Dernières publications de ድምፀ ተዋሕዶ (@demtsetewahido) sur Telegram

Publications du canal ድምፀ ተዋሕዶ

ድምፀ ተዋሕዶ
ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን
ለታማኝ መረጃዎ
17,522 abonnés
4,209 photos
91 vidéos
Dernière mise à jour 11.03.2025 07:38

Le dernier contenu partagé par ድምፀ ተዋሕዶ sur Telegram

ድምፀ ተዋሕዶ

21 Jan, 21:35

30

https://www.bbc.com/news/articles/cevexp8er9lo
ድምፀ ተዋሕዶ

19 Jan, 09:16

61

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2017 የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ድምፀ ተዋሕዶ መልካም በዓል እንዲሆንላቹ ይመኛል።
ድምፀ ተዋሕዶ

18 Jan, 16:13

253

የከተራ በዓል አከባበር በዝዋይ (ባቱ)  ከተማ 

ፎቶ :-FBC
ድምፀ ተዋሕዶ

17 Jan, 12:44

462

በአጭር ቃል ቅዳሜ ገሀድ ስለሆነ እንደ ማነኛውም በዐቢይ ጾም እንደሚውሉ ሰንበታት ሆና ትጾማለች እንጂ ጥሉላት ፈጽሞ አይበሉባትም!

✝️✝️✝️
ድምፀ ተዋሕዶ

08 Jan, 23:11

450

በዓለ ልደትን አስመልክቶ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት  የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር በነገው ዕለት ይከናወናል።

በተጨማሪም በነገው ዕለት ጥር ፩/፳፻፲፯ ዓ/ም በተዘጋጀው የቅዱስነታቸው የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር  ላይ  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች  ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
ድምፀ ተዋሕዶ

07 Jan, 11:01

502

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ መሪነት የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር በተገኙበት በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሯል!
ድምፀ ተዋሕዶ

06 Jan, 18:29

517

ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በተገኙበት እየተከናወ ነው።

ከቅዱስነታቸው ጋር ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና እጅግ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና ምእመናት ተገኝተዋል።

መርሐ ግብሩን በቀጥታ ሥርጭት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን(EOTC TV)፣ ሀገሬ ቲቪ እና አርትስ ቲቪ እያስተላላፉት ይገኛሉ።

እንኳን ለበዓለ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
ድምፀ ተዋሕዶ

04 Jan, 14:08

16

💁‍♂️ ለ ኦርቶዶክሳዊያን ብቻ የተከፈቱ በኢትዮጵያ የመጀመርያዎቹ ኦርቶዶክሳዊ ቻናሎች ❤️❤️❤️
ድምፀ ተዋሕዶ

29 Dec, 20:41

723

በሲዳማ ክልል በትራፊክ አደጋ ነፍሳቸውን ላጡ ወገኖቻችን ነፍስ ይማር፤ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ያድልልን።

ድምፀ ተዋሕዶ
ድምፀ ተዋሕዶ

29 Dec, 13:16

526

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አባቶች ጋር ለቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የነበራቸውን አገልግሎት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል ።
ለቅዱስ ፓትርያርኩ እና አብረዋቸው ለተጓዙ አባቶች በብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዓን አባቶች ጋር በመሆን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መረጃው የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው