ከአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ (፮) ክ/ጦር የተሰጠ የማስጠንቀቂያ መልዕክት !
*
መንግስት ነኝ ባዩ የአብይ አህመድ ወራሪና ወንበዴ ቡድን አሁን የደረሰበትን ሽንፈት እና ያለበትን የኢኮኖሚ ውድቀት ለመሸፈን ሲል በህዝባችን ላይ የተለያዩ የክፍያ መስፈርቶችን በማውጣት ህዝባችንን እየበዘበዘ ይገኛል።
በተለይም ደግሞ ከዚህ ቀደም ከህዝብ ላይ ይሰበስብ የነበረውን ግብር ማግኘትና ማስከፈል ስላልቻለ ብሎም በተለያዩ ስያሜዎች የሚሰበስበውን ገንዘብ በፈለገው መንገድ ማግኘት ስላልቻለ አማራጮችን ተጠቅሞ ካዘናውን መሙላት ይፈልጋል።
ለዚህ ዋነኛ ማሳያ ሆነው ለመተግበር እንቅስቃሴ እያደረጉት ያሉት ደግሞ
ጥቁር አስፓልት ኬላ፣ማዳበሪያ፣ጤና መድን እና መታወቂያ ናቸው።በእነዚህ ላይ ዋጋ ከመጠን በላይ በመጨመር ከህብረተሰቡ ገንዘብ መሰብሰብ አስቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
መንግስት አሁን ላይ መሸነፉን አውቋል።
ይህን ወዳጅም ጠላትም ጠንቅቆ ያውቀዋል።በዚህ የተነሳ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አስፓልት ላይ በመቅረጥ፣በማዳበሪያ ላይ ከፍተኛ ዋጋ በመጣል፣ጤና መድንን በመሰብሰብ፣በመታወቂያ ምክኛት ገንዘብ በመሰብሰብ ህዝብን እያማረረና እያሰቃዬ ይገኛል።
ተስፋ የቆረጠው የአብይ አህመድ የደም ግብር አስቀጣይ ካድሬ ከህብረተሰባችን ህጋዊ በሚመስል መንገድም በዘረፋም ለነገ መሸሻ ይሆናቸው ዘንድ ገንዘብ እየሰበሰቡ መሆኑን በአለን ተከታታይ እይታ ገምግመናል።በመሆኑም ወቅታዊውን የህዝባችን ቁመና እና የጠላትን ሁኔታ በማገማገም የሚከተለውን የክልከላ መግለጫ እንደ ክፍለ ጦር አውጥተናል።
1. ከዛሬ የካቲት 28/06/2017ዓም ጀምሮ በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የጤና መድን ክፍያ በየትኛውም ቀጠና ማለትም የፋኖ ሐይል በተቆጣጠራቸው ቀበሌዎች ብሎም የጠላት ኃይል በተቆጣጠራቸው ቦታዎች የሚኖር ሁሉ ምንም አይነት ክፍያ መክፈል የለበትም።ሲያስከፍል የተገኘ ብሎም ሲከፍል በተገኘ የትኛውም አካል ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።
2.ከዛሬ የካቲት 28/06/2017ዓም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች ብሎም ቀበሌዎች ማዳበሪያ በተለመደው ዩኒየን ወይም ህብረት ስራ ቦታዎች የተጠራቀመን ማዳበሪያ በትክክለኛው የዋጋ ተመን መግዛት ይቻላል።ከዛ ውጭ ጠላት ባለበት ቦታ ሒዶ መግዛት ፈፅሞ አይቻልም።አሁን ያለው የዋጋ ተመን ሆን ተብሎ የተለያዩ ክፍያዎች ተጨምረውበት ህዝባችንን ለመበዝበዝ የተደረገ ስለሆነ በወጣው የዋጋ ተመን መግዛት አይቻልም።በዚህ ዋጋ ሲሸጥ የተገኘ ብሎም ሲገዛ የተገኘ ሻጩም ገዥውም ይወረሳል።ህጋዊ እርምጃም የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።
የማዳበሪያ አቅርቦትን በተመለከተ የአማራ ፋኖ በጎጃም አዲስ መመሪያ እስከሚያወጣ ድረስ በየትኛውም ቦታ ህዝባችን ማዳበሪያ ወዳለበት ቦታ ሔዶ ከመጠን በላይ በተተመነ ዋጋ መግዛት አይችልም።
3, ክፍለ ጦራችን በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ከጤና፣ከቴሌ፣ከባንክ፣ከውሃ፣ከመብራት፣ከመንገድ ስራዎች፣ ከዩኒየን፣ከህብረት ስራ ማህበር ውጭ ያሉ የትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት ከዛሬ 28/06/2017ዓም ጀምሮ መክፈት ብሎም መስራት የማይቻል መሆኑን እንገልፃለን።ይህን ተላልፎ በሚገኝ የትኛውም ዓይነት የመንግስት ሰራተኛ ላይ በስራ ቦታው ላይ ቢሮ ገብቶ ሲሰራ ቢገኝ ለሚወሰደው ርምጃ ሀላፊነቱን ራሱ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን::...........
[አዲስ ትውልድ : አዲስ አስተሳሰብ :አዲስ ተስፋ ]
የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ የፍታሔ ንጉሴ /6ኛ ክፍለጦር!
የካቲት 28/2017 ዓ.ም