Últimas publicaciones de Defence Construction Enterprise (@dce2020) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Defence Construction Enterprise

Defence Construction Enterprise
Defense Construction Enterprise (DCE) is one of the leading construction companies in Ethiopia. We are different from other companies as we work in the most remote and difficult areas of the country. We are dedicated and devoted to build the country.
1,374 Suscriptores
971 Fotos
30 Videos
Última Actualización 06.03.2025 00:29

El contenido más reciente compartido por Defence Construction Enterprise en Telegram

Defence Construction Enterprise

25 Feb, 15:04

799

በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር የህግ ማእቀፍ ላይ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

                    የካቲት 18 ቀን 2017ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንርራይዝ የመንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1333/2016 ላይ ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ከየካቲት 17-18/2017ዓ.ም የዋናው ከመ/ቤት ግዥና አቅርቦት አስተዳር መምሪያ ባለሙያዎች፣ የግንባታ ፕሮጀክቶች ግዥና አቅርቦት ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የዋናው መ/ቤት የግዥ ኮሚቴ አባላት በዋናው መ/ቤት አዳራሽ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

እንደ ሃገር ጸድቆ ሥራ ላይ የዋለው የመንግስት ግዥና ንብረት አዋጅ ቁጥር 1333/2016 መሠረት ያደረገ የግዥ ሥርዓት ተከትሎ መሠራት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ይህም ማለት የመንግስት ግዥ ማለት የመንግስትን ገንዘብ በመጠቀም "ዕቃዎችን፣ የግንባታ ዘርፍ ሥራዎችን፣ የምክር አገልግሎቶችን እና የምክር ያልሆኑ አገልግሎቶችን በመግዛት ፣ በኪራይ ወይም በማኝኛውም ሌላ ተመሳሳይ ውል ማግኘት ነው" በማለት የሚደነግገውን አዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ ከዋለ አንድ አመት የሆነው ሲሆን ተፈጻሚነቱም በመንግሥት ተቋማት እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ላይ ነው፡፡
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የግዢና ንብረት የሥልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ውብሸት መንግስት እና አቶ አሳድ አብደላ የመንግስት ግዥና ንብረት አዋጅ ቁጥር 1333/2016 እና በአሁኑ ወቅት የግዥ ሥርዓትን ለማዘመን ሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶችና ከፍተኛ የትምህርት ቷማት የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ሲስተም ግዥ ሥርዓትን (e-GP system) መሠረት ያደረገ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡

ሰልጣኞች በግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅና መመሪያ ላይ በቂ እውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት እንዲኖራቸው እንዲሁም የተሻሉ የአሰራር ተሞክሮዎች እንዲለዋወጡ በማድረግ በቀጣይ የግዥ መመሪያዎችን አውቀው ተግባራትን ሲፈጽሙ ሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት በተግባር በመፈፀም ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ አሰልጣኞቹ ገልፀዋል፡፡

በሥልጠናው የተሳተፉ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎችም ሥልጠናው የግዥና ንብረት አስተዳደር ስርዓት ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ግልጽ የስልጣን ተዋረድንና ተጠያቂነትን የሚያሰፍንና የሙያ ስነምግባርን የተላበሰ ዘላቂ የግዥ ዘዴን የአሰራርን መዘርጋት የሚያስችል ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

#DCE
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.dce-et.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DefenseConstructionEnt
ቴሌግራም፦ DCE2020
ትዊተር፦ https://twitter.com/ @Defenseconstru1
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Defence Construction Enterprise

20 Feb, 07:41

1,133

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው ግማሽ አመት የሥራ አፈፃፀም ገመገመ።

            የካቲት12 ቀን 2017ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው ግማሽ አመት የሥራ  አፈጻጸም በዋና መ/ቤት ከሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር  ገመገመ።

ኢንተርፕራይዙ በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ለመፈጸም የተያዘውን ዕቅድ አፈፃፀም በገለፃ ከቀረበ በኋላ በቀረበው ሪፖርት ላይ አመራሩና ሰራተኛው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በቀረበው ሪፓርት ተቋሙን ሪፎርም የማድረግ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ሲሆን የአደረጃጀት ማሻሻያ ለማድረግ ክፍተቶች የመለየት ስራ በመሰራት ላይ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ሦስት የአሰራር ማንዋሎችን ማለትም የሥራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ፣ የቀላል ተሸከርካሪ የስምሪት ማኑዋል እና  የንብረት አወጋገድ መመሪያ ተዘጋጅቶ በማኔጅመንት ደረጃ ተደጋጋሚ ውይይቶች እንደተደረገባቸው በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽ ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮሎኔል (ኢንጂነር) ሰጠኝ ሊኪሳ፣ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች በመፍታት ላለፉት ዓመታት በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም በዚህ በጀት ዓመት በ6ወር ውስጥ የዘርፉ ዋና የትኩረት አቅጣጫ የሆኑትን ዋና ዋና ጉዳዮች ታሳቢ በማድረግ የሚታዪ ክፍተቶች በጋራ በመለየት ከተለመደው አሰራር ወጣ ባለ መልኩ ችግሮችን ለመፍታት  ያሉበትን ደረጃ ፈትሾ የማሻሻል ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ላይ በዋናው መስሪያ ቤት እና በግንባታ ፕሮጀክቶት መካከል መደጋገፍ፣ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል፣ ስራዎችን በቴክሎጂ ሲስተም በመደገፍ ዲጅታላይዝ ማድረግ፣ ውስጣዊ የአሰራር ስርዓትን በማስተካከል ስራን  ማሳለጥ እና ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ከአመራሩና ከሠራተኛው ይጠበቃል፡፡ ይሄንን ተግባራዊ ለማድረግ የአሠራር ሥርዓታችን የመፈተሽና አደረጃጀታችንን የማሻሻል ሥራ ይሠራል ብለዋል።

ኢንተርፕራይዙ እየገነባቸው ከሚገኙ የሕንጻና የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል በ2017 በጀት ዓመት ማጠናቀቂያ ድረስ ከሕንጻ ግንባታ በድሬዳዋ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ቢሮ እና ካምፕ ግንባታ፣ ድሬዳዋ የመከላከያ ሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንት፣ ቆሬ ዋር ኮሌጅ፣ ጎፋ መከላከያ ሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንት፣ ቃሊቲ ስቶር ውስጥ ለውስጥ መንገድ፣የሐረር ፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል እና የሀኪሞች መኖሪያ አፓርትመንት እና ከመንገድ ግንባታ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ አምቦ ወሊሶ መንገድ፣ ወለጋ ዪኒቨርስቲ ውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ነቀምቴ አየር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ግንባታቸውን አጠናቀን ለባለቤት ማስረከብ እንደሚጠበቅ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በአጽንዖት ተናግረው የሥራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ሠራተኛውም በቀረበው ሪፖርት ላይ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች አንስተው ሰፊ ውይይት አድረገው የጋራ ግንዛቤ ይዘው ሪፎርሙን ተቀብሎ የሚሰጠውን የአሠራር ማሻሻያ ለመተግበር ዝግጁ እንደሆኑም  በመግለጽ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

#DCE
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.dce-et.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DefenseConstructionEnt
ቴሌግራም፦ DCE2020
ትዊተር፦ https://twitter.com/ @Defenseconstru1
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Defence Construction Enterprise

13 Feb, 02:35

1,208

የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት ኮንክሪት የማንጠፍ ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 05 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርራይዝ ከሚገነባቸው የተለያዩ የዋና መንገድ እና የተቋማት ውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ሥራ ነው፡፡

የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የመንገድ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ሺበሺ ጫካ እንደሚሉት፤ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ የሚገኘው የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ 18 ኪሎ ሜትር ርዝመት 7 ሜትር የጎን  ስፋት አለው፡፡

የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ አስፋልት ማንጠፍ ሥራ እየተከናወነለት የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ፋይናንሻል 64 በመቶ ሲሆን ፊዚካል ደግሞ 66.6 በመቶ ደርሷል። በኪሎሜርት ደግሞ 12 ኪሎ ሜትር ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡ ቀሪ የግንባታ ስራዎች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

18 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው እና 7 ሜትር የጎን ስፋት ባለው በዚህ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ከአስፋልት ማንጠፍ ጎን ለጎን የአፈር ቆረጣና ሙሌት፣ አንድ ትልልቅ ድልድይ እና 10 የውኃ ማፋሰሻ የአነስተኛ እና ከፍተኛ ከልቨርቶች ሥራዎች ግንባታቸው ተጠናቋል።

በአሁኑ ወቅት የአፈር ሙሌት እና ቆረጣ ሥራዎች ተጠናቀው አንድ ትልቅ ድልድይ ግንባታ 80 ፐርሰንት ደርሷል፡፡ የድጋፍ ግንብ፣ የሰቤዝ ንጣፍ፣ የቤዝኮርስ ንጣፍ እንዲሁም የአስፋልት ኮንክሪት ማንጠፍ ስራዎች በመከናወን ላይ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሺበሺ ገልጸዋል።

በተጨማሪም 12 ሺ ሜትር ስኩዌር ስፋት ያለው የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ የአስተዳር ሕንጻ የሚገኝበት ዙሪያውን አስፋልት የማንጠፍ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡

የግንባታ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ 306 ሚሊዮን ብር በጀት ተይዞለት ግንባታው እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በ2017 ዓ.ም መጨረሻ አጠናቆ ለማስረከብ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

11 Feb, 14:17

1,198

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ - በአዲስ ምዕራፍ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 04 ቀን 2017 ዓ.ም

ሀገርን ለማልማት ራዕይ ሠንቆ መነሳት ለራስ ለዜጋ እና ለሀገር ዕድገት የሚኖረው አዎንታዊ አሥተዋፅኦ በብዙ መንገድ ይገለፃል።

የኢፌዴሪ መከላከያ አንድም የሠላም ሲቀጥልም የልማት ሃይል ነው የሚባለው በምክንያት ነው። ከሀገር አልፎ ለጎረቤት ሀገራት ሠላም እውን መሆን ይሠራል በየትኛውም መልክዓ-ምድር በልማት ይሳተፋል ያለማል።

በተቋሙ ሥር ከሚገኙ የልማት ድርጅቶች መካከል የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አንዱ ነው። ድርጅቱ ማንም ተቋራጭ ደፍሮ መግባት በማይችልበት አሥቸጋሪ የአየር ፀባይና መሠል መሠናክሎች ባሉበት አካባቢ በመግባት በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ማሥረከብ የቻለ ሥመ ጥር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ነው።

ድርጅቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አመራር አደረጃጀቱን እያሥተካከለ ቀደም ሲል የነበሩ ክፍተቶችን በማረም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በመውሰድና ውጤቶቹን በማየት አሁን ላይ በተሻለ የልማት መሥመር ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ኮሎኔል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ ገልፀዋል።

ኢንተርፕራይዙ በመንገድ ሥራ፣ በህንፃ ግንባታ በመሥኖ ሥራ ግንባታ እና በሌሎች የልማት ሥራዎች ላይ በመሠማራት ለመከላከያ እንደ ልማት ድርጅትነቱ የተፈለገውን አሥተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ዋና ሥራ አሥፈፃሚው አንስተዋል።

የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባሥቀመጡት የሥራ አቅጣጫ መሠረት በበርካታ የተቋሙ ክፍሎች ቢሮዎችን በተፈለገው መጠን መገንባት፣ የሠራዊቱን የመኖሪያ ቤት ግንባታ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ የመገንባት ሂደቱ ቀን ከሌሊት ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት ኮሎኔል ኢንጂነር ሠጠኝ ሊኪሳ በድሬዳዋ የተገነባው 768 የሠራዊቱ የመኖሪያ አፖርትመንት በቅርቡ እንደሚመርቅም ተናግረዋል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ የቢሮ ግምባታ፣ የአምቦ ወሊሶ የአሥፖልት መንገድ፣ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት ሥራ፣የምስራቅ ዕዝ የቢሮ ህንፃ ግንባታ፣ የምስራቅ ኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስ ቢሮ ቃሊቲ የሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ የአስፓልት ሥራ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች አሁን ላይ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት ግንባታቸው እየተፋጠነ እንደሚገኝም አሥረድተዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ይበልጥ ተደራሽ የልማት ድርጅት ለመሆን ዘመናዊ ማሽኖችን ፣ የግንባታ መሳሪያዎችን፣ ተሽከርካሪዎችን የመግዛት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የጠቆሙት ኮሎኔል ኢንጂነር ሠጠኝ የበላይ አካል የሚያደርገውን ድጋፍ እና ክትትል መሠረት በማድረግ የአደረጃጀት እና ሌሎች የማሻሻያ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

08 Feb, 15:56

996

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የውሰጥ ለውሰጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡
                               
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ግንባታ እያካሄደ የሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የውሰጥ ለውሰጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ፋይናንሻል 22.5 ፐርሰንት ሲሆን ፊዚካል አፈጻጸሙ 67 ፐርሰንት ደርሷል፡፡ የመንገድ ግንባታው አስፋልት የማንጠፍ ሥራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ግንባታውን ለማጠናቀቅ በትጋት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የወለጋ ዩኒቨርስቲ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ሥራ ባለቤቱ ወለጋ ዪኒቨርስቲ ሲሆን ግንባታውን የሚቆጣጠረውና የሚያማክረው ደግሞ የኢትዮጵያ እንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የህንፃና ከተማ ዘርፍ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር አስመራ ስዩም የግንባታ ሥራው በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግንባታውን ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው ፕሮጀክት አጠቃላይ በጀት 552 ሚሊዮን 690 ሺህ 296 ብር የተመደበለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የውሰጥ ለውሰጥ አስፓልት መንገድ አምስት ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ግንባታው ከተጀመረ በኋላ የመንገድ ጠረጋ ሥራ፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት ሥራ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ሥራዎች፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ፣ የከርቭ ስቶን እና የእግረኛ መንገዱን በታይልስ በመገንባት ለእግረኛ ምቹና ደህንነቱን የጠበቀ የማድረግ ሥራዎች እየተናወነ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት መንገዱን አስፋልት የማንጠፍ ሥራ እየሰሩ መሆኑን ኢንጂነር አስመራ ገልጸዋል፡፡

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የውሰጥ ለውሰጥ አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ የሆነ የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን ከ157 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶች የሥራ እድል እና የእውቀት ሽግግር መፈጠሩን ኢንጂነር አስመራ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

06 Feb, 18:33

923

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት እየገነባ ነው።
                                                       
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እየተገነባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ከ676 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚያስገነባው የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ቢሮና ካምፕ ግንባታ ፕሮጀክት ፊዚካል አፈጻጸሙ 42 ፐርሰንት መድረሱን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል (ኢንጂነር) እሸቱ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማዕከል ግንባታ በ9,860 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን የግንባታ ፕሮጀክቱ አንድ የቢሮ ሕንጻ ቤዝመንት ያለው ጂ+2፣ አንድ የእንግዳ ማረፊያ ሕንጻ፣ አንድ የወንዶች ማደሪያ፤ የክሊኒክ እና የካፊቴሪያ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የሚገነባ ቤዝመንት ያለው ጂ+ 2 ሕንጻ፣ አንድ የሴቶች ማደሪያ ሕንጻ ፎቅ ጂ+1 እንዲሁም የአጥር ስራ፣ የሳይት ወርክ ፣የጥበቃ ማማዎች እና የጥበቃ ቤቶች ስራዎች በግንባታ ምዕራፍ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

የወንዶች ማደሪያ፣ ክሊኒክ እና ካፊቴሪያ የሆነው ህንጻ ግንባታው የስትራክቸር ስራውን ለመጨረስ የታንከር ማስቀመጫ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን በአሁን ሰዓት የቤዝመንት፣የግራውንድ እና አንደኛ ወለል የብሎኬት ግንብ እና የልስን ስራው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

የሴቶች ማደሪያ ህንጻ የስትራክቸር ስራ የጣሪያ የብሎኬትና የጂፕሰም ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ለፊኒሺንግ ስራ ዝግጁ  መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል (ኢንጂነር) እሸቱ ገልጸዋል፡፡

የግንባታው ባለቤት ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሲሆን የማማከር ሥራን የሚሠራው የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የህንፃ እና ከተማ ዘርፍ ነው።ለግንባታው የተመደበው 676 ነጥብ 035 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚሸፈነው ደግሞ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ነው።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

06 Feb, 12:31

568

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በድሬዳዋ ከተማ የገነባው እና ለምረቃ ዝግጁ የሆነው መከላከያ ሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት
Defence Construction Enterprise

04 Feb, 10:49

700

በማጠቃለያ ምዕራፍ የሚገኘው የምሥራቅ ዕዝ የቢሮ ሕንጻ ግንባታ አፈፃፀም 88 ፐርሰንት ደርሷል፡፡
 
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እየገነባቸው ከሚገኙ የግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል በድሬዳዋ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የምስራቅ እዝ ቢሮ ሕንጻ ግንባታ አንዱ ነው፡፡ ባለአምስት ወለል ህንጻ ግንባታው ማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

የግንባታው ባለቤት የመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ ሲሆን የመከላከያ ኮንስትራክሽን ግንባታ ዲዛይን ደግሞ እያማከረ ይገኛል፡፡ ከተጀመረ 743 ቀናትን ያስቆጠረው ባለ አምስት ወለል ሕንጻ ለማጠናቀቅ ጥራት እና ዘመናዊነቱን ጠብቆ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን የግንባታ አፈፃፀሙ 88 ፐርሰንት ደርሷል፡፡

የቢሮ ግንባታው አሁን ያለበት ደረጃ የስትራክቸር ሥራው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ የሴራሚክና ግራናይት ማንጠፍ፣ የሳኒተሪ እቃዎችን መግጠም፣ የኤሌክትሪክ መስመሮች ዝርጋታ እና የአሳንስር የመግጠም ስራው፣ የአደጋ ጊዜ መውጫ በአራቱም የሕንጻዎቹ ክፍል ላይ ተሰርቷል፡፡

ብርሃን የሚያስተላልፍ የጣሪያ ሥራ እና የእንጨት በሮች ገጠማ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡ የውጭ ቀለም ሥራ ተጠናቆ የውስጥ ቀለም ሥራ እየተሠራ ይገኛል፡፡ የአልሙንየም በርና መስኮት ገጠማ እየተከናወነ ነው፡፡የኤሌክትሪክ ገመዶች የሚተላለፍበት ኬብል ትሪ ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ቀሪ ሥራዎቹ የኤሌክትሮ መካኒካል ማለትም ሽታ ማስወገጃ፣ የሙቀት ማቀዝቀዣ ኤሲ፣ እሳት አደጋ ጠቋሚ አምፖሎችና ሶኬቶችን የመግጠም ሥራ እየተሰራ ሲሆን የቢሮ ሕንጻው በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፈር መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

02 Feb, 09:04

778

ኢንተርፕራይዙ በድሬዳዋ ከተማ የሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንት ገንብቶ አጠናቋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በድሬዳዋ ከተማ የገነባው የሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለባለቤት ርክክብ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከሚገነባቸው ግንባታዎች መካከል አንዱ በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንቶች የግንባታ ፕሮጀክት ነው፡፡

ባለ አራት ወለል በ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታቸው ሲከናወን የቆየው የመከላከያ ሠራዊት የመኖሪያ አፓርትመንቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለባለቤት በማስረከብ  ሂደት ላይ የተሰጡ ጥቂት የእርማት ሥራዎች ጎን ለጎን እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ሰባት መቶ ስልሳ ስምንት አባዎራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው አፓርትመንቱ ባለ ሶስት መኝታ ሰባት ብሎክ፣ ባለ ሁለት መኝታ ስምንት ብሎክ እና ባለአንድ መኝታ አምስት ብሎኮች አሉት፡፡

አፓርትመንቶቹ በውስጣቸው ዘመናዊ ኪችን፣ ቁምሳጥን፣ መብራቶች፣ የመብረቅ መከላከያ፣ ሳተላይት ዲሽ፣ የዋይፋይ መሥመሮች፣ የውሀ ፖምፕ፣ የባኞ ቤት እቃዎች እና አካባቢዉ ሞቃታማ ስለሆነ ክፍሎቹን ማቀዝቀዣ ኤሲ ተገጥሞላቸዋል።

አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ በአፓርትመንቶቹ ዙሪያ ዛፎችን በመትከል እና በመንከባከብ አረንጓዴ የማድረግ ሥራም ተከናውኗል፡፡ በአፓርትመንቶቹ መካከል የውስጥ ለውስጥ መንገድ በኮብልስቶን እና የእግረኛ መንገዶቹ በኮንክሪት ታይል ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የገነባው ይህ መከላከያ ሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንቶች ግንባታ በቅርቡ ይመረቃል ተብሎ ይታሰባል።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

01 Feb, 11:30

789

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ የገነባው የሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለባለቤት ርክክብ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ጥር 24 /2017ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከሚገነባቸው ግንባታዎች መካከል አንዱ በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ የገነባው የመከላከያ ሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንቶች የግንባታ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በድሬዳዋ ከተማ የገነባው የመከላከያ ሠራዊት የመኖሪያ አፓርትመንት ግንባታው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ ለመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ  በማስረከብ ላይ ነው።

ባለ አራት ወለል የሆኑት እና በ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታቸው ሲከናወን የቆየው የመከላከያ ሠራዊት የመኖሪያ አፓርትመንቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለባለቤት በማስረከብ  ሂደት ላይ የተሰጡ ጥቂት የእርማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ሰባት መቶ ስልሳ ስምንት አባዋራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው አፓርትመንቱ ባለ ሶስት መኝታ ሰባት ብሎክ፣ ባለ ሁለት መኝታ ስምንት ብሎክ እና ባለአንድ መኝታ አምስት ብሎኮች አሉት፡፡

አፓርትመንቶቹ በውስጣቸው ዘመናዊ ኪችን፣ ቁምሳጥን፣ መብራቶች፣ የመብረቅ መከላከያ፣ ሳተላይት ዲሽ፣ የዋይፋይ መሥሮች፣ የውሀ ፖምፕ፣ የባኞቤት እቃዎች እና አካባቢዉ ሞቃታማ ስለሆነ ክፍሎቹን ማቀዝቀዣ ኤሲ ተገጥሞላቸዋል።

አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ በአፓርትመንቶቹ ዙሪያ ዛፎችን በመትከል እና በመንከባከብ አረንጓዴ የማድረግ ሥራም ተከናውኗል፡፡ በአፓርትመንቶቹ መካከል የውስጥ ለውስጥ መንገድ በኮብልስቶን እና የእግረኛ መንገዶቹ በኮንክሪት ታይል ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የገነባው ይህ መከላከያ ሠራዊት መኖሪያ አፓርትመንቶች ግንባታ በቅርቡ ይመረቃል ተብሎ ይታሰባል።