የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት ካውንስል አባላት የስትራቴጂና የግብይት ዓቅምን ለማሳደግ ያለመ የሁለት ቀናት ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናዉ በስኬታማ መንገድ እየቀጠለ ያለዉን የኮርፖሬሽኑን የለዉጥ ጉዞ የበለጠ ለማጠናከር እንዲሁም የቢዝነስ ስትራቴጂያዊ ጉዞ ቀጣይ የትኩረት ማዕከል ላይ ያተኮረ ሲሆን በዋነኛነት ቢዝነስ ስትራቴጂ፣ ማርኬቲንግ ስትራቴጂ፣ ቢዝነስ እና ፋይናንሻል ሞዴል በሚል ርዕስ ተከፋፍሎ ተሰቷል።
የኮርፖሬሽኑን ሀብቶች በመለየት ለዘላቂ ውድድር እና ትርፋማነት አቅምን እንዴት እናሳድግ? ጠንካራ ጎኑን እና ክፍተቶችን በመለየት ክፍተቶችን ከችሎታና ከብቃት ጋር በማጣመር በምን መንገድ እንቅረፍ ? በሚሉ ጥያቄዎች ላይ ሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጓል።
ስልጠናዉ በቀጣይም እያንዳንዱ የስራ ክፍል ስትራቴጂያዊ የግብይት ዓቅምን በማሳደግ የኮርፖሬሽኑን ስኬታማ ጉዞ በይበልጥ ለማስቀጠል እንደሚረዳ የስልጠናዉ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
የኮርፖሬሽኑን የለዉጥ ጉዞ የበለጠ ለማጠናከር የቢዝነስ እና የማርኬቲንግ ስትራቴጂያዊ ጉዞ ወሳኝነት ላይ አፅንኦት በመስጠት ስልጠናዉ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።