Dernières publications de ድምፀ ተዋሕዶ (@demtsetewahido) sur Telegram

Publications du canal ድምፀ ተዋሕዶ

ድምፀ ተዋሕዶ
ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን
ለታማኝ መረጃዎ
17,522 abonnés
4,209 photos
91 vidéos
Dernière mise à jour 11.03.2025 07:38

Le dernier contenu partagé par ድምፀ ተዋሕዶ sur Telegram

ድምፀ ተዋሕዶ

09 Mar, 09:39

311

የዓቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት ንባብ

ማቴዎስ 4
1: ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
2: አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።

አዳም በገነት ሳለ ሰይጣን ወደ እርሱ መጥቶ ከገነት ወደ ምድር አወጣው ባሕርይውም ደቀቀ። ጌታ ኢየሱስም የእኛኑ ደካማ ባሕርይ ይዞ ወደ ራሱ ግዛት ወደ ምድረ በዳ ወርዶ ሰይጣንን አሸነፈው አዳምንም ወደ ገነት መለሰው።

ኹላችንም በሰይጣን በተፈተነው በጌታ ኢየሱስ ኾነን ሰይጣንን አሸነፍነው ቀድሞ ወድቆ የነበረው አዳማዊ ባሕርይ በዳግማይ አዳም በጌታ ታደሰ ፤ ሰይጣን ወደ መጀመሪያው አዳም ግዛት መጥቶ አሸነፈው ኹለተኛው አዳም ደግሞ ወደ ሰይጣን ግዛት ሔዶ አሸነፈው።

እኛም ኃይልን በሚሰጠን በጌታ ኢየሱስ የሰይጣንን ፈተናዎች ኹሉ እናሸንፍ ዘንድ ተስፋ አለን ባሕርያችንስ ደካማ ነው ባከበረን በፈተናችን ኹሉ በሚራራልን በጌታ ግን እናሸንፋለን!

መልካም ቀን!
ድምፀ ተዋሕዶ

03 Mar, 20:38

512

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፬ኛው ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፫ኛ ዓመት የእረፍት መታሰቢያ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎት ታስቦ ይውላል።
ድምፀ ተዋሕዶ

03 Mar, 09:16

519

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 12ኛ በዓለ ሢመት የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመከናወን ላይ ይገኛል።
ድምፀ ተዋሕዶ

02 Mar, 17:38

613

አድዋ ላይ የሆነውም ይህ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትም በጦር ግምባር በድንኳን በቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሲያሳርጉ፣ ንጉሡም ቅዳሴውን ሲያስቀድሱ፣ የልዳው ኮከብ የፋርሱ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጣሊያኖቹ ላይ አንጎደጎደባቸው፤ አስደነገጣቸውም፡፡ በእነዚያ ልበ ሙሉዎች ጎራዴ ይዘው በመድፍ ፊት በሚቆሙ ደፋሮች ኢትዮጵያውያን ድል ተመቱ፡፡

የአድዋ ድል ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በገነባችው የመንፈሳዊ ሥነ ልቡና ብርታትና ለሀገርና ለሃይማኖት እስከ ሞት የመጋደል ወኔ የተገኘ መሆኑ ከድሉ እኩል መነገር ያለበት ነው። ኢትዮጵያውያን የኢጣሊያን ወረራ በሀገረ እግዚአብሔር ላይ እንደ ተደረገ ሰይጣናዊ ጥቃት ነበር የቈጠሩት።

እነሆ ዛሬ እኛ የድል አድራጊዎች ልጆች ተባልን፤ “ነጭም” “በጥቁር” ተሸነፈ፤ የነጻነትን ጣዕም ጥቁሮች ቀመሱ፤ የነጭ ፍልስፍና ተሻረ፤ ሰውን ያህል ፍጡር ባሪያ የሚያደርገው፣ አንዱን ገዥ ሌላውን ተገዥ የሚያስብለው የቅኝ ገዥዎች አስተሳሰብም ታሪኩ በጥቁር መዝገብ ተጻፈ፤ ይህም ከሆነ እነሆ ፻፳፰ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ አባቶቻችን ድል አድርገው ታሪክ ሠሩ፤ እኛ ደግሞ ድል ማድረግ፣ ታሪክ መሥራት ቀርቶ ታሪክን መሸከም ከብዶን ለመውደቅ እንፍገመገማለን፡፡

አድዋ አንድነት ነው፤ አድዋ እኩልነት ነው፤ አድዋ ነጻነት ነው፡፡ አድዋ የድሉ ባለቤቶችን መዘከር ነው፡፡ እነዚህን ዘንግቶ፣ የድሉ ፊታውራራዎችን በማንኳሰስ፣ የቤተ ክርስቲያንንም ሚና በመዘንጋት የሚከበር የአድዋ በዓል ትርጉም አልባና ታሪክን የማጥፋት ሴራ ነው፡፡

ለሀገርና ለሃይማኖት የተሠዉትን ሁሉ ነፍሳቸውን ይማርልን።

ተሚማ
ድምፀ ተዋሕዶ

28 Feb, 08:48

526

...........አባ መዓዛ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትምህርት በቂ ችሎታ አላቸው ከሚባሉ መምህራን አንዱ ናቸው፡፡ እኒህ የቤተክርስቲያን ሊቅ ዕውቀታቸውን በበለጠ በዓለም ዐቀፍ ቋንቋ ለማሻሻል ባላቸው ፍላጎት መሠረት ወደ ኢየሩሳሌም አንግሊካን ቤተክርስቲያን ሴንት ጆርጅ ኮሌጅ ተላኩ፡፡ ወደፊት ጵጵስና የሚሾም ብለው ጃንሆይ በተናገሩት መሠረት የኤጲስ ቆጶስነት ትምህርት እንዲሠለጥኑ ነበር የተላኩት፡፡ ሁለት ዓመት ተኩል የቤተክርስቲያን አስተዳደር (Church History and Administration) ተምረው ተመለሱ፡፡ ከውጭ ሀገር እንደተመለሱ ከ1951-1960 ዓ.ም በተማሩት ትምህርት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የካህናት አስተዳደሪ ሆነው ቤተክርስቲያንን በማገልገል ምእመናንን በማስተማር ሐዋርያዊ ግዴታቸውን ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡

በዚሁ መካከል በ1958 ዓ.ም የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ምክትል አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል፡፡ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ምክትል አስተዳዳሪ ሆነው እንኳን በበጎ ፈቃደኝነት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም እየተመላለሱ ያስተምሩ ነበር፡፡ በኋላም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ወደ እንግሊዝ ሀገር ኦክስፎርድ ኦስሄትሮፕ የሚባል የካቶሊክ ኮሌጅ በ1961 ዓ.ም ተልከው በእንግሊዝ ሀገር ለአራት ዓመታት ትምህርታቸውን ተከታትለው (Bachelor of Divinity in Basic Philosophy Super mental and Developmental Psychology) ዲግሪ ተቀብለው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ከሀገርና ከቤተክርስቲያን የተቀበሉትን ታላቅ አደራ አክብረው ሀገራቸውን ለማገልገል በውጭ ሀገር የቀሰሙትን ሥልጣኔና ልምድ ለሀገራቸው የሚያውሉ ምሁራን በርካታ ናቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ካፈራቻቸው ሊቃውንት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በምዕራቡ ዓለም በትምህርት ቆይታቸው በትምህርትና በልምድ ያካበቱትን ዕውቀት በተግባር ላይ ለማዋል የቻሉ ምሁር ናቸው፡፡ በዚህም መነሻ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ፣ የሰበታ ቤተ ደናግል የበላይ ኀላፊና የቦርድ አባል ሆነው አገልግለዋል፡፡ በባሕል ሚኒስቴርም በቋንቋ ጥናት አካዳሚ ውስጥ መርሐ ልሳን ተብሎ በሚታወቀው ክፍል በመምህርነት ሠርተዋል፡፡

በተፈሪ መኰንን ት/ቤት ውስጥ ከውጭ ሀገር በልዩ ልዩ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኢየሱሳውያን ያስተምሩ ስለነበር ብዙ ጊዜ የሃይማኖት ግጭት ይፈጠር ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ተማሪዎች በመንፈሳዊ ዕውቀታቸው ጠንካሮች ስለነበሩ በሚያቀርቡት ጥያቄ በተማሪዎቹና በመምህራን መካካልም በየጊዜው ግጭት ይፈጠራል፡፡ ዐፄ ኃይለ ሥላሴም ጉዳዩን ሲያጣሩ የግብረ ገብነት መምህር እንደሌላቸው በተማሪዎቹ ስለተነገራቸው በአባ ሐና አቅራቢነት በዚያን ጊዜ ስማቸው አባ መዐዛ ቅዱሳን ወደ ጃንሆይ ቀርበው በግብረ ገብ መምህርነት እንዲቀጠሩ ስለፈቀዱ ለተፈሪ መኮንን ት/ቤት የግብረ ገብ መምህር ሆነው ተቀጥረው ከ1949 ዓ.ም እስከ 1954ዓ.ም ድረስ በግብረ ገብነት አስተማሪነታቸው አገልግለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው በተፈሪ መኮንን ት/ቤት እያስተማሩ የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም በተጓዳኝ በትምህርት ቤቱ ግብረ ገብ የሚያስተምሯቸውን ተማሪዎች ሰፋ ያለ የሃይማኖት ትምህርት የሚቀስሙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲሉ በምስካዬ ኅዙናን መድኃ ኔዓለም ገዳም ወጣቶችን ስለሃይማኖት ማስተማር ጀመሩ፡፡ የዚህ አገልግሎት ፍጻሜም አንጋፋውን የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት ለመመሥረት አብቅቶታል፡፡ ብፁዕነታቸውም የዚህ ሰንበት ት/ቤት ከመሥራቾቹ አባላት አንዱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በወቅቱ ለምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ቋሚ ሰባኬ ወንጌል በመሆንም አገልግለዋል፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያን በሬዲዮ ትምህርት በምታስተምርበት ወቅት፤ አባ መዐዛ ቅዱሳን (በኋላ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል) በርቱዕ አንደበታቸው በብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ “ማኅበራዊ ኑሮ በቤተክርስቲያን'' እና “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት” በተሰኙ አርእስተ ትምህርት ይሰጡ ነበር፡፡ ብፁዕነታቸው በሕይወት ዘመናቸው ካከናወኗቸው ተግባራት ለምእመናን በሬዲዮ ስብከተ ወንጌልን በማስተላለፍ የሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላቸው ይናገሩ ነበር፡፡

በአርሲ ሀገረ ስብከት ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በመሆን ለ33 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በአርሲ ሀገረ ስብከት ቆይታቸውም በምእመናን የሚወደዱና የሚከበሩ ታላቅ አባት ነበሩ፡፡ ወደ አርሲ ሀገረ ስብከት በመጡበት የመጀመሪያ ሳምንታት ውስጥ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉትን ዐበይት ችግሮች ካጠኑ በኋላ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ አንድም የወጣቶች እንቅስቃሴ የሚደረግበት አጥቢያ አለመኖሩንና ሰንበት ት/ቤቶችም የተዘጉና ወጣቶችም በቤተክርስቲያን አካባቢ እንዳይታዩና ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር ይደረግባቸው እንደነበረ ካወቁ በኋላ <<የተሾምነው ምእመናንን ልንጠብቅ ነው እንጂ ልንበትን አይደለም፤ በቤተክርስቲያን ላይ ማንም ሊያዝዝ አይችልም ስለቤተክርስቲያን ኃላፊነቱ የእኛ ነው>> በማለት አቋማቸውን በአደባባይ ከመግለጻቸውም በላይ በዘመኑ በሥልጣን ላይ ከነበሩት የደርግ ሹማምንት ፊት ለፊት በመጋፈጥ ልጆቻቸውን ከጥቃት ታድገዋል፤ ተቋርጦ የነበረው የሰንበት ትምህርት ቤት እንዲቀጥል አድርገዋል፡፡
ብፁዕነታቸው የነገይቱ ቤተክርስቲያን ተረካቢ ወጣቶች መሆናቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ስለሆነ በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩ አድርገዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ወደ አርሲ ሀገረ ስብከት ተመድበው ሲመጡ የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር 117 (አንድ መቶ አሥራ ሰባት) ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሳቸው በሕይወት በነበሩባቸው ዘመናት ከ300 (ሦስት መቶ) በላይ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን በማስከተል ምእመናን በርቀት ምክንያት ሳይንገላቱ በአቅራቢያቸው ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከማድረጋቸውም በላይ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የይዞታ ማረጋገጫ እንዲያገኙ አድርገዋል፡፡ 
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዕረፍት ምክንያት ከነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ተመርጠው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ሆነው እስከተሾሙበት የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክነት ቅድስት ቤተክርስቲያን በመምራት አባታዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ልክ በዛሬዋ ቀን ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ዐርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም በደብር ቅዱስ ደብረ መዓዛ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ተፈጽሟል፡፡

የብፁዕ አባታችን በረከታቸው ይደርብን፡፡

ተዋሕዶ ሚዲያ
ድምፀ ተዋሕዶ
ድምፀ ተዋሕዶ

24 Feb, 00:59

605

ሌላውና መሠረታዊው የኦርቶቶዶክስ ነገረ ዕውቀት የሚያጠነጥነው ደግሞ መገለጥ ላይ ነው። መገለጥ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም በሮማ ካቶሊክ በተለይም ደግሞ ከቶማስ አኲናስ መምጣት በኋላ (በእምነት መግለጫዋ ላይም እንዳለው) የሰው አእምሮ ወይም የመረዳት ችሎታ (reason) ብቻውን እግዚአብሔርን በርግጠኝነት ለማወቅ በአጠቃላይ ሃይማኖትን ለማወቅ በቂ ነው ብለው ያምናሉ። (ይህን ሀሳብ Thinking Orthodox  እና የመሳሰሉትን መጻሕፍት አንብቦ የበለጠ መረዳት ይቻላል።)

በሁለቱም ኦርቶዶክሶች ግን ይህ ሀሳብ ተቀባይነት የለውም። እንደዚህ ከሆነ ሃይማኖት ከሳይንስ የሚለይበት መሠረታዊ ነገር ይጠፋል ወይም ያንሣል። ይህን ጉዳይ አሁንም በስፋት መግባት ባልፈልግም ኦርቶዶክሳዊው ነገረ ዕውቀት ከዚህ በጅጉ የራቀ እና የተለየ መንገድ ያለው ነው። ምንም እንኳ ሲስተማቲክ ቲዖሎጂ በእኛም ተቋማት እየተሰጠ እና በዚሁ መንገድ መጻሕፍት እየተጻፉና እየተዘጋጁ ቢሆንም መሠርታዊ ጥንቃቄ እና ኦርቶዶክሳዊውን ድነበር መጠበቅ ግን በብዙ የምሥራቅ ሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ብቻ ሳይሆን የተለመደም  ጭምር ነው።

በኦርቶዶክሳዊያን ዘንድ ደግሞ በሰው አእምሮ አድሮ የሚናገረው ራሱ እግዚአብሔር ነው። ይህም በጥልቅ መግቦቱ ለሰው ልጆች በመግለጥ የሚያሳየው ነው። ሰዎች በቅጥነተ ኅሊና ማለትም አእምሮአቸውን በማራቀቅ ብቻ ሊደርሱበት የሚቻላቸውም አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን “እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤” /1ኛ ቆሮ 3 ፤ 1 – 2/ የሚላቸው በክርስትና ለመንፈሳዊ ሕይወት ሕጻናት ስለሆኑ እንጂ ለእውቀት ለፍልስፍና እና ለአመክንዮ ሕጻናት ሆነው አልነበረም ባዮች ናቸው። ስለዚህ በመንፈሳዊ ሕይወት በተጋድሎ ውስጥ በምትገኝ የማትቋረጥ መገለጥ የሚሰጥ እንጂ የሰው አእምሮ የማሰብ ችሎታ ብቻውን ይደርስበት ዘንድ አይቻልም ብለው ያምናሉ። በተለይም ደግሞ መጀመሪያ ቅዱስ ወግሪስ እንደተናገረው የሚታመነው “እውነተኛ የነገረ ሃይማኖት ዐዋቂ የሚጸልይ ሰው ነው” የሚለው አባባል የሰው የሃይማኖት ዕውቀት የመረዳት ችሎታ ላይ እንዳያርፍ መጠበቂያ አጥራቸው ነው።

የኦርቶዶክሳዊ ነገረ ዕውቀት ሦስተኛው መሠረታዊ መለያ ደግሞ ሃይማኖታዊ ዕውቀት በመሠርቱ ለሰዎች ድኅነት ቅድሚያ የሰጠ (Pastoral) መሆኑ ነው። ይህም ማለት ጉዳዮች የሚብራሩት የሚተረጎሙት የሚሰበኩት የሰውን ድኅነት ቅድሚያ ሰጥተው እንጂ ለዕውቀት እና ለርቃቄ ተብለው አይደለም። ከዚህ የተነሣ ለድኅነት ከሚጠቅመው ውጭ እንኳን እንዳሁኑ ማንም ሊያየው በሚችል ሚዲያ ይቅርና ለኦርቶዶክሳዊያን ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን የጉባኤ ቀለም ለመናገር እና ለማራቀቅ የሚደክም የለም፣ ሲያጋጥምም አይመሰገንም። ምክንያቱም ለድኅነታቸው ሳይሆን ለመመስገን፣ ለምደነቅ ወይም ለመከበር ተብሎ ስለሚሆን እና እነዚህም ጠባያት ደግሞ የሥጋ ጠባዮች ስለሆኑ እነዚህ መግቢያ አድርጎ ሰይጣን እንዳያስተውም ስለሚፈራ ነው።

ሁልጊዜም ቢሆን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ችግሮች የሚፈጠሩት ቲኦሎጂን ወይም ነገረ እምነትን ለአማኞች ድኅነት ቅድሚያ ሰጥቶ ማስተማር ቀርቶ የራስን ፍላጎት ለማርካት በሚደረግ አላስፈልጊ ዕውቀት መሰል ክርክር ውስጥ ነው። ይህ ጉዳይ ከዚህም አልፎ ክርክር በማያስነሡ ጉዳዮች እንኳን የሚነሣው የተለየ ነገር ተናግሮ ማስደነቅና መከበርንም ሆነ ሌላ ነገር ሲፈለግ የሚያጋጥም ስለሆነ ነው።

እንዲያውም ከዚህም አልፎ አሁንም ብዙ ገዳማዊያን ሊቃውንት አንድ መሠረታዊ ሥጋታቸውን ደጋግመው ሲያነሡ አይቻለሁ። ይህም አሁን አሁን ኦርቶዶክሳዊያን ክርስትናን ወደ ዕውቀትነት እያወረዱት ነው የሚል ሥጋት ነው። ይህ ሥጋታቸው ደግሞ ተራ ሥጋት አይደለም። በአሁኑ ጊዜ በርከት ያሉ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስትናን ያጠኑታል፣ ለማወቅ ይጥሩለታል፣ ይወድዱታል፤ በዚያም ደስተኞች ይሆናሉ። ከዚህም የተነሣ ወደ እውነተኛው የመዳን ዕውቅት ሳይሸጋገሩ ልክ እንደ አካዳሚክ ዕውቀት በጥናት ላይ ብቻ ተመሥርተው ይቀራሉ። ይህ ባሕል እየሆነና እየተለመደ ስለሔደ ክርስቲያናዊው እውነተኛው ሕይወታዊውን ዕውቀት አካዳሚያዊ ዕውቀት እየተካው ስለሆነ ክርስትና አደጋ ላይ ነው ያለው ይላሉ። ይህን የሚሉበት ምክንያት ክርስቲያናዊ ዕውቀት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት በማድረግ ከመነገር በላይ ወደ ሆነው ወደ ሚኖረው ዕውቀት ካልተሸጋገረ አካዳሚያዊ ዕውቀት ይሆናል። ከዚህም የተነሣ እንደማንኛውም አካዳሚያዊ ነገር በሰው አእምሮ መረዳት (reasoning) ላይ ይወሰንና ስፉሕ አእምሮ ያላቸው ሰዎች ሲመጡ ያንን የሚያሻሽሉት የሚያስፋፉት፣ ጠባብ አእምሮ ያላቸው ሲይዙት ደግሞ እንደዚያው የሚያጠብቡት ይሆንና በመጨረሻም በሒደት የመበረዝ ፣ የመለወጥ ፣ የመጥፋት አደጋ ይገጥመዋል የሚል ተጨባጭ ሥጋት አላቸው።

የእኛ ዘመን ተሟጋች ትውልድ ደግሞ አብዛኛው መጀመሪያ የተማረው ዘመናዊውን ወይም ምዕራባዊውን ትምህርት ነው። ይህን አስቀድሞ መማር በራሱ ችግር አይደለም፤ ( ሊሆንም አይችልም። እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ ባስልዮስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮ ዘእንዚናዙ እና ሊሎችም ጭምር መጀመሪያ የተማሩት የዓለሙን ፍልስፍና ነውና።  የእኛ ትውልድ ግን ከመጠን በላይ ሲስተማቲክ በሆነው አካዳሚክስ ውስጥ ከማለፉ የተነሣ ነገሮችን ሳያውቀው በዚያ መጠን የመበየን፣ ጨርሶ የማወቅ እና አቋም መያዝ ድረስ መድረሱ ችግሩ ብቅ እያለ መሆኑን ያመለክታል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም  ክርስትናን ከትምህርት ከሚገኝ መጠነኛ ዕውቀት በሕይወት ወደሚደረስበት የመረዳት ዕውቀት ካልተሸጋገረ ችግር መግጠሙ አይቀሬ ነው። በሰሚዕ የሚገኝ ዕውቀት እና እምነት መግቢያ በር እንጂ መድረሻ አዳራሽ ወይም ቤት አይደለምና።

ይህ ጉዳይ ራሱን የቻለ ብዙ እንድንማማር የሚያደርግ ስለሆነ ጊዜውና ችሎታው ያላችሁ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ ዕውቀት ብታካፍሉን ብዙዎቻቸን መንገዳችንን ለማቃናት ብዙ ይጠቅመናል፤ ጉዳዮችን በአካዳሚ መንገድ እና ዓይን ከማየት፣ አለፍ ሲልም እንደ ፖለቲካ አቋምን ከመለካካት ሊያተርፉን ይችላሉ፤ ሲሆን ሲሆን ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ዓለም እንድንገባ እና መንገዳችንን ወደዚያ እንድናደርግ ሊረዱን ይችላሉ ብዬ አስባለሁ።

ከሰሞኑ ውይይቶች በተለይ አስተያየት መስጫ ላይ የማያቸው ጥያቄዎች እና መልሶች ብዙዎቹ ትውልዱ ወደዚህ አካዳሚያዊ የነገረ መለኮት ዕውቀት ሳያውቀውም ቢሆን እያደላ መሆኑን የሚጠቁሙ ይመስለኛል። በእኔ መረዳት ኦርቶዶክሳዊ የነገረ ዕውቀት አቀራረብ ቀርቶ ምዕራባዊ የምነለውንና የራሱ ሥነ ሥርዓት ያለውንም ያንን እንኳ የማያሟሉ፣ የነገሮቹን መቅድማቸውን እንኳ በውል ሳናገኘው አንኳር ጉዳዩ ላይ ገብተን እንደዚያ ያለ አስተያየቶች መወራወራችን በእጂጉ ያስፈራል። ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው በእጂጉ ያስፈራል። እኔን እስከገባኝ ደርሰ ከፍተኛ ድፍረት የተሞላው የአላዋቂ ክርክር ወስጥ መሆናችንን በታላቅ ትሕትና (ነገሩ እንኳ ሳስበው ድፍረትም ጭምር ነው) መጠቆም እፈልጋለሁ።

በማኅበራዊ ሚዲያ ልናደርጋቸው የሚገቡንን ውይይቶች እና ትምህርቶች በተመለከተ እኔ ከጠቆምኳቸው እና ከሌሎቹም መሠረታዊ ትውፊቶቻችን አንጻር በማየት በውስጥ መወያየት እና አቀራረቦችን ማስተካከል ይቻላል፤ ይገባለም ብዬ አምናለሁ።

መልካም ጾም !
መምህር ብርሃኑ አድማስ
ድምፀ ተዋሕዶ

19 Feb, 19:48

34

ለኃይማኖቱና ለሀገሩ እምቢኝ ያለ ህዝብ በዛሬው እለት የካቲት 12 ቀን 1929
የደብረ ሊባኖስ እና በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ የግራዚያኒ ጭፍጨፋ ሰለባ ሆነዋል።

ድምፀ ተዋሕዶ
ድምፀ ተዋሕዶ

08 Feb, 20:19

30

💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
ድምፀ ተዋሕዶ

08 Feb, 20:01

45

መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት
👇
ድምፀ ተዋሕዶ

08 Feb, 10:33

722

ከየካቲት ፫-፭
Feb 10-12
የበረከት ጾም ይሁንልን።
ድምፀ ተዋሕዶ።