ማቴዎስ 4
1: ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
2: አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።
አዳም በገነት ሳለ ሰይጣን ወደ እርሱ መጥቶ ከገነት ወደ ምድር አወጣው ባሕርይውም ደቀቀ። ጌታ ኢየሱስም የእኛኑ ደካማ ባሕርይ ይዞ ወደ ራሱ ግዛት ወደ ምድረ በዳ ወርዶ ሰይጣንን አሸነፈው አዳምንም ወደ ገነት መለሰው።
ኹላችንም በሰይጣን በተፈተነው በጌታ ኢየሱስ ኾነን ሰይጣንን አሸነፍነው ቀድሞ ወድቆ የነበረው አዳማዊ ባሕርይ በዳግማይ አዳም በጌታ ታደሰ ፤ ሰይጣን ወደ መጀመሪያው አዳም ግዛት መጥቶ አሸነፈው ኹለተኛው አዳም ደግሞ ወደ ሰይጣን ግዛት ሔዶ አሸነፈው።
እኛም ኃይልን በሚሰጠን በጌታ ኢየሱስ የሰይጣንን ፈተናዎች ኹሉ እናሸንፍ ዘንድ ተስፋ አለን ባሕርያችንስ ደካማ ነው ባከበረን በፈተናችን ኹሉ በሚራራልን በጌታ ግን እናሸንፋለን!
መልካም ቀን!