ISLAMIC SCHOOL @islam_and_science Channel on Telegram

ISLAMIC SCHOOL

@islam_and_science


ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL (Amharic)

ፍቅርን እና እብድ በጥንካሬ መሰረት የተከታይ ጅል ተመንጥለህ ጅልን ለመላኩ፣ ጅልም እንኳ፣ ደምስ ብሎህ እየበጠጠህ ተጠምተህልን ወሬውን ቈሩለህ፡፡ ፍቅረᅰጊና በነቅን ላይ ለሆነባችሁም...ኩሩኒን እናመርተን!ፈጣንህ በሪስህ ከፍተናል፡፡ ንዓንህናልሆንና ይሄውን ፈጥር ኑገው፡፡ አበሻሓናል ሰማነን፡፡ ጅሕልና ለቤቱ ነዉ፡፡ የቅዱሳን መተግበር እንኰሁ፡፡ በስብሽታ ወሬዉን ተዉው፡፡ 🎖ለሁሉም አካለ T.me/Aisuu_bot💠ሌሎች ትምህርቶች @IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

08 Dec, 04:54


አልሀምዱሊላህ😍😍😍

ዛሬ ደስ የሚል ዜና ሰማን ይህን ዜና ለመስማት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ነበር ያደርኩት የበሽር አሳድ መንግስት መፍረስ ለመስማት አልሀምዱሊላህ ይሄን ለማየት በቃን፡፡ አሏህ ደግሞ የፍልስጤሞችን ዋይታ ለቅሶ በቃችሁ ብሎ ደስታቸዉን የምንሰማ ያድርገን ያረብ

በነገራችን ላይ  ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር የነጠለው የአላሳድ ሥርወ-መንግስት ነበር፡፡

    ከግብፅ በመቀጠል ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትነጠል የአንበሳውን ድርሻ የተጫወተችው ሶሪያ ናት። የጀብሃ (ELF)  ጽ/ቤት በመክፈት፣ ዲፕሎማት ፓስፖርት በማቅረብ፣ ትጥቅና ስንቅ እንዲሁም ፖለቲካዊ ድጋፍ በማቅረብ የሶሪያ አጥፊነት ወደር አልነበረውም።

እ.ኤ.አ ከ 1971 እስከ እለተ ሞቱ 2000 የሶሪያ 18ኛ ፕ/ት የነበረውና በፀረ-ኢትዮጵያ አቋሙ ተስተካካይ ያልነበረው አሁን የተሰናበተው የበሽር አላሳድ አባት ሀፌዝ አላሳድ ኢትዮጵያን ለሚያደሙ ቅጥረኞች ሁሉ ዋነኛ ደጋፊ ነበር። ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር ለመነጠል በመጀመሪያ የተደራጀው ጀብሃ ከግብፅ በመቀጠል ሁለተኛ ቢሮው ደማስቆ (ሶሪያ) ነበር። የጀብሃ አባላት ፍልስጤም ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ ያስቻለው ይህ ሰው ነበር። በኋላ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ሻዕቢያ ጀብሃን አክስ'ሞ ሲመሰረት በመጀመሪያ አካባቢ የክርስቲያን ድርጅት ነው በማለት ድጋፍ ለማቋረጥ አንገራግሮ የነበር ቢሆንም ከእራሱ አልፎ ለህወሓትና ለሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ ድርጅቶች የሚለገስ የተትረፈረፈ ወታደራዊ ድጋፍ (ትጥቅ፣ ስንቅና ስልጠና) በማቅረብ ኢትዮጵያን ያደ'ማ በመጨረሻም ከቀይ ባህር የነጠለ የክፋት ብልቃጥ ነበር። የዚያድባሬ ደጋፊ ሆኖ Elite force የላከ ወራዳ ሰው ነበር።


☞ ከሀዲነቱ ወደር አልነበረዉም በሽር አላሳድ ሲያምነው የነበረውን የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሙአመር ጋዳፊ የሳተላይት ስልክ ቁጥር ለፈረንሳይ ደህንነት (DGSE) አሳልፎ በመስጠት በቁጥሩ መሰረት ጋዳፊ ያለበት ትክክለኛ ቦታ ተለይቶ ለአማጺያን እንዲሰጥ ያደረገ ከሃዲ ሰው ነው። ከግብፅ ጋር ባላቸው ቂም ጋዳፊ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ።

ከአመታት በፊት ሊቢያውያንን  በወግ በማእረግ ፡ አስተዳድረው ህዝባቸውን  በምቾት ፡ በደስታ ያኖሩ የነበሩት ታላቁ የሊቢያ መሪ ፡ ሙአመር አል ገዳፊ  የሊቢያን  ወርቅና ነዳጅ ፈልገው ጥርስ ውስጥ በከተቷቸው ምእራባውያን ሴራ በራሳቸው ህዝብ ተቃውሞ ተነሳባቸው ።
............
የአረብ አብዮት እሳት ሊቢያንና ህዝቦቿን ሊበላ ጫፍ ደረሰ ።
በመጨረሻም ደጉ መሪ ሙሀመድ አል ጋዳፊ ቤተመንግስታቸውን ትተው ወደተወለዱበት ከተማ ሲርጥ በመሄድ በሚስጥር ተቀመጡ ።
...................

ምእራባውያንና አሜሪካ ዋና ጠላታቸው የሆነውን ጋዳፊን ፈልጎ ማግኘት አቃታቸው  ።
እና የጋዳፊን አድራሻ ማፈላለግ ጀመሩ ። ያሉበትን ቦታ ወይም ይህን ለማወቅ የሚረዳ መረጃ አጥተው በተቸገሩበት ወቅት አንድ ሰው  ለፈረንሳይ የፀጥታ ሰወች የሚነግረው ሚስጥር እንዳለ አሳወቃቸው ።
....
ይህ ሰው በጋዳፊ ይታመን የነበረ እና የሳተላይት ስልካቸውን ቁጥር የሚያውቅ ነው ።
ጋዳፊን የሚፈልጉ ሀገራት ይህን ቁጥር ካገኙ ፡ በሲግናል አማካኝነት ያሉበት ቦታ እንደሚታወቅ ያውቃል ።
እናም ይህን በእምነት የተሰጠውን ትልቅ መረጃ ፡ አሳልፎ ለፈረንሳይ የስለላ ድርጅት  ሰጠ ።
......
ይህ መረጃ ከተገኘ በኋላ  የጋዳፊን መወገድ የሚፈልጉት ምእራባውያን ፡  በዘመናዊ መሳሪያ ታግዘው ጋዳፊ ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ አወቁ ።

ይህንንም መረጃ  ጋዳፊ ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ ፡ ለጋዳፊ ተቃዋሚዎች ሰጧቸው ። ጋዳፊ , ከድህነት አውጥተው ባበለፀጉት የሀገራቸው ህዝብ በተነሳባቸው ተቃውሞ ፡ በገዛ ሊቢያውያን  ተገኝተው በግፍ ተገደሉ ።
....

ጋዳፊን ማን አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው ነገር ጥያቄ ሆኖ ከቆየ በኋላ ግን. . የሰውየው ማንነት ታወቀ ። ይህ ሰው ፡ ይህ ጋዳፊ ከመሸጉበት ቦታ እንዲገኙ ስልክ ቁጥራቸውን አሳልፎ የሰጠው ከሀዲ ሰው ፡ የሶሪያው ፕሬዝደንት በሽር አልአሳድ ነበር ።
.............
አልአሳድ ፡ ይህንን መረጃ የሰጠው የስልጣን ዘመኑን ለማቆየት የሚያስችል ድጋፍ ከፈረንሳይ መንግስት ለማግኘት በማሰብ ነበር ።
.....


አልሀምዱሊላህ ታሪካዊዋ ሶሪያ ደማስቆ የእዉቀት የጀግኖች የሙስሊሞች መስፋፊያ የሆነችዉ ነፃ ሁናለች ኢንሻ አላህ ወደፊት የሙስሊሞች ድል ቅርብ ነዉ💪

ሀያሉ ፈጣሪያችን አላህ ለሶሪያ ህዝብ ፍትሀዊ መሪ እንድሰጣቸውና የተረጋጋች ሀገር ከመሆንም ባሻገር ደማስቆ ወደገናና ኢስላማዊ ታሪኳ ትመለስ ዘንድ ምኞታችንም ዱዓችንም ነው።


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

07 Dec, 16:20


የማስመሰል ዘመን || ሙሀመድ አሊ ቡርሃን

አሁን ላይ በሚባል ደረጃ የሚፈልገው የሆንከውን ትተህ ያልሆንከውን ስትነግረው ይቀርብሃል ፣ የሆነውን ሳይሆን ያልሆነውን እንድትነግረው ይፈልጋል።

ሁሉም ተመሳስለህ ኑር ይልኃል ፣ ያላመኑበትን እና ያልሆኑትን ተናግሮ ሰዎች ጋር እንደመኖር ከባድ ነገር የለም!! አስመሳዮች ጋር በህብረት ከመጓዝ በሀቅ መንገድ ላይ ለብቻ መጓዝ የተሻለ ሰላም አለው።

ይህ ችግር ኡማችን ላይ በጣም እየተስፋፋ ይገኛል።

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

04 Dec, 10:24


🎖  #የሚኒስትሩ_ጠባቂ_ጀብድ🎖
         አሚር ሰይድ

  

ከወደ ፓኪስታን የአሜሪካ ድጋፍ የተቸራት የረሱልንﷺ
ስም የሚያንቋሽሽ የአሲያ ቤቢ ድምፅ ተሰማ። እንደ አውሮፓዉያን የዘመን ቀመር ኦክቶበር 2011 አሜሪካ ወዳጅ ብላ ያወደሰችው የፓኪስታን ሚኒስትር የሀገረ ፑንጃብ ገዥ ሰልማን ተይሲር የአላህን ነቢይ
ሙሀመድ ﷺ ለተሳደበችው ለአሲያ ቤቢ ከለላን ሰጠ። የመናገር መብቷ ሊነፈግ አይገባውም ሲል ተደመጠ። ረሱልን መስደብ ወንጀለኛ የሚያደርገው የሀገሪቱ ህግ መሻሻል አለበት ሲልም ተናገረ።

    በዚህ ጊዜ የሚኒስትሩ ጠባቂ ይህን መሸከም ከበደው። መሳርያውን ጥይት አጉርሶ እየተንደረደረ ወደ ቢሮው አቀና። ከ20 በላይ ጥይት በሰውነቱ ላይ አርከፍክፎ ላይመለስ ወደ ቀብር ሸኘው፡፡
“ #ሙምታዝ_ቃዲሪ" ይሰኛል። በቁጥጥር ስር ውሎ የሞት ፍርድ ተወሰነበት። ከመሰቀያው ገመድ ላይ ተንጠልጥሎ ውሳኔው ተተገበረበት። ጀናዛው ለቤተሰቦቹ ሲሰጥ ታጥቦና ተከፍኖ ጀናዛ ተሰገደበት።

    #ነፍሱን ለረሱል ﷺ ክብር ቤዛ ያደረገውን የዚህን ጀግና ጀናዛ ለመሸኘት የፓኪስታን ጦር አባላትን ጨምሮ ከ12 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተሰበሰበ።

   #አላህ_ቀብሩን_ኑር_ማረፊያውን_ጀነተል_ፊርደውስ_ያድርግለት።


#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

03 Dec, 01:54


⚡️⚡️በቅርቡ የወጣ ሙዚቃ የሚያተኩረዉ ስለሚሲሁል ደጃል ነዉ፡፡

ትንታኔዉን ያዳምጡት


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

01 Dec, 02:05


💚
#ለሰረሱል_ክብር_ገድዬ_ለመሞት_ራሴን_አዘጋጀሁ

     አሚር ሰይድ

አንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር 1910 በቤሩት ምድር በአንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ የሚርመሰመስ ሰው የአላህ መልእክተኛ ሙሀመድ ﷺድምፁን ከፍ አድርጎ ይሳደባል።

አንድ መንገደኛ ውስጡ በግኖና በንዴት ጦፎ ከኋላ ኋላው ይከተለዋል፡፡ ቢላዋ በሚሸጥበት ሱቅ በኩል ሲያልፍ አንዱን ቢለዋ መዞ በተሰዳቢው ጉሮሮ ላይ ሰካው። በኃይል ሰምጥጦ ደምስሩን በጥሶ ገደለው።
ገዳዩም እስር ቤት ገባ፡፡

    ጉዳዩን ሲመረምር የነበረው የቤሩት ከፍተኛ ወንጀል ችሎት ከሁለት ዓመታት በኋላ ወንጀለኛው ለውሳኔ ይቀርብ ዘንድ አስጠራው። ተከሳሹ ችሎት ፊት ቆመ። አዳራሹ ከአፍ አስከ ገደፉ በሰው ተሞልቷል።

“ሰውየውን ለምን ገደልከው?" የዳኛው ጥያቄ ነበር

“የአላህን መልእክተኛ ﷺ ሲሳደብ በእጅጉ ተናደድኩ #ለረሱል_ክብር_ገድዬ_ለመሞት_ራሴን_አዘጋጀሁ ስለሳቸው ክብር ጉሮሮውን በጠስኩት" ሲል መሰሰ።

ዳኞቹ ከተወያዩ በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተሳሰፋ

...."ሆን ብለህ የግድያ ወንጀል ፈፅመሀል ድርጊቱን የፈፀምከው ለረሱል ክብር መሆኑም ተጋግጧል፡፡ ፍርድ ቤቱ በነፃ ይለቀቅ ዘንድ ወስኗል መዝገቡ ተዘግቷል፡፡

    ከውሳኔው በኋላ የታሰረበት ካቴና አንዲፈታለት ፖሊሱን አዘዘው ፡፡የመሀል ዳኛው ዩሱፍ አን-ነብሀኒ ከፍርድ ቤቱ የመቀመጫ ወንበር ወርዶ። ወደ ሰውዬው ቀረብ አለና “ልጄ ሆይ የምንወዳቸው ነቢን የተሳደበውን ሰው በየትኛው አጅህ ነው የገደልከው?" ሲል ጠየቀው

"በቀኝ አጄ" አለ

"አጅህን ዘርጋልኝ" እያለ በለቅሶ 😢 እጁን አቅፎ ይስመው ጀመር።

በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት አቀርቅረው ተላቀሱ። የቤሩት ፍትሕ ሚኒስትር የፍርድ ቤቶች ዋና ሀላፊ የገዳዩን አጅ የሳመውን ዳኛ ወደ መዲና ላኩት። የዘወትር ህልሙ ተፈፀመ።

" #ጌታዬ_ሆይ! የህይወቴን የመጨረሻ ቀናት ረሱል ባሉበት ከተማ ላይ አድርግልኝ ከሳቸው ጋርም አጎራብተኝ" በማለት ዱዓ ያደርግ ነበርና አላህ ዱዓውን ተቀበለው።

ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ

💞💞💚 ጠዋትም ማታም ሶሉ አላሀቢቡና ሰይዲና ሙሀመድ  ﷺ ﷺ

#ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

29 Nov, 16:14


🎖🎖አይሁዶች ለምን የነብዩሏህ የሱፍን ቀብር በመፈለግ ጊዜያቸዉንና ገንዘባቸዉን ያፈሳሉ??

መቃብሩንስ አግኝተዉ ከከፈቱት ቡሀላ ምን ተፈጠረ??

#ያዳምጡት
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

27 Nov, 02:10


        #ቀዕቃዕ_ኢብኑ_ዓምር
           አሚር ሰይድ



     ታላቁ የኢስላም የጦር መሪ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ የፋርስ ሙሽሪኮችን ለመዋጋት 10ሺህ ሙጃሂዶችን አዘጋጅቶ ወደ ጦር ሜዳ ዘመተ። የጦር ሜዳው ላይ የተሰለፉትን የፋርስ ወታደሮች ሲመለከት ከሙስሊሞች ሠራዊት በቁጥርና በትጥቅ የበለጡ እጅግ ግዙፍ ሆነው አገኛቸው። ሙጃሂዶቹን ማማከር የዘ።

“ወደ መዲና እንመሰስ? ወይንስ ሸሂድ እስከምንሆን ድረስ እንዋጋ?" በማለት ጠየቀ። ሁሉም በአንድ ድምፅ ተክቢራ አሰሙና አንዲህ በማለት መለሱ
.....“ከሀገራችን የወጣነው ሸሂድ ሆነን ለመሞትና በስሮቿ ጅረቶች በሚፈሱባት ጀነት ለመግባት አይደልን?!” አሉ።

ኻለድ የወታደሮቹ መልስ አስደሰተው። ግዙፉን የኪስራን ጦር ለመፋለም በቂ ሠራዊት አልነበረውምና ከመዲና ተጨማሪ ኃይል እንዲላክበት ለኸሊፋው አቡበከር ደብዳቤ ላከ።

  የኻሊድ ሠራዊት ከሰፈረበት ርቀት የበረሀውን አሸዋ እያቆራረጠ የሚመጣን ፈረሰኛ ተመለከቱ። የሚያነሳው አቧራ የሚመጣውን ሰው በቅጡ እንዳያዩ ጋርዷቸዋል። የኸሊፋው አቡበከር አጋዥ ጦር እንደሆነ ግን ገምተዋል። በትኩረት ሲመለከቱት አጓድ ፊቱን የሸፈነ ፈረሰኛ ነበር። ለማረጋገጥ ወደ ኋላው ተመለከቱ። ምንም ነገር የለም። ኸሊፋው ምን ነክቷቸው ነው የኪስራን ግዙፍ ሠራዊት ለመግጠም አንድ ፈረሰኛ የሚልኩት! አንድ ሰው? አዎ! እስላም በብዛት አያምንም። ወደሠራዊቱ ተጠጋና ኸሊፋው አቡበከር የሰጠውን ደብዳቤ ይዞ ወደ ፊት አመራ። ፊቱን ገለጠና ስሙን አስተዋወቀ “እኔ አሚሩል ሙእሚኒን የላኩኝ ትጥቅና ሠራዊት ነኝ" አለ። አቡበክር የላኩለትን ደብዳቤ ለኻሊድ ሰጠ። ደብዳቤውን ማንበብ ጀመረ።

"የአላህ ባሪያ ከሆነው አቡበከር ለኻለድ የተላከ:-

ወንድሜ! የላኩልክ አንድ ሰው ብቻ እንዳይመስልህ የቃዕቃዕ ድምፅ ከአንድ ሺህ ፈረሰኞች ይበልጣል ቃዕቃዕ ያለበት ሠራዊት ፈፅሞ አይሸነፍም" ይላል። የኻሊድ ፊት በፈገግታ ደመቀ "የአላህ ሠራዊቶች ሆይ! ፋርሶችን ለመግጠም ተዘጋጁ! ተጨማሪ ኃይል ደርሶናል” አለ።

     ጦርነቱ ተጀመረ። የጠላት ጦር መሪ ሁርሙዝ ወታደሮቹን አዘዘ “ከኻለድ ጋር ብቻ ለብቻ
በምንገጥምበት ሰዐት ከጀርባ መጥታችሁ ግደሉት" አለ።

    የመሪዎቹ ግጥሚያ ተጀመረ። ኻለድ ሁርሙዝንን በመግጠም ተዘናግቶ ሳለ የጠላት ወታደሮች በጀርባው በኩል መጡ። ጀግናው ቃዕቃዕ እንደ አንበሳ የጦር ሜዳውን ተቀላቀለ። አንድ በአጓድ ሁሉንም አንገታቸውን በጠሰ። ጦርነቱንም ሙስሊሞች አሸነፉ።
    አቡበክር ሲዲቅ ይህን ሲሰሙ ለኻሊድ አንዲህ በማለት ደብዳቤ ላኩ “ቀዕቃዕ ያለበት ሠራዊት አንደማይሸነፍ አሁን ያወቅክ ይመስለኛ"


       ያ የቀድሞው የድልና የክብር ታሪካችን የተገነባው አንደ ቃዕቃዕ አብኑ ዓምር ባሉ ጀግና ወጣቶች ነበር

ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

24 Nov, 06:56


🔥🔥ጀሀነም እና ጀነት መኖሩን ሳናይ እንዴት ማመን እችላለሁሀይማኖት በሚባልም ነገር አላምንም ብሎ አንድ ሰዉ  የጠየቀዉን ጥያቄን ዶክተር ዛኪር  የመለሱለት መልስ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

23 Nov, 03:26


በዜግነት ኤማራቲ በትውልድ ሩሲያዊ የሆነው  Khamzat Chimaev እና ሩሲያዊው ikram aliskerov ወሳኝ የተባለ የቦክስ ( mixed martial Art ) ግጥሚያ ባደረጉበት ወቅት ነው ።
በዚህ ጨዋታ ካማዛት ተቀናቃኙ የሆነውን ኢክራምን  ደጋግሞ በመምታትና በመዘረር ካሸነፈ በኋላ ፡ ሁልጊዜ እንደሚያደርገው ፡ ለእናቱ ደወለ ።
...
ሁለቱ ተፋላሚዎች ያደረጉትን ግጥሚያ በቴሌቪዥን ሲመለከቱ የቆዩት የካማዛት እናት አሸንፎ የደወለላቸውን የልጃቸው ድምፅ ሲሰሙ እያለቀሱ ያናግሩት ጀመር ።
....
ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው አሸንፌያለሁኮ
" አዎ ማሸነፍህንማ  አይቻለሁ "
እና ለምን ታለቅሻለሽ ?

" እንደዛ አድርገህ ስትመታው ሳይ እናቱን አሰብኳት ፡ እሱምኮ እናት አለው ። አንተ ልጁን በመታህበት ሁኔታ ፡ አንተን ሲመቱብኝ ባይ ምን አይነት ስሜት እንደሚሰማኝ አሰብከው ? እኔ ግን ብትችል ይህን ስፖርት ብትተው ነበር ደስ የሚለኝ "
.....
ካማዛት ይህን የእናቱን ንግግር ሲሰማ ፡ ያረጋጋቸው ጀመር ፡ ምንም እኮ አልሆነም እናቴ  ፡ ከሪንጉ በእግሩ እየተራመደ ነው የሄደው ያሰብሽው ያህል አልተጎዳም ።
የካማዛት እናት ይህን እንደሰሙ
እኔ አላምንህም ፡ በርግጥ እንደምትለው ደህና ሆኗል ? እያሉ ደጋግመው ጠየቁት ።
....
ለኚህ ደግ እናት ፡ ከልጃቸው ማሸነፍ ይልቅ ፡ የኔ ልጅ ቢሆንስ የሚለውን አስበው የተጋጣሚው ጉዳት ነበር ያሳሰባቸው ።
....
ሰው ስትሆን !👌

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

18 Nov, 10:25


አምላክ በሰዎች ስቃይ ይደሰታል ወይ? ብሎ
አንድ አሜሪካዊ ወጣት ለዶክተር ዛኪር የጠየቃቸዉ ጥያቄን የመለሱለት መልስ



join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

15 Nov, 16:09


   ታዋቂው አሜሪካዊ ዳዒ ሼህ ኻሊድ ያሲን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦"እናቴን ወደ ኢስላም ለማስገባት 35 ዓመት ዳዕዋ አድርጌላት አሻፈረኝ አለችኝ፣በመጨረሻ ግን በባለቤቴ እጅ ኢስላምን ተቀበለች፣ ባለቤቴ ዉዱዕ ትጥበት ታደርግላታለች ትንከባከባታለች።"

ሴትነት ማለት ይህ ነዉ❤️

  ሼህ ኻሊድ ያሲን ለብዙ ሺህ አሜሪካውያንና አውሮፓውያን መስለም ትልቅ የሒዳያ ሰበብ ነበሩ፣በመላው ዓለም በሳቸው ዳዕዋ በመማረክ የኢስላምን ብርሀን ያገኙ በሺዎች ናቸው።
አላህ ይቀበላቸው ይጠብቃቸው።

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

12 Nov, 23:05


ፍልስጤም ጋዛ የልጆች ለቅሶ የምግብ የዉሀ ችግር ጫማ የሚለብሱት እስኪያጡ ድረስ

ለቅሷቸዉ ልብ ይነካል😔


ያኢላሂ ድረስላቸዉ😔


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

12 Nov, 03:51


        #ዞምቢ
   አሚር ሰይድ

የቦሊዩድ ሲኒማዎች ዞምቢ ማለት የሙታን መንፈስ እንደሆነ አድርገው በመሳል ልጆችን ያስፈራሩበታል። ግን እሱ በብራዚል ታላቅ ስብዕና ያለው ኢስላማዊ መንግሥትን የመሰረተ ሙስሊም ንጉሥ ነው። ውልደቱ በአፍሪካ እምብርት፣ አትበቱ የተቀበረው በኮንጎ ምድር ነው። በጀግንነቱ ምክንያት ዞምቢ ጋጓጋ ብለው ይጠሩታል ጥቁሩ ደፋር እንደማለት ነው።

    በ 17 ክፍለ ዘመን ፖርቹጋል በኃይል የባሪያ ፍንገላ ዓለምን ያሸችበት ወቅት ነበር። በተለይ ከምእራብ አፍሪካ ወደ ብራዚል የሚጋዙ ባሪያዎች በርካታዎቹ ሙስሊሞች ነበሩ። የባህር ዳርቻዎችን በማጥቃት ሙስሊሞችን ማርከው በመርከቧ የታችኛው ክፍል በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ ያጉራቸዋል። የጉልበት ሥራ እንዲሰሩና ክርስትናን አንዲቀበሉ ያስገድዷቸዋል።

ከእነዚህ ሰዎች መሐል አንድ ወጣት ጦረኛ ተፈጠረ። ጀግናችን “ #ዞምቢ” ሰዎችን ወደ ትክክለኛው እምነት ወደ አስልምና ሳይሰለች ሳይታክት መጣራት ጀመረ። ተከታዮቹ ሲበዙ ከባርነት ቀንበር አምልጠው ጂሃድ አወጁ። የኢስላምን ጠላቶች ማጥቃት ጀመሩ። እስልምና በብራዚል መስፋፋቱ የእግር አሳት የሆነባቸው መስቀላዊያኖች እርሱንና ጓደኞቹን ለማጥፋት ተባበሩ፡፡ ለተከታታይ አስር ዓመታትም በርካታ የመስቀል ጦርነቶች ተደረጉ። በየመስኩ ተደጋጋሚ

ሽንፈቶችን አከናነባቸው፡፡

    ስር መሰረቱ የኮጓጎ ንጉሳዊ ቤተሰብነት የነበረው ይህ ሙስሊም ወጣት ዞምቢ ዶስ ፓልማሬስ ይሰኛል። በተዋጣ አስላማዊ ዲሲፕሊን፣ በቆራጥ ተፋላሚነቱ የሚደነቀው ይህ ጀግና በሀያዎቹ አድሜው በብራዚል የሙስሊሞች ግዛት Quilombo dos Palmares ንጉሥ መሆን ቻለ። ኢስላማዊ መንግሥትንም በይፋ አወጀ። በቆዳ ስፋቷ ፖርቹጋልን የሚስተካከለው የዞምቢ ግዛት ህዝቡ በፍፁም ኢስላማዊ መንፈስ ይታዘዘው ጀመር።

የዞምቢን ኃያልነት ያስተዋሉት የኢስላም ጠላቶች በእነሱ አስተዳደር ስር ሆኖ በነጻነት አንዲኖርና ለሌሎች አፍሪካውያን ሙስሊሞች ነጻነት አንዳይታገል ጠየቁት። ለሌሎች ሙስሊም አፍሪካውያን አገዛና እርዳታዬን አልነፍጋቸውም በማለት የፖርቹጋሎቹን ጥያቄ ውድቅ አደረገ። በዚሁ ወደ ግልፅ ጦርነት ገባ።

#ሙላቶ በተባለው የጦር መሪው የተከዳው ዞምቢ በአውሮጳውያን አቆጣጠር ኖቬምበር 20/1695 በፖርቹጋሎች ቁጥጥር ስር ዋለ። ሰውነቱን ጭንቅላቱንና የአካል ክፍቹን በጭካኔ ቆራረጡት😔። ተከታዮቹን በባርነት ሰጧቸው። ዞምቢ ጋጓጋ ምንም ታሪክ አንዳይኖረው ተደረገ። በብራዚል የሰፈሩ አፍሪካውያን ሙስሊሞችን በኃይል የካቶሊክ ኃይማኖትን አንዲቀበሉ አደረጓቸው።

ዞምቢ ምንም ያህል ለብራዚል ክብር የወደቀ ስለ ሙስሊም ወንድሞቹ የተፋለመ ጀግና ቢሆንም ኢስላማዊ ማንነቱ የጎረበጣቸው ብራዚላዊ ፀሀፊዎች በልብወለድ ታሪኮቻቸው ላይ አንደ አስፈሪ ፍጡር ስለዉ ይፅፉት ጀመር። ከ1968 ወዲህ በሆሊውድ የሚሰሩ አስፈሪ ፊልሞች ሁሉ የዞምቢን ስም እንደገፀ ባህሪ በመጠቀም በብዙ ሚለዮን ኮፒዎች ተቸበቸቡ።

በኢስላም ታላቅ መስዋዕትነትን የከፈለው አፍሪካዊው የላቲን አሜሪካ እንቁ ታሪኩን ለማድበስበስ የተጠቀሙበት መንገድ ዛሬም በሌሎች ሙጃሂዶች ላይ እየተጠቀሙና ስም እያጠፋ ነውና በቀደዱልን ቦይ አንፍሰስ ለማለትም ነው።

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

11 Nov, 06:53


🎖🎖ቢስሚላህ ብሎ የመጠጣትና የመብላት ጥቅሞች፡፡ነብዩ ሰዐወ ከ1400 አመት በፊት የተናገሩትን በዚህ ዘመን ሳይንቲስቶች ያረጋገጡት እዉነታ

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

10 Nov, 04:29


ጋ *ዛ

የ 8 አመቱ ህፃን Zain Mhanna እናቱ ከሞተች 2 ወር ጀምሮ ማታ ማታ ሄዶ ቀብሯ ላይ ይተኛል።😢

"ቀብሯን ሄጄ አቅፌ ስስመው እሷ ጋር በአካል የተገናኘሁ ይመስለኛል ወዲያው ልቤ ውስጥ ሰተት ብላ ትገባለች ይላል።

የጋዛው ጋዜጠኛ Saleh Al-Jafarawi በ Instagram አካውንቱ ባጋራው መረጃ መሠረት የልጁ እናት ሸሂ ድ የሆነችው ጋ *ዛ Nuseirat camp ላይ በተፈፀመ የእስራ *ል አየር ጥቃት ነው። እናቱ ሸሂድ ከሆነችበት ቀን ጀምሮ ህፃኑ አንድም ቀን ማታ ላይ ቀብር ከመዘየር ቀርቶ አያቅም ይላል።

ጋዜጠኛው ማታ ላይ በዚ ጨለማ በዚ ከባድ የአየር ድብደባ ብቻህን ሁልጊዜ እዚ ስትመጣ ጨለማና ቦምብ አትፈራም ወይ? ብሎ ህፃኑን ጠይቆት ነበር።

ህፃኑ ሲመልስ_ እኔ በዚች ምድር ምንም ምፈራው ነገር የለም። እናቴ በጣም ትናፍቀኛለች😔 እሷ ጋር መሄድ እፈልጋለሁ ሲል መልሶለታል።

ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

08 Nov, 17:47


ትዳር ማለት ምን ማለት ነዉ፡፡
ትዳር መስፈርትስ?ከአገቡስ ቡሀላ

ደስ የሚል ለአገቡም ላላገቡም መጠነኛ የሆነ ትምህርት👌

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

06 Nov, 04:10


  #ስለሒጃብ_የተከፈለ_መስዋዕትነት
         አሚር ሰይድ

ይህ ለሒጃባ ስትል የተሰዋችው ለጅልባቧ ስትል የሞተችው የአንደሉሷ ሙስሊም ሴት እውነተኛ ታሪክ ነው። ከስላና ተቃጥላ ስሰሒጃብ ስለክብሯ የወደቀች ድንቅ ሴት! ታሪኳ ሲደመጥ የብዙዎች ቀልብ አንብቷል። ስቃያቸው በስቃይዋ ተደምጧል። በሒጃባቸው ክብር ያልሰጡ አንስቶች ይገሰፁበት ዘንድ ታሪኳን እነሆ

ክስተቱን በአንደበቷ አንዲህ ትተርከው ይዛለች።

“የትውልድ ቀዬዬ አንደሉስ ምድር ነው። በሃያዎቹ የዕድሜ እርከን ውስጥ የምገኝ በሰውነት ቅርጼ ሞላ ደልደል ያልኩ ለግላጋ እንስት ወጣት ነኝ። ግና ይህን ሰውነቴን በጀልባብ ሸፍኜና ጠብቄ ሒጃቤን በአግባቡ እለብሳለሁ። የአንደሉስ ሙስሊሞች የስቃይን ፅዋ በመስቀላዊያኑ እጅ ሲጎነጩ እኔም አልቀረልኝም። ለሁለት ዓመታት የለበስኩትን ጅልባብ ሳላወልቅ ሳላጥብና ሳልቀይር እሥር ቤት ከረምኩ። በወታደሮች ግልምጫና ድብደባ መደፈርና መወገር ብዙ መከራዎችን አሳልፌ የመጨረሻዋ ቀን ላይ ደረስኩ።

    የለበስኩት ጅልባብ ተሰብስቦ ጉልበቴ ጋር ደርሷል። ሰውነቴ በጭቃ ተለውሶ በእግረ ሙቅ ተጠፍሬያለሁ። እጄ የፊጥኝ ታስሮ አንገቴ ላይ በጠለቀው ሰንሰለት እየተጎተትኩ ወደፊት አነዳ ይዣለሁ። በብረት ፍርግርጉ ኋላ ሳልፍ ታሳሪዎቹ በሾሉ ዓይኖቻቸው አፍጥጠው እየተመለከቱኝ የስድብ ናዳ አወረዱብኝ ተፉብኝ። አፈር እየበተኑ ድንጋይ ወረወሩብኝ። የእሥር ቤቱ ጠባቂዎች ጅራፍ በእጃቸው ይዘው ከበቡኝ።

ቀሳውስቱ በአንድነት ቆመው መዝሙራቸውን ያሰማሉ። ባለሥልጣናትና ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው በሚደርስብኝ ስቃይ ለመደሰት ወደ እኔ በትኩረት ይመለከታሉ። ከአንድ ግንድ ጋር ታስሬ ማገዶ በዙርያዬ ተበትኗል። ዘይትና ጋዝ ተርከፍክፎበታል። ከቀሳውስቱ አንዱ ወደእኔ ተጠጋ። ሁለት ምርጫ አቀረበልኝ። ጀልባቤን አውልቄ በህዝብ ፊት ይቅርታ እጠይቅ ዘንድ ዓለይያም ተቃጥዬና🔥🔥ሰውነቴ ነዶ በመሞት መካከል ምርጫ ሰጠኝ። ሒጃቤን እንጂ ሌላን አልመረጥኩም። ከፈለጋችሁ አቃጥሉኝ አልኩ ስለሒጃቤ መሞቴ ለኔ ክብር መሆኑን አላወቁም። አልንበረከክም ፈፅሞ የጌታዬን ትዕዛዝ አልጥስም ብትፈልጉ ሰውነቴን ቆራርጡት በያሻችሁም አካሌን አንድዳችሁ አክስሉት። አዎ! በፍፁም በሒጃቤና በክብሬ አልደራደርም። የክብር መገለጫዬ በከፍታ የሚውለበለብ አስላማዊ ዓርማዬ ነው ብዬ መለስኩለት።

ቄሱ የእሳቱን ነበልባል አንስቶ እንጨቱን ለኮሰው። ሰውነቴ መቃጠል ጀመረ። በቀላሉ አንድሞት አልፈቀዱልኝም እሳቱን አጠፋዉ ። ወደ እሥር ቤቱ ወሰዱኝ። ይህ የእሥር ቤቱን አጥር ተደግፌ የፃፍኩት እውነተኛ ታሪኬ ነው

#ይህን ማስታወሻ የአስር ቤቱ ግርግዳ ላይ አስፈራው ተገኝ፡፡  አጀብ ለአኛ ክብር ስንቶች አልቀዋል።

በጋታው ጠዋት በተመሳሳይ ቦታ የፊጥኝ ታስራ ተሰቃይታ በእሳት ነደደች። ዛሬ ግን አንደ ትላንቱ አላጠፉላትም። ለዓመታት የኖረችበት ስቃይ እነሆ አበቃ። ግን ነፃነቷን አንደሰጧት አላወቁም።

#አላህ መልካም ስራዋን ተቀብሎ ቀብሯን ኑር ማረፊያዋን ፊርደውሰል አዕላ ያድርግባት።

⚠️የአሁን ዘመን ያለን ሴቶች አስተካክለን ሂጃብ የማንለብስ  ነገ የዉመል ቂያማ ስንቀሰቀስ ለእስልምና ለሂጃባቸዉ ዋጋ የከፈሉ እንስቶች ጋር እንዴት አብረን እነሱ ጎን እንቆም ይሆን??
እስልምና በወንድ በሴት ሸሂዶች ደም ዋጋ ተከፍሎበታል...እኛስ ለእስልምና ለሂጃብ ምን ሰራን???



#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ



join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

03 Nov, 05:34


#ከኢማኒያን ለሙስሊም የተጠየቀ ጥያቄና ሙስሊሙ የሰጠዉ ምላሽ


t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

02 Nov, 04:20


  #እናቴ_ሆይ_የክብር_ሞት_ነዉ_የሞኩት_እንዳታለቅሺ 😔


      አሚር ሰይድ

     ትውልደ ኢራናዊት የግራፊከስ ባለሙያ፣ ሱናን የምትከተል ፅኑ ሴት ናት። ሪሐና ጀባሪ ትሰኛለች። አንደ አውጳውያን የዘመን ቀመር በ2007 የቀድሞው የኢራን ባለሥልጣን የቤቴን የውስጥ ክፍል ባማረ ዲዛይን እንድትነድፊልኝ አፈልጋለሁ በማለት ወደ ቤቱ አስጠራት። በአፓርታማው ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ሒጃቧን ገፎ ሊደፍራት ሞከረ።

የሺዐ አምነት ተከታይ ነበርና በእሷ የሱና አቋም እየተበሳጨ "አንቺ የአላህ ጠላት አንቺ ሴተኛ አዳሪ" አያለ የሱሪውን ዚፕ በመክፈት በኃይል መሬት ላይ ሲዘርራት ወደፊት ተጠጋት። በዚህ ጊዜ ነበር ከቦርሳዋ የማይለያትን ስለታማ ቢለዋ መዛ ደረቱ ላይ የወጋችው። ክብሯን ለማስጠበቅ የሰነዘረችው ስለት ሰውየውን ከአፈር ቀላቀለው።

የሺአ እምነት ተከታይ ብሎም የቀድሞ ባለ ስልጣን የነበረን ሰው ሱንይ የሆነች አንዲት ሴት ገደለችው ይህ የተቀነባበረ ሴራ ነው በሚል ተይዛ በኮሀርዳሽት፣ በፋሻፋዬ፣ በአቪጓ፣ በሻህር-ሬይ፣ በራሚን እና በቴህራን ታላቁ አሥር ቤት አየተዘዋወረች ሰሰባት ተከታታይ ዓመታት ማቀቀች።
....ዳኛ ፊት ቀርባ “ለምንድነው የገደልሽው??" ሲል ጠየቃት

“ከክብሬ ለመከላከል ሰሒጃቤ ዘብ ለመቆም” ስትል መለሰች
....ትኩር ብላ የዳኛውን ዓይን እየተመለከተች።

"የሰው ነፍስ ለማጥፋት ይህ በቂ ምክንያት አይደለም" አላት።
..... የሚጉረጠረጡ ዓይኖቿን ፍጥጥ አድርጋ
“ልክ ነህ ለእንዳንተ ዓይነቱ ክብር ሸረፍ ለሌለዉ ሰው ይህ በቂ ምክንያት አይደለም። ክብርህን ስለሸጥክ ምንነቱን አታውቀውም"
.....አለችው የሞት ፍርድ ተወስኖባት ወደ መሰቀያዋ ገመድ እየተራመደች “ #እናቴ_ሆይ የክብር ሞት ነውና የምሞተው አንዳታለቅሽ😔 አንዳታዝኒ” እያለች በ2014 አንገቷ ከገመዱ ገብቶ ተሸመቀቀች።

አላህ በእዝነቱ ይቀበላት!

⚠️የአሁን ዘመን ያለን ሴቶች አስተካክለን ሂጃብ የማንለብስ  ነገ የዉመል ቂያማ ስንቀሰቀስ ለእስልምና ለሂጃባቸዉ ዋጋ የከፈሉ እንስቶች ጋር እንዴት አብረን እነሱ ጎን እንቆም ይሆን??
እስልምና በወንድ በሴት ሸሂዶች ደም ዋጋ ተከፍሎበታል...እኛስ ለእስልምና ለሂጃብ ምን ሰራን???

ምንጭ_ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

29 Oct, 23:01


አንድ ፓስተር በነብዩ ﷺ እና ሙስሊሞችን በምሳሌ በመጥቀስ እንዴት አማኞችን እንደሚያተምር ይመልከቱ

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_pubIlic_group

ISLAMIC SCHOOL

29 Oct, 03:43


⚡️ #ከአንበሳ_ጋር_የተናነቀው_ሙጃሂድ
            አሚር ሰይድ

ሙስሊሞች እና የፐርሽያን ወታደሮች የሠይፍ ትንቅንቅ ቢያደርጉ ሁለቱም በተንጣለለ ሜዳ ላይ ተሰልፈዋል። ከሁለቱም በኩል የሚታየው ትዕይጓት ያስፈራ።

ግጥሚያው ከመጀመሩ በፊት ሁለቱም ቡድኖች ተርታቸውን ይዘው ለጥቂት ደቂቃዎች ከፎከሩ በኋላ ያለምንም ማስጠንቀቅያ ፐርሺያኖቹ የጦር አንበሳቸውን ወደ ሙስለሙ ቀጠና ሰደዱ።

ድልብ አንበሳውም የፐርሺያኖቹን ሠልፍ ሰንጥቆ እየጋለበ ወደሙጃሂዶቹ ሠልፍ መገስገስ ጀመረ። ይህን የተመለከተው ጀግና የሙስለሙን ሠልፍ ሰንጥቆ በመውጣት አንበሳውን ሊጋፈጥ ወደሱ አቀና። ይህ ሲሆን የሁለቱም ሠራዊቶች ትዕይንቱን በዝምታ እየተከታተሉ ነበር። ይህ ጀግና አካሄዱ አንበሳው ሊጋፈጠው ሳይሆን አሱን አጓበሳውን የሚጋፈጥ ነበር የሚመስለው።

አንበሳውም አየጋለበ ሙጃሂዱም እየሮጠ እኩል ሜዳ ላይ ተፋጠጡ። ብልህ ጀግና ነበርና በአንበሳው ጀርባ ላይ  በመውጣት ከላዩ ቁጭ ብሎ በሠይፋ ይቆራርጠው ጀመር። በመጨረሻም አንበሳውን ገድሎ ወደ አጋሮቹ ተመለሰ።

ይህን የተመለከቱ የፐርሺያ ሠራዊቶች አንበሳ ከማይፈሩ ህዝቦች ጋር መጋፈጥ ቢከብዳቸውም ሰልፉን ትተው ከመሸሽ መጋፈጥን መርጠው በሙጃሂዶች የሠይፍ እራት ሆነው አደሩ። ሙስሊሞች ድልን ተጎናፀፉ። በጊዜው የጦር አዛዥ የነበረው ጦርነቱ ከተረጋጋ በኋላ አንበሳውን ወደ ገደለው ጀግና በመሄድ ግንባሩን ሳመው።

ያ ጀግናም ከፈረሱ ወርዶ ዝቅ በማለት የጦር አዛዡን በመሳም፦ " ያንተ ዓይነቱ የኔን ግንባር ሊስም አይገባም” ብሎ ኢስላማዊ መተናነስን በታሪክ መዝገብ ላይ አሰፈረልን። ይህ ጀግና ስሙ #ሐሺም_ኢብኑ_ኡትባ ይባል ነበር።

"አናንተ መኖርን አንደምትወዱት መሞትን የሚወዱ ህዝቦችን ይዤላችሁ መጣሁ" በማለት የተናገረው ኻሊድ አብኑል ወሊድ ያለ ምክንያት አልነበረም!

ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

25 Oct, 03:44


የሚያምር ድምፅ የጁምአ ግብዣ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

03 Oct, 15:08


🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #የመጨረሻዉ_ክፍል
                  አሚር ሰይድ


ዚና ላይ ያለ ትዉልድ መጀመሪያ የሚያጣጥለዉ ትዳርን ነዉ...ከቤተሰብ ጉትጎታ ወይም ጫና ያገባ ከሆነ ደግሞ ለፍች ይቸኩላል፡፡ በተጨማሪ በሀራም ላይ መዘዉተር የአእምሮ እረፍት ስለሌለዉ ራሳቸዉን የሚያጠፉ ወጣቶች ተበራክተዋል፡፡ይህ ሁሉ ዚና ያመጣብን መዘዝ ነዉ፡፡

╔═══════════════════╗
🎖 #ጋብቻን_ማዘግየትና_ማጣጣል🎖
╚═══════════════════╝



     ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአዳጊ ሀገራት ውስጥ ወጣቶች ወደ ትዳር የሚገቡበት አማካይ ዕድሜ ከ25-30 ዓመት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ አዳጊ ወንድ በአማካይ በ16 ዓመቱ ለወሲባዊ ጉልምስና ይደርሳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም በዚሁ ጊዜ ወሲባዊ ኃይሉ ጣሪያ ይነካል፡፡ አንዲት ሴት ደግሞ አሁን አሁን ባለው ጥናት ከ8 ዓመት አንስቶ ለአካለ መጠን ልትደርስ ትችላለች፡፡ ታዲያ በርካታ ወጣቶች ይህንኑ ስሜታቸውን የሚያስተናግዱት የወንድ ወይም የሴት ጓደኛ በመያዝና ዝሙትን በመፈፀም ነው፡፡
#ለምሳሌ የሀይስኩል ተማሪዎችን ብናይ በአንድ ክፍል ውስጥ የወንድ ጓደኛ የማይኖራቸው ጥብቅ ሴቶች ከአስር አይበልጡም፡፡ ይህም ዝሙት ምን ያህል እንደተስፋፋ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

ሌላው ሴት የኮሌጅ ተማሪዎች ዘንድ የወንድ ጓደኛ መያዝን ማበረታታትና ትዳርን ማጣጣል እየተለመደ መጥቷል፡፡ ሴት ሙስሊም የመንግስት ሰራተኞች ዘንድም ይኸው ችግር እየተወራረሰ ይገኛል፡፡ ሁሉንም የሚያመሳስላቸው ነገር ደግሞ ቦይፍሬንድ መያዝን እንደ ጤናማ የህይወት ልማድ ማየታቸው ነው፡፡ በእውነቱ ይህ ትልቅ ውድቀት ነው፡፡ ለዝሙት መስፋፋትም ትልቁን አስተዋፅኦ እያበረከተ ያለው ይኸው ቦይ-ገርልፍሬንድነት ነው፡፡ ደዌው ወደ ሙስሊሞችም ተጋብቷል፡፡





         ╔════════════╗
          🎖  #የፍቺ_መበራከት🎖
         ╚════════════╝



   በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል የፍቺ መበራከት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረና ከባድ ቀውስን እየፈጠረ ያለ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በቅርቡ በተገኘው አንድ መረጃ እንኳን ከ14 ትዳሮች መካከል 12ቱ ሶስት ወር ሳይሞላቸው ፈርሰዋል፡፡ ይህ በውነቱ በጣም አስደንጋጭ ነው፡፡ አንዳንዶች ሙስሊሙ ወጣት ወደ ትዳር ሲቻኮልና በከተማዋም የሙስሊም ሰርግ በዝቶ ሲያይ ይደሰት ይሆናል፡፡ ግና በዚያው ልክ የሚፈርሱትን ትዳሮች ቢያይ በእጅጉ ያዝናል፡፡ ሙስሊሙ ወዴት እየሄደ ነው? በሚል ሀሳብም ይባዝታል፡፡ ለፍቺ መበራከት ትልቁ መንስኤ ደግሞ የተጋቢዎች ከትዳር በፊት በየፊናቸው የሚፈጥሩት ፆታዊ ግንኙነትና ዝሙት ነው፡፡

እንደሚታወቀው ከትዳር በፊት በርካታ ወጣቶች በቦይ–ገርል ፍሬንድነት (በወሲብ አጋርነት) አብረው ይቆያሉ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ አብረው የሚቆዩቱ ግን አብዛኞቹ ግንኙነታቸው በጋብቻ አይቋጭም፡፡ ከዚህም የተነሳ ሁሉም በየፊናው ሌላ የትዳር አጋር ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ግን ከዚህ በኋላ የሚመሰርቱት ትዳር ስኬታማ የመሆን ዕድሉ በጣሙን ዝቅተኛ ነው፤ ምከንያቱም ከትዳር በፊት ያለውን የወሲብን ሕግ ያላከበረ ከትዳር በኋላም ይህንኑ ልማዱን ይደግመዋልና ነው፡፡ ከዚያም ሁለቱም በየፊናቸው ሂያጅነትን ይጀምራሉ፡፡ ሂያጅነት ወደ ትዳራቸው ሲገባ ደግሞ ትዳሩ ወዲያው መናወጥ ይጀምራል፡፡ ቤቱ መረጋጋት ይሳነዋል፡፡ በውጤቱም ፍቺ ወሃን የመጠጣት ያህል ይቀላቸዋል፡፡ ከዚያም ወጣቱ « #ኒካህሽን_እንቺ››፣ «ትሄጃለሽ ወይስ ታድሪያለሽ በሶስት ፈትቼሻለሁ ወዘተ እያለ ትዳርን መቀለጃ ያደርገዋል፡፡ይህም ችግር ስራ የሰደደና ትልቅ ማህበራዊ ቀዉስን ፈጥሯል፡፡

እኔ ብዙ ለትዳር የደረሱትን ለምን አታገቡም?ትዳር ሲመጣላችሁ ለምን ትመልሳላችሁ?ብየ ስጠይቅ የብዙዎች መልስ ከተጋባን ቡሀላ ቢፈታንስ እያሉ በጓደኞቻቸዉ የደረሰዉን የፍች ታሪክና ሳይፋቱ ደግሞ ሴቶች ባለቻቸዉ ጋር እየኖሩ እንደሆኑ በማስረጃ ነግረዉኛል፡፡የፍች ስታቲክስ በየአመቱ የሚያሳየዉ በብዙ እጥፍ እንደሆነ ነዉ፡፡ደግሞ የሚገርመዉ በፍች ብዛት የሚያሳየዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ቀዳሚ መሆኑ ነዉ፡፡



╔══════════════════════╗
  🎖 #እራስን_የማጥፋት_ወንጀሎች_መበራከት
╚══════════════════════╝




    ጥናቶች እንዳመለከቱት ዝሙትና እራስን የማጥፋት ወንጀሎች የተቆራኙ ናቸው፡፡ በተጨማሪም እነዚያ በወሲብ ንቁ (አክቲቭ) የሆኑ ልጆች ከነዚያ እስከ ኒካህ ድረስ ወሲብን ከመፈፀም ከሚታቀቡት ይበልጥ ከሁለት ጊዜ እጥፍ በላይ በጭንቀት የመወረር ዕድላቸው ከፍ ይላል፡፡ ጥናቶቹ አያይዘውም እንደጠቆሙት እነዚያ በወሲብ ንቁ የሆኑ አዳጊ ወንዶች ከአስር ጊዜ እጥፍ በላይ እራሳቸውን የማጥፋት ሙከራን ያደርጋሉ፡፡

📌 #ሴቶችን_በተመለከተ ደግሞ እነዚያ ከጋብቻ በፊት ወሲብ የሚፈፅሙ አዳጊና ወጣቶች ሴቶች ከነዚያ ከማይፈፅሙቱ ሶስት እጥፍ እራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ እንግዲህ የዝሙት ዋጋ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ የዝሙት ፈጣን ዋጋው ሴሰኝነት ነው፡፡ ሴሰኝነትን ተከትሎ ደግሞ ከበሽታ ባሻገር ጭንቀት ብቅ ይላል፡፡ ጭንቀት ደግሞ ራስን ለማጥፋት ትልቅ መንስኤ ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ በኋላ ምንድነው ይሆናል ብለህ የምትጠብቀው? አዎን! ጭንቀት እራስን ለማጥፋት ትልቁ መንስኤ ነው፡፡


✏️✏️ #ራስን_ማጥፋትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሁለት ዓመታት በፊት በእስጢፋኖስ አበራ የተዘጋጀና በጥልቅ የዳሰሰ ጥናት የተደገፈው መጽሐፍ ላይ እንድ አስደንጋጭ እውነታን ቀርቧል፡-

ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ነገር ግን የነገሮች ግጥምጥሞሽ ሁሌም ያስደነግጠኛል፡፡ የነገሮች ግጥምጥሞሽ ሁሌም ያስጨንቀኛል፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ተመሳሳይ ነገሮች በአንድ ጊዜ ሲከሰቱ ሳይ በጣም እረበሻለሁ፡፡ ለምን እንዲህ ሆነን ብዬም እራሴን ደጋግሜ እጠይቃለሁ፡፡ መልስ ፍለጋም እራሴን ብዙ ጊዜ አስጨንቃለሁ፡፡ መልስ እስከማገኝ ድረስም ስለተፈጠረው ጉዳይ ጊዜ ሰጥቼ ማሰብ እና ማሰላሰል እጀምራለሁ፡፡»የሚል አካቷል

በተጨማሪ የመፅሀፉ ርዕስ «ውስጠ አዋቂ - ከአዲስ አበባ ጓዳ እስከ አደባባይ.. የተሰኘ ሲሆን እራስን ማጥፋት ሌላኛው የአዲስ አበባ ፋሽን፡ በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በአዲስ አበባ እራስን የማጥፋት ወንጀል በወጣቶች ዘንድ እጅጉን መጨመሩን ይገልፃል፡፡


✏️✏️ #ወደ_ሙስሊሞች_ስንመጣ ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ከኮልፌ መስጂድ ኢማም በመስጊድ ሲናገሩ እንደተሰማው እራስን የማጥፋት ወንጀል ተበራከቷል፡፡ እንደሚታወቀው በተለምዶ ኮልፌ አዲሱ መስጂድ ጀናዛ ሶላት በብዛት ይሰገዳል፡፡ በዚህም መነሻነት ለኢማሙ የሰዎችን አሟሟት አስመልከቶ በርካታ መረጃዎች ይደርሷቸዋል፡፡ የሟቾችን ሁኔታ ሲጠይቁ እራሳቸው ያጠፉ ወጣቶች እንደሚገኙባቸው ይነገራቸዋል፡

የወንጀል መጨረሻዉ ይሄ ነዉ መፍትሄዉ ከዝሙት መራቅ በዝሙት መስመርም ያለ እንደ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት ቶብቶ አልቅሶ ከወንጀል ፀድቶ አዛኝ ረሂም ለሆነዉ ጀሊሉ እጅ መስጠት ነዉ፡፡ በዝሙት ላይ እገፋለሁ ያለ ምርጫዉ በእጁ ነዉ በዱንያ ደስታ ማጣት የእርዚቅ መገፋት እና አሏህ እንዳለን ለወንጀለኞች ብርቱ የሆነ ቅጣት ይጠብቃቸዋል እንዳለዉ የአሏህን ቅጣት እወጠዋለሁ ጀሀነም ይሻለኛል ያለ ምርጫዉ በእጁ ነዉ፡፡👇👇👇

ISLAMIC SCHOOL

02 Oct, 16:58


በዉብ ቃሪዕ የቁርአን ግብዣ
ያዳምጡት ...ሼር አይዘንጉ

https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

01 Oct, 16:14


እኔ በአይኔ ሁለት ልጆች ወልደው አይቻለሁ፡፡»የላይኛዉ ምንጭ መፅሀፍ ገፅ 54

🔰 እቴጌ ገረመዉ ባዘጋጀችዉ የጭን መነባንብ በሚለዉ መፅሀፏ ገፅ 98 ላይ እንዲህ ብላለች

    «የኮሌጅ ተማሪዎች ድብቅ እውነታዎች ባሕር ዳር፦ የሀገራችን ተማሪዎች ከሚታሙባቸው የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ይማግጣሉ ከሚባሉት ከተማ እንደመሆኗ ለመታዘብ ቸኮልን፡፡ ወሲብ ንግድ ያጧጡፋሉ የተባለላቸውን ተማሪዎቻችን አመሸሽ ለመቃኘት የሚባለውን ነገር ለመታዘብ አንድ ቤት ከ30ደቂቃ በላይ መቆየት እያስፈልግም::ግን ይህን የሚያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ አፎን ከፍተው ሲመለከቱ ሊመሽብዎት ይችላል፡፡

  የአብዛኞቹን የሴት ልጆች አለባበስ የቡና ቤት ሴቶችም ሲሞክሩት የምንሸማቀብበት አይነት ነዉ፡፡እጆቻቸዉ እግሮቻቸዉ ሁሉ ስራ የበዛባቸዉ ናቸዉ፡፡ በአንድ እጅ ሲጋራ በአንድ እጅ ቢራ፣ መጨፈር፣ መጮኸ፤ በየሙዚቃዉ የሚያስጨፍሩት ወንድ መለያየት
ከሚያስጨፍሩት ወንድ ስልክ መቀበል፣ በሚያስጨፍሩት ወንድ አንገት ውስጥ መወሸቅ፣ በሚያስጨፍሩት ወንድ መተሻሸት፣ወዘተ ....እነዚሁ ሁሉ እጅግ አሸማቃቂ ድርጊቶች ናቸው፡፡ ይሄ ለእነሱ ጀብዱ ሁሉ የመሰላቸው ይመስለኛል፤ ያለማፈራቸውና ድንገት የሚያውቀኝ ሰው ቢመጣ ብለው ግራ ቀኝ ያለመገለማመጣቸው፡፡ ተመልካች ሆነው እንኳን ያፍራሉ፡፡ በተለይ እነሱን በማስተናገድ የሚታወቁት ቤቶችም ጢም ያሉ ናቸው:: እኛ ተማሪዎች የሚገኙበት ቤት ብለን እንደመጣን ሁሉ የመጡ ይሄኔ ስንት ይኖራሉ? በዚያ ላይ ጥሩ ዋጋ ያወጣሉ ሲሉም ሰማሁ፤ እንግሊዘኛ ይሞካከራሉና፡፡ የዚያኑ ያህል ሴቶቹ ከገንዘቡ ይልቅ የሚማርካቸው ግዳይ ጥለው ማደራቸው መሆኑ ይወራል፡፡



     ╔═══════════════╗
        🎖 #ዲላ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
     ╚═══════════════╝

 
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የሚስተዋሉ አጓጉል ወሲባዊ ባህሪያት (ዓባይነህ አናሾ እና ታረቀኝ ታደሰ የታተመ ጥናታዊ ጽሑፍ)

     እስካሁን እንደተገለፀው በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የሚታዩ ዋና ዋና አደገኛ ተያያዥ የወሲብ ባህሪያት እርስ በርስ ለወሲብ መነሳሳት።በአደባባይ መሳሳምና መተሻሸት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ያለ ኮንዶም ወሲብ መፈፀም፣ በርካታ የወሲብ ጓደኞችን ማፍራት፣ ያልተፈለገ እርግዝና፣ ማስወረድና ከሴተ አዳሪዎች ጋር መዳራት ናቸው፡፡

አደገኛ ወሲባዊ ባህሪይ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ላይ፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲዎች፣ የ ኮሌጆችን ጨምሮ የሚስተዋል ነው፡፡



╔═════════════════╗
   🎖 #ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═════════════════╝

    

   ከአዲስ አበባ ከተማ 513 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውና በ2010 እ.ኤ.አ ለ14ሺ ተማሪዎች የትምህርት ገበታ በዘረጋው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ላይ የኤች.አይሺ ሥርጭትን የሚገመግም ጥናት ተካሂዶ በአቶ ታሪኩ ደንጌታ አማካኝነት ለሕትመት በቅቷል፡፡ በጥናቱ መግቢያ ላይ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው በዩኒቨርሲቲ የሚኖሩ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ከሌሎች ወጣቶች በተለየ መልኩ ለኤች አይ.ቪ በሚያጋልጡ አደገኛ ድርጊቶች ላይ እንደሚሰማሩ ተገልጿል፡፡

⚡️⚡️በጥናቱ ላይ ከተሳተፉት ተማሪዎች ዉስጥ  
☞ 22.8% የሚሆኑት ወሲብን ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀሙት ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
☞ ወሲብ የመፈፀም ልምድ እንዳላቸው ከተናገሩት ወንድ ተማሪዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር አንሶላ የሚጋፈፉ መሆናቸውን እራሳቸው አምነዋል፡፡
☞ እንዲሁም ኮንዶም በአግባቡ የማይጠቀሙት 60% መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡

   ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሌሎች ወጣቶች በተሻለ ተምረዋል የሚባሉ ቢሆኑም ኮንዶም አለመጠቀምን ጨምሮ ሌሎች ጥንቃቄ የጎደላቸው ድርጊቶችን ሲፈፅሙ የሚስተዋሉ እነርሱ ናቸው፡፡ በተለይ ወሲብ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈፅሙ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ኮንዶም የመጠቀም ዝንባሌያቸው በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ መደብር ጎራ ብለው ኮንዶም ለመግዛት ስለሚያፍሩ ነው፡፡

╔═══════════════════╗
    🎖 #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═══════════════════╝
      

እትጌ ገረመዉ የጭን መነባንብ ሌሎችም በሚለዉ መፅሀፍ ከገፅ44-45 ድረስ ስለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይህ ሰፍሯል

   (ሊሊ!) እኔ የምልሽ! የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወንዶች እናንተ ጋ ሊዝናኑ አይመጡም? ሊሊ ይመጣሉ፤ ግን እነሱን ሌላ ቢዝነስ መፈለጊያ ነው የምንጠቀምባቸው፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከየት አምጥቶ ያወጣሻል? ማታ ቺቺኒያ አመሸሁ ለማለት ነው የሚመጡት፡፡ ለአልጋ መያዣ እንኳን ብር ስለማይተርፋቸው እስኪነጋ ድረስ ሲጨፍሩ ነው የሚያድሩት፡፡ እነሱን ለዳንስ ነው የምንጠቀምባቸው፡፡ በጣም አሪፍ ደናሾች ናቸው፡፡ ከነርሱ ጋር ሰትደንሺ የሚጎትትሽ አይጠፋም፡፡ ደግሞም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ቢኖረውም ማውጣት የለብሽም፤ አይፋቱሽማ፡፡ አንድ ቀን ካወጡሽ በቀን ሊያገኝሽ ይፈልጋል፤ ካልቃምን፣ ወደድኩሽ ምናምን እያሉ ይጃጃላሉ፡፡ስራ ቦታ በዚያ ምሸት ባዶ እጁን መጥቶ ውጭ አስጠርቶ እትት ሊል ይፈልጋል፡፡ አሁን አሁን ሁሉም ሴት ሰላወቀ ብር ቢኖራቸው እንኳን ማንም እሺ አይላቸውም፡፡»

በምን ታውቋቸዋላችሁ? ይለያሉ ማለት ነው? ልጅነታቸው፣ ሁለትና ሶስት ሆነው መምጣታቸው፤ አስሬ ብራቸውን እያወጡ መቁጠራቸው በአንድ ዕይታ ያሳልቀባቸዋል:: የሚጀምሩት በዳንስ መሆኑ መለያቸው ነው፡፡ እየደነሱ ሊገቡ ሁሉ ይችላሉ፡፡ ብታያቸው በዳንስ እና ስራችን የሆነ ቢዝነስ ማሯሯጫ በየቀኑ የምናስነካዉ እንኳን አንደርስባቸው ... የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ፌስቡክ የለሽም? የፌስቡክ አድራሻሽን ስጪኝ ስለሆነ #ላይክ ነው የምንላቸዉ፡፡ካለ እነሱ አራዳ ያለ አይመስላቸዉም፡፡ነገ ከቤተሰብ ስለሚላከልኝ ለዛሬ ተቸገሪልኝ የሚለው ብዛቱ ቀላል እንዳይመስልሽ፤ ባለፈው ሳምንት እምቢ ብለሽው ተመልሶ እንደ ጫትና ሲጋራ ለዱቤ ጥየቃ ይንጓተትሻል፡፡ ዱቤ መጠየቅ ከልክል ነው ብለን እንነቀስላቸው እየተባለ ሙድ የሚያዝባቸው ናቸው:፡»”


  ✏️✏️በጥቅሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻችን ገመና ባጭሩ ከሞላ ጎደል እስካሁን ያየነውን  ይመስላል፡፡ የዩኒቨርሲቲዎች መብዛት ብቻውን ለምሁር መፍለቅ በቂ አይደለም፤ ምናልባትም ትምህርትን ለብዙኃን ለማዳረስ ካልሆነ በቀር፡፡ ልክ ዩኒቨርሲቲዎች የበዙትን ያህል ተማሪውን ከትምህርቱ የሚያግዱ ነገሮችም አብረው ይበዛሉ! ምናልባትም ከዚያ በብዙ እጥፍም ሊያድጉ ይችላሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ተማሪው ከትምህርቱ ይታገዳል፡፡ ተማሪው ካልተማረ ደግሞ አስተማሪው አያስተምርም፡፡ ይህም በመሆኑም ተማሪው ትምህርቱን እንዲማር የተለያዩ ሥራዎች መሠራት አለባቸው:: በዚያው ልክ ተማሪውን ከትምህርቱ የሚያግዱ ነገሮችም እንዲጠፉ አብዝተው መሥራት ግድ ይላል፡፡


#በመጨረሻዉ_ክፍል
በዚና የተበከለ ትዉልድ የመጨረሻ ዉጤቱ
ጋብቻን ማዘግየትና ማጣጣል..የፍች መበራከት...እራስን የማጥፋት ወንጀሎች መበራከት በህብረተሰቡ ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ እንዳስሳለን


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

01 Oct, 16:14


🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #ምዕራፍ_አስር_ሰባት ➊➐
                  አሚር ሰይድ


╔═════════════════╗
      🎖 #የዩኒቨርሲስቲ_ገመና 🎖
╚═════════════════╝

ዩኒቨርስቲዎች ሁለት ጥቅም አላቸዉ ለሀገር የሚጠቅሙ ተማሪዎችን ማፍሪያና በዛ በተዘዋዋሪ ደግሞ ዩኒቨርስቲ ከገቡ ቡሀላ  ለአገር የማይጠቅሙ እነሱ ተበላሽተዉ ሌላ ትዉልድን የሚያበላሹ ተማሪዎች መፈልፈያ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ዩኒቨርስቲዎች ለወላጆች #ወልዶ_መጣያ ከሆኑ ሰነባብተዋል፡፡
ወላጅ ተጨንቆ አስቦ ከራሱ ቀንሶ ለተማሪ ልጄ ይላል ..ተማሪ ግን በጓደኛ ግፊት..የቤተሰብ ቁጥጥር ዩኒቨርስቲ ዉስጥ አለመኖር አላማቸዉን ዘንግተዋል፡፡በፊት ሴት ልጅ ሰነፍ ከሆነች አትማር ስል ብዙ ተከታዮች ለሌላ ይመስላቸዋል ግን ዩኒቨርስቲ ገብተዉ ያለዉን ፈተና መቋቋም ስለማይችሉ በማሰብ ነዉ ለምን በፊት ተማሪ በዉጤቱ በጉብዝናዉ ሳይሆን በኩረጃዉ በትቤት ህግ መላላት ምክንያት ነበር ወደዩኒቨርስቲ የሚገቡት..,እድሜ ይስጠዉና ዶክተር ብርሀኑ ነጋ እየሰራ ያለዉ ስራ በጣጣም አበረታች ነዉ...ተማሪን እያየን የtiktok ትዉልድ እያየን ነዉ በጀመአ ሲወድቅ፡፡ እኔ የሚገርመኝ እኛን የሚያስተዳድሩን በየመስሪያ ቤቱ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ከስንት አንድ ካልሆነ ጎበዝ ሁነዉ በትምህርት ደረጃቸዉ የሚያስተዳድረን እንጂ ከዛ ዉጭ ያለዉ በፊት በነበረዉ የዩኒቨርስቲ ፓሊሲ የተማሩ መሆናቸዉ በነዚህ ሰዎች ሙስና ይቀራል ማለት ዘበት ነዉ፡፡ ግን አሁን የተጀመረዉ ዩኒቨርስቲዎች ራሳቸዉን በራሳቸዉ ማስተዳደራቸዉ በጣም አሪፍ ነዉ፡፡
የዩኒቨርስቲ ትርጉሙና ትክክለኛ ተማሪ የሚገባት ከዘንድሮ ጀምሮ ይሆናል፡፡
በተጨማሪ በግል ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎችም ከዩኒቨርስቲ ህይወት ጋር በዚና መስመር እንደሚመሳሰሉ ማወቅ አለብን....

ለወደፊት ትምህርት ጥረት ይጠይቃል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተዘፍዝፎ የtiktok ፎሎዉ በመቁጠር ትምህርትን መጨረስ አይቻልም፡፡


ከታች ያለዉ ፁሁፍ በዝሙት መዘመን ስልጣኔ ወይስ የአለም ፍፃሜ በሚለዉ መፅሀፍ ከዛሬ 8አመት በፊት የተፃፈና የጥናት ፁሁፍ አቀርባለሁ...ዛሬስ ከ8ወይከ9አመት ቡሀላ የዚና ስልጣኔ መንገዶች በዝተዉ ዛሬ ላይ የዩኒቨርስቲ ዘመቻ በስንት ፐርንሰት ጨምሮ ይሆን??

╔══════════════════╗
        🎖 #ሐዋሳ_ዩኒቨርስቲ 🎖
╚══════════════════╝

«ዩኒቨርሲቲው ፆሙን ነው የሚያድረው፡፡» (ብሌን ሰይፈ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማጅመንት

ሄለን አለሙ የዩኒቨርስቲ ገመና በሚለዉ መፅሀፏ ሀሐዋሳ ዩኒቨርስቲ  ከተማረች ይሄንን ፅፋለች

‹‹ከዩኒቨርሲቲው ልጀምር፤ በተለይ ማታ ላይ ባዶ ይሆናል፡፡ ተማሪው ውልቅ ብሎ ይወጣል፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹ዩኒቨርሲቲው ፆሙን ነው የሚያድረው የሚለው ቃል ይገልፀዋል፡፡ የቀን ተማሪ ከማታ ተማሪ ጋር ተቀላቅሎ በባጃጅ እየተጋፋ ይወጣል። የሚገርመው የማታ ተማሪዎች የባጃጅ እጥረት እየገጠማቸው ግማሽ መንገድ በእግር ለመሄድ ይገደዳሉ፡፡ ለቀን ተማሪዎች ያ ሰዓት የማምለጫ ሰዓት ነው የሚመስለው። ውልቅ ብለው ሲሄዱ ሴት ከወንዱ በጣም ብዛት አለዉ

   አንዳንዴ ትልልቅ የቤት መኪኖች ቆመው ሲታይ ሠርግ እየታጀበ ይመስላል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ የመኪና ኤግዚቢሽንም ሊመስል ይችላል፡፡ በርካታ መኪና ይቆማል፡፡ መኪኖቹ የሚቆሙት ተማሪ ጥበቃ መሆኑ ይታወቃል። ሆን ተብሎ እዚያ አካባቢ ሴት ተማሪዎችን ለመጠበቅ ይቆማሉ፡፡ ተማሪዎች የሚወጡበት ሰዓት ይታወቃል፤ ይቀጣጠራሉም፡፡

ተማሪዎችን የሚያሻሽጡ ደላሎችም አሉ፡፡ ደላላ የሌለበት ምን ነገር አለ? ያለ ደላላ ይሄ ነገር ሊፈጠር አይችልም፡፡ ለምሳሌ አንድ ሀብታም ዩኒቨርሲቲ መጥቶ ተማሪ ለመጥበስ ይጓተታል ማለት ዘበት ነው:: ቢሞከርም የሚሳካለት ከስንት አንዱ ነው፡፡ ይሄም ይሳካል ብዬ የማስበው አንዳንዴ ከግቢ በፀሐይ ትወጪና ባጃጅ ልታጪ ትችያለሽ፡፡ ያኔ ሊፍት ሲሰጥ የሚሄድ ተማሪ ሊኖር ይችላል፡፡ መጠባበሱም
ሊፈጠር የሚችለው በዚህ አጋጣሚ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ብዙ ነገር የሚጧጧፈው በደላላ ነው፡፡ ሀብታምም መጥቶ በር ሲቆም ያለቀ ነገር ይዞ ለመሄድ ነው፡፡ ልክ ተጠቅሎ እንደተቀመጠ የሱቅ ዕቃ እንጂ ገና ዋጋ አይደራደርም፡፡ ደላሎቹ ደግሞ ከውጭ ብቻ የሚመጡ አይደሉም፡፡ ከውስጥም (ከተማሪዎች) አሉ፡፡ የእነሱ የሱሳቸው የመሸፈኛ ገቢ የሚገኘው ሴትን ከሀብታሞች ጋር በማቃጠር ነው::


╔═══════════════════╗
     🎖 #አርባ_ምንጭ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═══════════════════╝


«የሴቶችና የወንዶች ዶርም በጣም ተቀራራቢ ስለሆነ ሴት ለማግኘት ድካም የለብንም፡፡»(ዳዊት ተስፋሁን፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒዉተር ሳይንስ ተማሪ)

«እንደ እንስሳ በየሜዳው የሚፈፅሙት ወሲብ ከአዕምሮ በላይ ነው የሆነብኝ (አዜብ ኃይሉ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዎሎጂ ዲፓርትመንት ተማሪ)

‹‹የካምፓስ ሕይወት ከባድ ነው፡፡ወደዛ ስንገባም ብዙ ነገሮች ይነገሩናል፡፡ተማሪ ጥሩም መጥፎም እንዳለ፣ ተማሪ በኤች.አይ.ቪ እንደሚያዝ፣ ከእንዲህ ዓይነት ልጆች ጋር አትግጠሚ፤ እንዳትበላሺ የሚሉና መሰል ምክሮች ከቤተሰብ ተነግሮኝ ነበር፡፡ ያኔ ምክሩን ባልንቅም ግን እውነት አይመስለኝም ነበር፡፡ነገር ግን ብዙ ነገር አየሁ፡፡ጥሩ የሚሆነው ግልፅ ካወራን ነው፡፡ ግልፅ እንነጋገር ከተባለ እዛው ሜዳው ላይ በግልፅ ወሲብ ይደረጋል፡፡ ወሲብ በጣም ከሚደረግባቸው ቦታዎች ውስጥ በጣም ከፍተኛው ስቴዲየም አለ፤ ኳስ ሜዳው ላይ ጨለም ሲል እዛ ሁሉም ተማሪ ወሲብ ያደርጋል፡፡
ከማስታውሰው ነገር አንዱን ልናገር፡፡አንድ ቀን እያጠናን ድንገት መብራት ይጠፋል፡፡አብራኝ ስታጠና የነበረችው የዶርሜ ልጅ ናት፡የሄደችውም እንደኔው ከአዲስ አበባ ነው፡፡እና ከዚህች ጓደኛ ጋር ስናጠና መብራት ጠፍቶ ወደ ዶርም ለመሄድ መንገድ ስናቋርጥ ድምፅ ሰማን፤ እያጠኑ ነው ብለን ነበር፡፡ነገር ግን እነሱ ወሲብ እያደረጉ ነው፡፡ የምሬን ነው! እረግጠናቸው ነው የተራመድነው፤ በጣም በጣም የሚያስጠላ እንደዚህ ዓይነት ነገር አለ፡፡ እኔ ይህ እንደ እንስሳ በየሜዳው የሚፈፅሙት ወሲብ ከአዕምሮዬ በላይ ነው የሆነብኝ፡፡ በየሜዳው ወሲብ ሲያደርጉ በጥበቃዎች ይያዘሉ፡፡»የላይኛዉ ምንጭ መፅሀፍ ገፅ 61


╔═════════════════╗
     🎖 #ባህር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═════════════════╝

    

«በ2003 ብቻ 600 ተማሪዎች አስወርደዋል፡፡» (እየሩሳሌም ፍቃዱ - በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሊትሬቸር ተማሪ)

«እዚህ ገምቼ የሄድኩት ትምህርት ፈልጌ ነው፡፡ነገር ግን እዚያ ከሄድኩ በኋላ ብዙ ነገር አይቻለሁ፡፡ እኔ በነበርኩበት ጊዜ ግቢ ውስጥ በፀረ-ኤድስ ክበብ እሳተፍ ነበር፡፡ እዚያ ውስጥ ስታቶች ሲሰሩ አያለሁ፤ በዓይናችንም የምናየው አለ፡፡ ብዙ መጥፎ ነገሮች አሉ፡፡ በዚያው ልክ ብዙ ጥሩ ነገሮች አሉ፡፡

#ለምሳሌ እኔ ካየሁት ዉስጥ ባህርዳር ፓፒረስ የሚባል ትልቅ ሆቴል አለ፡፡ፈረንጆች ይጠቀሙበታል፡፡የግቢ ልጆች ስልክ ቁጥር ከሆላ የተፃፈበት ፎቷቸዉ ከዚያ ይገባል፡፡ልክ እንደ ካታሎግ፡፡የመረጣትን ደዉላችሁ ጥሩልኝ ይላል፡፡በዚህ መልክ ከትምህርት ባሻገር ሌላ ስራ ይሰራሉ ማለት ነዉ፡፡ግቢ ዉስጥ በ2003 ብቻ 600 ተማሪ ነዉ ያስወረደዉ፡፡በአንድ አመት ዉስጥ የተሰራ ስታቲክስ ነዉ፡፡ግቢ ዉስጥ የሚወልዱም አሉ፡፡👇👇👇

ISLAMIC SCHOOL

30 Sep, 18:00


💚ነብዩ ﷺ አኢሻ ረዐ ለምን 9 አመቷ ላይ አጯት?ብለዉ ለሚጠይቁ ሰዎች መልስ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

29 Sep, 16:21


⚡️⚡️ ከ1954-64 ዓ.ም. የግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ የእልፍኝ አሽከር የነበረ፣ስዩም ጣሰው የተባለ ታዛቢ «የንጉሡ ገመና» በሚል ርዕስ ካዘጋጀው ዜና መዋዕል የተቀነጫጨበ ዘገባ እነሆ፡፡

«ከግርማዊነታቸው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሴቶች፣ አብዛኞቹ በዚህ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የሚሠሩ ናቸው፡፡ የሴቶቹም ዓይነት እንደሚከተለው ነው፡፡ እነርሱም
☞የጽዳት ሠራተኞች፣
☜የአበሻ ወጥ ቤቶች፣
☞እንጀራ ቤት፣
☞ ቅንጬ ቤት ሲኾኑ፣ ከውጭ ደግሞ ያሉት ከተለያዩ ቦታዎች ነው፡፡ ሴቶቹ አብዛኛውን ጊዜ የሚገቡት ቀን ከምሳ መልስ፣ ዕረፍት በሚያደርጉበት ጊዜ፣ ከ8- 10፡3ዐ ሰዓት ባለው ሰዓት ውስጥ ነው፡፡ ጃንሆይ ገብተው ከተኙ በኋላ፣ ትንሽ ቆይተው ደወል ይደውላሉ፡፡ በዚያን ጊዜ፣ በዚህ ነገር የተለየ ባለሟል የኾኑ አሽከሮች በተራቸው ይገቡና < #እከሊትን_ጥራ> ሲባል ይጠራል።

«ምናልባት እርሱ ከተጠራችው ሴት ጋር ሽርክና ከሌለው፣ ወይም ከምትወስደው ገንዘብ በብዛት ካላካፈለቸው፣ <እርሷ አኹን የለችም> በማለት፣ የርሱ ሽርክ፣ ብዙ ገንዘብ በየጊዜው የምትሰጠውን ሴት <እከሊት አለች፡፡ እርሷ ከሥራዋ አትጠፋም> በማለት ይቀላምድና ይጠራል፡፡ሲገቡና ሲወጡ የተለየ ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡ነገር ግን፣ ሴቶቹ በሚያሳዩት መለዋወጥ የተቀረው ሰው እዚያ ቦታ እንደ ደረሰች ይገባዋል፡፡ ቢሮ የሚደረገው ደግሞ ሌላ ነው፡፡ ቢሮ በሚሠሩበት ጊዜ፣ ረፈድ ሲልና አንዳንድ ባለሥልጣኖችን ካነጋገሩ በኋላ፣ ገለል ብለው ቢሮ አጠገብ ካለው መኝታ ቤት ጐራ ይላሉ፡፡ ከዚያም፣ በዚያ አካባቢ ከሚሠሩት ሴቶች ውስጥ የፈለጉዋትን አስጠርተው፣ ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ፣ ወደ ቢሮአቸው ይገባሉ፡ መኝታ ቤቱና ቢሮው በጣም የተቀራረበ በመኾኑም ሌላ፣ በዚያ አካባቢ ማንም ሰው አይገኝም፡ መግቢያውም የተለያየ ስለሆነ፣ጃንሆይ ወደዚያ ሲሄዱ፣ ወደ ሽንት ቤት እንጂ፣ ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳሉ ብሎ ከቢሮ ያለው ባለሥልጣን አይገምትም፡፡ሆስቴሶቶችንና ሌሎችን ደግሞ ምድር ቤት ካለው ቢሮ ነው የሚያገኙዋቸው፡፡

«የገንዘብ አሰጣጣቸው ደግሞ ሌላ ነው፡ የሚሰጣቸው እንደ ሴትየዋ ኹኔታ ነው፡፡ለምሳሌ፣ ለሥራ ቤት፣ እንጀራ ቤትና ወጥ ቤት የሚሰጣቸው በጣም አነስተኛ ነው።በመቶ የሚቆጠር ሲሆን፣ከፅዳት ሠራተኞች ደግሞ እንደ ሴትየዋ ሁኔታ ነው፡፡ ነቃ ነቃ ያሉት፣በብዙ ሺህ ብር ይወስዳሉ፡፡ ይሀውም፣ ከ70-80 ሺህ ብር ይሰጣታል፡፡ ከዚሁ ውስጥ ከ5-10 ሺህ የሚጠጋ ብር ለአስገቢዋ ቀረጥ ትከፍለዋለች፡፡ ስለዚህ፣ በዚያ ቦታ ያሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የወጣላቸው ሀብታሞች ይሆናሉ።በዚያ ውስጥ ያሉ ሴት ሠራተኞች መጠነኞቹ ማለቴ ነው፡፡በተቀጠሩ ከ7-10 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ፣ በሺህ ሳይሆን፣ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ንብረት ይኖራቸዋል። ግማሾቹ! እንዲያውም ለሽርሽር ፈረንጅ አገር ድረስ መሄድ አለብን እያሉ፣ በመንግሥት ኪሳራ ለራሳቸውና ለአስተርጓሚያቸው ጭምር እየተከፈለ፣ ተንሸራሽረው የተመለሱ አሉ

«ጃንሆይ ፈረንጅ አገር ሂደው ሲመለሱ፣ ለየአንዳንዱዋ ገረድ የአልማዝ፣ የወርቅ ጌጣጌጥና ሰዓት በብዛት ያመጡና ያከፋፍላሉ፡፡ ከውጭ በተመለሱ ስሞን፣ በዚያ አካባቢ የሚታየው  ፍፁም ሌላ ነው፡፡ ተጠርታ በምትገባበት ጊዜ፣ መታሰቢያ ያመጣንልሽ› እየተባለ፣ከየዓይነቱ ተሸክማ ትወጣለች፡፡ አንዳንዶቹ ያላቸው ጌጣጌጥ ዓይነትና ውድነት በፍፁም ለማመን ያስቸግራል፡፡ ብዙዎቹ፣ የግርማዊት እቴጌ መነንን ጌጥ እየተሰጣቸው ሲያጌጡበት በማየት፣የግርማዊት አሽከሮች እንባቸውን ሲያጐርፉ ይታዩ ነበር።

«በጉዳይ ሰበብ እየቀረቡ፣ በዙ የዘረፉ፣ ከቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ ከውጭም ጭምር ነበር፡፡ ለምሣሌም ያህል፣ የአየር መንገድ መሥሪያ ቤት፣ ሆስቴስ ከሴት አዳሪ ደግሞ፣ የቢትወደድ ነጋሽ ልጅ ሲኾኑ፣ ከባለትዳሮችም ጋር ግንኙነት ነበራቸው። የሚገናኙትም አብዛኛውን ጊዜ ከቢሮ ነው፡፡»

ይህን የዓይን ምስክርነት ማስተባበል ያስቸግራል፡፡ የኢያሱ ውንጀላ ሲጤን፣ ዐመድ በዱቄት ይሥቃል እንደ ተባለው ኾኖ ይታያል
#ምንጭ:-አቤቶ ኢያሱ አነጋገስና አወዳደቅ በአጥናፍሰገድ ይልማ ሚያዚያ 2006


╔═══════════════════════╗
  🎖 #በቀድሞ_አረቦች_የነበረ_የጋብቻ_አይነት
╚═══════════════════════╝

      አቡ ዳውድ ዓኢሻን ረዐ  ጠቅሰው እንደዘገቡት በቅድመ ኢስላም ከዐረቦች ዘንድ አራት የጋብቻ አይነቶች ነበሩ
#አንደኛው ጋብቻ ዓይነት☞ የተለመደው አይነት ጋብቻ ነው። ወንዱ የእንስቷን ቤተሰብ ያናግራል። ሲፈቀድለት ጥሎሿን ሰጥቶ ያገባታል።
#ሁለተኛዉ ጋብቻ ዓይነት ☞ባል ሚስቱን ከወር አበባ ስትፀዳ ወደ ሌላ ወንድ ሄዳ እንድታረግዝ ያደርጋታል።ወደተባለው ሰው ትሄድና ይገናኛታል። ማርገዟ እስኪረጋገጥ ድረስ ባሏ አይደርስባትም። ማርገዟ ሲረጋገጥ ባሏ ከፈለገ ይገናኛታል። ይህን የሚያደርገው ልጅ ፍለጋ ነው። ይህ ዓይነቱ ጋብቻ «ኢስቲብዳዕ» ይሰኛል።
#ሶስተኛው ጋብቻ ዓይነት ☞ቁጥራቸው ከአስር የማይበልጥ ወንዶች አንዲትን እንስት ይገናኟታል። በነዚህ ግንኙነቶች አርግዛ ከወለደች ከቀናት በኋላ ወደ ወንዶች መልዕክት ትልካለች። ክእሷ ጋር ግንኙነት የፈፀመው ወንድ ፈፅሞ ሊቀር አይችልም ሁሉም ሲመጡ፡-ሁላችሁም እንደተገናኛችሁኝ ታውቃላችሁ።እነሆ ወልጃለሁ።እገሌ ሆይ! ልጁ ልጅህ ነው።»በማለት የአንዱን ስም ትጠራለች። እርሱም አባትነቱን ይቀበላል
☞ #አራተኛው የጋብቻ ዓይነት☞ ብዙ ወንዶች አንዲትን ሴት ይገናኟታል። ይህች ሴት መገናኘት ለሚፈልጋት
ወንድ ምልክት ይሆን ዘንድ በሩቅ የሚታይ ምልክት ከበሯ አጠገብ ታንጠለጥላለች። ወንዶች ምልክቱን እያዩ ገብተው ይገናኟታል።እምቢ አትልም። ስትወልድ የተገናኟት ሁሉ ይሰበሰባሉ። ዘር አዋቂ ልጁን ወደ አንደኛው ያስጠጋል።ሰውየውም አባትነቱን ወዶ ይቀበላል።ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ሲላኩ ይህን የመሀይምነት ዘመን ጋብቻ ውድቅ በማድረግ የአሁኑን የእስልምና ጋብቻ ብቻ አፀደቁ፡፡

በጦርነት ወቅት እንስቶች ከወንዶች ጋር ይሆናሉ፡፡ አሽናፊው ወገን የተሸናፊውን እንስቶች እንደልቡ ያለ ገደብ ይገናኛል።በዚህ ግንኙነት የሚወለዱ ልጆች እድሜልካቸውን ሐፍረት እንደተሰማቸው ይኖራሉ።

የመሐይምነት ዘመን ወንዶች የሚያገባቸው ሚስቶች ገደብ አልባ ነበሩ። እሁትማማቾችን፤ የአባትን ሚስቶች እርሱ ከሞተ ወይም ከፈታቸው በኋላ ያገባሉ።

ፍች የወንዶች ያልተገደበ ስልጣን ነበር። ዝሙት በሁሉም የሕብረተስቡ ክፍሎች ተስፋፍቷል። ከዚህ ውርደት ውስጥ ነፍሶቻቸውን ላለመዘፈቅ የወስኑና የጸኑ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ካልሆኑ በቀር መላ ማሕበረሰቡ ከዝሙት ባህር ውስጥ ተዘፍቋል። ከባሮች ይልቅ ጨዋ ሴቶች ከዝሙት በመራቅ ይሻላሉ።ባሮች እጅግ በሚያሳቅቅ ሁኔታ በዝሙት ተዘፍቀዋል።አብዛኛዎቹ የቅድመ ኢስላም ሰዎች ከዚህ ውርደት ውስጥ በመዘፈቃቸው ነውር መስሎ አይታያቸውም።
ነብዩ ﷺ ከተላኩ ይሄን አስቀርተዉ አንድ ወንድ ከአራት በላይ እንዳያገባ ሀራም መሆኑ ታወጀ፡፡

እስኪ እሰቡት ከክርስትና ከበፊቱ ከአረቦች ባህል የኢትዮ የጥንት ንጉሶች ለሴቶች ክብር የሰጠዉ እስልምና መሆኑን ላስተነተነዉ ሰዉ ግልፅ ነዉ፡፡
አንድ ልጅ ተወልዶ አባቱ አይታወቅም እየተባለ ..አባቱን በእናቱ አያት ስም አርገዉ ከሚጠሩ..አራት አግብቶ አባትህ እንትና ነዉ ብሎ መናገር ይሻላል


#በቀጣይ_ክፍል
ስለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ገመና እንዳስሳለን

ክፍል ➊➐ ይቀጥላል


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

29 Sep, 16:21


🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #ምዕራፍ_አስር_ስድስት ➊➏
                  አሚር ሰይድ



╔════════════════════════╗
🎖#መፅሀፍ_ቅዱስ_ስለሁለተኛ_ሚስት_ምን_ይላል?
╚════════════════════════╝


     መፅሀፍ ቅዱሱም ሌሎች የሌላ ሀይማኖት መለኮታዊ መፅሀፍ ለራሱ አልከለከሉም...
#ለምሳሌ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ በህጋዊ መንገድ በጋብቻ ከ 2 በላይ ሚስት ያገቡትን ሰዎችና ነብያቶችን  እና ቅዱሳን ሰዎች እንመልከት:-


☞ ”ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት #ሚስቶች_ቢኖሩት: ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ…”(ዘዳግም:21:15)

☞ ሌላ ሴት (ሚስት) ቢያገባ ለመጀመሪያ ሚስቱ ምግቧን ፣ ልብሷንና , የጋብቻ መብቷን አይከልክላት።
( ዘጸሃት 21፡10)


📌ነቢዩ ሰለሞን (ጠቢቡ ሰለሞን) ከ1000 ሚስቶች በላይ ነበሩት

➊ ነገሥት 11:3 ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሶስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት።(1ኛ ነገሥት 11:3)
700 ሚስቶች + 300 ቁባቶች = 1,000 ሚስቶች

➋ ☞አብራሃም (ነቢዩ ኢብራሂም) #3ሚስቶች ነበሩት።
“የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።”(ኦሪት ዘፍጠረት 16:3)

  #በተጨማሪ የዱሮ ስርአት ናፋቂዎች ከአንድ በላይ ሚስት ሲቀልዱ ሲሳለቁ እናያለን..ነገር ግን የድሮ መንግስቶች አፄዎች ስንት ሚስቶች ነበራቸዉ?የሚለዉን እንመልከት

╔══════════════════╗
     🎖 #አፄ_ቴድሮስና_እቁባቶቻቸው🎖
╚══════════════════╝


   አብደል ጀሊል ሸህ አሊ ካሳ ኪነት ያገነነዉ አፄ በሚለዉ መፅሀፉ ከገፅ 229-231 ድረስ ስለአፄ ቴድሮስ እቁባቶች የተወሰነ ነጥብ አስቀምጧል፡፡ አፄ ቴድሮስ ከ100 በላይ ሚስት ነበራቸዉ ይለናል....ከመፅሀፉ የተወሰነዉን  ፁሁፍ እነሆ ፡-

   ምንም እንኳን የንጉሡ ግልባጭ የሆነትና ፀሀፊ ትዕዛዛቸው የሆኑት ደብተራ ዘነበ ንጉሱን ምንዝር የማይዎድ!» ቢሏቸውም ንጉሱ የፈለጓትን ሴት ወስደው ሚስታቸው ያደርጉ ነበር። ማን ያርዳ የቀበረ ማን ያውራ የነበረ ነውና የእሱ እስረኛ ሆርመዝ ራሳም በግልፅ እንዳስቀመጠው ቴዎድሮስ የክርስቲያን ጠላቶቻቸውን ሚስቶች እንኳን ቢሆን ባሎቻቸው በህይወት እያሉ ወስደው አያገቡም ነበር። ግን የሙስሊም ወንዶችን ለማዋረድ ባሎቻቸውን በሕይወት እያሉ ነጥቀው ስለማግባታቸው ተዘግቧል።

☞ሆርሙዝ ራሳም እንዳስቀመጠው ቴዎድሮስ አስገድደው የሰው ሚስት ክርስትናን አስጠምቀው ያገቡ ነበር።  የፈለጓትን በውበቷ የፈዘዙባትን ሁሉ።

☞ሪቻርድ ፓንክረስት ንጉሱ ለእተመኙ የጻፉትን ደብዳቤ ባጠኑበት ፁሁፍ ላይ ራሳምን ዋቢ አድርገው ወይዘሮ እተመኙ የጁ ሙስሊም ኦሮሞ ስትሆን የየጁ ሙስሊም ኦሮሞዎች የአንዱ ሚስት የነበረች፣ ስለ ውበቷ ማማር ቴዎድሮስ በሰማ ጊዜ አስመጥቶ አስገድዶ ክርስትና እንድትነሳ በማድረግ አግብቷታል።ብለዋል፡፡

☞ ሐጅ አደም ኩርማን ስለ ተባሉ በሃይማኖታቸው ምክንያት ከጎንደር ስለተሰደዱ ባለሀብት፣ ውብ ሚስታቸውንና ንብረታቸውን በቴዎድሮስ ስለተቀሙ ሰው ሆርሙዝ ራሳም በቅጽ አንድ መጽሐፉ ላይ አስፍሯል። ሐጅ አደም ኩርማን ለሆርሙዝ ራሳም ሚስታቸው በጎንደር ከተማ ላይ በውበቷ የምትታወቅ፣ ከልጅነቷ ጀምረው የሚያውቋትና ያገቧት ሴት እንደ ነበረች ነግረውታል። ስለ ደም ግባቷ ንጉሡ መረጃ እንደደረሳቸው ተመኟት፣ ምንም እንኳን #ከመቶ_በላይ ሚስት ቢኖራቸውም ሀይማኖቷን ለውጠው ወስደዋታል፤ በኋላም የማእድ ቤት ሰራተኛ ሆና ሆርሙዝ በቴዎድሮስ ማጀት ውስጥ አግኝቷታል።

ወልደዩሃንስ ወርቅነህ እና ገመቹ መልካ በመፅሀፋቸው ላይ የአቶ አፈወርቅን ፅሁፍ ጠቅሰው እንዲህ ፅፈዋል፡- “በዘመኑ በድሃው ቤተሰብ በተለይ በኃይል በተወረሩ ህዝቦች ላይ የማይሠራ ግፍ አልነበረም፡፡ ከታጣቂ ነፍጠኞች እስከባላባቱና ሀገር መሪው ቤተሰብ በማፍረስ ጭምር ቆንጆ› ሆና የታየቻቸውን ሴት ነጥቀው ይወስዳሉ፡፡ ባል እያለ ሚስቱን እፊቱ ይደፍራሉ፡፡ የደረሰች ሴት ልጁን አምጣልኝ ብለው ለአባቷ ትእዛዝ ከሰጡ እስከ ቤት ድረስ ይወስዱላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ አቶ አፈወርቅ ገብረየሱስ በቴዎድሮስ  ዘመን ከተፈፀመው በመነሳት ያቀረቧቸው አንድ ጉዳይ የጊዜውን የነፍጠኞች ግፍ ሊያንፀባርቅ የሚችል ነው::ይላሉ ጽሀፊዎቹ፡፡

አንዳንድ አጥባቂ ሀይማነተኞች አፄ ቴድሮስ ሀይማኖተኛ ነበር ወዘተ ይባላል ግን ከ100 በላይ ሚስቶች እንደነበሯቸዉ መናገርም መስማትም አይፈልጉም



╔════════════════════╗
   🎖#የቀዳማዊ_ኀይለ_ሥላሴ_ሚስቶች🎖
╚════════════════════╝


    
ቀዳሚዊ ሀይለ ስላሴ እኔ የሰለሞን ዘር አለብኝ ስዩመ እግዝአብሄር ነኝ ይላሉ፡፡ ለሙስሊሞችም ሀይማኖታቸዉን ለማስቀየር የተራቀቀ ፓሊሲ የነበራቸዉ ንጉስ ነበሩ፡፡
   ቀዳሚ ሀይለ ስላሴ ብዙ ሚስቶች ነበሯቸዉ፡፡የቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ሚስቶች፣ቁባቶች እና ሴሰኝነት ፣ #ከጋብቻ_ውጭ_የበራቸውን_ጾታዊ ግንኙነት እንመልከት፡፡ከንጉሡ ሕልፈት በኋላ፣ በታተሙና ገና ባልታተሙ የታሪካቸው ድርሳናት ተመስክሯል፡፡ግን ፀሀፊዎች ልጅ እያሱ አራት ሚስት ማግባቱን ሲያጣጥሉ ሲያንቋሽሹ እናዳለን...ምናልባት'ኳ እንደ ልዩነት ሊታይ ይችላል ከተባለ፣ ልጅ ኢያሱ የ በአብዛኛው ከመሳፍንት፣ ከመኳንንት፣ ከባላባት፣ እስላም ሴት ልጆች ጋር በህጋዊ መንገድ ያገባ ሲኾን፣ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ግን፣ የነበራቸው ጾታዊ ግንኙነት በይበልጥ ከቤተ መንግሥት ሴት አገልጋዮች ጋር መኾኑ ነው፡፡

⚡️⚡️ የጥላኹን ብርሃነ ሥላሴ ቤተ፣ 1ኛ መጽሐፍ (ገጽ 345 - 82) የሚከተለው ሰፍሯል፡፡ « አንድ ልጅ ከጋብቻ ውጭ ከተወለደ፣ ላባቱ ክብር ሲባል ብቻ፣ ልጁን አባት አልባ ማድረግ ፍትሐዊ ስለማይኾን፣ መዘርዘሩ ተገቢ እንደ መኾኑ መጠን፣ እኔም የጃንሆይ ልጆች ናቸው የሚባሉትን ኹሉ መርምሬ፣ የደረስኹበትን እንደ ሚከተለው ዘርዝሬያለኹ፡፡

➊ ከወሎዬይቱ ወይዘሮ ወይኒቱዐመዴ፣ ሮማነ ወርቅን፣

➋ ከወይዘሮ ይመኙሻል ክብረት ከተባሉት የቤተ መንግሥት ሠራተኛ☞አቶ ኪዳኔ ተፈሪን ወልደዋል

➌ የልዑል ዐልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ግቢ ሠራተኛ ከነበሩትየአቶ ግርማ ባለቤት (ስማቸውን ማግኘት አልተቻለም) ☞አቶ መንግሥቱን፣

➍ የቤተ መንግሥት ፅዳት ሠራተኛ ከነበሩት ከወይዘሮ አሰገደች አበራ፣ ትግሥት ካላና ቴዎድሮስ ካሳ እየተባሉ፣ በእንጀራ አባታቸው ስም የሚጠሩትን፡፡

➎ የቤተ መንግስት ሰራተኛ ከነበሩት ወይዘሮ አልማዝ☞ መክብብ አበበ የሚባል፣ በእንጀራ አባቱ ስም የሚጠራ ልጅ፣

➏ የቤተ መንግሥት ሠራተኛ ከነበረችው ፀሐይ መገርሳ☞ ኹለት (ለጊዜው ስማቸው ያልተገለጡ) ልጆች፡፡

➑ የቤተ መንግሥት ሠራተኛ ከነበሩ ወይዘሮ ፀሐይ ድፋባቸው☞ ሰለሞን ሠርፀ ወልድ እየተባለ በእንጀራ አባቱ ስም የሚጠራ ልጅ ወልደዋል።»

ጃንሆይ፣ ከነዚህ ስምንት ልጆች ሌላም፣ በርካታ ዲ*ቃ*ሎች እንዳሏቸው ታምተዋል፡፡ ጃንሆይ በይፋ ያልቆበቷቸው፣ ነገር ግን ሸማ የተጋፈፏቸው ሴቶች ቁጥር፣ ኢያሱ ከነበሯቸው ቁባቶችና ሚስቶች በቁጥር እንደሚበዙ አንዳንድ ገና ይፋ ያልወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡👇👇👇👇

ISLAMIC SCHOOL

28 Sep, 16:56


የፍልስጤን ደጋፊ የነበረዉ የሳዉዲ ንንጉስ ፋይሰል አብደል አዚዝ


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

27 Sep, 16:06


የቅምጦች ለመሆናቸው ማረጋገጫዎቹም አንድም ከውስጠ አዋቂዎች በተገኘው መረጃ ሲሆን ሁለትም እነዚህ ሴቶች ልጅም ሆነ ቤተሰብ ከአጠገባቸው የሌላቸው፤ የቤት ሰራተኛም ሆነ የቤት ዕቃ ያልተሟሉላቸው፣ ቅምጦቹ በየስድስቱ ወሩ ስለሚቀያየሩ በነርሱ መካከል ምንም ማህበራዊ ሕይወት አለመኖሩ፣ ቄንጣቸው፣ መቀማጠላቸው ብዙውን ጊዜ ብቻቸውን መሆናቸው፣ ወዘተ ናቸው፡፡ የኋላ ኋላም ያስቀመጣት ወንድ ከተወሰኑ ወራት በኋላ ጥሏት ስለሚጠፋ ቅምጧ የቤት ኪራይ መከፈል አቅቷት የቤት ዕቃዎችን ለመሸጥ ስትገደድ ማየት የተለመደ ነው፡፡

በእውነቱ ከቅምጥነት ጋር በተያያዘ በርካታ ሚስቶች ለባሎቻቸው ከሁለተኛ ሚስት ይልቅ ቅምጦችን እንዲይዙ መፍቀዳቸው ማህበረሰባችን ምን ያህል እንደዘቀጠ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡
እርሷ የወሲብ ሕይወቷንና ብሎም መላ ሕይወቷን ለምታበላሸው ቅምጥ ዕውቅና ሰጥታ አላህ (ሱ.ወ) የፈቀደውን መከልከሏ በእውነቱ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሀይማኖቱ ወሬውም አልደረሰውም እንዴ? ያስብላል፡፡

ለባሏ ቅምጥ መያዝን የምትፈቅድ ሚስት በዚህ እኩይ ድርጊቷ ለራሷ ወሲባዊ ደህንነት ካለማሰቧም በተጨማሪነት ለባሏ ሕይወትም  አለማሰቧን እንመለከታለን፡፡ ይህም የርሷን ራስ ወዳድነት በጉልህ ያሳያል፤ ምክንያቱም ባሏ በወንጀል ላይ እየወደቀ ዕውቅና መስጠቷ እርሷም የወንጀል ደጋፊ ናትና፡፡  በእውነቱ ይህች ሚስት ባሏ ለአላህ (ሱ.ወ) ቁጣ የሚዳርግ ኃጢአትን ሲሠራ እርሷ ግን ስለብቸኛ ሚስትነቷ ብቻ በመጨነቅ እጥፍ ድርብ የሆኑ ኃጢአቶችን ትፈፅማለች፡፡ወጣም ወረደም የሁለቱም ድርጊት ለዝሙት መስፋፋት ትልቅ አስተዋፅኦን ያበረክታል፡፡



╔════════════════════════╗
   #ምዕራባዉያን_አለም_ሁለተኛ_ሚስትነት_ክልከላ
╚════════════════════════╝


  ሰውየው በምዕራቡ ዓለም ነዋሪ ነው እናም በሁለት ሚስቶቹ ታጅቦ በጎዳና ላይ እየሔደ ፖሊስ ያስቆመውና  "በሀገራችን ህግ ሁለት ሚስት ሊኖርህ አይችልም፤" ይለዋል ሰውየውም "ይቅርታ! አንደኛዋኮ ገርል ፍሬንዴ ናት ሲለው ፖሊሱ ጥሎት ሔደ።
#ሸይኽ_አህመድ_ዲዳት

የምዕራቡ ዓለም ሺህ ገርል ፍሬንድ የሴት ጓደኛ ቢኖርህ አብረሀቸው ብትተኛ፣ዲቃላ ብትወልድ ጉዳያቸው አይደለም ነገር ግን ሁለት ህጋዊ ሚስቶችን ለማግባት ስትፈልግ ያግዱሀል።

በነዚህ ሀገራት ያሉት ሴቶችም በተመሳሳይ መልኩ ከሌሎች ወንዶች ጋር ቢማግጡ ህጉ አይከለክላቸውም። ይህ ነው የነሱ ስይጣኔ ታዳ ኢትዮም ይሄንኔ የምዕራባዉያን አስተሳሰብ ተቀብላ ሁለተኛ የሚባል ነገር ሴቶች ጆሯችን አይስማ በዉጭ እንደ ሆንክ ሁን አይነት አቋም ይዘዋል፡፡


╔═════════════════════╗
 🎖ነብዩ ﷺ ለምን ከአራት በላይ ሚስት አገቡ?
╚═════════════════════╝

አብዘሀኛዉ ሙስሊም ሌሎች ሀይማኖቶች ነብዩ ﷺ ሚስት ሲያገቡ ነዉ የኖሩት እያሉ ሲያሾፉ የሚያገባዉን ሲያንቋሽሹ ይስተዋላሉ...ግን ለኒዚህ ሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች ሙስሊሙ አጥጋቢ መልስ ሲመልስ አይሰተዋልም....በነብዩ ﷺ ጊዜ ነብይ ከመሆናቸዉ በፊት ጀምሮ የአረቦች ባህል ላይ እንኳን ሁለት ሶስት ከ10 በላይ የነበራቸዉ ብዙ ወንዶች ነበሩ...ከሰለሙ ቡሀላ ካላችሁ ሚስቶች አራቱን ብቻ አድርጉ ተብለዉ ያደረጉ ሱሀቦችም ነበሩ፡፡
   ነብዩ ﷺ ከአራት በላይ ያገቡበት ምክንያቶች የተወሰነዉን ለማብራራት ልሞክር፡-

ዐረቦች በባህላቸው አማችነትን በጣም ያከብራሉ። በተለያዩ ጎሳዎች መካከል መቀራረብና ትስስር ለመፍጠርም ይጠቀሙበታል" የአማችን ወገን መውጋትን እንደ መጥፎ ድርጊትና እንደነውር ይመለከታሉ፡፡ እናም ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ

ከተለያዩ ጎሳዎች በርካታ ሴቶችን በማግባት የጎሳዎችን የጠላትነት ስሜት ለመስበርና ጥላቻቸውን ለማቀዝቀዝ ችለዋል።
#ለምሳሌ
📌 #ኡም_ስለማህ>>የአቡ ጀህልሀና የኻሊድ ቢን ወሊድ ጎሳ የሆነው የበኑ መኽዙም ጎሳ አባል ናት።
ነቢዩ ﷺእርሷን ካገቡ በኋላ ኻሊድ በሙስሊሞች ላይ ያሳይ የነበረውን ጭካኔ ቀነሰ። ከዚህም አልፎ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሰለመ።

☞ #ኡሙ_ሀቢባ>>> አቡ ሱፍያንም እንደዚሁ ልጁን ኡም ሐቢብን ነቢዩ  ካገቧት በኋላ ከርሳቸው ጋር አንድም ጦርነት ፊት ለፊት አልገጠመም።

📌 #ሶፍያንና_ጁወይሪየህን>>ነብዩﷺ ሶፍያና ጁወይሪያን ካገቡ በኋላ ከበኒ ሙስጠለቅ እና ከበኒ ነዲር ጎሳዎች የጠነከረ የጠላትነት ድርጊት አልታየም። ጁወይሪየህ ለወገኖቿ ትልቅ በረከት ነበረች። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እርሷን ባገቡ ጊዜ ሶሐቦች ከወገኖቿ መካከል በምርኮ የተያዜ መቶ ቤተሰቦቿን የነቢዩ ﷺ አማቾች ናቸው በማለት በነፃ ለቀዋቸዋል። ይህ በጎ ድርጊት በልቦና ላይ ምን ያህል በጎ ስሜት ሊያሳድር እንደሚችል ማሰቡ አይከብድም።


📌 #ከጋብቻዎቻቸው መካከል አንዱ የመሐይምነትን ዘመን ከንቱ ባህል ለማክስም የተደረገ ነው። እርሱም የማደጎ ልጅ ጉዳይ ሲሆን፤ የማደጎ ልጅ በዐረቦች ዘንድ በመሀይምነት ዘመን ልክ እንደ እውነተኛ ልጅ ይታይ ነበር። ይህ አስተሳስብ በሕብረተሰቡ ውስጥ ጥልቅ መሠረት ያለው በመሆኑ በቀላሉ ሊወገድ የሚችል አልነበረም፡፡

ይህን አጉል ባህል ለማክሰም ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ
የአክስታቸውን ልጅ ዘይነብን እንዲያገቡ አዘዛቸው። ዘይነብ የዘይድ ባለቤት ነበረች። ግን ከዘይድ ጋር ስምምነት አልነበራቸውም። ዘይድ ሊፈታት አስቦ ነበር። ይህም የሆነው የከሐድያን ሕብረት መዲናን ለመውረር በመጣበት የአህዛብ ዘመቻ ወቅት ነበር። የአላህ መልዕክተኛ ግን የሙናፊቆችን፣ የጣኦታውያንን እና የአይሁዶችን የስም ማጥፋት ዘመቻና ይህ ዘመቻ በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ሊያስከትለው የሚችለውን መጥፎ ስሜት ስለሰጉ ራሳቸውን ከዚህ ፈተና ለመጠበቅ ሲሉ ዘይድ ባይፈታት ምርጫቸው ነበር።

ይህ ማመንታት ከተላኩበት ታላቅ ቁም ነገር የቁርጠኝነት ባህሪ ጋር የማይጣጣም በመሆኑ አላህ እንዲህ ሲል ተቻቸው:-
‹‹አላህ ፀጋውን ስለግሰውና አንተም ውስታ ለዋልክለት ሰዉ "ሚስትህን ያዝ: አላህንም ፍራ።” ባልከው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ)። (በወቅቱ) አላህ ገልፅ ሊያደርገው ያቀደውን ነገር በውስጥህ ደበቅክ፡ ልትፈራ የሚገባው አላህን ብቻ ሆና እያለ ሰዎችን ፈራህ፡›› አል-አህዛብ: 37)

በመጨረሻ ዘይድ ፈታት። የአላህ መልዕክተኛም ﷺ
በበኒ ቁረይዟ አይሁዶች ላይ ከበባ ባደረጉ ጊዜ፣ የእፎይታ ጊዜዋን (ዒዳህ) ካጠናቀቀች በኋላ፣ አላህ እንዲያገቧት ስላዘዛቸውና ሌላ ምርጫ ስላልተወላቸው አገቧት። የጋብቻ ውሉን የፈፀመው አላህ ራሱ ነው።

ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ፡፡ የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው፡፡(አል አህዛብ 37)

ይህን ያደረገው ከማደጎ ልጅ ጋር የተያያዘውን አጉል ባህል በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባርም ለማፈራረስ ነው፡
     ‹‹በአባቶቻቸው (ስምም) ጥሯቸው ይህ ከአላህ ዘንድ ትክክለኛዉ ነው፡፡››(አል አህዛብ 5)
ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ያገቧቸዉ ሚስቶች ዲነል ኢስላም እንዲስፋፋ ቁረይሾች ትዳርን እንደሚያከብሩ በዝምድና የተሳሰሩት ጋር በጭራሽ ጦር እንደማይገጥሙ ስለሚታወቅ ነዉ፡፡

#በሚቀጥለዉ_ክፍል
የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ሁለተኛ ሚስት ላይ ሙስሊሞችን ሲያንቋሽሹ ይሰማሉ..ቅዱስ መፅሀፍ ሁለተኛ ሚስት እንደማይከለክል አቀርባለሁ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

27 Sep, 16:06


🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #ምዕራፍ_አስር_አምስት ➊➎
                  አሚር ሰይድ

╔══════════════════════╗
🎖  #ሴቶች_ሁለተኛ_ሚስትን_የመከልከል_አባዜ🎖
╚══════════════════════╝

98% ሴቶች ሁለተኛ ሚስት የሚለዉን ወሬ ባይሰሙት ደስ ይላቸዋል.፡፡ሴቱ ሁሉንም ሀዲስ  ያዳምጣል ግን ለወንድ የተፈቀደዉን ሁለተኛ ማግባት ባይሰሟት ደስ ይላቸዋል፡፡ ወንድም ብዙ ሱና አለ ፆሙ የለይል ሶላቱ ወዘተ እያለ ሱናዉን እንተግብር ብሎ የሚያወራዉ ሁለተኛ ሚስትና ምግብ በጀመአ እየበላ ሊተርፍ ሲል ሱናዉን ሀይእናድርግ ይላል፡፡
ግን ስለሁለተኛ ሚስት የሚያወራዉ 99%ወንድ ሁለተኛ ማግባትን ያወራል ከዚህ መሀል ግን 85%ያላገባዉ ወንድ ነዉ ስለ ሁለተኛ ማግባት የሚፈተፍተዉ.. 10%ያገባዉ ወንድ አገባለሁ እያለ ያወጋል ግን Money ኢንጅሩ...4%ወንድ አቅም ያለዉ ነዉ ግን 2%አግብቶ ሰላም ስለሚያጣ አያገባም 2%ወደቆላዉ አካባቢ ያለ አግብቷል፡፡
የሚመለከተዉ 4%አቅም ያለዉን ወንድ ነዉ እንጂ የሚፎክረዉን አይደለም....እናም ሀብታም ወንዶች ሁለተኛ ሚስት ቢያገቡ የመጀመሪያዋ ሚስት ንዝንዝ፡ፍች፡ቤተሰብ መበታተን፡ንብረት መከፋፈልን ሁለተኛ ሚስት ማግባትን ትተዉ በብር ሀይል የሚንቀሳቀሱ ሴቶችን የወሲብ ቅምጥ ይዘዉ በየፔንሲዮኑ..በያዙት መኪና..አፓርታማና ኮንዶሚኒየም ይዘዉ ዚና እየሰሩ ነዉ ..በተለይ በአዲስ አበባ ይሄ ጉዳይ ጎልቶ ይታያል፡፡

አንዳንዴ ወንድነት መለየት አለበት አቅም ካለህ አላህን እንጂ ሚስትህን ልትፈራ አይገባም..ነገር ግን የኛ ማህበረሰብ ወንድ ሁለተኛ ሲያገባ ብር በአደነዘዘዉ ጭንቅላቱ የሚያስበዉ ቢክራዋን ነዉ፡፡
የዲን እህቱን ለመጠቅም አስቦ አይደለም..ወንዶች ሁለተኛ ሲያገቡ እነዚህን ታሳቢ ቢያደርጉ አሪፍ ነዉ
☞ባሏ የሞተባት ሴት
☞ባሏ የሞተባት ሴት ልጅ ያላት
☞በድህነት ላይ የምትኖር
☞እድሜዋ ከ35 አመት በላይ የሆነችን
☞አሏህ ሲሰጥ ሁሉንም ቆንጆ አድርጎ ነዉ ማስጠሌ የሚባል የለም ..ግን በተፈጥሮ ለምጥ ወይ የአካል ጉዳት ያለባቸዉን(አይነስዉራን,እጃቸዉ ወይ እግራቸዉ የተጎዱ)ወዘተ
እነዚህ ጋር ሁለተኛ ሚስት ቢደረግ አጅሩ ምንዳዉ እጥፍ ድርብ ነዉ ባይ ነኝ፡፡
የሚገርዉ ደግሞ በጣም አሳሳቢ ችግር ሁለተኛ ሚስቶች የመጀመሪያዉን ለማስረሳት እሷ ትሻላለች እንድትባል እንክብካቤ የወንድን ስስ ልብ በመጠቀም ሁለተኛዋ ተሽላኛለች ብሎ እንዲያስብ አድርገዉ ከመጀመሪያ ለማጣላት ጥረት እያደረጉ አንዳንዶችም ተሳክቶላቸዉ ይሄ ነገር በጣጣም አሳሳቢ ሁኗል፡፡

#ሴቶች_በሁለተኛ_ሚስት_ከመያገባ_ዚና_ቢሰራ_ይቀላቸዋል፡፡

አንድ ሸህ ሁለተኛ አግብተዉ ሁለተኛ ሚስታቸዉ ቤት እንዳሉ የመጀመሪያ ሚስታቸዉ ቤት ይቃጠላል..ተደዉሎ ቤቱህ ተቃጥሏል ሲላቸዉ ቶሎ ብለዉ ቢመጡ ቤቱ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል..በጣም አዘኑና የመጀመሪያ ሚስታቸዉን ሌላዉ ግድ የለም ይቃጠል ኪታቤን አታወጭልኝም ነበር ወይ??ሲሏት
....ኪታቡ የጠቀመዉ አንቱን ነዉ እኔን ብቸኛ አድርጎ አብሮ ይቃጠል ብየ ነዉ☺️ አለች ይባላል፡፡

የሌላ ሀገር ሸህ ደግሞ ሚስታቸዉ ጋር ተጣልተዉ ሸይጧን ተጨምሮ መማታት ጀመረች....ሸህየዉ መምታቷን እንድታቆምላቸዉ አረ ቢታኩ አረ በኪታቡ ሲሉ...ዝም በሉ ደግሞ በኪታቡ ትላለሁ እንዴ ለአንቱ ብቻ የሚጠቅም ኪታብ አለች🙄 ይባላል

  አንዳንድ ወንዶች ሁለተኛን ሲያስቡ ለሸህዋ ብቻ የሚያስቡ አሉ ሀብታም ሴት ቤት ያላት ብለዉ የሚፈልጉ አሉ እዚህ ላይ ምንም ማለት አይቻልም ለምን ሁለተኛ ሚስነት የተጠየቀችዉ ሴት ሀሳብ ይወሰናልና ለምን ሀብታም ሁኗ ቤት ያላት ሁና አንደኛ አጥታ ሁለተኛም ባገኝ አገባለሁ ብላ አስባ ሊሆን ይችላልና፡፡

🔰🔰 በተጨማሪ ደግሞ 90% የሚዋደዱ ሰዎች አይጋቡም...እሱም አግብቶ ለአገባት ሚስቱ ፍቅር የማይሰጥ የሚስት ሀቋን የማይወጣ ሚስቱ ጋር ተኝቶ ሀሳቡ የማይለቅ  ከሆነ የተወሰነ አመታት በዚህ ሙድ የሚያሳልፍ ከሆነ እሷም በማግባቱ ሰላም ካጣች መፍትሄዉ ሁለተኛ እሷኑ ማግባት ነዉ...እሷም አግብቷ ባሏ ጋር ተኝታ ሀሳቡ እሱ ጋር የምትሆን ከሆነ ለባሏም ሰላም ስለማትሰጠዉ የተሻለዉ አማራጭ ባሏን ፈታ በፊት የምወደዉ ካላገባ እሱ ጋር መሆን ካገባ ደግሞ ባሏን ፈታ አቅም ካለዉ ሁለተኛ እሱ ጋር መኖር ይሻላል..

ብዙ ጊዜ ልጅ ሲወለድ ፍቅር ይመጣል የሚባል የሚል አመለካከት አለ ስህተት ነዉ የሚኖረዉ የልጅ ፍቅር ነዉ..አንዳንድ ሴቶች ቢክራ ሁነዉ እንኳ ከባላቸዉ ፍቅር ያልያዛቸዉ በፊት የሚወዱትን እንደሚያስታዉሱ አግብተዉም ወልደዉም የሚወዱትን ሰዉ አይረሱም...ይሄን ወንዶች አናቅም ሴቶች ግን ያቁታል እናም የማይወዱት ጋር ከመኖር የሚሻለዉ አቅም ካለ ሁለተኛ መሆን ይሻላል፡፡ዱንያ የደስታ ምንጭ አይደለችም ደግሞ ደስታ ፍቅር የሌለዉ የትዳር ቤት ያዉ የማይሞቅ የሚበርድ ዋሻ እንጂ ቤት ነዉ ብለን አንቁጠረዉ


╔════════════════════╗
  🎖 #የሙስሊም_አለቆች_ሴት_ሰራተኞቻቸውን
      #በቅምጥነት_መያዝና_ኮንዶሚኒየም
           #ተከራይተው_ማስቀመጥ🎖
╚════════════════════╝


      ቀበጦቹ ሒጃቢስቶች የማይገቡበትና የማይሰሩት ስራ ዓይነት የለም፡፡ብዙዎቹ አሰሪ ነጋዴዎችም ለቢዝነሳቸው መዋዛት ከወንድ ይልቅ ሴትን ፊት ለፊት ማስቀመጥ ይፈልጋሉ፡፡ ታዲያ በተለይ አዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ ..የተለያዩ የንግድ ማዕከላት ..ሌላም ክፍለ ሀገር ከተሞች ጨምሮ ልብ ብላችሁ ከሆነ በየሱቁ ከፊት ለፊት የሚቀመጡት ለሻጭነት የሚቀጠሩት ድብን ብለው ዓይን ውስጥ የሚገቡ ቀበጥ ሴቶች ናቸው፡፡ ከንፈራቸው ሊፒስቲክን ጠግቧል፡፡ዓይናቸው በቀለም ድብን ብሏል፡፡ ሲታዩ ለሱቅ ሥራ የመጡ አይመስሉም፡፡


   መመሳሰላቸው በአካላዊ ገፅታ ብቻ ሳይሆን ከአለቃ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነትም ጭምር ነው፡፡ አለቆችም ቢሆኑ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡ በተለይ በስራ ጉዳይ ግልፅ የማይሆኑትን ያህል በሴት ዙሪያ ከሚጠየቁት በላይ መረጃን ይሰጣሉ፤ ስለሴት ሲያወሩ የአድማጭን ጆሮ ይበጥሳሉ፡፡ ያካበቱት የብልግና ልምድ አንጠፍጥፈው ይሰጣሉ፡፡ ታዲያ አንዱ አለቃ ለአንዷ ቀበጥ ሒጃቢ ከፈረሸ (ማለትም ኮንዶሚኒየም ተከራይቶ ካስቀመጣት) ይህ ድርጊት ወዲያው ለሌሎችም ይዳረሳል፡፡ሌሎች አለቆችም ተመሳሳይ መንገድን ይከተላሉ፡፡ቀበጦቹ ሒጃቢስቶችም ለመፈረሽ ሲሉ የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡
አንዳንዶች እንደሚሉትና መረጃዎችም እንደሚያመለከቱት በርካታ ሚስቶች ባሎቻቸው ቅምጥን ሲይዙ እምብዛም አይቃወሙም፡፡ቅምጥም እንደሚይዝ ያቃሉ ለምን ከሴት የሚደበቅ ነገር የለምና... ለነርሱ ግብዳውና የእግር ስር እሳት የሚሆንባቸው በነርሱ ላይ ሌላ ሚስትን ማግባት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ፣ በዚህ በኩል ካልተመጣባቸው በርካታ ሚስቶች ባሎቻቸው ለሚዘፈቁበት ቅምጥነት ዕውቅናን ይሰጣሉ፡፡ሰርክ አደራ የሚሉትና የሚፈሩት ሁለተኛ ሚስት እንዳትመጣባቸው ብቻ ነው፡፡ ይህም ስር የሰደደ በመሆኑ በርካታ ባሎች በዚህ በመደፋፈር የቅምጥነት ሽምያውና ንግዱ ተጧጥፎ ቀጥሏል፡፡ ለአብነትም በየንግድ ታዎሮቹ ላይ ያሉ አሠሪዎችን ጨምሮ በርካታ አለቆች ሴትን በማስቀመጥ ያገኙትን ተሞከሯቸውን በመለዋወጥ በየስድስቱ ወሩ አንዳንድ ቅምጥ እንደሚቀያይሩ ታውቋል፡፡ ሌላዉ ቅምጥነትና ስር መስደዱን የሚጠቁሙ መረጃ በቅምጦች የተያዙ አፓርታማዎች ኮንዶሚኒየም መገኘትና መብዛት ነዉ፡፡እነዚህ አፓርታማዎችና ኮንዶሚኒየሞች👇👇👇

ISLAMIC SCHOOL

26 Sep, 17:03


የአንደኛዉ የአለም ጦርነት የተጠናቀቀበትና

ሙስሊም መስሎ የሰለለዉስ ሎረንስ እና የእስራኤል አመሰራረት


join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

25 Sep, 15:59


በቀጣይነት ግን እየለመደች ስለምትመጣ ምንም እንኳን ሒጃብ ለብሳ ብትመጣም ያው አስቀድማ ሚሪንዳ ማዘዝዋ ያለ ነው፡፡ እርሱም ከባለፈው ተሞክሮ በመነሳት ዛሬ ኸምሩን በዛ አድርጎ ከሚሪንዳው ጋር ይቀላቅልላታል፡፡ እርሷም ወዳጅዋን ላለማስቀየም ስትል አትምረውም፡፡ በመቀጠልም አብዝቶ በብርጭቆዋ ውስጥ ይጨምርላታል፡፡ እርሷም ስለማታስከፋው ትጠጣዋለች፡፡ ምናልባትም ያሁኑ ሴቶች ዓይን አውጣዎች ስለሆኑ በዚሁ ዕለት ሒጃቧን ከፀጉሯ ላይ አውርዳ ቦርሳዋ ውስጥ በመከተት ሚሪንዳውን ትታ ድራፍቱን ልትጀምር ትችላለች፡፡ እኔ በፊት በፊት ባለኝ መረጃ ሴቶቹ ከሚሪንዳ ወደ ድራፍት ሙሉ በሙሉ ለመግባት ከአራት እስከ አምስት አጋጣሚዎችን እንደሚወስድባቸው ነው፡፡ ነገር ግን አሁን አሁን የሙስሊም ሴቶች ልቅነትና ሀፍረት ቢስነት በእጥፍ ስለጨመረ ምናልባትም በሁለተኛው አልያም በሶስተኛ የግብዣ አጋጣሚ ሒጃቧን አውልቃ ልትጠጣ ትችላለች፡፡ ከዚህን ዕለት ጀምሮም ሚሪንዳን በማቆም በድራፍት አልያም በቢራ ልትቀጥል ትችላለች፡፡ ከካፊር ሴት ጋ የሚገጥመው ወንድም በዚሁ እሳቤ ውስጥ ይገባል፡፡››
በዚህ ጉዳይ ቤተሰብ ሴት ልጅህ የት እንደዋለች ጓደኛዋ ማን እንደሆነ መከታተሉ ኸይር ነዉ...አብዘሀኛዉ ሴቶች እቤት ሌላ እዉጭ ሌላ ናቸዉ...አረ ጎበዝ ሴት ልጅና ቤተሰብ ሳይተዋወቅ ዳዲ ማሚ እያለች ሳትተዋወቁ እየኖራችሁ ነዉ ጎበዝ




╔════════════════════╗
🎖#የባለመኪናዎች_የሴት_ቀበኛነት_አባዜ🎖
╚════════════════════╝



    የዘልዛላ ባለመኪናዎች የሴት ቀበኝነትና ሴሰኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ በተለይ በሊፍት ስም በርካታ ህሊናቸውን የሸጡ ባለመኪናዎች ሴቶችን እያማገጡ ይገኛሉ፡፡ ከቀበጥ ሒጃቢስቶች ቀጥሎ ምናልባትም ሙስሊሙን ማህበረሰብ እየተፈታተነ ያለው ጉዳይ ይኼው ነው:: በነገራችን ላይ የቀበጥ ሒጃቢስቶችን፣የሌላ ሀይማኖት ወንዶች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሙስሊም ሴቶችን፣ የስትኪኒ ወንዶችን፣ የዘልዛላ ባለመኪናዎችን ገመና ገለጥ አድርጎ ማየቱ ለሕዝቡም ትልቅ ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡ ስለዚህ ነገሮችን በጥሞና ማጤንና ከዚህ የሚለቀቁትን መረጃዎች በወጉ ማስተዋል ግድ ይለናል፡፡

በርካታ የዘመናችን ሴቶች (ቀበጥ ሒጃቢስቶችን ጨምሮ) ከዶላር፣ ከፋሽንና ከዕቃ ዕቃ (የሞባይል፣ የላፐቶፕ፣ የጨርቃ ጨርቅ ስጦታ) ባልተናነሰ መልኩ መኪናዎችን እንደሚያመልኩ ይታወቃል፡፡ ከዚህም የተነሳ የሴቶች ጭን ማስተር ኪው በዘልዛላ ባለመኪናዎች እጅ እንዳለ ሁሉ መታሰብ ተጀምሯል፡፡

   የነዚህ የዘነዛላ ባለመኪናዎች ገመናም በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡ በከተማዋ የመኪና ውስጥ ወሲብ መስፋፋቱንና መለመዱን ተከትሎ የነዚህ ግለሰቦች ድርጊትም በሰፈው የተለመደ ሆኗል፡፡ በተለይ ሙስሊም ዘልዛላ ባለመኪናዎች አደገኛንታቸው እየጨመረ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከየሰፈሩና ከየመስጊዱ አመሻሽ ላይ መጥተው ሴቶችን ፒክ አድርገው በየአካባቢው በሚገኙ ጨለማ መንገዶች ዳር በማቆም ማጨማለቃቸውን ገፍተውብታል፡፡ሙስሊም ያልሆኑ ዘልዛላ ባለመኪናዎች ብዙውን ጊዜ በሰዓት እላፊ ጊዜያቸው አብዝተው የሚያመሩት የሴተኛ አዳሪነት በብዛት ወዳለባቸው አካባቢዎች ነው፡፡ ነገር ግን ሙስሊም ዘልዛላ ባለመኪናዎቹ ትኩረታቸውን ያደረጉት የቤት ልጆች ላይ ሲሆን መኪናዎቻቸውን በየሰፈሩ በሚገኙ ጨለማ ቦታዎች በማቆምም የመኪና ውስጥ ዝሙትን አስፋፍተዋል፡፡ ይኼው የተለመደ እኩይ ድርጊታቸው በተለይ በረመዷን ውስጥ የሴቶች ልቅነት ስለሚበዛ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ሴቶችን ከመስጊድ አካባቢ ፒክ አድርገው የሚሄዱ መኪናዎችም ጋጋታ ሲፈጥሩ ይታያሉ፡፡



╔════════════════════╗
🎖#ላማገጧት_ሴት_ስጦታን_መጀባትና_ላማገጣት
         #ወንድ_ስጦታን_መቀበል🎖
╚════════════════════╝


     በርካታ ዘልዛላ ወንዶች ለሚያማግጧቸው ሴቶች የተለያዩ ስጦታዎችን ሲጀቡና ዝሙተኛ ሴቶችም ካማገጧቸው ወንዶች ስጦታዎችን ሲቀበሉ ይታያሉ፡፡ በእውነቱ የዚህ ዓይነቱ ድርጊት እጅግ አደገኛ ነው፡፡ የማይወጡት የኃጢአት ቀለበት ውስጥም ይከታል፡፡ ይኸውም ለሚያማግጧቸው ሴቶች ስጦታዎችን የሚጀቡ ወንዶች ተውበት ለማድረግ ቢፈልጉ እነዚያን #ስጦታዎች_መልሰው_መውሰድ_ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያንን ደግሞ ማድረግ አይሳካላቸውም፡፡ ለዝሙተኛ ሴቶችም ቢሆን ተውበት ለማድረግ ከፈለጉ በብልግናቸው ሳቢያ የተጀቡትን ስጦታ መመለስ አለባቸው፡፡ ይህን ማድረግ ግን በቀላሉ አይሳካም፡፡ ስለዚህ እዚህ ደረጃ የደረሱ ዝሙተኛ ወንዶችና ዝሙተኛ ሴቶች ታላቅ መጥመምን ጠመዋል፡፡

አህመድ አዲስ አበባ ታዋቂ ባለሱቅ እንዲህ ብሏል፡-
«ስንቶቹን ሙስሊም ጥንዶች ቀን በጠራራ ፀሐይ ወደ ፔንሲዮኖች ተያይዘው ሲገቡ እያየን አይደል እንዴ? ያለ ምንም ኃፍረትና መሸማቀቅ ወደ ዝሙት ቤቶች ዘው ብለው ሲገቡ እያስተዋልን አይደል እንዴ? አንዳንዶቹማ የዝሙት አልቤርጎዎችን እንደ መኖሪያ ቤታቸው የቆጠሩ ይመስላል፤ ወደነዚህ ቤቶች ሲገቡ ምንም ኃፍረት አይታይባቸውምና፡፡ የዝሙት ውሏቸውን ሲያጧጡፉ አንዳችም ወንጀል የሰሩ አይመስላቸውም፡፡ በብልግና ብቻ መኪና የተጀባቸው ሴቶች አሉ፡፡ በከተማዋ ውስጥም ለባለጌ ሴቶች የተጀቡ መኪናዎችም ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ ለእንትና እኮ መኪናዋን የጀባት ያ ያማገጣት ሰውዬ ነው ይባላል፡፡ በርግጥ ዝሙተኞች ከብልግናቸውም በላይ ስጦታን ሲቀባበሉ ስታይ የባሰ ትደነግጣለህ፡፡ ወደፊት ከኃጢአታቸው እንዴት ይቶብቱ ይሁን? ብለህ ስታስበው ትጨነቃለህ፡፡ አላህ ይጠብቀን እንጅ፣ በርካታ ዝሙተኛ ሴቶች መኪና ተጀብተዋል፡፡»ብሏል አህመድ ባለሱቁ


   📚📚 በጥቅሉ እነዚህና እስካሁንም የተነሱ ነጥቦች ዝሙት በሙስሊሞች መካከል መስፋፋቱን የሚጠቁሙ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ሌሎችም ያልተነሱ ነጥቦች ይኖራሉ፡፡ ይህም በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በሀገረ ደረጃና በሕዝበ ሙስሊሙ ደረጃም ዝሙት ተስፋፍቷል፤ ይፋም ወጥቷል፡፡ ይህም ማህበረሰባችን በዝሙት ደዌ መታመሙን ያመለከታል፡፡ ፈጥኖ ፈውስ ካልተገኘለትም በሽታው የባሰ ሥር እየሰደደ ከባድ ማህበራዊ ውድቀትን ሊያስከትል ይችላል፡፡

#በቀጣይ ክፍል☞ሴቱ ሁሉንም ሀዲስ  ያዳምጣል ግን ለወንድ የተፈቀደዉን ሁለተኛ ማግባት ባይሰሟት ደስ ይላቸዋል፡፡ ወንድም ብዙ ሱና አለ ፆሙ የለይል ሶላቱ ወዘተ እያለ ሱናዉን እንተግብር ብሎ የሚያወራዉ ሁለተኛ ሚስትና ምግብ በጀመአ እየበላ ሊተርፍ ሲል ሱናዉን ሀይእናድርግ ይላል😉፡፡
ግን ስለሁለተኛ ሚስት የሚያወራዉ 99%ወንድ ሁለተኛ ማግባትን ያወራል ከዚህ መሀል ግን 85%ያላገባዉ ወንድ ነዉ ስለ ሁለተኛ ማግባት የሚፈተፍተዉ 10%ያገባዉ ወንድ አገባለሁ እያለ ያወጋል ግን Money ኢንጅሩ😆...4%ወንድ አቅም ያለዉ ነዉ ግን 2%አግብቶ ሰላም ስለሚያጣ አያገባም 2%ወደቆላዉ አካባቢ ያለ አግብቷል፡፡
የሚመለከተዉ 4%አቅም ያለዉን ወንድ ነዉ እንጂ የሚፎክረዉን አይደለም....እናም የሀብታም ባል ሴቶች ሁለተኛ ሚስት በመከልከላችሁ ባሎቻችሁ ዚና ላይ እንዴት እንወደደቁ እንዳስሳለን


#ምዕራፍ ➊➎
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot



join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

25 Sep, 15:59


🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #ምዕራፍ_አስር_አራት ➊➍
                  አሚር ሰይድ
ምንጭ☞60%በዝሙት መዘመን ስልጣኔ ወይስ የአለም ፍፃሜ ከሚለዉ መፅሀፍ የተቀነጨበ

╔════════════════════╗
🎖 #የሙስሊም_ሴቶች_ከካፊር_ወንድ_ጋር
       #ወሲባዊ_አጋርነት_መመስረት🎖
╚════════════════════╝


    አሁን  ላይ የዱንያም የአኼራሜ መስመር እቅድ የሌላቸዉ የፈጣራን ትዕዛዝ ዘንግተዉ የስሜት ህዋስያንና ሸይጧን የሚያዛቸዉ የሚያሾራቸዉ ሙስሊም ሴቶች ሙስሊም ወንድ ለትዳር ካልሆነ እነሱን ማዉራት ማናገር ሲፈራ ሙስሊም ወንድ አይመቸንም በሚል ከሌላ ሀይማኖት ተከታይ ጋር የወሲብ ጓደኛ በብዛት ሁነዉ ከአንደኛ ደረጃ ትቤት እስከ ዩኒቨርስቲ ስራ ቦታ ሳይቀር....በዚሁ የወሲብ ጓደኝነት የተነሳ በሀራም የተጀመረ በረካ የለዉምና የአላህ ቁጣ በዱንያም በአኼራም ስለሆነ ሀይማኖታቸዉን ቀይረዉ አግብተዉ እያየን ነዉ፡፡ አብዘሀኛዎቹ ሴቶች ግን ወይ የወሲብ ጓደኛ ብቻ ሁነዉ ትዳር ከመጣ እናቆማለን የሚል አቋም ይዘዉ እድሜያቸዉን እየገፉ ይገኛሉ፡፡
ወቅቱ አብዘሀኛዉ ሴት ሀያዕ ስለሌሊቸዉ በዝሙት ላይ ማሳለፍ ስለሚፈልጉ የሌላ ሀይማኖት ወንድ ሲያወራቸዉ መንገድ ላይ ሲሸኛቸዉ እጥፍ ድርብ ደስታቸዉ እየሆነ እየተስተዋለ ነዉ...,ለምን እሱ ዚና እንስራ ብሎ ለመጠየቅ አይፈራም...ሴቱም የአላህን ህግ ለመጣስ የከለከለዉን ለመከልከል ሀያአቸዉ በራሳቸዉ ምክንያት እንዲነሳ ስላደረጉ... ከሌላ ሀይማኖት ወንድ ጋር የዚና ጓደኛ ላለመሆን ቢጠና የብናኝ ያህል ኢማንና ሀያዕ ያስፈልጋል ሴቱ ይሄን ኢማን ያጡት ይመስላሉ....እንደምታዩት በየመንገዱ ሙስሊም ሴቶችን አብሮ ሲሄድ የምታዩት:ፔንሲዮን ላይ መዝናኛ ቦታ የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ወንድ ጋር አብረዉ ነዉ፡፡

የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ወንድ በይፋ በጠራራ ፀሀይ እየታየ ሴቱን ሲያበለሽ....ሙስሊሙ ደግሞ እንጋባለን እንዴት አታምኚኝም ነገ ባልሽ አይደለሁ እያለ የሴቱን ትዳር ፈላጊነት በመጠቀም በዚና ዱንያንም አኼራቸዉንም እያበላሹ እየተስተዋለ ነዉ፡፡

በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነዉ ቢወራ ቢወጋ ሆድ ይፈጀዉ ብዙ ትዝብት ይፈጥራል፡፡እኔ በጣጣም ብዙ የማቃቸዉ በዚህ ህይወት የሚያሳልፉ አሉ

ግን እስኪ ሌላዉ ለጊዜዉ ይታፈንና.. እዉነተኛ መረጃ በጥናት የተገኘ  እነሆ:-
     

ዳዊት* (ስሙ የተቀየረ) በኮልፌ አጠና ተራ አካባቢ የአንድ ፔንሲዮን ኃላፊ ሲሆን አገልግሎት የሚሰጡትም ለጥንዶች ነው፡፡ ይህ ፔንሲዮንም በሰፈሩ ዝሙትን እንዳስፋፋ ይነገርለታል፡፡ ታዲያ ከደንበኞቹ መካከል ግማሾቹ ሙስሊሞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ከነዚህም መካከል አስካሪ መጠጥን ሳይቀር የሚጠጡ እንዳሉ ይናገራል፡፡ የነዚህን ሙስሊም ሴቶችና ክርስቲያን ወንዶችን መጨረሻቸውን በተመለከተ ለሰባት ዓመታት አብረው በጓደኝነት የዘለቁ እንዳሉም ይናገራል፡፡ እርሱም እነሱን በቅርበት እንደሚያውቋቸው ገልፆ እርሷ ነጋዴ ስትሆን እርሱ የቢሮ ሰራተኛ እንደነበረ ይገልፃል፡፡ በተጨማሪነትም ክርስቲያኑ ወንድ ሙስሊም ሴቶችን ለጊዜያዊነት እንጂ ለዘላቂነት እንደማይፈልጋቸው ጭምር በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲህ ሲል ያብራራል፡-

«እነዚህ ጥንዶች ይህን ያህል አብረው ሲቆዩ ስለ ሀይማኖት አንዴም ተነጋግረው ኢያውቁም፡፡ ታዲያ በአንዲት መጥፎ አጋጣሚ የልጅቷ አክስት አንድ ከውጭ አገር የመጣ ባል ተገኝቶልሻል፤ ስለዚህ ኒካህ ይደረግላችሁና አግቢው አለቻት፡፡ የዚህን ጊዜ ልጅቷ እኔ እኮ ጓደኛ አለኝ ስትል ለአክስቷ መለሰችላት፡፡ አክስትም ደህና እንግዲህ! በቃ አንቺ የፈቀድሽው ሰው እስካለ ድረስ በቃ ኒካሕ ይደረግላችሁና ተጋቡ አለች፡፡ የዚህን ጊዜ ልጅቷ የምታደርገው ሁሉ ግራ ገባት፡፡ ከዚህ ክርስቲያን ጓደኛዋ ጋር በወሲብ አጋርነት አብረው ከመቆየት ውጭ ስለወደፊቱ ህይወታቸውና እምነታቸው ከዚህ በፊት በግልፅ አልተነጋገሩም፡ አሁን ነገሮች ፈጥጠው መጡ፡፡ ነገሩ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ሆነ፡፡ እንዳትተወዉ ልጁን ወደዋለች፡፡ እንዳይጋቡ በሀይማኖት ጉዳይ ምንም የፈጠሩት ስምምነት የለም፡፡ በዚህን ጊዜ ልጅቷ እኔ ዘንድ መጣችና ሁኔታውን አስረዳችኝ፡፡ ከርሱ ቤተሰቦች መካከል ደግሞ እህቱ ብቻ የሁለቱን ግንኙነት እንደምታውቅ ጨምራ ነገረችኝ፡፡ ከዚያም እኔ የርሱን እህት አስጠራኋትና ያለውን ነገር አብራራንላት፡፡ እርሷም እስካሁን እንዴት ሳይነጋገሩ ይህንን ሁሉ ዓመታት አብረው እንደቆዩ ስታውቅ ብትገረምም ያለውን ነገር ወዲያው ለወንድሟ ነገረችው፡

እርሱ በበኩሉ ይህንን ሲሰማ በጭራሽ እንደማይሆንና እርሷን የፈለገውን ያህል ቢወዳትም እምነቱንና ቤተሰቦቹን ትቶ ኢስላም እንደማይሆን በመግለፅ አቋሙን አሳወቀን፡፡ እርሷም በበኩሏ እምነቷንና ቤተሰቦቿን ትታ ክርስቲያን እንደማትሆን ገልፃ በዚሁ ሰበብ ግንኙነታቸው ተቋረጠ፡፡ በርግጥ ልጅቷ ነጋዴ ስለሆነችና ገንዘብም ስላላት በቤተሰብ በኩል ሌላ ባል አግብታለች:: ሆኖም ግን አሁንም ድረስ ስታገኘኝ እርሱን እንደምትወደው ትነግረኛለች፡፡ እርሱም እንዲሁ እርሷን እንደሚወዳት ይናገራል፡፡ እንደውም እሱ ሌላ ክርስቲያን የሴት ጓደኛ ይዞ መጥቶ ለኔም አስተዋውቆኛል፡፡

#በተጨማሪም ዳዊት የታዘበው ነገር ቢኖር ልክ እንደዚሁ ሁለት ጓደኛሞች ሁሉ ብዙውን ጊዜ ሙስሊም ሴቶችና ክርስቲያን ወንዶችም ስለወደፊቱላት ጓደኛሞች አስቀድመው ሳይነጋገረው እንዲሁ በደፈናው ብዙ ጊዜ አብረው እንደሚቆይኑና የኋላ ኋላ እንደሚለያዩ አርግዘው እንደሚያስወርዱ ይናገራል፡፡

#ሌላው ስለሙስሊም እና ክርስቲያን ወንድና ሴት ጥንዶች ገመና የሚናገረው ሰልሀዲን ነው፡፡ እንዲህም ይላል፡-

   ምን አለ መሰለህ? በተለይ ከክርስቲያን ወንድም ሆነ ሴት ጋር ወሲባዊ አጋርነትን የሚመሰርቱ ሙስሊሞች ከዝሙት በተጨማሪ አልኮል ላይ የመውደቅ ዕድላቸው ሰፊ ነው:: ከዚህም የተነሳ በተለይ ሴቶቹ ከኢስላም የመውጣት ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህንንም በተለያዩ አጋጣሚዎች አስተውለናል፡፡ የዝሙቱ ግልፅ ስለሆነ አንተም ስለሱ አትጠይቀኝም፡፡ ወደ አልኮልስ እንዴት ይገባሉ ?ማለትህ ግን አይቀርምና እነሆ የማውቀውን ልንገርሀ፡፡

አየህ! ሴቶች #በተፈጥሮ_ሚሪንዳን_ይወዳሉ፤ በተለይ ሙስሊሞቹ፡፡ የሴቶች ምርጫ ግርም ይለኛል፡፡ ሁሉም ሚሪንዳን አብዝተው ይፈልጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት በክርስቲያን ወንድና በሙስሊም ሴት መካከል የወሲብ አጋርነት ሲኖር እርሱ ሊጋብዛት ሬስቶራንት አልያም ፔንሲዮን ይዟት መሄዱ የማይቀር ነው፡፡ የዚህን ጊዜ እርሷ ሚሪንዳ ታዛለች፡፡ እርሱ ግን ወንድ በመሆኑ፣ ብሎም ካፊር በመሆኑ የወንድነት መገለጫው መጠጥ ስለሆነ ቢራ አልያም ድራፍት ያዛል፡፡ ከዚያም እርሷም ሚሪንዳዋን እየተጎነጨች፣ እርሱም ድራፍቱን እየጠጣ የወዳጅነት ጨዋታው እየደራ ሲመጣ እርሱ ቀስ እያለ #ከድራፍቱ_ላይ_ወደ_ሚሪንዳዋ_ይቀላቅልባታል፡፡ እንደምንም ብላ እርሱን ላለማስከፋት ስትል እየተግደረደረች ትጠጣለች፡፡ ቀጥሎም በሚሪንዳ ብርጭቆዋ ላይ ከድራፍቱ በዛ አድርጎ ይጨምራል፡፡ አሁንም ትጠጣዋለች፡፡ ምናልባትም በመጀመሪያው ቀን ይህንን ያህል ከቀማመሰች ይበቃት ይሆናል፡፡ በተለይ ከዚህ በፊት መጠጥ ቀምሳ የማታውቅ ሙስሊሟ ከሆነች ለዛሬው በዚሁ ትከተባለች፡👇👇👇

ISLAMIC SCHOOL

23 Sep, 17:37


#የዱአ_በር

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

22 Sep, 16:39


ሲኒማ ቤቶች ሒጃብ በለበሱ ሴቶችም እየተለመደ የመጣ የመዝናኛ ዘርፍ እንደሆነ ይታያል፡፡ በርካታ ሒጃብ የለበሱ ሴቶች ከወንዶች ጋር፣ ወይም ከሴቶች ጋር
በጀማዓ እየሆኑ፣ አልያም ብቻቸውን ሲሰለፉና ሲገቡ ይታያሉ፡፡ በተለይ ቀበጥ ሒጃቢስቶች (ግብዣ ፍለጋ የሚወጡቱ ይባላሉ) አብሶ እሑድ እሑድ ወደ ሲኒማ ቤቶች አብዝተው እንደሚሄዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የዚህም ዓላማ ወይ አስቀድመው ከወንዶች ጋር እዚያ ተቀጣጥረው ይሆናል፤ አልያም እዚያው ለመሞዳሞድ ይሆናል ምክንያቱም በአንፃራዊነት ሲታይ ወደዚያ የሚመላለሱ ወንዶችም ኪሳቸው ደህና እንደሆነ ይገመታልና፡፡ መቼም አንዲት ሴት የጥገኝነት ሜንታሊቲ አዳብራ ወደዚህ የምትመጣ ከሆነ በውነቱ ይህ ለርሷ ተጨማሪ ውድቀት ነው፡፡ ለሰው ልጅ ክብሩ ከገንዘብ ይበልጥለታልና፡፡



   በተለይ የቀበጦቹ ሒጃቢስቶች የእሑድ እሑድ ሽር ብትን ለሲኒማ ቤቶች መልካም ገቢ እንደሆነ ሲታመን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ግን ትልቅ ማፈሪያ መሆናቸው አይካድም፡፡ ብዙ ሙስሊሞችም በነርሱ ድርጊት በመሸማቀቅ አምርረው ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ይህም በመሆኑ እባካችሁ ይህንን የምታደርጉ እህቶች ድርጊታችሁ ኢስላምን ሳይቀር የሚያሰድብ በመሆኑ ከዚህ እንድትታቀቡ ዘንዳ በአላህ (ሱ.ወ) ስም እንጠይቃችኋለን፡፡ «ሌላው ስለኔ ምን አገባው, የምትሉ እንኳን ብትሆኑም ኢስላም ከብር ስትሉ ከዚህ ድርጊታችሁ ታቀቡ እላለሁ፡፡


╔══════════════════════╗
 🎖 #ዘፈን_በሙስሊሞች_መካከል_መንሰራፋትና   
       #የሙነሺዶች_ተቀባይነት_መጨመር
╚══════════════════════╝


ዒምራን ቢን ሑሰይን (ረ.ዐ) ቀጣዩን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

   አንድ ጊዜ ሀቢቡና ሙሀመድﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ከዚህ ኡምመት የሆኑ የተወሰኑ ሰዎች በመሬት ይዋጣሉ፣ የተወሰኑቱ ወደ እንስሳነት ይለወጣሉ፣ እንዲሁም የተወሰኑቱ በድንጋይ ይወገራሉ (ይቀጠቀጣሉ) አሉ። ከሰሓቦች መካከል አንዱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ያ መቼ ነው የሚሆነውን ሲል ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ዘፈኖችና የሙዚቃ መሳሪያዎች በተንሰራፉበትና አስካሪ መጠጥ በብዛት በሚጠጣበት ጊዜ ነው አሉ፡፡ (ቲርሚዚ)


    ዘፈን ለዝሙት ትልቁን በር የሚከፍት ዓይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡ ዘፈን የሰዎችን ሙድ በመቀየር ለታሰበው ዓላማ መንገዱን ጨርቅ የማድረግ ኃይሎም ከፍ ያለ ነው፡፡ በተለይ የፍቅርና ወሲብ ቀስቃሽ ዘፈን በሴቶች ሙድና ስሜት ላይ ከፍተኛ  ተፅዕኖን በመፍጠር አርሷን ወደዝሙት በቀላሉ የማስገባት ኃይሉ አቻ የለውም፡፡

የሴቶችን ስሜት በማጦዝና በማሾር እነርሱን ከፍተኛ የሆነ ፆታዊ ስሜት ውስጥ  ይከታቸዋል፡፡ በተለይ በዘፈን ላይ አልኮል ከወሰደችበት ሴቷ መቅለጥ ነው፡፡ እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ» እንደሚባለው የዘመኑ ሴቶች እንኳን ዘፈን ተከፍቶባቸው ይቅርና በፊትም #ልባቸው_ከንፈራቸው_ላይ_ነው ይባላል፡፡ የሆነ ሆኖ ሴቶች ረቂቅ እንደመሆናቸው መጠን ልባቸው በዘፈን በቀላሉ ይከፈታል፡፡

ያው ዘፈን የትም ያለና የተለመደ ነገር ነው፡፡ ዘፈን የማይገባበት ቦታ የለም ማለት ይቻላል፤ መስጊድ ሲቀር፡፡ በርግጥ ወደ መስጊድም ገብተው ሞባይላቸውን ሳይለንት ሳያደርጉ ዘፈን የሚያፈተልከባቸው ሰጋጆች ሰርክ ያጋጥማሉ፡፡ ስለዚህ ዘፈን መስጂድ ድረስ ሁሉ በተዘዋዋሪ መጥቷል ማለት ይቻላል፡፡

በተጨማሪነትም ዘፈን በሙስሊሞች መካከል መንሰራፋቱን ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል አንዱ የተለያዩ #ኢስላማዊ_ዲጄዎች ብቅ ብቅ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ኢስላማዊ ዲጄዎች በተለይ የበርካታ ሰዎችን ሰርግ መጀመሪያ አካባቢ በነሺዳ በማድመቅ የሚታወቁ ሲሆን አሁን አሁን ግን ምናልባትም ከሁለት ነሸዳዎች ለጥቆ ወዲያው ወደዘፈን እንደሚገቡ መረጃዎች ያመለከታሉ፡፡ እነዚህ ዲጂዎችም በተለይ በወጣት ሙስሊም ሴቶች ( #ቀበጥ_ሒጃቢስቶች) ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙ ሲሆን በርካታ ቀበጥ ሐጃቢስቶችም ከዲጄዎቹ ጋር አልጋ መውደቃቸው ይነገራል፡፡በተጨማሪ በጣጣም ብዙ ቀበጥ ሒጃቢስቶች ሚዲያ ላይ ከምናቃቸዉ የመድሰክ ሰዎች  ጋር አልጋ ላይ ወድቀዋል

⚠️⚠️⚠️ በተለያዩ ከተሞች በተለይ በአዲስ አበባ ጋጠወጥ ሴቶች ይሄን አመለካከት ይዘዋል፡፡ቢክራን ለታወቂ ሰዉ መስጠት በሚል ገና ከአንደኛ ደረጃ ትቤት ያሉ ሴቶች ጀምሮ እስከ ካምፓስ ድረስ ያሉ ተማሪዎች በዚህ አደገኛ አባዜ ነገ ስትዳር ሲመጣ ቢክራ ነሽ አይደለሽም ብሎ ይጠይቀኛል አይጠይቀኝም እያሉ የሚያስቡበትን የማይመለስ ቀይ የደም ሴላቸዉን በሀራም እየሸኙት ነዉ፡፡ በመድረክ የምናቀዉ ዘፋኞች ታዋቂ ሰዎች በምድረክ የምናቀቸዉ እነስም አይጠሬ☺️ሙስሊሞች(እነማን እንደሆኑ የገባዉ ይግባዉ)
በሴቱም አስገዳጅነት በታዋቂ ሰዎች ቸልተኝነት ለታዋቂ ሰዉ ድንግልናን መስጠት የሚል ፋሽን ከተጀመረ ሰነባብቷል፡፡እባካችሁ ሴቶች ...የሴትነት ህይወት ቀላል አይደለም፡፡ሴትነት ማለት አላማ ግብ ላይ ለመድረስ በዙሪያዉ የተተከለ እሾህ ብዙ ነዉ እሱን እያፀዱ እየነቀሉ የመኖር ህይወት ነዉ፡፡እሾሁ እየወጋ መሄጃ እንዳያሳጣሽ ተጠንቀቂ!!!






#በቀጣይ_ክፍል፡-የሙስሊም ሴቶች ከካፊር ወንድ ጋር ወሲባዊ አጋርነት መመስረት እና የዘልዛላ ባለመኪናዎች አባዜ እና ላማገጧት ሴት ስጦታን መጀባትና ከማገጣት ወንድ ስጦታን መቀበል ላይ ያተኮረ ፁሁፍ ይቀርባል


#ምዕራፍ ➊➍
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot



join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

22 Sep, 16:38


🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #ምዕራፍ_አስር_ሶስት ➊➌
                  አሚር ሰይድ


  የዝሙት ወደ ሙስሊሙ ሰተት ብሎ የገባባቸዉ መንገዶች በሂደትና በተጠና ሲስተም ነዉ...ከነዚህ ዉስጥ በጥቂቶቹ
✏️ማስሚዲያዎች(ቴሌቪዥን፣ሬድዮና ጋዜጦች)
✏️ ፊልም ቤቶች እና ሲኒማ ቤቶች
✏️ ዘፈን በሙስሊሞች መካከል መንሰራፋትና
✏️ የሙስሊም ሰርግ ዲጄ መጨመርና የሙነሺዶች ተቀባይነት መጨመር በዋናኛነት ይነሳሉ


╔══════════════════════╗
🎖 #ማስሚዲያዎች( #ቴሌቪዥን፣   #ሬድዮና_ጋዜጦች)
╚══════════════════════╝



ዐብዱረሂም አህመድ እንዲህ ይላል
   ሚዲያው በተለይም ሴቶቹን አሳምኗቸዋል፡-
☞እንደፈለጉ ወሲብ ቀስቃሽ ልብሶችን እንዲለብሱ፣
☞ የፈለጉትን ፋሽን እንዲከተሉ፣
☞ በፈለጉት ቄንጥ እንዲራመዱ፣
☞ፍቅረኛ መያዝን ከፈለጉ ያለ ሀፍረት እንዲይዙ፣
☞ድብን ብለው የወንዶች ዓይን ውስጥ መግባቱ ፈፅሞ እንዳያሳስባቸው፣
☞ ምን ይሄ ብቻ በፈለጉት ሰዓት እንዲወጡና በፈለጉት ሰዓት እንዲገቡ፣
☞የፈለጉበት ቦታ ያሻቸውን ነገር እንዲሰሩ፣
☞እቤት ውስጥ መዋል የሚለውን ሐሳብ እርግፍ አድርገው እንዲተዉት፣
☞ወደፈለጉበት አካባቢ በነፃነት መዘዋወር እንደሚችሉ፣ ይህንን ሁሉ በወጉ ነግሯቸዋል፡፡ እነርሱም ተቀብለው ተግባራዊ አደረጉት፤ እያደረጉትም ይገኛሉ፡፡ በቃ ሚዲያው እነዚህን ነገሮች ለሴቶች ስላሳመናቸው ነፃ እንዳወጣቸውም ይገመታል፡፡

    ሌላው የሚዲያ ትልቁ ሚና ሴትና ወንድን የትኛውንም ነገር ለመስራት ሲፈልጉ ጥንድ ጥንድ አድርገው ማሳየታቸው ነው:: ዜና አንባቢዎች ወንድ እና ሴት ናቸው፡፡ የስፖርት ዝግጅት አቅራቢዎች ወንድና ሴት ናቸው፡፡ የፖሊስ ፕሮግራም አዘጋጆዎች ወንድና ሴት ናቸው፡፡ በቃ! ወንድና ሴት ተጣምረው ካልተገኙ የየዘርፉ ስራ ሁሉ የሚሰራ አይመስልም፡፡ ከዚህም የተነሳ ይሄ ነገር ወደ ማህበረሰቡ በሚገባ ተጋብቷል፡፡ ለምሳሌ አሁን አሁን ወንዱ ሲቅም ሴቷ ጫት ትቀነጥሳለች፡፡ በተለይም አብዛኞቹ መቃሚያ ቤቶች የሙስሊም እንደመሆናቸው መጠን የሙስሊም ሴቶች ተሳትፎም እጅጉን ጎልቷል፡፡ ይህም ሥራቸው መሆኑ ነው፡፡የሴቶች እኩልነት ይሄም ልማድ በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነትን አግኝቶ ፊልድ እንኳን ሲወጣ ወንድና ሴት አንድ ቦታ ይመደባሉ፡፡ እንደሚዲያዎቹ ቢሆንማ ወንድና ሴት ካልተጣመሩ እንጂ ለብቻቸው መስራት የሚፈቀድላቸውም አይመሰልም፡፡

ለአንድ ሲሪሞኒ  ሽንኩርት እንኳን ለመግዛት ወንድና ሴት መጣመር አለባቸው፡፡ የማስታወቂያው ስራውማ  አይነሳም፡፡  ሞተር ሳይከልን እንኳን ሴቶች ናቸው የሚያስተዋዉቁት፡፡ እንደውም ያለ ሴት የንግድ ማስታወቂያን ማስነገር አይታሰብም፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ የሚያስተላልፈው መልዕከት አለው፡፡›› (ዐብዱረሂም አህመድ ይሄን መልዕክት አስቀምጧል

   ለዝሙት መስፋፋት አበይት መንስኤዎች ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ ማስሚዲያ ነው፡፡ ማስማዲያ በዋናነት ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮንና ጋዜጦችን ያካትታል፡፡ በተለይ ቴሌቪዥን የዝሙት መዳረሻ መንገዶች ከሆኑት ነገሮች መካከል እንደ እርቃንነትና ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ፣ ዘፈን፣ የተለያዩ ኢ-ሞራላዊ ማስታወቂያዎችን በመንገር፣ ፊልሞችን፣ ድራማዎችን፣ ልቅ የወንድና የሴት ግንኙነቶችን በሰፊው ሲያሰራጩና ወደነዚህ ድርጊቶችም ሕዝቡን በመጥራትና አርአያ በመሆን ይጠቀሳሉ፡፡

   አብዛኞቹ የቲቪ ቻናሎች፣ በተለይም በልዩ ልዩ ፊልሞቻቸውና ድራማዎቻቸው የቦይ‐ገርልፍሬንድ  ግንኙነትን በተምሳሌትነት በማስተዋወቅና በማስፋፋት ትልቁን አስተዋጽኦ ተጫውተዋል፡፡ በጋብቻ ያልተጣመሩ ተዋናዮች እንደፈለጉ በፍቅር ስም ለባለትዳሮች ብቻ የተፈቀዱትን ነገሮች ሲያደርጉ የቲቪ ቻናሎች ደግሞ እነዚኑ የዝሙት ድርጊቶች የማሰራጨትና ወደታዳሚዎቻቸው የማድረሱን ኃላፊነት ተወጥተዋል፡፡

አብዛኞቹ የቲቪ ቻናሎች የሚያሰራጯቸው ዘፈኖች፣ ፊልሞች፣ ድራማዎች፣ ማስታወቂያዎች፣ ዜናዎች፣ ወዘተ በኢኽቲላጥ (ልቅ የተቃራኒ ፆታዎች ቅልቅል) የተሞሉ ናቸው፡፡ ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ ይደንሳሉ፡፡ በወንድና በሴት የፊልም ተዋንያን መካከል ልቅ የሆነ ኢንተራከሽን አለ፡፡ ማስታወቂያዎች ላይም እንዲሁ፡፡ በዜናዎች ላይም ሴትና ወንድ ተጣምረው መታየታቸው የተለመደ ነው፡፡ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ላይም ሴትና ወንድ በፕሮግራም መሪነት አብረው ይሰየማሉ፡፡ ከሞላ ጎደል በየፕሮግራሞቹ የወንድና የሴት ጥምረት የተለመደ ነው፡፡ ይህ ሁሉ እኩይ ልማድ ሕዝቡን ወደ ዝሙት ለመጥራት ትልቅ መሳሪያ ሆኗል፡፡



╔═══════════════════╗
🎖#ፊልም_ቤቶች_እና_ሲኒማ_ቤቶች🎖
╚═══════════════════╝



    ለዝሙት መስፋፋት አበይት አስተዋፅኦ ካበረከቱ የሚዲያ ዘርፎች መካከል በየሰፈሩ ያሉት ፊልም ቤቶችና ሲኒማ ቤቶች ናቸው:: «ነውር የሚባል ነገር የለም, የሚለውን የምዕራቡን ዓለም አስተሳሰብ በመዝናኛ መልክ ወደ ህዝብ ያሰርፁትም እነዚሁ ሚዲያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የመዝናኛ ዘርፎች እንደ ዝርፊያ፣ ሽብር፣ ግድያ፣ ወዘተ ያሉ ወንጀሎችን የሚያበረታቱ ኢ-ሞራላዊ ፊልሞችን የሚያሳዩ ሲሆኑ ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞች ግን ዋናው የስራ መስካቸው ነው፡፡ ብዙዎቹ ፊልም ቤቶች ደንገዝገዝ ሲል ሮማንቲክ ፊልሞችን ማሳየት ይጀምራሉ፡፡ መሸትሸት ሲልም የወሲብ ፊልምን ሳይቀር ያሳያሉ፡፡ በሌላ በኩል ሳይንሳዊ፣ ምሁራዊ፣ ታሪካዊ፣ ማህበራዊና መንፈሳዊ ፊልሞች የነዚህ ቪዲዮ ቤቶች መነሻቸውም መዳረሻቸውም ሆነው አያውቁም፡፡ ከነርሱም እንደዚህ ዓይነት ሰናይ ነገሮች አይጠበቁም፡፡ እናም የእኩይነት ባህሪያቸውና አፍራሽነታቸው ገሃድ የወጣ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን በጥቅሉ በየሰፈሩ የሚገኙ በካዮችን፣ መልካምነት የማይታይባቸውን፣ ይልቁንም ትውልድን የሚያበላሹ እኩይ የመዝናኛ ቤቶችን «የብልግና ሱቆች ብንላቸው የበለጠ ይገልፃቸዋል፡፡

    በተለይ ፊልም ቤቶች በመጠንና በዓይነት በዝተው በየሰፈሩ የሚገኙ በመሆናቸው ለሕፃናት፣ ለአዳጊዎች እና ለወጣቶች በመዝናኛ ስም በርካታ አፍራሽ ነገሮችንና ብልግናን የሚያስተምሩ ናቸው:: ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረውም በርካቶች በተለይም ምሽት ላይ ሮማንቲከና የወሲብ ፊልምን በማሳየት የተጠመዱ

ናቸው:: ከወሲብ ፊልም የሚያገኙት ገቢም ከሌላው ከፍ ይላል፡፡ በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ፊልም ማየት የተለመደ ነው፡፡ በየዓመቱ የሚመጡ ተመራቂ ተማሪዎችም አዳራሾችን ቀድመው በመከራየት ገና ተማሪው እንደገባ እነርሱም ፊልሞቻቸውን በማሳየት ለምርቃቸው የሚሆኑ ገቢዎችን ይሰበስባሉ፡፡ ታዲያ እነርሱ ዘንድም ሳይንሳዊ ወይም ምሁራዊ ፊልሞች አይታወቁም፤ እነዚያው በየፊልም ቤቶቹ የሚታዩ ኢ-ሞራላዊ ፊልሞች ናቸው እንጂ፡፡የወሲብ ፊልሙን ሴቶችም ገብተው ያያሉ፡፡

  ሌላው በመዝናኛ ስም ትውልዱን የሚያበላሸው ሲኒማ ቤት ነው፡፡ ምንም እንኳን ሲኒማ ቤቶች በንፅረት ከፊልም ቤቶች ለምቾት የቀረቡና ከአይደፈሬው ወሲብ የራቁ ቢሆኑም ግና እነርሱንም ከብልግና ሱቆች ጋር አንድ የሚያደርጋቸው ሳይንስን፣ ታሪክን፤ ማህበራዊነትን፣ ሞራሊቲን የሚያስተምሩ ፊልሞችን ሳይሆን ኢ-ሞራሊቲንና ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን ማሳየታቸው ነው::👇👇👇

ISLAMIC SCHOOL

21 Sep, 16:27


#ለምን_ተስፋ_ትቆርጣለህ??

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group

ISLAMIC SCHOOL

20 Sep, 17:31


  “እህቴ ሆይ! አንቺ ምናልባትም አሁን በሕይወት እያለሽ የተሟላወን ሒጃብ ለመልበስና በአግባቡ ለመሸፋፈን ላትፈልጊ ትችያለሽ፡፡ ያው በግልፅ እንደምናየው
☞ሽቶ ተቀባብተሸ፣
☞ከናፍርሽን ሊፒስቲከ አጥግበሽ፣
☞ጡቶችሽን አሹለሽ፣
☞ደረትሽ ከፍተሽ፣
☞ ዓይኖችሽን ተኳኩለሽ፣
☞እጆችሽንና እግሮችሽን ገላልጠሸ፣
☞ወሲብ ቀስቃሽ ጨርቆችን ለበስሽ የትም እየታየሽ ነው፡፡ ከሩቁ ድብን ብላሽ የሰው ዓይን ውስጥም እየገባሽ ነው፡፡ በእውነቱ #ቀበጦቹ_ሒጃቢስቶች ዓይነ ግቡ ለመባል ከፍተኛ ጥረትን እያደረጉ ነው፡፡

ነገር ግን አስታውሺ! አንድ ቀን ከራስ ፀጉርሽ እስከ እግር ጥፍርሽ ድረስ በተገቢው ሁኔታ ትለብሻለሽ፡፡ ግን የዛኔ #ወደመቃብር_ነው_የምትወርጂው፡፡ ስለዚህ ያንን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሟላ ሒጃብን የምትለብሽበት ዕለት አታድርጊው፡፡ እባከሽን አሁኑኑ ልበሺው ዞሮ ዞሮ ከቤት፤ ኖሮ ኖሮ ከመሬት, ሲባል አልሰማሽም? ገላ ፈራሽ ነው፤ ውበትም ጠፊ ነው፡፡ አዎ! ምንም ያህል ብታምሪ፣ የቱንም ያህል ድብን ብለሽ የወንዶች ዓይን ውስጥ ብትገቢ አንድ ቀን ሟች ነሽ፡፡ እናም ከወዲሁ የአኼራ ሕይወትሽን ገንቢ፡፡ በዱንያ ሳለሽ ለቀብርሽ ስንቅ ያዥ፡፡

  #ሙስሊሟ_እህቴ_ሆይ! ልክ እንደ ሉል ሁኚ፡፡ እንደሚታወቀው ሉል ውድ እና ብርቅ ነው:: ለዚህም የበቃው የረጋበት ቦታ ነው፡፡ ሉል ለአሳሾች እሩቅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ውድ ሆኗል። አንቺም እንደዚያ መሆን አለብሽ፡፡

በሌላ በኩል እንደዘመኑ ቀበጥ ሒጃቢስቶች እዚያም እዚህ አትታይ፡፡ የትም የሚገኘው እኮ #ድንጋይ_ነው፡፡ እንደ አበባም አትሁኚ ተጠቅመውብሽ ይወረውሩሻልና፡፡ እናም አንቺ ትከከለኛ ሒጃቢ ሴት ሁኚ። በዚያን ጊዜ ሒጃብሽ መከበሪያሽ ይሆናል፡፡ ምንዳሽም ጀነት ይሆናል፡፡



╔══════════════════════╗
  #እስልምናን_ስትተገብሪዉ_ወደ ኢስላም_ትጠሪያለሽ
╚══════════════════════╝



⚡️⚡️አሜሪካዊው ታላቁ ዳዒይና በቁርኣን ተፍሲር ትልቅ ዕውቅናን ያገኘው ኑእማን አሊ ካህን በበኩሉ በምዕራቡ ዓለም እጅጉን የተንሰራፉ ነገሮች በተለይ ወለድና ዝሙትን የመሳሰሉ ኃጢአቶች እነሱ ዘንድ ከሞላ ጎደል እንደማይታወቁ ይናገራል፡፡ በተለይም ከጥቂት ዓመታት በፊት የደረሰውን የምዕራቡን ዓለም የገንዘብ ቀውስን አስመልክቶ ቀውሱ ሙስሊሞችን እምብዛም እንዳላጠቃቸው በመጥቀስ አሜሪካዊው ሙስሊም ከወለድ የራቀ መሆኑን እንደማሳያ ያነሳል፡፡

#ቀጥሎም ዝሙትን አስመልከቶ አሜሪካዉያን ሙስሊሞች ከዚህ መራቃቸውን እንደ ማሳያ የሚያነሳው ነገር ቢኖር የመስሊም ሴቶችን ታላቅ ግብረገብነትና የሒጃብ አለባበሳቸውን በመጥቀስ ነው::

በዚህች ሀገር የሴቶች ትልቁ መከበሪያቸው ሒጃብ ነው:: የራስ መተማመናቸውና ለኢስላም ያላቸው ፍቅር ያስደንቅሃል፡፡ ሴቶቹ እንዴ ከሰለሙ በኋላ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን ሊከተሉ ቀርቶ ከቶውኑ አያስቡትም፡፡ ቀድሞውኑ ኢስላምን አጥንተውትና መርጠው ስለሚመጡ ሰዉ ምን ይለኛል የሚለውን ነገር ከመጤፍ አይቆጥሩትም፡፡ ወንዶቹም ቢሆኑ አብዛኞቹ ያገቡ ስለሆኑ ስለዝሙት አይነሳባቸውም፡፡

እንደውም በአንድ አጋጣሚ የተከሰተውን ነገር ለምን አልነግራችሁም? በአንድ ወቅት አንዲት ደምቃና የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ተሸሞንሙና የወጣች እንስት ከአንድ ወጣት ሙስሊም ጋር በባቡር ላይ ይገናኛሉ፡፡ ሰዉ ሁሉ አተኩሮ ያያታል፡፡ እርሷም እየተገማሸረች የምትወጣው ለዚህ ነው፡፡ ወንዱ ሁሉ በአድናቆትና በምኞት ይመነጥራል፡፡ ይህ ወጣት ግን አንዳችም ትኩረት ላይሰጣት ቀረ፡፡ እርሷ ግን አልፎ አልፎ ትገረምመዋለች፡፡ እርሱ ወይ ፍንክች አላለም፡፡ ታዲያ ተሳፋሪው ቀስ በቀስ እየወረደ ሲቀንስ እርሷ አውቃ የወጣቱ ዓይን ውስጥ ለመግባት ተጠጋችው፡፡ እርሱ ግን አሁንም ከምንም አልቆጠራትም፡፡ ወዲያ ወዲህ ብትቀበጥም አላተኮረባትም፡፡
..... በመጨረሻም በኃይለኛው ተቆጥታ ለመሆኑ አንተ ወደኔ አንዴም የሚታየው እኔ ይህን ያህል ቀፋፊ ነኝ እንዴ? ቆይ እንዲህ ከሆነ እኔ ለማነው ተጋጊጬ የምወጣውን ስትል አቧረቀችበት፡፡

እርሱ ግን በተረጋጋና የራስ መተማመን መንፈስ በተሞላበት ሁኔታ ይህንን ለምን እንደማያደርግ አስረዳት፡፡ አየሽ! እኛ ሙስሊሞች ዕይታችንን እንድንቆጣጠር ታዘናል፡፡ ስለዚህ ወደ ባዳ ሴት ሆነ ብሎ መመልከት የተከለከለ ነው፡፡ ለዚህ ስል ብቻ ነው እኔ ወደ አንቺ የማላየው፡፡ ከዚህ ውጭ በግል ምንም ያደረግሸኝ ነገር የለም፡፡ የእምነት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው ወዳንቺ የማልመለከተው አላት፡፡ ልጅቷ በሰማችሁ ነገር ተገረመች፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰውና እምነት እንደዚያ ሰይጣንን አብዝታ በምታበረታታው ሀገረ አሜሪካ መኖሩ አስደነቃት፡፡ እምነት ሰውን ከብልግና ሲታደግ አስተዋለች፡፡ እናም ለመሆኑ ያንተ እምነት ምንድነው? ስትል ወጣቱን ጠየቀችው፡፡ እርሱም እምነቱ ኢስላም መሆኑን ነገራት፡፡ ስለኢስላምም አንዳንድ ነገሮችን ነገራት፡፡ ከዚያም ስልክ ተለዋወጡና በዚሁ ተለያዩ፡፡

ልጅቷ በሰማቸውና ልጁ ላይ ባየችው እፁብ ድንቅ ምግባር እጅጉን ተደምማለች፡፡ እንዲህ ዓይነት ወጣት ገጥሟት ስለማያውቅ ስለርሱ እምነት ልታጠና ጓግታለች፡፡ ወዲያው በነጋታው ደውላ የቁርአንን ኮፒ እንዲሰጣት ጠየቀቸው:: እርሱም የቁርአን ኮፒ ሰጣት ልጅቷም ቁርአንና ሌሎችንም ኢስላማዊ መጻሕፍት ለስድስት ወራት አከታትላ አጠናችው፡፡ ስድስት ወሩ እንዳለቀም ለልጁ ደወለችና ኢስላምን መቀበል እንደምትፈልግ አበሰረችው፡፡ እሱም ወደመስጊድ ወሰዳትና ሰለመችም፡፡ የአላህን አንድነትና ብቸኛ አምላክነቱን መሰከረች፡፡ገና ልትሰልም ስትመጣ እራሱ ሒጃቧን በወጉ ለብሳ ነበር፡፡ እናም አሁን በኛ ማዕከል ውስጥመደበኛ ሴት ዳዒይ ስትሆን በርሷ ሰበብም በርካታ ሴቶች ወደ ኢስላም መጥተዋል፡፡
(ምንጭ፡- ቮይስ ኦፍ ኢስላም - አሜሪካ)

በመጨረሻም ኑእማን አሊ ካን አያይዞም እንዲህ ይላል፡-
«በአሜሪካ ፊትናው ከባድ ነው:: ግና የሰለምቴው ንቃተ ሕሊና ከፍተኛ ነው::

ሙስሊሙ ሐራምና ሐላልን በሚገባ ለይቶ ያውቃል፡፡ እዚህ በአላህ (ሱ.ወ) ሕግ ማቻቻል የሚባል ነገር የለም፡፡ አንዳች ነገር ሐራም መሆኑን ካወቁ ከቤተሰብ ጋር የሚያለያይ እንኳን ቢሆን ለኢስላም ሲሉ ያደርጉታል፡፡,, (ምንጭ፡- ቮይስ ኦፍ ኢስላም - አሜሪካ)

✏️አላዋቂነት ለሁሉም ኃጢአት አብይ ምክንያት ነው፡፡ በተለይ ዝሙት ላይ የድንቁርና አሻራ እጅጉን ይጎላል፡፡ የሰው ልጅ ዓይን ስላለው በጭለማ ውስጥ እንደማያይ ሁሉ ጭንቅላት ስላለው ብቻ ዕውቀት አለው ማለት አይቻልም፡፡ ዕውቀት ከሌለው ደግሞ ድንቁርና መጥቶ እንደ ወቃቢ ይሰፍርበታል፡፡ በርግጥም ከድንቁርና የበለጠ ክፉ ውቃቢ የለም፡፡ ታዲያ የድንቁርና ውቃቢ ያለበት ሰው ቢያንስ በአራት መንገዶች ዝሙት ላይ የወድቃል በአይኑ በምላሱ በእጁ...

#በቀጣይ_ክፍል
ፊልም ቤቶች፣ ሲኒማ ቤቶች እና ማስሚዲያዎች እንዴት ዝሙትን እንዳስፋፉ የሚያተኩር ፁሁፍ ይቀርባል


አደራ ለአንድ ሰዉ እንኳን ቢሆን ሼር ማድረግ እንዳይዘነጉ


#ምዕራፍ ➊➌
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot



join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group