Ethiopian Surveyors @ethiopiansurveyor Channel on Telegram

Ethiopian Surveyors

@ethiopiansurveyor


Ethiopian Surveyors

Ethiopian Surveyors (English)

Are you interested in the world of surveying and mapping in Ethiopia? Look no further than the Ethiopian Surveyors Telegram channel! With the username @ethiopiansurveyor, this channel is dedicated to bringing together surveyors, cartographers, and mapping enthusiasts from Ethiopia and beyond. Whether you are a professional surveyor looking to stay updated on the latest industry news and trends or a newcomer interested in learning more about the field, Ethiopian Surveyors is the perfect place for you. Get access to valuable resources, educational materials, job opportunities, and networking events all in one convenient location. Join our community today and connect with like-minded individuals who share your passion for surveying and mapping in Ethiopia. Stay informed, stay connected, and stay inspired with Ethiopian Surveyors!

Ethiopian Surveyors

20 Nov, 13:41


Call for a virtual expert meeting
GIS society of Ethiopia.


“GIS Community for location solutions and mapping your success“

Date: - Saturday, Nov 23, 2024 (9:00am – 6:00am)

Link: - https://meet.google.com/ivz-hvdj-bdc
Cc: - https://t.me/Geo_opp_Eth

Ethiopian Surveyors

08 Nov, 15:02


ትምህርት በቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በማታ ፕሮግራም ትምርት መከታተል ለምትፈልጉ
_______
Cc: Ethiopian Surveying Professionals  Association

Ethiopian Surveyors

08 Nov, 08:33


የስራ ማስታወቂያ !
______
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Ethiopian Surveyors

15 Oct, 18:17


🔊 የስራ ማስታወቂያ ! 🔊

🔗 Quantity Surveyor
🔗 GIS Data Analysis

📃 ምዝገባ Online
ለመመዝገብ ታች ላይ በተቀመጠው የቴሌግራም ግሩፕ ገብተው Vacancy ላይ ሊንኩን ያገኙታል!
የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀሉ (Geospatial Ethiopia )
https://t.me/Geo_opp_Eth

Ethiopian Surveyors

30 Sep, 04:55


ለቅዳሜ እና እሁድ (Weekend) ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Ethiopian Surveyors

09 Sep, 17:00


Vacancy
_______
Oromia Construction Corporation

0 years experience

Civil Engineer & COTM

Ethiopian Surveyors

25 Jul, 12:52


ለሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች

Remote Sensing እንዲሁም በGeodesy መማር ለምትፈልጉ!

https://t.me/Geo_opp_Eth/5

Ethiopian Surveyors

16 Jul, 13:54


🔊 የስራ ማስታወቂያ ! 🔊

🔗 በ ጀማሪ የቅየሳ ባለሙያ
🔗 ዲፕሎማ እና ዲግሪ
🔗 ምዝገባ Online
ለመመዝገብ ታች ላይ በተቀመጠው የቴሌግራም ግሩፕ ገብተው Vacancy ላይ ሊንኩን ያገኙታል!
የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀሉ (Geospatial Ethiopia )

https://t.me/Geo_opp_Eth

Ethiopian Surveyors

05 Jul, 06:44


ሰላም ቤተሰቦቻችን ከዚህ ቀደም በጣም ጠቃሚ የሆነ Geo-ETH የተባለ Youtube ቻናል አስተዋውቀናችኋል!
------------------------------------------
በዘርፉ ብዙ እውቀት እና ልምድ ባላቸው በዶ/ር አንድነት አሻግሬ የሚዘጋጅ በተለያዪ ርዕሶች ላይ ያተኮረው ይህ የYoutube ቻናል ArcGIS Pro ሶፍትዌር በአማርኛ እና ቀለል ባለ መንገድ አጋርተውናል::

ከታች በተቀመጠው Link በመግባት እንከታተል Subscribe እናድርግ በተጨማሪም Video እንዲሰሩልን የምንፈልጋቸውን ጥያቄዎቻችንን የYoutube ቻናላቸው ውስጥ በመግባት Comment ላይ ጥያቄዎቻችንን እናስቀምጥላቸው !
-------------------------------------------

https://www.youtube.com/channel/UCOCF38dTok_YXIYfJTAsezw

Ethiopian Surveyors

19 Jun, 17:25


ሰላም ቤተሰቦች!
-------------------
ዛሬ የምናስተዋውቃቹህ ገጽ Geospatial Opportunities የሚባል ሲሆን በጂኦስፓሻል ዘርፍ የሚወጡ

🔗 የስራ ማስታወቂያዎች
🔗 ስኮላርሺፕ
🔗 አጫጭር ኮርሶች እንሁም አጠቃላይ ጂኦስፓሻል መረጃዎችን የምናገኝበት ገፅ ስለሆነ ሊንኩን ላይ  በመግባት Join እናርግ!
https://t.me/Geo_opp_Eth

Ethiopian Surveyors

15 Jun, 09:49


ሰላም ቤተሰቦች!
-------------------
ዛሬ የምናስተዋውቃቹህ ገጽ Geospatial Opportunities የሚባል ሲሆን በጂኦስፓሻል ዘርፍ የሚወጡ

🔗 የስራ ማስታወቂያዎች
🔗 ስኮላርሺፕ
🔗 አጫጭር ኮርሶች እንሁም አጠቃላይ ጂኦስፓሻል መረጃዎችን የምናገኝበት ገፅ ስለሆነ ሊንኩን ላይ  በመግባት Join እናርግ!
https://t.me/Geo_opp_Eth

Ethiopian Surveyors

27 May, 13:34


ሰላም!
የዚህ Diffrential GPS ባትሪ የሚሸጥ ያለው ያናግረኝ !
0910543849

Ethiopian Surveyors

01 May, 15:01


የጂፒኤስ ጠለፋ ምንድን ነው?፤ ለአቬሽን ችግር የሆነውስ እንዴት ነው?

የጠለፋ እና የስፑፊንግ ተግባር ብዙ አይነት በመሆኑ ምክንያት አየር መንገዶች ይህን ለማስወገድ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ለማግኘት ይቸገራሉ
ምንጭ (አል-ዐይን)


የጂፒኤስ ጠለፋ ምንድን ነው?፤ ለአቬሽን ችግር የሆነውስ እንዴት ነው?

የጠለፋ እና የስፑፊንግ ተግባር ብዙ አይነት በመሆኑ ምክንያት አየር መንገዶች ይህን ለማስወገድ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ለማግኘት ይቸገራሉ

የጂፒኤስ መስተጓጎል ከባለፈው አመት ወዲህ በመላው ዓለም መጨመሩ አውሮፕላኖች ከመሰመራቸው ለቀው አደጋ ሊያጋጥም ይችላል የሚለውን ስጋት ከፍ አድርጎታል

ኢስቶኒያ በጥቁር ባህር የጂፒኤስ ናቪጌሽን መሳሪያዎቿን በመጥለፍ ሩሲያን ከሳለች።ይህ የኢስቶኒያ ክስ ለወራት እንዲህ አይነት ሙከራ እየተደረገብን ነው ሲሉ የነበሩትን አየርመንገዶችን ስጋት የሚያስተጋባ ነው።

የኢስቶኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማረጋገጫ ያላቀረቡበት ይህ ክስ ፊንኤየር በጂፒኤስ መስተጓጎል ምክንያት በምስራቅ ኢስቶኒያ የሚያደርገውን በረራ ለአንድ ወር ማቆሙን ተከትሎ የመጣ ነው።

የጂፒኤስ መስተጓጎል በተለይ ከባለፈው አመት ወዲህ በመላው ዓለም መጨመሩ አውሮፕላኖች ከመሰመራቸው ለቀው አደጋ ሊያጋጥም ይችላል የሚለውን ስጋት ከፍ አድርጎታል።

ጂፒኤስ ጃሚንግ እና ስፑፊንግ ምንድን ነው?

ጂፒኤስ (ግሎባል ፖዚሺኒንግ ሲስተም) ማለት  ከመርከብ እና አውሮፕላን እስከ መኪና ድረስ በመሬት ላይ ያሉትን ሁሉ የሚያስስ የሳተላይቶች እና አቅጣጫ ለመጠቆም የሚያስችሉ የመቀበያ መሳሪያዎች ጥምረት ነው።

ጂፒስ ከዚህ በፊት አውሮፕላኖች ለማረፍ ይጠቀሙበት የነበረውን አድካሚ የሬዲዮ ሲግናል የሚተካ በአቬሽን ዘረፍ በጣም አስፈላጊ  የሆነ የአሰሳ መሳሪያ ነው።
ነገርግን ይህን የአስሳ መሳሪያ በቀላሉ እንዲዘጋ ወይም የተሳሳተ አቅጣጫ እንዲይዝ ማድረግ የሚቻል እንደሆነ ተገልጿል።

ጂፒኤስ የሚጠለፈው ሲግናል በሚያሰራጩ መሳሪያዎች፣ የራዲዮ ኮሙኒኬሽንን ሰብሮ በመግባት እና በአብዛኛው ደግሞ ከሳተላይት የበለጠ ጥንካሬ ያላቸውን ሲግናሎች ከመሬት በመልቀቅ ነው። 

ስፑፋንግ ወይም መረጃ ከትክክለኛው አካል እንደመጣ ማስመሰል አንድ ሀገር የጠላትን አውሮፕላን ወይም ድሮን ስራውን እንዳያከናውን ለማድረግ የሚጠቅም ሲሆን  ይህ ከጠለፋ የበለጠ አደገኛ ነው።

የንግድ አውርፕላኖች የጂፒኤስ መቀበያ ያንን የተሳሳተ ሲግናል ከተቀበለው ልክ ያልሆነ ሰአት ወይም ኮኦርዲኔት(አቅጣጫ) በማሳየት አብራሪውን እና የአየር ትራፊኩን በማወዛገብ ችግር ይፈጥራል።

የት ነው የሚከሰተው?

ኦፒኤስ ግሩፕ ባለፈው ታህሳስ ወር በኢራቅ፣ በኢራን እና በእስራኤል ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ እና በጥቁር ባህር የግል እና የንግድ አውሮፕላኖችን ያስተጓጎለ ስፑፊንግ መጨመሩን መግለጹ ይታወሳል።

ቴክኖሎጂው ድሮኖችን ከኢላማ ውጭ ለማድረግ ጥቅም ላይ እየዋለ ስለሆነ በጦርነት ቀጣና አቅራቢያ ያሉ ቦታዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል። የባልቲክ ሀገራት በተለይ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ጉዳዩን ለአመታት ሪፖርት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ጠለፋ በባልቲክ ባህር መባባሱን የፊንኤየር አብራሪ እና የፊኒሽ የአብራሪዎች ማህበር የጥንቃቄ እና የጸጥታ ኮሚቴ ሊቀመንበረ ላውሪ ሶይኒ ገልጸዋል።

ሶይኒ እንዳሉት የጂፒኤስ ጠለፋ በአሁኑ ወቅት ከፖላንድ በባልቲክ በኩል እስከ ስዊድን እና ፊንላንድ ጠረፍ ድረስ እየተከሰተ ነው።

በአየር መንገዶች ላይ የሚፈጥረው ችግር ምንድን ነው?

አብዛኞቹ ዘመናዊ አየርመንገዶች አቅጣጫ ለመወሰን ከጂፒኤስ በተጨማሪ የተለያዩ ሴንሰሮችን እና ምንጮች ይጠቀማሉ።ይህ ማለት ጣልቃ የሚገባ ሲግናል ካለ ሊበሩ የማይችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል።

ይሁን እንጂ አብራሪዎች እና የኢንዱስትሪው ባለሙያዎች እንዳሉት ከሆነ አብዛኞቹ አየርመንገዶች በጂፒኤስ ይተማመናሉ። ጠለፋ ወይም ስፑፊንግ ከተከሰተ ጂፒኤሱ ሙሉ በመሉ ሊዘጋ እና በድጋሚ ለማስጀመር የማይቻለበት ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል። ጂፒኤሱን እንደገና ስራ ለማስጀመር የሚደረግ ሙከራ የመነሻ እና የማረፊያ ሰአት እንዲዘገይ ምክንያት ይሆናል።

የጠለፋ እና የስፑፊንግ ተግባር ብዙ አይነት በመሆኑ ምክንያት አየር መንገዶች ይህን ለማስወገድ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ለማግኘት ይቸገራሉ።

በዚህ ምትክ የአየር መንገድ ባለስልጣናት አብራሪዎች ጠለፋ እና ስፑፊንግን እንዲለዩ የሚያስችል ስልጠና ለመስጠት አቅደዋል።

2,594

subscribers

155

photos

12

videos