Dernières publications de ድምፀ ተዋሕዶ (@demtsetewahido) sur Telegram

Publications du canal ድምፀ ተዋሕዶ

ድምፀ ተዋሕዶ
ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን
ለታማኝ መረጃዎ
17,522 abonnés
4,209 photos
91 vidéos
Dernière mise à jour 11.03.2025 07:38

Le dernier contenu partagé par ድምፀ ተዋሕዶ sur Telegram

ድምፀ ተዋሕዶ

28 Dec, 15:54

637

እኳን አደረሰን
ድምፀ ተዋሕዶ

27 Dec, 12:16

478

ይበል፤እኛም እንጠብቃለን።
ድምፀ ተዋሕዶ

26 Dec, 22:03

544

ደንበኛ የቀሳጢ ስራ በአደባባይ።
ድምፀ ተዋሕዶ

30 Nov, 12:53

649

እስመ ኀረያ እግዚአብሔር ለጽዮን፥
ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ፥
ዛቲ ይእቲ ምእራፍየ ለዓለም፤
ዝየ አኅደር እስመ ኅረይክዋ።

እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፥ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና፥ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ። መዝ ፩፻፴፮ ፥ ፲፫

እንኳን አደረሳችሁ
ድምፀ ተዋሕዶ
ድምፀ ተዋሕዶ

29 Nov, 22:03

570

እኛ ህዝበ ክርስቲያኖች እንደ አንድ ክርስቲያን አንድ ነገር ማድረግ እማንችል ከሆነ፤መንግስት ደርዘን ነፍስ በየ ሳምንቱ ሊሰጠን እኛም የሳምንት ቀባሪ ከመሆን አንድንም።መንግስት በቀጥታ ጠብ መንጃ አንስቶ እንኳ ባይገል(የገደለው እንዳለ ሆኖ)፤ሕዝቡን ባለመጠበቁ ለሞቱት ነፍሳት ባለማዘኑ ወይ በመሳለቁ፤እንደ ነፍሰ ገዳይ፣እንደ ወንጀለኛ ነው።
ድምፀ ተዋሕዶ

23 Nov, 16:38

878

እንኳን ለጾመ ነቢያት አደረሳችሁ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት መሠረት ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ነቢያት ነው።

ጾመ ነቢያት ከኅዳር 15 ጀምሮ በየዓመቱ እንደሚጾም የአበው ሥርዓት  የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያመለክታል።

በጾሙ በረከት ረድኤት እንድናገኝ
እግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን።

ድምፀ ተዋሕዶ
ድምፀ ተዋሕዶ

22 Nov, 12:51

665

https://youtu.be/WngGtWEeINw?si=h2fRT0gx-9RhKaC5

ይህን ድንቅ ዝግጅት ይመልከቱ❗️
ድምፀ ተዋሕዶ

21 Nov, 13:12

100

ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤
ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና ፤
አንተኑ ዘመራሕኮሙ ፍና፤
ወአንተኑ ለእሥራኤል ዘአውረድከ መና፤
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል፤
ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ፤
አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዐቢይ፡፡


የሰላማችን መልአክ የሆንክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ
ስለ እኛ ስለምንማለድ፣
ጸሎታችንንም ወደ ታላቁ ንጉሥ መንበር ፊት አሳርግ !

በዓለ ሢመቱ ወበዓለ መራኄ ፍኖቱ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት!

ሚካኤል ማለት «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው።
ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤
ሚ - የሚለው «መኑ» "ማን" ማለት ነው፥
ካ - የሚለው «ከመ» "እንደ" ማለት ሲሆን፥
ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው።

Hebrew: [mixaˈʔel]; Hebrew: מִיכָאֵל‎,
romanized: Mīḳāʾēl, Mīkā'īl, Mīkāl or Mīkhā'īl
lit. 'Who is like El?';
Greek: Μιχαήλ, romanized: Mikhaḗl;
Latin: Michahel;
Coptic: ⲙⲓⲭⲁⲏⲗ;
Arabic: ميخائيل ، مِيكَالَ ، ميكائيل‎,
☆ Michael is an archangel in Judaism, Christianity, and Islam.

The name Michael means "like unto God" or "Who is like unto God?"
Most Known passages about the Archangel Micahel in the bible: Rev 12: 7-9, Jude 1:9, Joshua 6: 1-5, Daniel 3: 25-28,

The Archangel Michael was also with all the saints and martyrs. He strengthened them and enabled them to endure patiently until they finished their strife. According to Holy Scripture and Tradition, he has interceded for humanity multiple times and continues to serve as the Defender of the Faith.


ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥

"መኑ ፡ ይመስለከ ፡ እምነ ፡ አማልክት ፡ እግዚኦ ፤
ወመኑ ፡ ከማከ ፡ ስቡሕ ፡ በውስተ ፡ ቅዱሳን ፤
መንክር ፡ ስብሐቲከ ፡ ወትገብር ፡ መድምመ ። "


«አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት መካከል) አንተን የሚመስል ማነው?
በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነው?» ብሏል። (ዘጸ 15፥11)
ቅዱስ ዳዊትም፦

" አልቦ ፡ ዘይመስለከ ፡ እምነ ፡ አማልክት ፡ እግዚኦ ፤
ወአልቦ ፡ ዘከመ ፡ ምግባሪከ"


«አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። (መዝ 85፥8 )

"ሰላም ለልብከ መዝገበ ርኅራኌ ወየዋሃት
ኅሩመ በቀል ወቅንዐት
ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት
ለደቂቀ ያዕቆብ ዘአኅለፍኮሙ በማእከለ ባህር ግርምት
አኅልፈኒ ሊተ እምኀቡእ መስገርት።
"

የርህራሄ እና የየዋህነት መፍለቂያ ለሆነው ልብህ ሰላም እላለሁ። በነገደ ሃይላት ላይ የተሾምክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ
የያዕቆብ ነገድ ህዝበ እስራኤልን ሌሊቱን በብርሃን አምድ
ቀኑን በደመና ጋርደህ እየመራህ
በባህር መካከል እንዳሳለፍክ
እኔ ኃጥእ የምሆን ባሪያህንም ሰይጣን ከሸመቀው
ከእኔ ከተሰወረው አንተ ከምታውቀው የፈተና ወጥመድ ሁሉ አሻግረኝ።

"አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤
ለለ አሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ፤
ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤
ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤
ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ፡፡
"

ሚካኤል ሆይ ለእያንዳንዱ በየ ክፍሉ ለተነገሩ መልኮችህ ሁሉ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርባለሁ፡፡
ልዑል መልአክ ሆይ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽብህ ኃያል መልአክ ነህና የምስጋናዬን እጅ መንሻ ተቀብለህ ከላይ ከኢየሩሳሌም ሰማያዊት የጸሎቴን ዋጋ እጥፍ ድርብ አድርገህ ላክልኝ።

የቅዱስ ሚካኤል ልመናው እና አማላጅነቱ አይለየን፤ መልካም በዓል፡፡
አሜን !
May His Intercessions be with us all Amen.

ጴጥሮስ አሸናፊ
ድምፀ ተዋሕዶ
ድምፀ ተዋሕዶ

20 Nov, 11:02

17

❤️ የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ 👇

👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

👤 ሊቀ መዘምራን . ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ

👤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

👤 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

👤 ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

👤 ዘማሪ| በሱፍቃድ አንድአርጋቸው

👤 ዘማሪት ሲስተር ሊዲያ ታደሰ

👤 ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ

👤 ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ

👤 ዘማሪ ዲያቆን ብርሃኑ በቀለ

👤 ዘማሪት አዜብ ከበደ

👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ

👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ

👤 ዘማሪት ሰላማዊት በርታ

🔗የሁሉንም ዘማሪዎች ለማግኘት🎚
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ድምፀ ተዋሕዶ

20 Nov, 09:17

74

ማኅሌተ ጽጌን የደረሱት አባት ማን ናቸው?