እስኪ እኛ ማነን እንጠይቅ መርምሩ
የዚች አለም ስሪት ምን ይሆን ሚስጥሩ
አደምን ሲፈጥር ያኔ በጥንስሱ
መላኢኮች ናቸው ሱጁድ የወረዱት ለሱ
ከቶስ ለምን ይሆን አሏህ የፈጠረን
እኛስ ምን አረግን ምንስ ምላሽ ሰጠን
በአሁን ጊዜ አለም በጣሙን ተናውጣ
መች ይሆን ሚደርሰን የሞታችን እጣ
ጊዜው ግን አሁን ነው የመመለሻው ቀን
ሱጁድ ላይ ተደፍተን አሏህ ማረን ብለን
አኛ ግን እምቢ አልን ፈጣሪን እረሳን
✍ አማር ታጁ(@Amuu77)
Join us 👉👉 👇👇
@Allahisoneee
@Allahisoneee