አቡ ሱሀይል @hamidabuhamid Channel on Telegram

አቡ ሱሀይል

@hamidabuhamid


ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢِ
"ﺍﻗْﺮَﺃْ ﺑِﺎﺳْﻢِ ﺭَﺑِّﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺧَﻠَﻖَ"
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታ ስም"
አል ዐለቅ ምእራፍ/1

በዚህ ገፅ ላይ የተለያዩ ኢስላማዊ መልእክቶችና፣በተለያየ ዘርፍ የሚሰጡ ት/ቶችን በድምፅና በቪዲዮ ያገኙበታል።

አቡ ሱሀይል (Amharic)

አቡ ሱሀይል ለሁሉም ኢስላማዊ መልእክቶች እና የሚሰጡ ት/ቶችን ማሰብህን በዚህ አዝምሮ እንዲህ ሲል የገለጸው ኢስላም መደብ የሚለዋዋጭ ለማግኘት ከመጀመሪያ በላይ ያገኙበታል። አንዲሆን በፊታው የቴሌግራም መረጃዎችን እና ቪዲዮዎችን ከድምፅ እና ቪዲዮ በመላክ አቅምን ይፈጠራል። እንደምታሳክ ነው? አቡ ሱሀይል ለሁሉም ኢስላማዊ መልእክቶች እና የሚሰጡ ት/ቶችን ማሰብህን ለማግኘት ችግር እንድሚል ይጠቀሙ።

አቡ ሱሀይል

22 Nov, 20:56


የኡማው ሊቅ ኢብኑ ዐባ፟ስ(ረ.ዐ)

“ ጨው በውሃ ውስጥ እንደሚሟሟው፣
የሙእሚን ልብም የሚሟሟበት ዘመን ይመጣል !
በማለት ተናገሩ
¶ ለምን? ተብለው ሲጠየቁ
«መለወጥ የማይችላቸውን
መጥፎ ተግባራት ሲመለከት » በማለት መለሱለት።
📚 አል–ዑቁوባት/46

አቡ ሱሀይል

21 Nov, 18:10


#ጉዳዮችህን
ጉዳዮች እርሱ ዘንድ ወደማይገዝፉበት
ከፍ አድርጋቸው !
📚ሒልየቱል–አውሊያእ 7/7
✒️ሱፍያን አል–ሰውሪይ(ረ.ዐ)

አቡ ሱሀይል

19 Nov, 18:05


# ያለቦታው አጥባቂዎች ጠፉ !

ሚዛናዊውን ሐይማኖት ከልክ በላይ ስታጠብቀው፣ሐቅን በአንተና በሸይኾችህ አረዳድ ብቻ ወስነህ ስታጠበው፣መንፈሳዊነትን ከአስኳሉ ነጥለህ እላያዊ አምልኮ ብቻ ስታስመስለው …
የሚሰጥህ ውጤት ጥፋትና ብልሹነት ነው!
እየኾነ ያለውም ይህ ነው!
#አዋጅ! ከልክ በላይ አጥባቂዎች ጠፉ፣ከልክ በላይ አጥባቂዎች ጠፉ፣ከልክ በላይ አጥባቂዎች ጠፉ !
… ረሱለላህ (صلىٰ الله عليه وسلم)

# ያ ሙቀሊ፟በል–ቁሉቢ ሰቢ፟ት ቁሉበና ዐላ ዲኒክ
ወነጂ፟ና ሚነል–ፊተን 🤲
T.me/hamidabuhamid

አቡ ሱሀይል

16 Nov, 18:09


# ሰላማዊ ህይወት
አንድ ሰው ወደ ወህብ ቢን ሙነቢህ(ረ.ዐ) ዘንድ በመምጣት
“ነፍሴ ከሰዎች እንድ(ገ)ነጠል አወጋችኝ” ይላቸዋል
እርሰዎም … ተው አታድርገው!
ላንተም ሰው የግድ ያስፈልጉሃል፣ለሰዎችም አንተ የግድ ታስፈልጋቸዋለህ፤እነሱ ካንተ ጉዳይ ይኖራቸዋል፣አንተም ከነርሱ ይኖርሃልና አታድርገው …
ነገር ግን ስትቀላቀላቸው ሰምቶ አልሰሜ፣አይቶ አላዬ፣ዝምተኛ ተናጋሪ ኹን ” በማለት መለሱለት።
____
ሲየር (4/440)
# የጊዜው ዑዝላህ (መነጠል፣መገንጠል)ይህ ነው፤ነገር ግን በየቀኑም ኾነ በየ ሳምንቱ ራስን ከአላህ ጋር ማግለል(ኸልዋ)ፈፅሞ መቅረት የሌለበት የነፍስ መገምገሚያና ማበልፀጊያ፣ወደ ከፍታዋ ማረ፟ጊያ መሰላል ነው።
ጫጫታና ጋጋታ በበዛበት፣ውጥረትና ኹከት በሞላበት፣እውነተኛ ማንነትን ሸፍኖ፣ያልኾኑትን ማስመሰል በበዛበት ተጨባጭ፣የውስጡን ጥሪ እንደሚያዳምጥ፣የነፍሱን ሰላም እንደሚያፍለላግ ሰው ዓቅለኛ የለም! !!
____
T.me/hamidabuhamid

አቡ ሱሀይል

13 Nov, 19:20


“ ሁለቴ በሽንት ማለፊያ የሚያልፍ ፍጡር
ኩራተኛ ሲኾን ይደንቃል !”
#አሕነፍ ቢን ቀይስ (ረ.ዐ)

አቡ ሱሀይል

09 Nov, 18:53


https://t.me/DARULHIJRATEYNISLAMICCOLLEGE?livestream=d44e4732d4ef883847

አቡ ሱሀይል

09 Nov, 18:53


🔮የዳሩል ሒጅራተይን ኢስላማዊ ኮሌጅ የዒልም መጅሊስ የኪታብ ደርስ እንድትገኙ ይጋብዛቹዋል📘

📗የሸይኽ ዐብዱል ፈታሕ አቡ ጉዳህ ሰፈሐት ሚን ሰብሪል ዑለማእ

             11ኛ መጅሊስ

🟢በኡስታዝ ዐ/ሐሚድ (አቡ ሱሀይል)  ሸርህና ተዕሊቅ

ዛሬ ቅዳሜ ማታ ከምሽቱ 4:00_5:00

ደርሱ በቀጥታ የሚተላለፈው በዳሩል ሒጅራተይን ኢስላማዊ ኮሌጅ የቴሌግራም ቻናል…
https://t.me/DARULHIJRATEYNISLAMICCOLLEGE

📝ዑለማዎች ዒልምን ለመቅሰም የከፈሉትን መሰዋትነት አብረን እንመልከት

አቡ ሱሀይል

09 Nov, 14:21


⛔️<የሰው ዓይን እውነት ነው፥ግመልን በድስት፣ሰውየውን በመቃብር ውስጥ ያስገባዋል> ረሱለላህ ﷺ

  አውቀንም ኾነ ሳናውቅ ለሰዎች ህመምና ስቃይ ምክንያት እንዳንኾን እንጠንቀቅ፤በሌሎች ላይ መልካምና ውብ ነገር ስንመለከት ዝም ብሎ ከመደነቅና ከመደመም ይልቅ ማሻአላህ በማለት እንባርካቸው።

እራሳችንንም እንደው ቢያንስ በጠዋትና በማታ ውዳሴዎች እንጠብቅ፤ያለንን ነገር ኹላ ወደ አደባባይ ይዘን አንውጣ፤እዩኝ እዩኝ ማለት መጨረሻው ደብቁኝ ደብቁኝን ያመጣል።

ይህ ከሰሞኑ በሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያገኘሁት ወጣት አይመን አል ዐሊይ ይባላል፤ የጆርዳን የውበት ንጉስ በሚለው የሚዲያ መጠሪያው ይታወቃል፥በሚያነሳቸው ማህበራዊ ጉዳይ contentoch ብዙ ተከታዮችንም አፍርቷል፤አኹን ላይ ግን በምታዩት መልኩ በአንድ አመት ልዩነት ውስጥ በሆስፒታል አልጋ ላይ ተኝቶ በጠና ህመም እየተሰቃየ ይገኛል።

# አላህ ሙሉ ዓፊያውን ይመልስለት 🤲

አቡ ሱሀይል

06 Nov, 20:03


«ስንት አለ
ሳያውቀው በፀጋዎች እየተዘገየ
በመሀይማን ሙገሳ እየተፈተነ
አላህ ጉዳዩን ስላሳካለትና፣ነውሩን ስለሸፈነለት እየተሸወደ ያለ!

እነዚህ ሶስቱ ብዙኃኑ ዘንድ የደስታና የስኬት ምልክት ተደረገዋል !
የእውቀታቸው መዳረሻም ይህ ኾኗል»

📚መዳሪጁ–ሣ፟ሊኪን 1/518

አቡ ሱሀይል

05 Nov, 18:23


# በፈተና ወረቀት የታሸገ ፀጋ
لكلّ شيءٍ إذا فارقته عِوضٌ
وليس للهِ إن فارقت من عِوضِ
ኹሉን ነገር ስትለየው ተለዋጭ አለው
ስትለየው ተተኪ የሌለው አላህ ብቻ ነው !
ኢብኑ ዐረቢይ(ረ.ዐ)
____
ፈተናዎች በውስጣቸው ካጨቋቸው እጅግ ብዙ ስጦታዎች ውስጥ አንዱና ትልቁ ፀጋ
ከአላህ በቀር …ማንም ቢርቅህ፣ማንንም ብታጣ፣ዋይ ማትልበትን ብርታት ይስታጥቁሃል !
# አልሐምዱ ሊላህ

አቡ ሱሀይል

03 Nov, 17:54


ኢብኑ ዐሳኪር (ረ.ዐ) ከአንድ የሰዪድ ሺብሊይ (ረ.ዐ) ባልደረቦች አንስተው በ‹‹ታሪኽ›› መጽሐፋቸው ላይ እንደዘገቡት፤ሺብሊይን (ረ.ዐ) ከሕልፈታቸው በኋላ በህልሙ ተመለከታቸውና፣አላህ ባንተ ላይ ምን ፈፀመ? ሲል ይጠይቃቸዋል
ሺብሊም ፡- ከፊቱ አስቆመኝና፡- አቡ በከር ሆይ! ለምን ይቅር እንዳልኩህ ታውቃለህን?አለኝ

እኔም፡- በጽድቅ ተግባራቶቼ፤አልኩ
እርሱም፡- አይደለም አለኝ
መልሼ ፡ በአምልኮዬ ቅን በመኾኔ፤ አልኩ
እርሱም ፡- አይደለም አለኝ
አኹንም ፡- በሐጅ፣በጾምና በሰላቴ ነው፤አልኩ
እርሱም አይ! ለዛም አይደለም ይቅር ያልኩህ አለኝ
ቀጥዬ ፡ ወደ ደጋግ ባሮች በመሰደዴና እና እውቀትን ፍለጋ ጉዞዬን በማዘውተሬ ። አልኩ
እርሱም፡- አይደለም አለኝ!

በመጨረሻም ፡- ጌታዬ ሆይ… በእነሱ አማካኝነት ይቅር እንደምትለኝ እና እንደምትምርልኝ አስቤ አጥብቄ የያዝኳቸው የነበሩት መዳኛዎች እነዚህ ናቸው፤አልኩ

እርሱም፡- ይቅር ያልኩህ በእነዚህ ኹላ ምክንያት አይደለም ። አለኝ

አምላኬ ሆይ ታዲያ በምን ነው ? ስል ጠየቅኩ

እርሱም :– በባጝዳድ ጎዳናዎች ላይ ስትሄድ፣ ብርድ አድክሟት፣ከግድግዳ ጥግ ወደ ሌላ ግድግዳ ጥግ ስትጠጋ የነበረችን ድመት ተመልክተህ፣ከዛም አዝነህላት ለብሰህ በነበረው የቆዳ ልብስ ውስጥ ያስገባሃትን ታስታውሳለህን? አለኝ
እኔም፡- አዎን አልኩ
እሱም “ለዚያች ድመት በማዘንህ ነው፣እኔም ያዘንኩልህ ” አለኝ ።
_
T.me/hamidabuhamid

አቡ ሱሀይል

02 Nov, 18:52


ባል ለስራ ጉዳይ ወጣ ይላል
ሚስትም አመሻሽ ላይ "ያላንተ ቤቱ ጨለማ ነው” ብላ መልእክት ትሰድለታለች ❤️

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በዃላ በሯ ተንኳኳ
ሚስት በሩን ስትከፍት
ወንድሟ ፋኖስ ይዞ ቆሟል 😳

ምነው በዚ ምሽት? ሰትለው
ባልሽ ደውሎ መብራት እንደጠፋ ነግሮኝ ነው! 😜🙈
# አላህ ያግባባን ማለት ይሄኔ ነው

አቡ ሱሀይል

02 Nov, 17:39


አቡል–ሑይሰን አል–ኑሪይ (ረ.ዐ) ስለ ሱፊዮች ሥነ ምግባር ተጠይቀው፣እንዲህ በማለት መለሱ
“ሌሎችን ማስደሰት፣አዛቸውን መሸከም ”።

አቡ ሱሀይል

31 Oct, 02:51


በዙሪያህ ያለው ውድመት ኹሉ አይጎዳህም
ዋናው ነገር ውድመቱ ልብህ ጋር አይድረስ !

አቡ ሱሀይል

28 Oct, 03:24


አቡ ሁረይራህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፤አንድ ሰው ወደ ረሱለላህ በመምጣት
“ አንቱ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ኾይ! እከሊት እኮ … በማለት ስለ ሰላቷ፣ፆሟና ምፅዋቷ ጠቀሰ … ነገር ግን ጎረቤቶቿን በምላሷ ትተናኮላለች ” አላቸው …

ረሱለላህም “እርሷ የእሳት ናት!” በማለት ተናገሩ !
_ አሕመድ ዘግበውታል
___
ሐይማኖተኝነትን በውስን ተግባራት ብቻ ለገደበ፣የአምልኳዊ ተግባራትን ፍሬ ለዘነጋ ጥልቅ መልእክትን ያዘለ ሐዲስ
ስንቱ ነው ሰላቱን፣ፆሙን፣ሐጁን ቀጥ አድርጎ እየፈፀመ…ከጎረቤት በላይ የሚቀርቡትን አካላት አዛእ የሚያደርግ !!
_<<<<>>>_
# ኢላሂ መረዳቱን ስጠን
በድካሞቻችን ብኩን አታድርገን !!!

t.me/hamidabuhamid

አቡ ሱሀይል

25 Oct, 07:35


“ስስት(ቋጣሪነት)እና እኩይ ሥነ ምግባር
በአንድ አማኝ ውስጥ አይሰበሰቡም !!!”
#ረሱለላህ ﷺ

አቡ ሱሀይል

19 Oct, 10:10


# በዳውድ ጥበባዊ ንግግሮች ውስጥ ተከታዩ ይገኝበታል

አንድ ዐቅለኛ(አስተዋይ)ሰው አራት ወቅቶችን ቸል ሊል አይገባውም
እነሱም:–
1- ነፍሱን ከጌታው ጋር የሚያገልበት ወቅት
2- ራሱን የሚገመግምበት ወቅት
3- ነውሩን ከሚነግሩት እውነተኛ ወንድሞቹ ጋር የሚቀማመጥበት ወቅት
4- ነፍሱን የተፈቀደ ኾኖ ከሚያምራት ተድላ የሚያርቅበት ወቅት ናቸው።
ይህ ወቅት ለተቀሩት ወቅቶች የበለጠ የሚያግዘውና፣ልቡንም የሚያሳርፍበት ወቅት ነው።

አቡ ሱሀይል

18 Oct, 07:00


‏﷽
۞ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِي  يَاأيُّهَاالَّذِينَ آمَنُواصَلُّواعَلَيْهِ  وَسَلِّمُواتَسْليما ۞

اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ  وَبَارِكْ عَلَى سَيِّدِنا
ونبيّنا םבםב رسول ٱɑɺɺ."ﷺ".

اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا ونبينا محمد ﷺ وعلى آله وصحبه وسلم تسليماً كثيراً ﷺ

2,443

subscribers

760

photos

55

videos