቀበል እንትጋ። መልካም ፆም።
መሥዋዕት ተብለው የፍየል፣ የበግ፣ የርግብ ወዘተ መሥዋዕት በማቅረብ ይፈጸም የነበረ ሲሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጹም፣ ጸልይ፣ ስገድ፣ መጽውት የሚለው መጠን እንደካህኑ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ቀኖና በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አስተምህሮ መሠረት ሰው ከስሕተቱ የሚታረምበት መንፈሳዊ ተግሣጽ ሲሆን ይህ ግን ምድራውያን ነገሥታት ለወንጀለኞች እንደሚሰጡት ቅጣት የሚታይ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ይቅር የሚለው ኃጢአተኛነቱን አምኖ በማዘኑ፣ በመቆጨቱና ከጥፋቱ በመመለሱ እንጂ ስለበደሉ በሚከፍለው ካሳ ብዛት አይደለምና፡፡ ለዚህም ቀደም ብለን ባየነው የጠፋው ልጅ ታሪክ ላይ ልጁ ለመናዘዝ ወደ አባቱ እየመጣ ሳለ “አባቱ ግን ገና ሩቅ ሳለ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው” (ሉቃ.፲፭፥፳) የሚለው የሚያሳየው የአባቱን ርኅራኄ እንጂ ቀኖናው ከኃጢአቱ አቻ መሆኑን አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና” (፩ኛ ጴጥ.፬፥፫) ባለው መሠረት ነው።አባቶቻችንም ይህንን መሠረታዊ ትምህርት አብነት አድርገው ኃጢአተኛው በኃጢአት ባሳለፈበት ዘመን ፈንታ ቀሪ ዘመኑን በጽድቅ ጎዳና እንዲመላለስ የሚያበቃውን ቀኖና ይሰጡታል፡፡ ሐዋርያው “የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና” በማለት መናገሩ ከተመለሳችሁ ይበቃል ማለቱ አይደለም፡፡ በኃጢአት ፈንታ ፈቃደ እግዚአብሔርን ፈጽሙ ማለቱ እንጂ፡፡ አባቶች ካህናትም በዚሁ መሠረት ለኃጢአተኛ ሰው በቀማህበት ፈንታ መጽውት፣ ያለ ልክ በመብላትና በመጠጣት፣ በስካር፣ በኃጢአት ባሳለፍክበት ዘመን ፈንታ ጹም፣ ጸልይ፣ ስገድ በማለት ለኃጢአተኛው ቀኖና የሚሰጡት መንፈሳዊውን ጣዕም እንዲቀምስ ነው፡፡ እንዲያውም አባቶቻችን ለባለጸጋ ጾምን፣ ምንም ለሌለው ድሃ ምጽዋትን በማዘዝ ኃጢአተኞች ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመፈጸም በሰውነታቸው ላይ ጨክነው መወሰንን እንዲለማመዱ ያዛሉ፡፡ ምክንያቱም ለባለጸጋ ምግብ በቤት ውስጥ ሞልቶ ተርፎ እያለ መጾም፣ ለድሃ ደግሞ ቆጥቦ ያስቀመጠውን ወይም ለምኖ ያገኘውን ገንዘብ መመጽወት ከባድ ነውና፡፡ ይሁንና ድሃ ጦሙን አድሮም ቢሆን ይመጸውታል፤ ባለጸጋም ለተወሰነ ቀን ነውና እንደምንም ራቡን ታግሦ ይጾማል፡፡ ከዚህም የተነሣ ሰውነታቸው ኃጢአትን ከመጸየፍ በተጨማሪ ለጽድቅ መታዘዝንም ይለማመዳል፡፡ ስለዚህ ተነሳሕያን የሚሰጣቸውን ቀኖና በዛ ብለው ሳያንጎራጉሩ፣ አነሰም ብለው ሳይጠራጠሩ በካህኑ ቀኖና ላይ የእግዚአብሔር ቸርነት እና የተነሳሒው ትሩፋት ተጨምሮበት ከታላቅ በደልና ኃጢአት እንደሚያነፃቸው አምነው ቀኖናቸውን ተቀብለው መፈጸም ይገባቸዋል፡፡ ፫. ሥጋውንና ደሙን መቀበል በክርስትና አስተምህሮ የአገልግሎቶች ሁሉ መደምደሚያው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ነው፡፡ የካህናትና የመምህራን መሾም ዋና ግቡ ምእመናንን አስተምረው ለሥጋውና ለደሙ ማብቃት ነው፡፡ ምክንያቱም የመንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ ግቡ ሰማያዊ ርስት መውረስ ነውና፡፡ ያለክርስቶስ ሥጋና ደም ደግሞ ሰማያዊ ርስት ማለትም የዘለዓለም ሕይወት የለም፡፡ ምክንያቱም “..እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፤ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ዮሐ.፮፣ ፶) ተብሎ ተጽፏልና፡፡ በጠፋው ልጅ ታሪክ አስቀድመን እንደተመለከትነው ልጁ ወደ አባቱ ቤት ሲመለስ አባቱ ፍሪዳ አርዶ፣ ድግስ ደግሶ ተቀብሎታል፡፡ የጠፋው ልጅ አዳም ነው፡፡ የጠፋውን አዳምን ፍለጋ የመጣው ደግሞ ክርስቶስ ነው፡፡ “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና” (ሉቃ.፲፱፥፲) እንዲል፡፡ ለአዳም ልጆች የሕይወት ምግብ ሊሆን የታረደው ፍሪዳም ራሱ ክርስቶስ ነው፡፡ በቀራንዮ ኮረብታ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ፣ ደሙን አፍስሶ መሥዋዕት ሆኗልና፡፡ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መሥዋዕት ከመሆኑ አስቀድሞ ሐሙስ ማታ “እንጀራን አንሥቶ ባርኮ ቈርሶ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፤ እንዲሁም ጽዋውን አንሥቶ አመስግኖ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” (ማቴ.፳፮፥፳፮) በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም የክርስቶስ ሥጋና ደም ለእኛ የሕይወት ምግብና መጠጥ ሆኖ መቅረቡን የሚናገር ነው፡፡ ስለዚህ እኛም የዘለዓለም ሕይወት ለማግኘትና ሰማያዊ ርስትን ለመውረስ የክርስቶስን ሥጋና ደም መቀበል ይኖርብናል፡፡ “ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል” (ዮሐ.፮፥፶፮-፶፯) የሚለውም ይህንኑ የሚያስገነዝበንነው፡፡ በኦሪቱ በነበረው የመሥዋዕት ሕግ እስራኤላውያን የፋሲካውን በግ ሲመገቡ ጫማቸውን ተጫምተው፣ ወገባቸውን ታጥቀው፣ ኩፌታቸውን ደፍተው በትራቸውን ይዘው እየተቻኮሉ እንዲመገቡ ታዘው ነበር (ዘፀ.፲፪፥፲፩)፡፡ ይህም ዛሬ ላለነው ክርስቲያኖች ምሳሌ ሆኖን የአማናዊውን በግ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ስንቀበል በጎ ምግባር ሠርተን፣ ወንጌሉን ተጫምተን፣ የንጽሕናን ዝናር ታጥቀን፣ አክሊለ ሦክን፣ ነገረ መስቀሉን እየዘከርን (መስቀሉን ተመርኩዘን)፣ ሞት እንዳለብን በማሰብ እንዳይቀድመን ፈጥነን ንስሓ በመግባት ሥጋውንና ደሙን መመገብ የሚገባን መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ ቀደም ብለን ባየነው የጠፋው ልጅ ታሪክም አባት ልጁ ከጠፋበት ሲመለስ ፊሪዳውን ከማረዱ በፊት “ባሪያዎቹን ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ ስጡት” በማለት ልጁ ታጥቦ ንጹሕ የሆነውን ልብስ ለብሶና አዲስ ጫማ ተጫምቶ እንዲዘጋጅ ነበር ያደረገው፡፡ ልጁን ወደ ልቡ እንዲመለስና የአባቱን ቤት እንዲያስብ ያደረገው ረሃብ ነበር፡፡ “እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ አለ” በማለት መናገሩ ምስክር ነው፡፡ ከአባቱ ቤት ካለው ማዕድ ለመቀበል ግን አስቀድሞ ያንን ማዕድ አቋርጦ በመውጣት የበደለውን አባቱን ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት፡፡ ስለሆነም አባቱን ማረኝ አለው፡፡ አባቱም ይቅር አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ከፊሪዳው ተመገበ፡፡ እኛም ገና በአርባና በሰማንያ ቀናችን ጀምረን ስንመገብ የኖርነውን ሥጋውንና ደሙን መቀበል አቋርጠን ወደ ተለያየ የኃጢአት ሕይወት ብንገባም እንኳ ወደ ልባችን ተመልሰን ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ስንመጣ አስቀድመን ስለጥፋታችን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባን ያስገነዝበናል፡፡ ይህም ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ንስሐ ገብተን መዘጋጀት የሚገባ መሆኑን ይገልጣል። አንድም የንስሓ ጉዞ መጨረሻው በክርስቶስ ሥጋና ደም መታተም የሚገባው መሆኑን እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡ በአጠቃላይ ሰው በኃጢአቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር ከተለየ በንስሓ መመለስ ይኖርበታል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንም በነቢዩ ላይ አድሮ አምላካዊ ጥሪውን ያስተላለፈውና “ወደ እኔ ተመለሱ” እያለ የሚጠራን ለንስሓ ነው፡፡ ስለሆነም ሁላችንም በንስሓ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰን፣ ቅዱስ ሥጋውን በልተን፣ ክቡር ደሙን ጠጥተን ከቅዱሳን ማኅበር እንዲጨምረን የሚጠበቅብንን መወጣት አለብን፡፡ በንስሓ ተመልሰን በቤቱ እንድንኖር እግዚአብሔር በቸርነቱ፣ ቅዱሳን በአማላጅነታቸው አይለዩን። አሜን!!
በትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን።
ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን "ማረው፣ ይቅር በለው" ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!!

እግዚአብሔር ሲቀጣን
"አንድ ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡
"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገጽ 36)

ይህን ቪድዬ አዳምጡት በጣም ትጠቀሙበታላችሁ! ናብሊስ የተሰኘ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው። በጣም ጠቃሚ ጉዳዮች ነው የሚያነሱት። ከታች ያለውን ቪድዮ ሁላችንም እናዳምጠው ለሌሎችም እንዲያዳምጡት ሼር።
ያዩትን ሁሉ መመኘት፤ ከፍትወት እስራት ነፃ መዉጣት | ናብሊስ | ሀገሬ ቴቪ
https://youtube.com/watch?v=FxhCfRvmD54&si=gH0_cRFzhsG_ZMVF

🔹🔸🔹🔸🔹
#እመቤቴ_ሆይ፤ ባትወለጂ እግዚአብሔርን በሥጋ ተገልጦ እናየው ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ ፍቅር፣ ምሕረት እና ፍጹም መልካምነት በእውነት ሥጋን ነሥተው በክርስቶስ እናይ ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ንጽሕና በሰውነት ተገልጦ እናይ ነበርን? በፍጹም። ይኸውም ያንቺ የቅድስና ሕይወት ነው። ከሊቃውንት አንዱ የአንቺ አንዲቷ ትንፋሽ ከቅዱሳን ሁሉ ገድል፣ ምስጋና እና ምልጃ ሁሉ የከበረች እንደሆነች ተናገረ። ይህ ሁሉ ከሰው ኅሊና ስለሆነው ንጽሕናሽ ነው። በዘወትር ቋንቋችን አንቺን "ንጽሕት" ብቻ ማለት ንጽሕናን ማጉደፍ ይሆናል እኮን። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ያንቺ ንጽሕና እና ቅድስና በቃል ከመነገር ይልቅ፤ በዝምታ የልብ ለኆሳስ ቢመሰገን የተገባ ነው። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔር ትእዛዝ በምልዓት ሲፈጸም፤ ሕጉ ሲደረግ ምን እንደሚመስል በምን እናውቅ ነበር?
አንቺ ባትወለጂ የክህነት ንጽሕና በምን ይጠበቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የንስሐ መንገዱን ማን ያመለክተን ነበር? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ መታዘዝ፡ የእኛን ዐመጸኛነት እንዴት ይገስፀዋል? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ ትሕትና፡ የኔን ትዕቢት ይሰብረው ዘንድ እንዴት ይቻለዋል? ስለ አምላካዊው ኀይሉ፤ ጠላት ሰይጣን ለልጅሽ ይገዛል። የልጅሽ የክርስቶስን ስም ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። አንቺ ግን በትሕትናሽ ሰይጣንን አራድሽው። እርሱ መንፈስ ሲሆን "ሥጋ ለባሽ" ብሎ በሚንቃት "በአንዲት ሴት" መሸነፉ ሁልጊዜም ግራ ይገባዋል። ስምሽን የሚጠሩ ሰዎች ፊትም መቆም አይቻለውም። ስምሽን ሲጠሩ ኀይላቸውን ትተው ኀይልሽን ይይዛሉና። ይኸውም እግዚአብሔር ነው። ስምሽን ሲጠሩ ትዕቢታቸውን ጥለው በትሕትናሽ ይጋረዳሉና። ስምሽን ሲጠሩ ጥርጣሬያቸውን በሃይማኖትሽ ያሸንፋሉና። በንጽሕና ቀሚስሽ ስለ እድፈታቸው ከሚከሳቸው ይጋረዳሉና። ሰይጣን ከእነርሱ ዘንድ አይቀርብም። እመቤቴ ሆይ አንቺ ባትወለጂ ከመልካሙ ሁሉ በአፍአ በቀረን ነበር እኮን። አሁንም "መጥተን" ሳለን የቀረን አታድርጊን። እኛ ራሳችንን ብንተው፤ አንቺ አትተዪን። እኛ ብንርቅ፡ አንቺ አትራቂን። እኛ ብንዘነጋ፡ አንቺ አትዘንጊን። መሐርነ፡ ወተሣሃልነ!
ፀሀፊ Micky Asres

🌿 🌿 🌿 🌿 🌿 🌿 🌿
ከእንቅልፍ የምትነቁበት ዘመን....
(ልዩ መልእክት ናት አንብቧት)
ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መላክ እንዳዘዘው አደረገ ማቴ. 1፥24
እግዚአብሔር ካዘዘ መቼና የት አደርገዋለሁ አትበል። በታዘዝህበት ቅጽበት ወደ ሥራ ብትገባ እግዚአብሔር ካንተ ጋር አብሮ ይሠራል።
ወደ ኋላ ብታፈገፍግ ግን እንደ ዮናስ መንገድህን ያሰነካክልብሃል።
እግዚአብሔር ባላዘዘህ በኩል በመርከብ ከምትሻገር እግዚአብሔር ባዘዘህ በኩል ያለ መርከብ ብትሻገር ይሻልሃል። ከግዚአብሔር ጥበቃ ውጭ ሆነህ በመርከብ ከምትሳፈር በእግዚአብሔር ጥበቃ ውስጥ ሆነ በባሕር ቢያሰጥሙህ ይሻልሃል ዮና. 1፥15።
ከባለ ሰረገላው ፈርዖን ይልቅ እግረኛው ሙሴ ተሻግሮ መሄዱን አልሰማህምን? እግዚአብሔር ባዘዘህ መንገድ ላይ ደፍረህ ተመላለስ።
እባብና ጊንጥ ብትረግጥ፤ በእፉኝት ጉድጓድ አጠገብ ብትቀመጥ፤ አንበሳው በሚያናፋበት፣ ነብር በነገሠበት ጫካ እንድታልፍ ብትገደድ ምንም ሳትጨነቅ አድርገው። ምክንያቱም ያዘዘህ ሁሉን የሚችል አምላክ ነውና።
ዮሴፍ ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘውን እንጅ ሌላ ለማድረግ አላሰበም። ለዚህ ነው ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ “ዮሴፍም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ የእግዚአብሔር መላክ እንዳዘዘው አደረገ” ብሎ የጻፈለት።
የዮሴፍን ደግነቱን አስተውሉ! እንደ ናቡከደነፆር በሕልም ዳን. 2፥1፣ እንደ በለዓም በራእይ ዘኁ. 23፥5 እግዚአብሔር ያዘዘውን ከማድረግ አልዘገየም።
የግብጹ ንጉሥ ፈርዖን የከነዓን ሰዎች በረሀብ ምክንያት ሲሰደዱ አገሩን ከረሀብና ከስደት ያተረፋት በሕልሙ ያየውን መልዕክት ተቀብሎ ከዮሴፍ ጋር በመሥራቱ ነበር።
እግዚአብሔር የምታመልጥበት መንገድ ሳይተውልህ መከራ አያመጣብህም።
እንደ ናቡከደነፆር በቸልተኝነት ካልተውኸው በቀር ማንንም ቢሆን በመከራ የተወበት ጊዜ የለም።
እስኪ አስቡት ለሰዶምና ገሞራ ሰዎች የሚድኑበት ነገር ይገኝ እንደሆነ ከአብርሃም ጋር የተነጋገረውን ስትመለከቱ ቸርነቱ አያስገርማችሁም? እንደ ዮሴፍ ነቅቶ ወደ ታዘዘው ሥራ የሚገባ ቢገኝ እግዚአብሔርስ ለሁሉም የመዳንን መንገድ ያዘጋጃል።
ነቅተን ሳለን የሰማነውን ወንጌል ይዘነው እየተኛን በተቸገርንበት ዘመን ሆነን ስናስበው ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቅቶ ያደረገው ነገር ያስገርማል። ከታዘዘው በቀር ምንም አላደረገም፤ የታዘዘውን ለማድረግም አልዘገየም። የመንቃት ምልክቱ ይህ አይደል? የታዘዙትን መፈጸም! ሳይጠራጠሩ ማድረግ! የመንቃት ምልክቶች እኮ ናቸው።
የተሰበክነውን ሁሉ አለመስማታችን፣ የሰማነውን ሁሉ አለማድረጋችን በእንቅልፍ ውስጥ ለመሆናችን ምልክት ነው። እያደረግነው ያለውን እስኪ ተመልከቱት በአዚም ውስጥ ያለ ሰው የሚያደርገውን እያደረግን ይመስለኛል። የምንናገረውን አናስተውለውም። የቆምንበትን ቦታ ልብ አንልም። በቤተ መቅደስ ቆመን በዓለም ስላለው ነገር እናወራለን። በዐውደ ምሕረት ሆነን በገበያ ያለ ሰው የሚያደርገውን እናደርጋለን። ዘምረን ስንጨርስ እንዘፍናለን፤ ቀድሰን ስንመለስ እንረክሳለን፤ ፆመን ስንገድፍ ከፆም በኋላ ሰይጣን መኖሩን እንረሳለን። ከዚህ በላይ በእንቅልፍ ላለመንቃታችን ምልክት አለ?
የነቁትንማ ተመልከቷቸው ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ውዳሴ ያቀርባሉ፤ ገንዘብ ቢሰጣቸው ዐሥራት እያመጡ እግዚአብሔርን ባለዕዳ ያደርጋሉ፤ የተሰጣቸውን ነገር ሁሉ ለጽድቅ ሥራ ይጠቀሙበታል። አሁንስ ነቅተን የታዘዝነውን ማድረግ ይገባናል።
መጽሐፍ የሚለው “ከእንቅልፍ የምትነቁበት ጊዜው እንደደረሰ ዕወቁ” ሮሜ 13፥11 ነውና። ከኃጢአት እንቅልፍ የመንቃት ጊዜው ደርሷል። የጌታ መልአክ ዮሴፍ ሊያደርገው የሚገባውን ነገር እንደነገረው ሁሉ እኛም የሚመጣብንን ፈተና ሁሉ አስቀድሞ በነቢያት በሐዋርያት ነግሮናል። ለእኛ መላእክቶቻችን ነቢያትና ሐዋርያት ናቸው። እግዚአብሔር በሐዋርያት በኩል የሚያስጨንቅ ዘመን እንደሚመጣ አልነገረንም? 2ጢሞ. 3፥1፣ ረሀብና ቸነፈር በየሀገሩ እንደሚሆንስ አላነበብንም? መንግሥት በመንግሥት ላይ፣ ሕዝብም በሕዝብ ላይ እንደሚነሣስ አልሰማንም? ማቴ. 24፥7 ከእንቅልፍ ስላልነቃን ልብ አንለውም እንጅ በእውነት ከገጠመን ሁሉ ፈተና ያልተነገረን የትኛው ነው?
ዮሴፍ እመቤታችንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሔሮድስ ሰይፍ ያድናቸው ዘንድ የእግዚአብሔር መልአክ አዘዘው ማቴ. 2፥13 ዮሴፍ ፈጥኖ አደረገው በገሊላ ባሉ ሰዎች የተደረገው በእመቤታችንና በልጇ ላይ አልተደረገም።
ዛሬ በዓለም ላይ እየደረሰ ያለው ጥፋት እንዳይደርስብን እኛም ከእንቅልፋችን ነቅተን የታዘዝነውን ማድረግ ይገባናል።
ሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮነ መልአክ

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን ለመድኃኔዓለም ለስቅለቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን ማኅሌተ ጽጌን ከአባ ገብረ ማርያም ጋር በመሆን ለደረሱት ለታላቁ አባት ለአቡነ ጽጌ ድንግል፣ ጌታችን በዕለተ አርብ የጠጣው መራራ ሐሞት እያሰብ ሁል ጊዜ አርብ አርብ ኮሶ ይጠጡና የመድኃኔዓለም ዝክር ይዘክሩ ለነበሩት ለታላቁ አባት ለአቡነ መብዓ ጽዮንና በዋሻ ውስጥ አርባ ዓመት ለኖሩ መና ሲመገቡ ለነበሩት ለታላቁ አባት ለአቡነ ጊዮርጊስ ዘጣና ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ ለሀገረ ቃው ኤጲስ ቆጶስ ለአባ መቃርስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በዋሻ ከሚኖር ከጳውሎስና ከዮልያኖስ ከእነርሱም ጋር ላሉ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን፤ ስብሐት ዋህድ ዘምስለ ምሕረት፤ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ። ትርጉም፦ እርሱ የቅዱሳን ክብራቸው፤ የጻድቃን መድኃኒታቸው ነው፤ ምድርን በሮማን አበባ አስጌጣት፤ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ከምሕረት ጋር ያለ የወልድ ምስጋና በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው።
+ + +
❤ "ሰላም ለሕማሙ ወሰላም ለሞቱ። ሰላም ለገቦሁ ቅድስት ዘውኅዘ እምኔሃ ደመ ወማይ፡ፅሙር። አንቅዕተ ብዕል ወክብር። ሰላም ለግንዘቱ በዘጠብለልዎ ሰላም ለመቃብሩ ኀበ ቀበርዎ"። ትርጉም፦ ለሕማሙ ሰላምታ ይገባል፤ ለሞቱም ሰላምታ ይገባል። የሀብት (የብልጥግና) የክብር ምንጮች የኾነ ደምና ውሃ አንድነት (ተባብሮ) ከርሷ የፈሰሰ ለኾነች ለቅድስትጐኑ ሰላምታ ይገባል። በሚጠቀልሉት ገንዘብ ለኾነ ለግንዘቱ ሰላምታ ይገባል፤ በቀበሩት ዘንድ ላለ መቃብሩ ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጣና፦ አገራቸው ጣና ዘጌ ነው። በዋሻ ውስጥ አርባ ዘመን ሙሉ ዘግተው ሲኖሩ መና ከሰማይ እየወረደላቸው ውሃም በዋሻ ውስጥ ፈልቆላቸው ይኖሩ ነበር። አንድ ቀን መልአክ መጥቶ ምን ቢጋደሉ የጌታችንን ስጋውን በልተው ደሙን ካልጠጡ እንደ ማይድኑ ነገራቸው። በመልአኩም ትዕዛዝ መሰረት ከዋሻው ወጥተው ሊቆርቡ ቤተ ክርስቲያን ገቡ በቅዳሴም ላይ ሳሉ አንድ ድንቅ ምስጢር ተመለከቱ ይህም በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ካህኑ "ሀበነ" ሲል ጌታችን በዕለተ አርብ እንተ ተሰቀለ ሆኖ ደሙ ሲፈስ የካህኑ እጅ በደም ተነክሮ በመንበሩ ቆሞ ቢያዩት በድንጋጤ ሳይቀሳቀሱ አርባ ዓመት ተኝተዋል ይህም በሰው አቆጣጠር በጌታችን ዘንድ ግን ምን ያይህል ጊዜ እንደ ሆነ እራሱ ባለቤቱ ያውቀዋል። በመጨረሻም ጻድቁ በዐረፉ ጊዜ መቃብራቸውን አራዊት ቆፍረውላቸው መነኰሳቱ ገንዘው ቀብረዋቸዋል። ታቦታቸው በጣና ይገኝል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት።
+ + +
❤ አቡነ መብዓ ጽዮን፡- አባታቸው ንቡረ ዕድ እናታቸው ደግሞ ሀብተ ጽዮን ይባላሉ፡፡ በሌላኛው ስማቸው ተክለ ማርያም ይባላሉ፡፡ ይህንንም ስም ያወጣችላቸው እመቤታችን ናት፡፡ እመቤታችንን ከሕፃንነታቸው ጀምረው እጅግ ይወዷት ነበር፡፡ ትንሽ ልጅ ሳሉ አንድ ካህን ወደ ሀገራቸው በእግድነት መጣና አባታቸው ሀብተ ጽዮን አሳደሩት፡፡
❤ እንግዳውም ካህን የእመቤታችንን ሥዕል ምስለ ፍቁር ወልዳን ይዞ ነበር፡፡ ሲተኛም በራስጌው ያኖራት ስለነበር በሀብተ ጽዮንም ቤት አድሮ ጠዋት ተነሥቶ ሲሄድ የእመቤታችንን ሥዕል በራስጌው እንዳኖራት እረስቶ ሄደ፡፡ ያንጊዜ ሕፃን የነበሩት አባ መብዓ ጽዮንም ሥዕሏን ወስደው ሳሟት፣ በእርሷም ደስ ተሰኙባት፡፡ ለሌላም ሰው አልሰጥም ብለው በአንገታቸው አሰሯት፡፡ ሀብተ ጽዮንም "ይህችን የእግዳው ካህን ንብረት የሆነች የእመቤታችንን ሥዕል ከቤት እንዳላስቀምጣት ኃጢአት ይሆንብኛል እንዳልሰጠውም ከየት አገኘዋለሁ" እያለ ሲቀጨነቅ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ያንን እንግዳ አገኘው፡፡ ባገኘውም ጊዜ ከቤት የተዋትን የእመቤታችንን ሥዕል እንዲወስድ ነገረው፡፡ መጀመሪያ ሕፃን መብዓ ጽዮን እንዳገኛትና በጣም እንደወደዳት ለሌላ ሰውም አልሰጥም ብሎ በግድ ቀምቶ እንዳስቀመጣት ነገረው፡፡ እንግዳውም ይህን ሲሰማ "የሥዕሊቱ ባለቤት እርሷ የሕፃኑ እንድትሆን ፈቅዳለታለች፤ ከእኔ ዘንድ መሆኗን ፈቅዳ ቢሆንማ ኖሮ ባልተረሳችኝ ነበር ለዚያ ላገኛት ልጅህ የተገባች ናት" ካለው በኋላ እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጥተው ተለያዩ፡፡
❤ አቡነ መብዓ ጽዮን ዕድሜያቸው ከፍ ሲል ወላጆቻቸው ሚስት ሊድሩላቸው ሲሉ እርሳቸው ግን አላገባም ብለው የዚህን ዓለም ጣዕም ንቀው ነው የመነኑት፡፡ የምንኩስና ልብስ ከለበሱበት ጊዜ ጀምረው በበቅሎና በፈረስ ላይ ተቀምጠው አያውቁም፤ በአልጋም ሆነ በምንጣፍ ላይ አልተኙም ይልቁንም የአንድ ሰው ሸክም የሚያህል ትልቅ ድንጋይ በደረታቸው ተሸክመው ከአመድ ላይ ይተኙ ነበር እንጂ፡፡ ከሰንበት ቀናት ውጭ ሲቀመጡም ድንጋዩን በራሳቸው ላይ ይሸከሙታል፣ ሲሰግዱም በጀርባቸው ያዝሉት ነበር፡፡
❤ አባታችን ለቅዱስ ሥጋ ወደሙ እጅግ ትልቅ ክብር ስለነበራቸው የቆረበ ሰው ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ሲሄድ እንቅፋት እንኳን ሲመታው ስለሥጋ ወደሙ ክብር ብለው እግሩ የደማበትን ሰው ደሙን ይጠጡት ነበር፣ ደሙ የፈሰሰበትንም አፈር ይልሱታል፡፡ ይህም የመድኃኔዓለምን ሥጋና ደም ከማክበራቸው የተነሣ ነው፡፡ ጻድቁ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መራራ ሐሞት መጠጣቱን አስታውሰው ሁልጊዜ ዐርብ ዐርብ ኮሶ ይጠጡ ነበር፡፡ መድኃኔዓለምም በየጊዜው በሕፃን አምሳል ይገለጥላቸዋል፡፡ በዕለተ ዓርብም እንደተሰቀለ ሆኖ ይገለጥላቸው ነበር፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ለአቡነ መባዓ ጽዮን በመሠዊያው ላይ በነጭ በግ አምሳል ይገለጥላቸው ነበር፡፡
❤ መከራ ሞቱን እያስታወሱ ሰውነታቸውን ይጎዱ እንደነበር በቅዱስ ገድላቸው ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡- "በተቀደሰች በዓርባ ጾምም የመድኃኔዓለምን ግርፋት እያሰበ ሰውነቱን በእጅጉ ገረፈ፡፡ ደሙ ከመሬት እስኪወርድ ድረስ ልቡንም አጥቶ ከምድር ላይ ወደቀ፡፡ የመድኃኔዓለምን መከራውን አስቦ እንደሞተም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም ወደ እርሱ መጣና "ተነሥ እኔ ቁስልህን እፈውስሃለሁ" ብሎ የጀርባውን ቁስል ዳሰሰው፡፡ ምንም ሕማም እንዳላገኘውም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም አባታችንን "በአንተው እጅ ትገደልን? እኔ እንኳ የተገደልኩት በአመፀኞች በአይሁድ እጅ ነው" አለው፡፡ በዚያችም ሰዓት ጌታ የመባዓ ጽዮንን ከንፈሮቹን ይዞ ሦስት ጊዜ እፍ አለበትና "የከበረ ትንፋሼም ከትንፋስህ ጋራ ይጨመር፣ ሥጋህም ከነፍስህ ጋራ የከበረ ይሁን› አለው፡፡ "አንተ በላዩ እፍ ያልህበትም የተቀደሰና የከበረ ይሁን" አለው"፡፡