Neueste Beiträge von ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ (@historicalheromedia) auf Telegram

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ Telegram-Beiträge

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ
በዩትዩብ ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ
👉https://www.youtube.com/@Historicalheromedia
ጥቆማ ለመስጠት
👇👇👇
@ethiotemsaletbot
6,409 Abonnenten
1,411 Fotos
138 Videos
Zuletzt aktualisiert 11.03.2025 07:48

Der neueste Inhalt, der von ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ auf Telegram geteilt wurde.

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

10 Mar, 18:05

779

💚💛ሰበር ዜና‼️

ጀግኖቹ በሸዋ ቀጠና የሚንቀሳቀሱት የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለጦር የነበልባል ብርጌድ  በሃምሳ አለቃ ፍቃዱ ጥላሁን ዋና ጦር አዛዥነት በምክትል ለኦፕሬሽናል ምክትል ጦር አዛዥ አስር አለቃ ሸዋቀና ኦርጌሳ የሚመሩት የብርጌዱ ቃኚና መሃንዲስ ከሺ አለቃ ሁለት በጋራ በመሆን በባለገድሎቹ በሃምሳ አለቃ መክት ዋና ሺአለቃ መሪና በምክትል የሺአለቃዋ መሪ እምሽ በጋሻው በተጠና መልኩ ከሺ አለቃ ሁለት እና የብርጌዱ ቃኚና መሃንዲስ በጥምረት ለልዩ ኦፕሬሽን ወደ አረርቲ ከተማ የተላኩት ክንደ ብርቶቹ እንደ ረመጥ እሳት ጠላትን የሚገላምጡት የሸዋዎቹ ቆንጅዬዎች የአባቶቻችን የእምዬ ሚኒሊክ ግርፎች የካቲት ወር መሰናበቻ በቀን 30/6/2017ዓ.ም ከምሽቱ 3:20 ገደማ መሀል አረርቲ ከተማ አዲሱ ከብት ተራ አካባቢ ለቅኝት የወጣው የአብይ ወንበዴ አማራ ጠሉ ስመ መከላከያ ሰራዊት ላይ እሳቶቹ የነበልባል ብርጌድ አራት ፋኖች በከፈቱት ተኩስ የአገዛዙ ሁለት ከፍተኛ አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸው በነፍጣቸው ጠላትን በሚያበራዩት የሸዋ ፈርጦች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል።

ቀጫጭኖቹ ፋኖች እስከወዲያኛው ከዚህ ምድር ከሸኟቸው የአብይ ወንበር ጠባቂዎች ሁለት ከፍተኛ አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸው አምስት ክላሽ ኮቭ እና አንድ መገናኛ ሬድዮ ማርከው ግዳጃቸውን በተገቢ መንገድ ፈፅመው ወደ ሰላም ቀጠና እየተገማሸሩ የወጡ መሆኑን የብርጌዱ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አሳውቋል።

  ድል ለአማራ ፋኖ!!!
  ነፃነታችንን በተባበረ አማራዊ ክንዳችን።

ዘላለማዊ ክብር ስለነፃነት ለተሰው ሰማዕታት።

መረጃው/የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክ/ጦር የነበልባል ብርጌድ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ነው።

      መጋቢት 1/7/2017ዓ.ም
         ነበልባሎቹ።
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

10 Mar, 18:04

766

💚💛ሰበር ዜና‼️

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በምዕራብ በለሳ ወራህላ ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው ፈንጣ ሀዋሪያት ከሚባል ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ/ም ከጥዋቱ  አራት ስዓት ጀምሮ የብልፀግናን ጥምር ወንበር  አስጠባቂ ሀይል ማለትም መከላከያ፣ አድማ በታኝ እና ሚኒሻን በተለመደው  የውጊያ ምት  ቁም ስቅሉን አያበሉት ለእነሱ ቀኑ ወር ያህል እረዝሞባቸው መውጫ ቀዳዳ አሳጥቷቸው ውሏል።

ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በለሳን  ሙሉ ለሙሉ ከአገዛዙ ለማፅዳት ዘመቻ  ከጀመረበት የካቲት 20 ጀምሮ ገጠሮችን ሙሉ ለሙሉ አስለቅቀን  አርባያ ከተማ እና ከመኪና መንገድ ብቻ ተወስኖ እንዲቀመጥ አድርገናል ሲል የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ታድሎ ደሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተናግሯል።

የአገዛዙ ሀይል በማንኛውም ስአትና ሁኔታ ፣ ቀንም ሆነ ለሊት ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  የሚገጥመነን እርምጃ  አናውቅም በማለት እንቅስቃሴአቸውን ሁሉ በዙ 23 የታጀበ ቢያደርጉም ከጀግኖች ምት እና ሞት መዳን አልቻሉም ማንም እንደ ማያድናቸውም እያሳየናቸው እንገኛለን፣ በዛሬው ውጊያ ጠላት ዳግመኛ ከፍተኛ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት  በሽንፈትና በውርደት ተመልሷል ብሏል።

ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ሰሞኑን በበለሳ ከመከላከያ፣ከአድማ ብተና፣ እንዲሁም የተለያየ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ከአገዛዙ በግፍ የተባረሩ  በርካታ አዲስ ሀይሎች ወደ ክፍለ ጦራችን እየተቀላቀሉ ጉልበት እየሆኑን እንዲሁም ለአማራ ህዝብ ተጨማሪ ጥንካሬ በመሆን ከነባሩ ሀይል ጋር በቅንጅት እየተዋጉ ይገኛሉ።

የበለሳ ህዝብ ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጎን  በመሆን የብልፅግናን ስርዓት ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ቆርጦ ተነስቶ አብሮ ተሰልፎ የህይወት ዋጋ እየከፈለ ይገኛል። መንግስትን ጎትተን ቤተ መንግስት አስገብተነው ዋጋችን እረስቶ አመድ አፋሽ አድርጎን በለሳን በማንኛውም ልማት ወደ ኋላ አስቀርቶን የሚኖረውን ስርዓት ከዚህ በላይ እንዲቀጥል አንፈቅድለትም በማለት ከፋኖ ጋር እየታገሉ  ያሉ አርሶ አደሮች እና ልጆቻቸው ቁጥር እጅግ ብዙ ናቸው። የደጃች ዳኛው ተሰማ ልጆች እንደ አያቶቻቸው  የህልውና ፣ የነፃነት  እና የፍትህ ተጋድሎ እያደረጉ ዳግመኛ  ታሪክ እየሰሩ ይገኛሉ።

ጠላት በአሁኑ ስአት ሀይሉን ተራራ ላይ እንደ ዝንጀሮ መንጋ ሰብስቦ በሞርተር እና ዲሽቃ ነብሱን ለማትረፍ እየጣረ በከፍተኛ የድረሱልን ጥሪ እየጮኸ ይገኛል።

ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጥቁር አስፓልትና ከተማ ዙሪያ  የማይለቀውን የአንባገነኑን ስርዓት እግር በእግር እየተከታተለ  እግሩን እያሳጠረለት፣ ቁጥሩን እየቀነሰለት፣ ሞራሉን እየሰበረው እንደሚገኝ ፋኖ ታድሎ ደሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

ከጎንደር ሰማይ ሰር ውጊያ እና ግዳጅ ላይ የሚገኘው ክፍለ ጦራችን በቅርቡ የጥይት ድምፃችን አባይ ማዶ አራት ኪሎ ጥግ   ለማድረግ ድርሻችን እና ግዴታችን እየተወጣን  እንገኛለን ሲል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግ/ሀላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ  (ካስትሮ ) ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

© ኢትዮ 251 ሚዲያ
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

10 Mar, 18:03

690

💚💛የአማራ ፋኖ በጎጃም አደረጃጅቱን እያጠነከረ ይገኛል‼️

በአማራ ፋኖ ጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሥር የሚገኘው ሶማ ብርጌድ ከቀን 29/6/2017 - 01/07/2017 ዓ.ም ድረስ ልዩ ጉባኤ አድርጓል።

በጉባኤው የሶማ ብርጌድ አመራርና የሁሉም ሻለቃ ተወካይ አባላት፣የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አመራሮች እንዲሁም የአማራ ፋኖ በጎጃም የፖለቲካ መኮንኖች ተሳታፊ ሆነዋል።

ሦስት(3) ተከታታይ ቀናትን በፈጀው ጉባኤ አጠቃላይ የብርጌዱ የሥራ አፈፃፀም በጥልቀት የተገመገመ ሲሆን ወቅታዊ የሕዝብ ጥያቄዎችና ፍላጎቶች በልኩ ተዳሰው ተለይተውበታል።

በመጨረሻም የብርጌድ አመራር እንደገና የማዋቀር (Reform) ሥራ በመሥራት እና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን በማሥቀመጥ ጉባኤው ተጠናቋል።

አዲስ የብርጌድ አመራሮች ዝርዝር፦
1. ሰብሳቢ - ፋኖ እርቂሁን ጫኔ
1.1. ም/ሰብሳቢ - ፋኖ አብርሃም አበበ
2. ጽ/ቤት ኃላፊ - ፋኖ ወንዴ የሺዋስ
3. ወታደራዊ አዛዥ - ፋኖ አሳምነው አንዳርጌ
3.1. ም/ወታደራዊ አዛዥ - ፋኖ ፋንታሁን አለማየሁ
4. ዘመቻ መሪ - ፋኖ ይከበር ኃይሉ
4.1. ም/ዘመቻ መሪ - ፋኖ ምናለ ተሜ
5. የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ - ዋና ሳጅን ይልቃል አስሬ
6. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ - ፋኖ መንበረ ልዑል
7. ሕዝብ ግንኙነት - ፋኖ ሙሉቀን ካሣ
8. የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ - ፋኖ ስማቸው ዘሩ
9. የሎጀስቲክስ ኃላፊ - ፋኒት ትዕግስት ጫንያለው
10. የሰው ሀብት - ፋኖ ሙሉቀን ግዛቸው
11. ኦርዲናንስ - ፋኖ ልየው ይበልጥ
12. መረጃና ደህንነት ........
13. ጤና ዘርፍ ኃላፊ - ፋኖ አስናቀ ደምሴ
14. ወታደራዊ አስተዳደር - ፋኖ መንበሩ ሹማቸው
15. ቀጠናዊ ትስስር ኃላፊ - ፋኖ አሳምነው በላይነህ
16. የሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ - ኮማንዶ አቡሽ ባንቲ
17. የሕግ ክፍል - ዋና ሳጅን ደምመላሽ
- ፋኖ መኩ ጌትነት ሆነው ተመረጠዋል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም!!!
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

10 Mar, 09:29

1,079

💚💛27 የአገዛዙ ሚኒሻዎች ፋኖን ተቀላቅለዋል‼️

የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች ደጀን ወረዳ አንዱ ሲሆን በደጀን ወረዳ የሚገኜው ዛምበርሃ ብርጌድ በጠላት ሀይል ላይ እየፈፀሙት ያለዉን መጠነ ሰፊ ጥቃት ተከትሎ በደጀን ወረዳ ሰብሸንጎ ቀበሌ ከሚገኘዉ የጠላት ካምፕ ከሞት የተረፋት 27 ሚሊሻዎች የአገዛዙ ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው ዘር ተኮር ጭፍጫፋ በመረዳት መጥፋታቸው ተርጋግጠዋል።ኅ

ከጠፉት ሚሊሻወች ውስጥ የተወሰኑት ዛምበርሃ ብርጌድን የተቀላቀሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ አካባቢያቸዉን ለቀዉ ኮብልለዋል።

ከደጀን ወረዳ ሰብሸንጎ ቀበሌ ካምፕ ውስጥ የአገዛዙ ስርዓት በመክዳት ፋኖን የተቀላቀሉ ሚኒሻዎች መካከል:-
1 ይርመድ አበበ                          
2 ጥበቡ ያለዉ
3 መሰረት በላይ
4 ለወየ ቢተዉ
5 አማረ በልስቲ
6 መሰል ስንሻዉ
7 ሞሱ ጓንቸ
8 ሽሜ ጓዴ
9 ደመቀ አልመዉ
10 ሻንበል አማረ
11 አሸዋ ታደሰ 
12 ንጉሴ ቁሜ
13 ንጉሴ አባትፈንታ
14 ጓንቼ ዳምጤ
15 ደምሴ እጅጉ
16 ትልቅሰዉ አልማዉ
17 ጌትነት ግሩም
18 አንለይ አስናቀ
19 ትልቅ አሻግሬ
20  አንለይ አለሙ
21 ጥላሁን መላኩ
22 አሻግሬ ብዙነህ
23 ብርሌው ሞላ
24 አንለይ ታለማ
25 ብርቁ ዋለ
26 መሰንበት የተባሉ የሚኒሻ አባሎች የአገዛዙ ስረዓት በግደታ አስገድዶ እንዳስገባቸው ለፋኖ አባላቱ በማስረዳት የአማራን ህዝብ አንወጋም በማለት ጠላት ያለበትን ቀጠና ለቀዉ መውጣታቸው ተናግረዋል።

ዛምበርሀ ብርጌድ በደጀን ወረዳ አባይ ማዶ በፌደራል ፖሊስ ላይ  የፈፀሙትን ገድል ይዘን እንመለሳለን።
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

08 Mar, 18:51

1,469

💚💛 እርስ በርስ ተታኮሱ ‼️

2 መከላከያና 3 ሚልሺያ ሲሞቲ በርካቶች ቆስለዋል።

የአብይ አህመድ አሸባሪ ሰራዊት እርስ በርሱ እየተታኮሰ ይገኛል። ሚልሺያ፣አድማብተና እና መከላከያ ሊተማመኑ አልቻሉም። በተለይ ከፋኖ ጋር ስንገጥም የአብይ መከላከያ ስንቆስልም ሆነ ስንሞት ሬሳችንን እየጣለ ፣ቁስለኛንም ሳያነሳ ትቶን ይሄዳል በማለት ሚልሺያና አድማ ብተና ብዙ ጊዜ ቅሬታውን ቢያቀርብም እንደሰው ባለመቆጠራቸው ተኩስ አንስተዋል።

የአብይ የግል መከላከያ ነኝ ባይም በበኩሉ ሚልሺያና አድማብተና መረጃ እየሰጠ በወጣን ቁጥር በደፈጣ እያስመታን ነው ።ስለዚህ ከነሱ ጋር ለመዋጋት ይከብደናል ።አጠገባችንም ማየት እንኳ አንፈልግም ለብቻችን ሆነን ብንሞትም ብንድንም ይሻለናል እያሉ በተለያየ መድረግ እንደገለፁ የሚታወቅ ነው።

ለዚህ ነው በዛሬው እለት ብቻ ሁለት ቦታ እርስ በእርስ ገጥመው የዋሉ። ደብረማርቆስ የጁቤ መገንጠያ እና ሸበል በረንታ መርገጭ እርስ በእርሳቸው በመግጠም 2 መከላከያ እና 3 ሚኒሻ መሸኘቱን እና በርካቶች መቁሰላቸውን አረጋግጠናል።
አላማ የሌለው ጦር ያለው አማራጭ ራሱን ማጥፋት ወይም መክዳት ነው ።
የአብይ አህመድ ጦር ተስፋ ቆርጦ በመፈራረስ እና በመበተን ብሎም እርስ በእርሱ እየተላለቀ ይገኛል።
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

08 Mar, 07:27

1,470

💚💛"ለአማራ ሚኒሻ የምንከፍለው ስሌለን አርሶ አደሩን ማዳበሪያ ፣ጤና መድህንና ፣ የአፈር ግብር በእጥፍ እናስከፍለው"‼️

ፋሽስት አብይ አህመድ

ዛሬ ፋሽስቱ አብይ አህመድ የኦሮሞ ጄኔራሎች እና ባለስልጣናት ሰብስቦ ፦

"ተወደደም ተጠላም አማራን በሁሉም መንገድ ማዳከም አለብን ። ታላቋን ኦሮሚያ ለመመስረት አማራን ማዳከም ቁጥር አንድ ስራችን ነው። አማራን ለማዳከም ብዙ አማራጮችን ነድፈን ተንቀሳቅሰን አንዱ ብቻ ሚስጥር ሾልኮ ወጥቶብን ለመከራና ለውርደት ተዳርገናል ። እሱም ትጥቁን አስፈትተን ዳግም አማራ እንዳይኖር አድርገን ማጥፋት ነበር ግቡን አልመታልንም።"

ለማስታወስ!
👇👇👇👇👇👇
የኦነግ ብልፅግና ሴራ በአማራ ህዝብ ላይ ከብዙዎቹ በጥቂቱ ፦

1ኛ. ለኦነግ ብልፅግና ታዛዥ የሆኑ ባለስልጣናትን መመደብና አፈንጋጭ ካለ እየለየን ማጥፋት(የእነ አምባቸው ፣ ምግባሩ፣ ጄ/ አሳምነው ፅጌ ሞት ምክንያት ይኸ ነው) ለእኛ ታዛዥ የሆኑትን ብቻ እንሾማለን።

2ኛ. አማራን ወደ ብዙ ማንነት ለመክፈል ከፍተኛ በጀት መድበን ሰፊ ስራ እንዲሰሩ ማገዝ(አገው ሸንጎ፣ቅማንት፣ወሎ ክልል ነው ብለን ከሀገሪቱ በጀት በላይ መድበን እየሰራን ነው)

3ኛ. ስጋት የሆኑ የነቁ አማራን እየተከታተሉ ዳግም እንዳይታዩ ማጥፋት (እነ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች እና የነቁ ፖለቲከኞች እስር ምክንያቱ ይኸ ነው)

4ኛ. የጫካው ክንፍ ብለን የመደብነው ሸኔ በኦሮሚያ ምድር የሚኖረውን አማራ ጠራርጎ ማስወጣት(ከህፃን እስከ አዛውንት በጅምላ መጨፍጨፍ ፣ማፈናቀል ፣ንብረቱን መዝረፍና ማውደም )

5ኛ. በአዲስ አበባ አማራ የሚባል ዳግም ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ማድረግና ቀድሞ የሚኖረውንም በኮሊደር ልማት፣በህገ ወጥ ስም ቤቱን በማፍረስ፣ የመንግስት ሰራተኛውን በሪፎርም ሰበብ ቀስ እያረጉ ማስወጣት ፣ በፀጥታ ሰበብ የአማራን ወጣት እያዋከቡ ማሠር፣ መሠወሰርና ማስወጣት በሚል ምን ያህል ግፍና በደል በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ነው።(ኮሊደር ልማት እያለ የሚያሽቃብጠው የሴራውን ምንጭ ካለመረዳት ነው) በኮሊደር ልማት ከተነሱ በኋላ ቦታው እየታጠረ ለማን እየተሰጠ እንደሆነ የሚያውቅ ማንም የለም። በልማት ስም ንፁህ ኦሮሞ ለሆኑ ባለሀብቶች እየተሰጠ መሆኑን ስንቶቻችን ነን የምናውቀው ? በሸገር ከተማ በሚል ስንት ሰው ነው ቤቱ በላዪ ላይ ፈርሶ የተፈናቀለው ? ለዚያውም አማራ በማንነቱ እየተለየ ? ቤት እንኳን ተከራይቶ እንዳይኖር አልተባረሩም ።

6ኛ. በየትኛውም መንገድ አማራን በኢኮኖሚም በጦርነትም ማዳከም በዘንድሮ አመትም ማዳበሪያ በሰፊው የሚጠቀመው አማራ ስለሆነ የማዳበሪያውን ዋጋ በእጥፍ ጨምረን በማስከፈል የምናገኘውን ብር ለጦርነቱ ማስኬጃ እንዲውል እናደርጋለን ።

7ኛ. አማራ ከወያኔ ጋር ያለውን ልዩነት የበለጠ እንዲሰፋ በማድረግ ለወያኔ ድጋፍ በማድረግ  ስር የሰደደ ቂምና ቁርሾ እንዲኖራቸው በማድረግ ከጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳይወጣ ማድረግ ።

8ኛ. ትምህርት ቤቶችንና መሰረተ ልማትን ፋኖ ነው በሚል በድሮን በማውደም ህዝቡን ማማረር

9ኛ. አማራ አማራ የሚሸቱ ማንኛውንም ስራ ከቅርስ ጀምሮ ኦሮሞ ኦሮሞ እንዲሸት አድርገነዋል ። የሚኒሊክ እና የአፄ ቴዎድሮስ ፎቶ ያለበት ቲሸርት ጭምር እንዳይለበስና ልሙጥ ባንዲራ ከእናቶች እና ህፃናት ቀሚስና ልብስ ላይ እንዲነሳ አድርገነዋል ።

ሌሎችም ብዙ ተቆጥረው የማያልቁ ግፍና በደል በአማራ ህዝብ ተፈፅሟል እየተፈፀመም ነው።

አማራ ያሸንፋል
የኦነግ ብልጽግና ሴራ እያንዳንዱን ቆጥረን እንመልሳለን ።
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

07 Mar, 18:36

1,463

💚💛የጠላት ኃይል አከርካሪውን ተመቷል‼️

የካቲት 28/2017 ዓ.ም

መነሻውን ግንደወይንና ደብረወርቅ ያደረገው ጥምር የጠላት ኃይል ኮሶዝራ መዳረሻውን ለማድረግ ቢንቀሳቀስም በአይበገሬዎቹ የጎንቻና የእናርጅ አናብስቶች ከፍተኛ ጥቃት ተፈፅሞበታል።

በገንቦሬ አቅጣጫና ፈለገብርሀን በርካታ ሰራዊቱን በማስጠጋት ወፊትን አቋርጦ ብዙም ሳይራመድ ኮርች ተራራ ላይ ያልጠበቀው ጠንካራ ውጊያ ገጥሞታል።

ለማጥቃት በራሱ ተነሳሽነት ስምሪት የወሰደው የጠላት ኃይል የአረንዛው ጎንቻ ብርጌድና የሶማ ብርጌድ ባደረጉት የጥምረት ውጊያ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ በማድረግ አስክሬኑን አሸክመው ሲያሯሩጡት ውለዋል።

የ9ኛ እና 8ኛ ክ/ጦር ብርጌዶች በአደረጉት አስደናቂ ኦፕሬሽን ጠላት የሚደርስበትን ምት መቋቋም አቅቶት ወደመጣበት ምሽጉ ተመልሷል በዚህም የጠላትን እቅድ በማክሸፍ ወንድማማቾቹ የበላይነቱን ወስደዋል።

በተመሳሳይ ከቀናት በፊት በአርብ ገበያ በተደረገ አውደ ውጊያ በአባይ ሸለቆ ብርጌድና አረንዛው ጎንቻ ብርጌድ በጠላት ላይ ባደረሰው ኪሳ ጠላት ጫካ ውስጥ ቅጠል አልብሶ የደበቃቸውን የራሱን አስክሬን ከህብረተሰቡ  ጋር በመተባበር ለሰው ልጅ የሚገባውን ክብር በማሰብ የህዝባችንን ክብርና የሞራል ልዕልና ለመጠበቅ የጠላት አስክሬንን በክብር አሳርፈናል(ቀብረናል)።

አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ !
የአማራ ፋኖ በጎጃም የሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ባየ ደስታ መኮነን
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

07 Mar, 18:34

1,399

ከአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ (፮) ክ/ጦር   የተሰጠ የማስጠንቀቂያ መልዕክት !
*

መንግ
ስት ነኝ ባዩ የአብይ አህመድ  ወራሪና ወንበዴ ቡድን አሁን የደረሰበትን ሽንፈት እና ያለበትን የኢኮኖሚ ውድቀት ለመሸፈን ሲል በህዝባችን ላይ የተለያዩ የክፍያ መስፈርቶችን በማውጣት ህዝባችንን እየበዘበዘ ይገኛል።

በተለይም ደግሞ ከዚህ ቀደም ከህዝብ ላይ ይሰበስብ የነበረውን ግብር ማግኘትና ማስከፈል ስላልቻለ ብሎም በተለያዩ ስያሜዎች የሚሰበስበውን ገንዘብ በፈለገው መንገድ ማግኘት ስላልቻለ አማራጮችን ተጠቅሞ ካዘናውን መሙላት ይፈልጋል።

ለዚህ ዋነኛ ማሳያ ሆነው ለመተግበር እንቅስቃሴ እያደረጉት ያሉት ደግሞ
ጥቁር አስፓልት ኬላ፣ማዳበሪያ፣ጤና መድን እና መታወቂያ ናቸው።በእነዚህ ላይ ዋጋ ከመጠን በላይ በመጨመር ከህብረተሰቡ ገንዘብ መሰብሰብ አስቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
መንግስት አሁን ላይ መሸነፉን አውቋል።
ይህን ወዳጅም ጠላትም ጠንቅቆ ያውቀዋል።በዚህ የተነሳ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አስፓልት ላይ በመቅረጥ፣በማዳበሪያ ላይ ከፍተኛ ዋጋ በመጣል፣ጤና መድንን በመሰብሰብ፣በመታወቂያ ምክኛት ገንዘብ በመሰብሰብ ህዝብን እያማረረና እያሰቃዬ ይገኛል።

ተስፋ የቆረጠው የአብይ አህመድ የደም ግብር አስቀጣይ ካድሬ ከህብረተሰባችን ህጋዊ በሚመስል መንገድም በዘረፋም ለነገ መሸሻ ይሆናቸው ዘንድ ገንዘብ እየሰበሰቡ መሆኑን በአለን ተከታታይ እይታ ገምግመናል።በመሆኑም ወቅታዊውን የህዝባችን ቁመና እና የጠላትን ሁኔታ በማገማገም የሚከተለውን የክልከላ መግለጫ እንደ ክፍለ ጦር አውጥተናል።

1.  ከዛሬ የካቲት 28/06/2017ዓም ጀምሮ በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የጤና መድን ክፍያ በየትኛውም ቀጠና ማለትም የፋኖ ሐይል በተቆጣጠራቸው ቀበሌዎች ብሎም የጠላት ኃይል በተቆጣጠራቸው ቦታዎች የሚኖር ሁሉ ምንም አይነት ክፍያ መክፈል የለበትም።ሲያስከፍል የተገኘ ብሎም ሲከፍል በተገኘ የትኛውም አካል ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።

2.ከዛሬ የካቲት 28/06/2017ዓም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች ብሎም ቀበሌዎች ማዳበሪያ በተለመደው ዩኒየን ወይም ህብረት ስራ ቦታዎች የተጠራቀመን ማዳበሪያ በትክክለኛው የዋጋ ተመን መግዛት ይቻላል።ከዛ ውጭ ጠላት ባለበት ቦታ ሒዶ መግዛት ፈፅሞ አይቻልም።አሁን ያለው የዋጋ ተመን ሆን ተብሎ የተለያዩ ክፍያዎች ተጨምረውበት ህዝባችንን ለመበዝበዝ የተደረገ ስለሆነ  በወጣው የዋጋ ተመን መግዛት አይቻልም።በዚህ ዋጋ ሲሸጥ የተገኘ ብሎም ሲገዛ የተገኘ ሻጩም ገዥውም ይወረሳል።ህጋዊ እርምጃም የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።

የማዳበሪያ አቅርቦትን በተመለከተ የአማራ ፋኖ በጎጃም አዲስ መመሪያ እስከሚያወጣ ድረስ በየትኛውም ቦታ ህዝባችን ማዳበሪያ ወዳለበት ቦታ ሔዶ ከመጠን በላይ በተተመነ ዋጋ መግዛት አይችልም።

3, ክፍለ ጦራችን በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ከጤና፣ከቴሌ፣ከባንክ፣ከውሃ፣ከመብራት፣ከመንገድ ስራዎች፣ ከዩኒየን፣ከህብረት ስራ ማህበር ውጭ ያሉ የትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት ከዛሬ 28/06/2017ዓም ጀምሮ መክፈት ብሎም መስራት የማይቻል መሆኑን እንገልፃለን።ይህን ተላልፎ በሚገኝ የትኛውም ዓይነት የመንግስት ሰራተኛ ላይ በስራ ቦታው ላይ ቢሮ ገብቶ ሲሰራ ቢገኝ ለሚወሰደው ርምጃ  ሀላፊነቱን ራሱ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን::...........

[አዲስ ትውልድ : አዲስ አስተሳሰብ  :አዲስ ተስፋ ]

የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ የፍታሔ ንጉሴ /6ኛ ክፍለጦር!

የካቲት 28/2017 ዓ.ም
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

06 Mar, 12:29

1,651

💚💛ሰበር የድል ዜና‼️

በአማራ ፋኖ በጎጃም የተደመሰሱ ኮሎኔሎች ስምንት ደርሰዋል ።
አራት ብርጋዴየር ጀኔራሎች ተደምስሰዋል ። ዋና ዋናውን ካፀዳነው መንጋውን በከበባ ለመዋጥ ሰዓታት አይወስድብንም ።
ከአካባቢያችን ጭኖ የሚያስወጣው የሜካናይዝድ መሳሪያ አይኖርም ። አድማ ብተና እና ሚሊሺያ ጊዜው ሲደርስ ፋኖን ተቀላቅሎ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ጉዞ አካል ነው።

አዳዲስ ሰልጣኝ አማራዎችም ፋኖ በመሆናቸው ተመርቀው እንደታጠቁ እንደተነጋገርነው ያደርጋሉ።

ጠብ መንጃውን አብይ በሐገሪቱ በጀት ይገዛል ። እኛ ደግሞ በጥበባችን እንታጠቀዋለን።ምክንያቱም ሐገር የጋራ ነው።😎

በነገራችን ላይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አማራ ተደራጅቶ ዘመን አመጣሽ መሳሪያ የታጠቀበት ታሪካዊ አጋጣሚ ይህ ዘመን ነው።

ገና ገና ሚሊዮኖች ተደራጅተው ፣ አሰልጥነው ዘመናዊ መሳሪያ ይታጠቃሉ። ትውልዱን ዘመናዊ መሳሪያ ከጠራ የብሔርተኝነት ሪዮት ዓለም ጋር አቀናጅተን የማስታጠቅ ስራችንን ማስቆም አይቻልም ።

ስንዴ ዘርቶ ሙጃ ለበቀለበት ህዝብ ፤ የእጁን ለተቀማ ማህበረሰብ ፤ ደጁን ለተወረሰው አማራ መዳኛው ነፍጥ ነው።

አማራ አሸናፊ እንዲሆን ምንም እናደርጋለን !!

አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
(የአማራ ፋኖ በጎጃም )
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

03 Mar, 18:13

2,499

💚💛የፍርድ ቤት ውሎ‼️

ዛሬ የካቲት 24/2017 ዓ/ም በፌደራል ከፍተኛው ፍርድቤት በዋለው ችሎት በአማራነታቸው ታፍነው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከሚገኙ የህሌና እስረኞች መካከል አስማረ  ወረቀት እና ሰለሞን ተፈራ ቀርበዋል።

1 በአስማረ ወረቀት መዝገብ ለዛሬ የተቀጠረው ተከሳሹ አማራ ፋኖ በሚል የፌስቡክ ገፅ መረጃዎች አሰራጭተሐል ለዚህም ማሳያው ከፌስቡኩ ታይም ላይን ላይ የተገኘው የስልክ ቁጥር ያንተ ነው የሚል ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል ትዛዝ በመስጠቱ የተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮች  ጥር 30 በዋለው ችሎት የተከሳሹ ስልክ ከነ ሲም ካርዱ የካቲት መጨረሻ ወይም መጋቢት መጀመሪያ ጠፍቶበት ሲም ካርዱን ከሳምንት በኃላ መልሶ ያወጣው መሆኑን የመሰከሩ ሲሆን በዚህም መሰረት ተከሳሹ ከቴሌ ሲም ካርዱ የወጣበት ቀን እንዲገለፅለት የጠየቀ በመሆኑ ቴሌ ዛሬ በላከው መረጃ የተከሳሹ ስልክ ቁጥር መጋቢት 11/2016 ዓ/ም የወጣ መሆኑን ገልፃል ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኝ ከሳሽ አቃቤ ህግ እና የተከሳሽ ጠበቃዎች የክርክር ማቆሚያ በ10 ቀናት ውስጥ እንዲያስገቡ ትዛዝ የሰጠ ሲሆን ለመዘገቡ ውሳኔ ደግሞ ለመጋቢት 26/2017 ዓ/ም ተቀጥሯል።

2 የሰለሞን ተፈራ መዝገብ ለዛሬ የተቀጠረው የተከሳሹን የምነት ክህደት ቃል ለማድመጥ ሲሆን ተከሳሽ ወንጀሉን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም በማለት የምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ከሳሽ አቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ የሰውም የሰነድም ማስረጃ አለኝ ያለ በመሆኑ የከሳሽን የሰው ምስክሮች ለመስማት ለመጋቢት 26/2017 ዓ/ም የተቀጠረ ሲሆን ከሳሽ የሚያቀርባቸው የሰው ምስክሮች ብዛት 4 መሆኑን እና አድራሻቸውም ቤንሻንጉል ጉምዝ መሆኑን ገልጿል።