የካቲት 18 ቀን 2017ዓ.ም
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንርራይዝ የመንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1333/2016 ላይ ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ከየካቲት 17-18/2017ዓ.ም የዋናው ከመ/ቤት ግዥና አቅርቦት አስተዳር መምሪያ ባለሙያዎች፣ የግንባታ ፕሮጀክቶች ግዥና አቅርቦት ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የዋናው መ/ቤት የግዥ ኮሚቴ አባላት በዋናው መ/ቤት አዳራሽ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
እንደ ሃገር ጸድቆ ሥራ ላይ የዋለው የመንግስት ግዥና ንብረት አዋጅ ቁጥር 1333/2016 መሠረት ያደረገ የግዥ ሥርዓት ተከትሎ መሠራት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ይህም ማለት የመንግስት ግዥ ማለት የመንግስትን ገንዘብ በመጠቀም "ዕቃዎችን፣ የግንባታ ዘርፍ ሥራዎችን፣ የምክር አገልግሎቶችን እና የምክር ያልሆኑ አገልግሎቶችን በመግዛት ፣ በኪራይ ወይም በማኝኛውም ሌላ ተመሳሳይ ውል ማግኘት ነው" በማለት የሚደነግገውን አዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ ከዋለ አንድ አመት የሆነው ሲሆን ተፈጻሚነቱም በመንግሥት ተቋማት እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ላይ ነው፡፡
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የግዢና ንብረት የሥልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ውብሸት መንግስት እና አቶ አሳድ አብደላ የመንግስት ግዥና ንብረት አዋጅ ቁጥር 1333/2016 እና በአሁኑ ወቅት የግዥ ሥርዓትን ለማዘመን ሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶችና ከፍተኛ የትምህርት ቷማት የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ሲስተም ግዥ ሥርዓትን (e-GP system) መሠረት ያደረገ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡
ሰልጣኞች በግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅና መመሪያ ላይ በቂ እውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት እንዲኖራቸው እንዲሁም የተሻሉ የአሰራር ተሞክሮዎች እንዲለዋወጡ በማድረግ በቀጣይ የግዥ መመሪያዎችን አውቀው ተግባራትን ሲፈጽሙ ሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት በተግባር በመፈፀም ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ አሰልጣኞቹ ገልፀዋል፡፡
በሥልጠናው የተሳተፉ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎችም ሥልጠናው የግዥና ንብረት አስተዳደር ስርዓት ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ግልጽ የስልጣን ተዋረድንና ተጠያቂነትን የሚያሰፍንና የሙያ ስነምግባርን የተላበሰ ዘላቂ የግዥ ዘዴን የአሰራርን መዘርጋት የሚያስችል ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
#DCE
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.dce-et.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DefenseConstructionEnt
ቴሌግራም፦ DCE2020
ትዊተር፦ https://twitter.com/ @Defenseconstru1
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡