ካናዳ በስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንደሆነች ተሰምቷል።
ካናዳ ዶናልድ ትራምፕ ልክ ስራ ሲጀምሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ከሀገር ለማባረር ከያዙት እቅድ ጋር በተያያዘ ሊከሰት ለሚችል ማንኛውም ነገር የራሷን ዝግጅት ማድረግ መጀመሯ ተሰምቷል።
በዶናልድ ትራምፕ እቅድ ምክንያት ወደ ሀገሪቱ ለመግባት የሚሞክሩ የስደተኞች ቁጥር ሊበዛ ይችላል በሚል ስጋት የራሷን ዝግጅት እያደረገች ነው።
የትራምፕ ትግበራ በካናዳ ድንበር የጥገኝነት ጠያቂዎችን (asylum) ቁጥር ያበዛዋል በሚል ስጋት ተደቅኗል።
ካናዳ ሂደቶችን በንቃት በመከታተል ላይ ትገኛለች የተባለ ሲሆን ሊከሰት የሚችለውን ማንኛውም አይነት ሁኔታ ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረገች ነው።
የትራምፕ ጥብቅ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ሚሊዮኖችን ማባረር እና የዜግነት ህግን መቀየርን ያጠቃልላል። ይህም ብዙ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ ካናዳ ለመሻገር እንዲሞክሩ ሊያደርግ ይችላል።
የካናዳ ባለስልጣናት በድንበር ላይ ሊከሰት የሚችለውን ችግር ለመፍታት ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጉ ነው።
ብዙዎች የትራምፕ እርምጃ ወደ ካናዳ ትልቅ የስደተኞች ማዕበል ይዞ ይመጣ ይሆን ? ብለው እያሰቡ ናቸው።
ባለስልጣናቱ ግን የደንበር ቁጥጥርን ለማጠናከር እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ሰዎች እንዳይገቡ ፣ ድንበር ላይም ችግር እንዳይፈጠር ትኩረት አድርገው እየሰሩ ነው ተብሏል።
@tikvahethiopia