__
የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በግንቦት 2016 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
ነገር ግን ከሲስተም ችግር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለማስተናገድ የምዝገባ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን ምዝገባውም እስከ ግንቦት 2/2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በምዝገባ ላይ ያላችሁን ማንኛውም ቅሬታ በስልክ ቁጥር 011(8)-27-59-36 እንዲሁም 011(8)-27-59-45 መደወል የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
በምዝገባ ወቅት ለመመዝገብ ያስቸገራችሁ ወይም የአያት ስም አልገባ ያላችሁ ተመዛኞች Do you have MoH IDNO or Ministry of Education (MoE) User Name ? በሚለዉ ጥያቄ ላይ Yes የሚለውን በመጫን ከዚህ በፊት በጤና ሚኒስቴር የተሰጣችሁን MoH IDNO ወይም በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጣችሁን User Name በማስገባት እና የቀረውን ዘርዝር መጠይቅ ጨርሶ በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡