Últimas Postagens de ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 (@bookshelf13) no Telegram

Postagens do Canal ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"
18,903 Inscritos
2,716 Fotos
24 Vídeos
Última Atualização 27.02.2025 06:07

O conteúdo mais recente compartilhado por ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 no Telegram


‹‹..ጥሩ ነው ወጣት መሆን፡፡ ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሃል፡፡ መልክ ባይኖርህም አንጎል ይኖርሃል፡፡ ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሃል፡፡ ፍቅር ባይኖርህም ተስፋ ይኖርሃል፡፡ እውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሃል፡፡ መጨቆን ቢበዛብህ ሬቮሊሽን ታነሳለህ፡፡ መኖር ቢያስጠላህ ወይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ፡፡ ሠው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሃል፡፡ ወጣት ነህና፡፡… ››

(ትኩሳት - ስብሐት ገ/እግዚአብሔር)

🤖🤖🤖

የትኩሳቱ ባህራም እጅግ የሚደንቀኝ ባህሪ ነው። ኢራናዊ ሆነ እንጂ ከአማርኛ ስነፅሁፍ ታላላቅ ገፀባሕርያት አንዱ ይሆን ነበር። የምናብ ውጤት ሳይሆን ስጋ የለበሰ፣ ደም የሚዘዋወርበት፣ ልቡ የሚመታ የእውነት የነበረ ሰው መሆኑ ይበልጥ ይደንቀኛል።

©©©

ባህራም ከልቡ ኮምዩኒስት ነው። አሜሪካንና ኢምፔሪያሊዝምን አምርሮ ይጠየፋል። ከስብሃት ጋር የተዋወቁት በአንድ አጋጣሚ ነበር።

ስብሐት ብዙ ግዜ የሚተኛው ጠዋት ነው። ከሰአት እነተመስገን ክፍል ስለሚገቡ ቁልፋቸውን ተቀብሎ ሲፅፍ ይውላል። ማታ? ማታማ የኤክስን ጎዳናዎች ንጉስ ይሆንባቸዋል። ብቻውን በአውራ ጎዳናዎቹ ይዘዋወራል።

ከምሽቱ በአንደኛው እንደተለመደው ሲዘዋወር አንድ ጥግ ላይ አንዱ ኢራናዊ ከሁለት አሜሪካውያን ጋር ትግል ገጥሟል። አበሻነቱ ነሽጦት ጠጠር አንስቶ አነጣጥሮ ወረወረ። አንዱን አሜሪካዊ ግንባሩ ላይ አገኘው። ወዲያው ደንግጠው ሁለቱም ሸሹ።

ኢራናዊውን ያውቀዋል። ከነተመስገን ጋር ብዙ ግዜ ያየዋል። አጠገቡ ሲደርስ ልብሱን እያራገፈ ይስቃል። ያ ኢራናዊ ባህራም ነበር። ባህራም ኢትዮጵያዊ ጓደኞች ነበሩት። ስለዚህ ከስብሃት ጋር በአይን ይተዋወቃሉ። ያን ቀን ለመጀመሪያ ተጨባብጠው ተዋወቁ።

ባህራም በተሰባበረ ፈረንሳይኛ

"ጣልያኖችንም ያባረራችኋቸው በዚሁ ድንጋይ የመወርወር ጥበባችሁ ነው እንዴ?!" ብሎ ይቀልዳል። "እኛም አሜሪካኖችን ከሃገራችን ለማባረር ጥሩ መሳሪያ ሳይሆን አይቀርም" አለ ባህራም እየሳቀ።

ፈረንሳይኛው ብዙ የሰዋሰው ስህተት አለው። ቢሆንም ለመግባቢያ በቂ ነው። በቀልዱ አብረው ከሳቁ በኋላ

"ሰልፍ ዲፌንስ እንደምታውቅ እነ ተመስገን ነግረውኛል። ለምን አልተጠቀምክበትም"

"ምክንያቱም ኮምዩኒስት መሆኔን ይደርሱበታል"

ካለ በኋላ "ሃለላሴ ሙት" አለ በአማርኛ። ሁለቱም ከልባቸው ሳቁ።

በመጨረሻ

"የኢትዮጵያ እና የኢራን ወዳጅነት ለዘለአለም ይኑር"

"Yankee go home" አለ። ከዚያ በኋላ እያፏጩ እየተሳሳቁ ወደ ሲቴ አመሩ።

©©©

ባህራምና ኒኮል የፍቅር ጓደኞች ናቸው። የተገናኙት ፓርቲ ላይ ነው። ኒኮል በየምሽቱ አለመጠን ጠጥታ ካገኘችው መንገደኛ ጋር አብራ የማደር ባህሪ(one night stand) አምጥታ ነበር። በአንዱ ምሽት ሰክራ ከባህራም ጋር ወደቤቱ ሄዱ። ጠዋት ስትነቃ ራሷን ባህራም አልጋ ውስጥ አገኘችው። ጫፏን አልነካትም። ባህራም በግዜ ተነስቶ ቁርስ እያበሰለ ነበር። መንቃቷን ሲያይ በታላቅወንድማዊ የቁጣ ቃና

"በቃ ካገኘሽው ወንድ ጋር ጠጥተሽ ማደር ጀብዱ፣ አዋቂነት ይመስልሻል አይደል" አላት።

"በገዛ ህይወቴ ምንም አያገባህም" አለች እየተቆናጠረች።

"እንዴት አያገባኝም?! እኔም እህት አለኝ እኮ። እህቴ እንዲህ ስትሆን እንዴት አያገባኝም።"

ኒኮልና ባህራም ከዚህ ወዲህ የማይለያዩ ጥንዶች ሆኑ። የሚወራው ግን ሌላ ነው። ይቺ ባለ አመዳም ከንፈር ባህራምን ያማለለችው በገንዘብ ነው። ቤቶቿ ሃብታም ስለሆኑ ብዙ ብር ይልኩላታል እየተባለ ይወራል። ባህራም በድንቅ ስብእናው እንዳማለላት የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው።

©©©

ስብሐት ስለ ባህራም እንዲህ ይላል፦

ባህራም ሰውነቱ በፀጉር የተሸፈነ ነው። ግን ንፁህ ልጅ ነው። ፈረንሳይኛው የተሰባበረ ነው። ቢሆንም ትልቅ ስብእናውን ከማየት አላገደኝም። አያችሁ ሰዎች በሚናገሩበት ግዜ ከመልእክታቸው በቃላት የሚያስተላለፈፉት 20% ብቻ ነው። የቀረውን የምንረዳው ከአካላዊ ገፅታቸው ነው። የባህራም የተሰባበረች ፈረንሳይኛ የምትገልፀው የስብእናው መጠን 20% ነው። ዋናውን የሰውዬውን ስብእና የምትረዳው በፊቱ ገፅታ፣ በእጆቹ እንቅስቃሴ፣ በድምፁ ቃና ነው። ለዚህ ነው ባህራም በፈረንሳይኛ ቢንተባተብም ታላቅ ስብእናውን ስብሐት ከማየት ያላገደው።

©©©

ነገር ግን ይህ የተሰባበረ ፈረንሳይኛ በትምህርት ውጤቱ ላይ ጣጣ አመጣበት። አስተማሪዎቹ ስለ መልሱ ትክክለኛነት እንጂ ስለ ተፈታኙ ስብእና አያገባቸውም። ባህራም በአንዱ ትምሀርት F አመጣ። ወደቀ። አንድ አመት ደገመ። ይህንኑ በተሰባበረው ፈረንሳይኛው ለስብሐት በሚያሳዝን ቃና ይነግረዋል፦

"ፈረንሳዮች በቋንቋቸው ስትመጣ አይወዱም። የማይረባ ሃሳብ በትክክኛ ሰዋሰው ከነገርካቸው ያደንቁሃል ፣ ያጨበጭቡልሃል። ሃሳብህ ምን ትልቅ ቢሆን ፈረንሳይኛህ ከተሰባበረ አይሰሙህም። ተራው ህዝብ እንዲህ ነው። ፐሮፌሰሮቹም እንዲህ ሲሆኑ ግን ይገርምሃል። እኛ በደንብ የምናውቀውን ፅንሰሃሳብ ፈተንሳይኛውን አምጠን እንደምንም 3 ገፅ እንፅፋለን። ፈረንሳዮቹ በቋንቋቸው እየተራቀቁ 6 ወይም 7 ገፅ ይፅፋሉ። ታዲያ ፕሮፌሰሮቹ ሃሳብህን አያዩም። ሰዋሰውን እየመዘኑ ይጥሉሃል። አሁን ተመልሼ የማላገኘው አንድ አመት ባከነብኝ። እኔም፣ ቤተሰቤም፣ ሃገሬም አንድ አመት ተነጠቅን።

©©©

ኤክሳንፕሮቫንስ ውስጥ ከመላው አለም የመጡ ብዙ ተማሪዎች አሉ። ተማሪዎቹ በስኮላርሽፕ የሚማሩ ሲሆን ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ወጪ የሚመሩት ከቤተሰቦቻቸው በሚላክላቸው ገንዘብ ነው። የባህራም ቤተሰቦች ግን ገንዘብ መላክ አቁመዋል። ባህራም እጅግ ተጨንቋል። በመጀመሪያ ለደህንነታቸው። ለጥቆ ለኑሮ የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚያገኘው ከነሱ በመሆኑ። ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት ተቆጠሩ። የቤተሰቦቹ ጉዳይ ግን የውሃ ሽታ ሆነ። ለቀናት የሚበላው አጥቶ ተራበ። ክብሩን ረሳ። ቀጥ ብሎ አከራዩ አሮጊት ጋር ሄደ። ርቦኛል አላት። ዳቦና ወተት ሰጠችው። ሆን ብሎ ሰክሮ አብሯት አደረ።

©©©

በአማርኛ ስነፅሁፍ ውስጥ የሚደንቁኝ አራት ስብእናዎች አሉ። የፍቅር እስከ መቃብሩ ጉዱ ካሳ፣ የሰንሰለቱ ስነወርቅ፣ የሀዲሱ ሀዲስ እና አራተኛው የትኩሳቱ ባህራም ናቸው።

🤖🤖🤖

ኒኮል

ኒኮልን የሚከጁሏት ብዙ ናቸው።ባህራም ጓደኛዋ ነው ፣ ጃምሺድና ሉልሰገድ በድብቅ ይተኟታል።። እንደውም ለጃምሺድ እና ልዑልሰገድ ሞት ምክንያት የሆነችው ኒኮል ነች።ስብሐትም በወሬ ብቻ የሚያውቀውን የጭኗ ውስጥ ሙቀት እያለመ በስሜት ይቃጠላል።

ተካ ደግሞ አለ። ሴት መተኛት ያምረውና ኒኮልን ሲያያት ጥሩ ምርጫ ሆና አገኛት―ዘርዛራ ጥርስ፣ አመዳም ቆዳ፣ ባህራም እራሱ የሚተኛት ለገንዘቧ ብሎ መሆን አለበት ሲል አሰበ። አንድ ቀን ቤቷ ሲሄድ ብቻዋን አገኛት።

"ምነው ያለወትሮህ" ብትለው

" ለአንቺ የሚሆን ጨዋታ አለኝ" አላት።

አካሄዱ ሲገባት፣ በትህትና ቤቷን ለቆ እንዲወጣ በሩን አሳየችው። ተካ ግን ዘወትር ሌሎች ሴቶች ላይ እንደለመደው፣ እጇን ጠምዝዞ ፣ ፀጉሯን ጨምድዶ ፣ በጥፊ እያጮለ በሃይል ሊገናኛት ሞከረ። ኒኮል እያለቀሰች ነፍሰጡር መሆኗን ስትነግረው ግን፣ የሱሪውን ዚፕ ቆለፈና፣ ከቤቷ ውልቅ ብሎ ወጣ።

ብዙም ሳይቆይ፣ ባህራም በሌላ ጉዳይ ተናዶ ቤት ሲመጣ፣ ኒኮልን ፀጉሯን ተንጨባሮ ፣ ፊቷ ደም መስሎ ፣ እያለቀሰች አገኛት። ጉዳዩን ከኒኮል አፍ እንደተረዳ፣ ተካን ፍለጋ በፍጥነት ከቤት ወጣ። ኒኮል ደግሞ፣ ባህራም ተካን ካገኘው ይጎድለዋል ብላ ስለፈራች ከኋላ ሱክ ፣ ሱክ እያለች ትከተለዋለች።

በጣም የምወደው አኒሜሽን ፊልም Kung fu Panda
በጣም የምወደው የጃክ ብላክ ፊልም Kung fu Panda
በጣም የምወደው የmartial art ፊልም Kung fu Panda
በጣም የምወደው ኮሜዲ ፊልም Kung fu Panda

🤖🤖🤖

የፓንዳው ስም ፖ ነው። ፖ ትልቅ ህልም አለው። በህልሙ "ድራገን ዎሪየርን"(ተዋጊ ድራገን) ለመሆን ያልማል። ይህ ህልም ሰማይን ተንጠራርቶ ለመንካት እንደመሞከር ነው። ማንም ሰው የፓንዳውን ህልም ቢሰማ ሳቅ ይገድለዋል። ይህ ፓንዳኮ ድቡልቡል፣ ቦርጫም፣ ምንም አይነት የማርሻል አርት ስኪል የሌለው፣ በአባቱ የሾርባ ምግብ ቤት ውስጥ የሚያስተናግድ ተራ ፓንዳ ነው።

ድራገን ዎሪየር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ከ"ፉሪየስ ፋይቭ"(አምስቱ ሃይለኞች) አንዱ ነው። ፉሪየስ ፋይቭን ያሰለጠናቸው ማስተር ቺፉ እራሱ ነው። በቻይና ምድር ከቺፉ የበለጡ ጥበበኛ ማስተር ኡግዌ ብቻ ናቸው። ከቺፉ የበለጠ ጦረኛ ታይ ሎንግ ብቻ ነው።

ታይሎንግ ተጥሎ የተገኘ ትንሽ ነብር ነው። ማስተር ቺፉ እራሳቸው ናቸው ተንከባክበው ያሳደጉት። ሲያድግ ግን ታይሎንግ ክፉ ሆነ። የድራገን ዋሪየሩን ሚስጥር የያዘውን ጥቅል ፈለገ። ይኼኔ ማስተር ኡግዌ ጣልቃ ገብተው ታይሎንግን ፀጥ አስደረጉት። ከዚህ በኋላ ታይሎንግ ለብቻው አንድ ከባድ ጥበቃ የሚደረግበት እስር ቤት ታሰረ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ድራገን ዋሪየሩ የሚመረጥበት ቀን ነው። ብዙ ህዝብ ተሰብስቧል። ፖ ደግሞ አርፍዷል። ሲደርስ በሩ ተዘግቶ ጠበቀው። ከጉጉቱ የተነሳ ተቀጣጣይ ሮኬቶችን ተጠቅሞ ወደ ስቴዲየሙ ገባ። ራሱን ያገኘው አንድ ጣት ወደሱ እየጠነቆለ ነው። እጁ የማስተር ኡግዌ ሲሆን ድራገን ዎሪየር እንዲሆን የተመረጠውም እራሱ ነበር። ከኡግዌ በስተቀር ሁሉም ደንግጦ ነበር። ማንም የሚያየውን አላመነም። ይህ አስቂኝ ድብልብል ፓንዳ ድራገን ዎሪየሩን ሊሆን?! ሊታመን የማይችል ነገር ነው።

ከዚህ በኋላ ፖ ውሎና አዳሩ ከፉሪየስ ፋይቭ ጋር ነበር። ግን አንዳቸውም ሊያዩት አይፈልጉም። ፓንዳውን ቺፉ ጠልቶታል። ፉሪየስ ፋይቮች ጠልተውታል። በፖ እምነት ያላቸው ማስተር ኡግዌ ብቻ ናቸው።

እነሆ ማስተር ኡግዌ ከዚህ ምድር የሚለዩበት ቀን መጣ። በአትክልት ስፍራቸው ሆነው ቺፉን ለስንብት ያነጋግራሉ፦

"ቺፉ ፓንዳውን እንደምታሰለጥነው ቃል ግባልኝ። ድራገን ዋሪየሩ እሱ ነው"

"ማስተር ኡግዌ ያ እኮ በአጋጣሚ የሆነ ነገር ነው"

"ቺፉ አጋጣሚ የሚባል ነገር የለም። አሁን ፓንዳውን እንደምታሰለጥነው ቃል ግባልኝ"

"እሺ ቃል እገባለሁ"

ማስተር ኡግዌ አሁን ነፍሳቸው ሰላምን ስላገኘች በአበቦች ተከበው ከምድር ተለዩ። ቺፉ ብቻውን ቀረ። የገባውን ቃል አስታወሰ። በፓንዳው ባያምንም ቃሉን ለመጠበቅ ሲል ያሰለጥነው ጀመር።

በሌላ በኩል ታይሎንግ በከባዱ ከሚጠበቀው እስር ቤት አመለጠ። ፉሪየስ ፋይቭ ይህን ሲሰሙ ሊያስቆሙት ተነሱ። ነገር ግን አንዳቸውም ታይሎንግን መቋቋም አልቻሉም። ሁሉም ተሸንፈው ተመለሱ። ለቺፉም የሆነውን ሁሉ ነገሩት። ፓንዳው ይህን ሁሉ ሲሰማ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ቺፉ ግን ተከታትሎ አስቆመውና የድራገን ዋሪየሩን ጥቅል ማየት እንዳለበት አሳመነው። ፖ ጥቅሉን ቢያየው ባዶ ነው። ምንም አልተፃፈበትም። ቺፉም ተቀብሎ አየው። ያው ነው። በመጨረሻ ፖ ወደ ቤቱ ሄደ። ታይሎንግን ፍራቻ ሁሉም መንደርተኛ ስደት ጀመረ። በሰፈሩ ውስጥ ማስተር ቺፉ ብቻ ታይሎንግን እየጠበቀ ቀረ።

ፓንዳው ከአባቱ ጋር የስደት ጉዞውን እንደጀመሩ እንዲህ አሉት፦

"ዛሬ የሾርባዬን የጣእም ሚስጥር እነግርሃለሁ"

"እሺ"

"የጣፋጩ ሾርባ ሚስጥር ምንም ነው"

በዚህ ቅፅበት ፖ ሁሉም ነገር ገባው። የድራገን ዋሪየር ሚስጥሩ ራሱ ነው። አባቱን ተሰናብቶ ወደ መንደሩ ተመለሰ። ታይሎንግ ቺፉን አሸንፎ የድራገን ዋሪየሩን ጥቅል ሲመለከት ደረሰ። ነብሩ ጥቅሉን እያዟዟረ ቢያነበው ባዶ ነው። ድንገት ድምፅ ሰምቶ ዞር ቢል ፖ ነው፦

"ለመጀመሪያ ግዜ ሳየው እኔም አልገባኝም ነበር"

"ስለ አንተ ሰምቻለሁ። ድራገን ዎሪየር ተብለህ የተመረጥከው አንተ ነህ አይደል" ነብሩ ጮክ ብሎ ሳቀ። ፖ አልተናደደም። ታይሎንግ እና ድራገን ዋሪየሩ ጦርነት ጀመሩ። ታይሎንግ በንቀት ነበር ፖን የገጠመው። ፖ ግን ቀላል ባለጋራ አልነበረም። የጥቅሉ ሚስጥር በራስ ማመን መሆኑን የተረዳው ፖ ድብልብል ሰውነቱን እና ያልተለመዱ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ታይሎንግን አሸነፈው። አዎ ይሄ ድብልብል ፓንዳ ሃያሉን ታይሎንግ ረታ። ይሄ ሁሉም የሚዘባበትበት ፍጥረት የጥቅሉን ሚስጥር ተረድቶ ድራገን ዎሪየሩን ሆነ። እነሆ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማእዘን ራስ ይሆናል የተባለው ተፈፀመ።

🤖🤖🤖

Kung fu Panda ብዙ የሩቅ ምስራቅ ፍልስፍና በጥበብ ቀለል አድርጎ የሚያሳይ ፊልም ነው።

ለምሳሌ አንዷን እንይ። The Furious Five ፖን ጠልተውታል። ቺፉ ተጠይፎታል። በፖ የሚተማመኑት ማስተር ኡግዌይ ብቻ ናቸው። ታዲያ ፖ ከሌሎቹ ጦረኞች ጋር ለመቀላቀል ሲሞክር

Tigress: ቦታህ እዚህ አይደለም

Po: አውቃለሁ። ይሄ የአንቺ ክፍል ነው

Tigress : አልገባህም። እኔ ለማለት የፈለግኩት ይህ ቤተመንግሥት ቦታህ አይደለም። አንተ ለኩንግ ፉ ሃፍረት ነህ። ለእኛና ለምንሰራው ነገር ቅንጣት ታህል ክብር ካለህ፣ ነገ ሳይነጋ ገና በሌሊት ከዚህ ተነስተህ ትሄዳለህ"

[ፖ ልቡ በሃዘን እየደማ ድምጹን አጥፍቶ በሩን ዘግቶ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ይሄዳል]

Crane : ተመልከት። እዚህ ቦታህ አይደለም።

Po :አዎ አውቃለሁ። አየህ ህይወቴን ሙሉ ድራገን ዋሪየር ለመሆን አልም ነበር . . .

Crane : አልገባህም። እዚህ ክፍል ማለቴ ነው። ይህ የኔ ክፍል ነው። ይህ የኔ ድንበር ነው።

ፖ ሁለቴ ተሸወደ። ህይወት ሁለት ሶስቴ በተመሳሳይ ቀልድ የሚሸውደን እኛስ?!!

🤖🤖🤖

ሰዎች ይለወጣሉ?

ይህ ጥያቄ ለብዙ ግዜ ያወዛግበኝ ነበር። አስቤ አንዳንዴ "አዎ ይለወጣሉ!" ብዬ ስደመድም በሌላ ግዜ ደግሞ "ጭራሽ አይለወጡም!" እል ነበር።

ሰው ብጠይቅም ፣ መፅሀፍት ባገላበጥም አጥጋቢ ምላሽ አግኝቼ አላውቅም።

ከዚያ በኋላ "Kung Fu Panda"ን ተመለከትኩት። እዛ ውስጥ ለዘመናት ላወዛገበኝ ጥያቄ መፍትሔ ያገኘሁ መሰለኝ።

የዚህ ተወዳጅ የአኒሜሽን ፊልም ዋና ገፀባህሪ ድብልብል ፓንዳ ነው። ይህ ፓንዳ በአባቱ ምግብ ቤት ውስጥ ነው የሚሰራው። በመላው ቻይና የማርሻል አርት ችሎታቸው የሚመሰገኑትን "The Furious Five" እንደ ጣኦት ያመልካል። እነደነሱ ብሎም ተወዳዳሪ የሌለውን ጦረኛ "Dragon Warrior"ን ለመሆን ይመኛል። ነገር ግን ይህ ሊሆን የማይችል ቅዠት ነው።

ነገር ግን ይሆናል! ይህ ድብልብል ፓንዳ የድራጎኑ ጦረኛ ይሆናል። የማይታመን ነው። የቻይና ጎበዛዝት ሁሉ ሊያሸንፉ ያልቻሉትን ሀይለኛውን ነብር "ታይ ሎንግ" ይረታል። ምንድነው ነገሩ? ይሄ ፓንዳ አሁንም ድብልብል ነው። አሁንም ገልጃጃ ነው። አስቂኝ ባህሪያቶቹም አልተቀየሩም። በሌላ በኩል ደግሞ ተለውጧል። ምንም የማርሻል እውቀት የሌለው ፓንዳ ሀያሉን ነብር ረቷል። ከዚህ የበለጠ ምን ለውጥ አለ። እህስ? ይሄ ፓንዳ ተለውጧል ወይስ አልተለወጠም? ግራ የገባው ነገር ነው!

ይህ ተፈጥሮ የሚባል ነገር ሚስጥሩን ደረስኩበት ብለህ ገና ማጣጣም ከመጀመርህ ሌሎች ሺህ ሚስጥሮችን በዱካው ፈልፍሎ ሬት ያስልስሃል።

🤖🤖🤖

Kung fu Panda

የሩቅ ምስራቅ ፍልስፍናውን፣ የማርሻል አርት ጥበቡን፣ ቀልድና ሳቁን አጭቆ የያዘ ፊልም ነው። ታሪኩ ወጥ ነው። ቀልዶቹ ያልተሰለቹ ናቸው። ገፀባህሪያቱ ላይ በደንብ ተጨንቀዋል። ዳያሎጉ ተሰምቶ አይጠገብም። ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ ሌላ ነገር አታስቡም። ጃክ ብላክ የተዋጣለት የድምፅ ተዋናይ ነው። በመልክም ቢሆን ከፓንዳው ጋር ብዙ አይለያይም😆 ፊልሙ የተዋጣለት እንዲሆን የኮምፒውተር አኒሜሽን ባለሙያዎቹ የስድስት ሳምንት የማርሻል አርት ስልጠና ወስደው ነበር። የድምፅ ተዋናዮቹ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደተመረጡ ያስታውቃሉ፦ ደስቲን ሆፍማን፣ ጄኪ ቻን፣ አንጀሊና ጆሊ፣ ሉሲ ሉ፣ ኢያን ማክሼን፣ ሴት ሮጀን፣ ዳን ፎግለር፣ ማይክል ክላርክ ዱንካን። ተዋናዮቹ ገፀባህሪያቱን እጅግ የመጠኑ ናቸው። ሁለተኛው ክፍል ግን በወጥነት፣ በለዛ፣ በታሪኩ ወረድ ያለ ነው። ያው ሆሊውድ አንድ ፊልም ተወዳጅ ሲሆን እንደ ለማኝ ድሪቶ እየቀጣጠሉ የሚሰሩት ውራጅ ነው።

ሌላው ደግሞ ተወዳጁን የጥንት ሙዚቃ "Kung fu Fighting" ሲሎ ግሪን እና ጃክ ብላክ ለዚህ ፊልም ማጀቢያ እንደገና ተጫውተውታል።

🤖🤖🤖

የምንግዜም ምርጥ የአኒሜሽን ፊልሜ ነው። አስቂኝ ነው፤ ብዙ ፈገግታዎች ታጭቀውበታል። ደጋግሜ ስመለከተውም ቀልዶቹ አያረጁብኝም። ዘወትር እንደ አዲስ እንደ ሞኝ ያስገለፍጡኛል።

ደሞ! ገፀባህሪዎቹም ሁሉም የማይረሱ ናቸው—አስቂኙና ድብልብሉ ፖ፣ ቁጡው ቺፉ፣ የተረጋጋው ማስተር ኡግዌይ፣ ሃይለኛው ታይ ሎንግ ወዘተ

ደግሞም የተመረጡት የድምፅ ተዋናይ ብዛትና ጥራት
ደስቲን ሆፍማን፣ ጃክ ብላክ፣ ጃኪ ቻን፣ ሉሲ ሉ፣ አንጀሊና ጆሊ፣ ማይክል ክላርክ ዱንካን፣ ኢያን ማክሼን፣ ሴት ሮገን ወዘተ

ቀልድ ብቻ አይደለም ፊልሙ፤ ብዙ ቁምነገርም ታጭቆበታል። የሩቅ ምስራቅ የረቀቀ ፍልስፍና፣ የቻይናውያን ባህል፣ አመጋገብ፣ ማርሻል አርት፣ መልከአምድር ወዘተ በታማኝነት የተገለፀበት ድንቅ ፊልም ነው። አኔሜተሮቹ ለ6 ሳምንት የማርሻል አርት ስልጠና መውሰዳቸው መዘንጋት የለበትም። ሁሉም ትእይንቶቹ ፍጹም ናቸው። በነገራችን ላይ ቻይናውያን በፊልሙ ይቆጫሉ—አሜሪካውያን እንዴት ከኛ በበለጠ ባህላችንን ተረድተው ለአለም አሳዩበት ብለው።

I'm not a fan of the sequels, though!

© Te Di

12 የዕውቀት ጠብታዎች ከኖህ መርከብ!

__⚓️-⚓️-⚓️___

1️⃣ ወደ መልካም ነገር የምትወስድህ ጀልባ ስትመጣ ፈጥነህ ተሣፈር፣ የመዳንህ መርከብ ስትቀርብ በቶሎ በእርሷ ላይ ውጣ፤ በሕይወት ዘመንህ አንዴ ካልሆነ ያቺን መርከብ ደግመህ ላታገኛት ትችላለህና – በፍፁም መርከብህን አታስመልጥ!

2️⃣ ሁልጊዜ ይህን ነገር አስታውስ፡- ሁላችንም ያለነው በአንዲቱ ጀልባ ውስጥ ነው፤ ጀልባይቱ ብትሰበር ሁላችንም እናልቃለን፤ ጀልባይቱ በሠላም ብትጓዝ ሁላችን እንተርፋለን! ይሄን አትርሳ – ሁላችንም ያንዲት ጀልባ ተጓዦች መሆናችንን!

3️⃣ በህይወትህ ልታደርጋቸው የምትመኛቸውን ነገሮች አስቀድመህ ዐቅዳቸው! ልብ በል፤ ኖህ መርከቡን መገንባት የጀመረው ዝናቡ መዝነብ ከጀመረ በኋላ አልነበረም! ደመናም በሠማይ ሣይዞር፤ የዝናብ ጉርምርምታም ሣይሰማ – አስቀድሞ ነው መርከቢቱን ማነፅ የጀመረው!

4️⃣ የአካል ጥንካሬህን ሁልጊዜም ጠብቀህ ተገኝ፤ ሁልጊዜም ብቁ ሁን! ማን ያውቃል? ምናልባት በ600 ዓመትህ፤ የሆነ ሰው ድንገት መጥቶ፤ አንድን እጅግ ታላቅ ነገር እንድታከናውን ሊጠይቅህ ይችላልና!

5️⃣ መናቆርን ብቻ ሥራዬ ብለው በያዙ ነቃፊዎች ትችት በፍፁም አትበገር! መሥራት ያለብህ ትክክለኛ ነገር ካለ፤ ዝም ብለህ ሥራህን ቀጥል! ለወሬኛ መድኃኒቱ ያ ነው – ትክክለኛ ሥራህ በስተመጨረሻ ይገለጣል!

6️⃣ ወደፊት ልትደርስበት አጥብቀህ የምትፈልገውን የህይወት ራዕይ፤ በታላቅ ሥፍራ ላይ አኑረው! ታላቅን ሕልም አልም! ለከበበህ ቁጥቋጦ ሣትበገር፤ ከፍ ባለ ሥፍራ ላይ የሕይወትህን ዋርካ ቀልስ! በታላቅ ሥፍራ ላይ የራዕይህን ማደሪያ መቅደስ ለመገንባት – አልመህ፤ ቆርጠህ ተነስ!

7️⃣ ጥንድ ጥንድ ሆነህ መጓዝ፤ ለክፉም ለደጉም ይበጃልና፤ ጉዞህ የተቃና እንዲሆን፤ ከጥንድህ ጋር መጓዝን አስብበት!

8️⃣ ከፈጣኖች እንደ አንዱ ነኝ ብለህ፤ በፍጥነትህ አትመካ፤ ፍጥነት ሁልጊዜም ላያድንህ ይችላልና! በደንብ አስተውል፤ በመርከቡ ውስጥ እኮ፤ ቀርፋፋዎቹ ቀንዳውጣዎችም፤ ፈጣኖቹ አቦሸማኔዎችም – ሁለቱም እኩል ፍጥነት ባለው ቀሰስተኛ መርከብ ተጉዘው ነው፤ በህይወት የተረፉት!

9️⃣ ጭንቀት ሲይዝህ፤ ካለህበት ነገር ወጣ በል፤ ትንሽ ዘወር በል፤ ለተወሰነ ጊዜ ቅዘፍ! ከችግርህ በላይ ሆነህ ስትንሣፈፍ – ያስጨነቀህ ነገር እልፍ ማለቱ አይቀርም!

🔟 ይህን ነገር ሁሌም አስታውስ፤ የኖህ መርከብ የታነፀችው ልምድ በሌላቸው በአማተሮች እጅ ነው! እንዲያም ሆኖ፤ ታላቅን ማዕበል ተቋቁማ፤ የተጓዦቿን ህይወት አተረፈች! ታይታኒክስ?

ታይታኒክ የተገነባችው፤ አሉ በሚባሉ ዕውቅ ባለሙያዎች ነው! ግን የአንድ ቀንን ማዕበል መቋቋም ተስኗት፤ ተሣፋሪዎቿን ውሃ አስበላቻቸው! አየህ አይደል?

በሙያ ልቀት ብቻ አትመካ፤ ከሌሎችም ዘንድ ከአንተ የበለጠ ጠቃሚ መፍትሄ ሊገኝ እንደሚችል ዕወቅ! የታናናሾችህ የእጅ ሥራ፤ ህይወትህን የመታደግ አቅም ሊኖረው እንደሚችል – በዘመንህ ሁሉ አስብ!

1️⃣1️⃣ ማዕበሉ የቱንም ያህል ቢናወፅ፤ አምላክህ ከአንተ ጋር ካለ፤ ማዕበሉ ፀጥ እንደሚል፤ ቀስተደመናም በሠማይህ ላይ ሊወጣ እየጠበቀህ እንደሆነ፤ በፍፁም ልብህ እመን!

የማዕበሉ ወጀብ በመንገድህ ላይ በርትቶ ሲፀናብህ፤ የአንፀባራቂው ቀስተደመናህ መውጣት እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያበሥር፤ አንዳች የተስፋ ምልክት እንደሆነ ዕወቅ!!

1️⃣2️⃣ በጉዞዎችህ ሁሉ ከላይ የተነገሩት ጥንቃቄዎች አይለዩህ! የቱንም ያህል ማዕበሉ በመንገድህ ቢፀና፤ በስተመጨረሻ ጉዞህ እንደ ኖህ የተቃና ይሆንልሃል!

ይህ የሚሆነው ግን፤ ጉዞህን ከራስህ አልፎ - የሌሎችንም ሕይወት የሚታደግ እንዲሆንልህ አድርገህ ስታቅደው ነው! እንደ ኖህ፤ ያሰብከው ይሰምርልህ ዘንድ፤ ሥራዎችህን፤ ጥረቶችህን፤ በረከቶችህን ሁሉ ለሌሎች የሚተርፉ አድርጋቸው!

መልካም ጉዞ!

ቦን ቮያዥ!

⚓️♥️

_____

የእንግሊዝኛ መልዕክቱ (ከከበረ ምስጋና ጋር):-

«Everything I need to know about life, I learned from Noah’s Ark». ውርስ ትርጉም የራሴ። Aug 14, 2018.

© Assaf Hailu

Differential Equation በአማረኛ
በደራሲው መብትና ፍቃድ የተለጠፈ
© መብቱ የተጠበቀ

Mathematical Logic በአማረኛ
በደራሲው መብትና ፍቃድ የተለጠፈ
© መብቱ የተጠበቀ

ግጥም፣ አጫጭር ተረቶች፣ ጥናታዊ ፅሁፍ፣ መጣጥፍ…
በደራሲው መብትና ፍቃድ የተለጠፈ
© መብቱ የተጠበቀ

"I call my book a memoir. I have a whole section in the book called “Theory as Memoir.” I think for me, what critical theory is doing in the book is engaging with my experience of loss, as well as my sense of the past as memory, but it is also a way to translate that memory into some kind of shared human knowledge while also submitting to the limits of human knowledge. I primarily think about the past as a web of relations that connects me to other historically situated and embodied persons. To write about the past is to talk about the ways [in which] those relationships have come to possess me in the way ghosts are known to possess a person’s body and to also think about the contingencies of human knowledge based on that possession." ትልሃለች። ለማላውቅሽ፡ እኛን ለምታውቂን እመቤት💙

!
(ይሕቺን የጽሕፈት ቅርጽ (በቅርጽ ብቻ ) ከአንዲት ስሟ ከገነነ፤ ስመ ቢስ አጭር ልቦለድ የተዋስኋት ነች። parody ለመስራት ግን ከአላማዬም ከነገሬም የለም)

© Khalid Yohannes

[...] *

በመጀመሪያ ’ከማርና ከወተት ተዋጽኦዎች፤ ይሻላሉ ዘርፍ የሌላቸው ጨዋታዎች።' የሚለውን ተረት እንደዘበት ጣል አድርገን እንጀምር፡፡ እንዲህ ያለ ተራች ከሌለ እኔ እለዋለሁ። ገና በጠዋቱ የሚቆረስ እርጎ ሳጣ፥ ቀጣይ የካፌው ባለቤት ብሶተኛ ወደሆነበት ካፌ መግባቴ፡ ይናድ ቀርቶ፤ ይነቀነቅ የማይመስለው የጠዋት ሞቅታዬን ረበሸው። ይሕችን እንኳን ለአመል አልክ ብባልና ስሜ ቢነሳ ምን ችግር አለው?! (hehe )

ልደታ በዚህ ጠዋት ቢበዛ መዝሙር ከየባሩና ሬስቶራንቱ ይወረወራል፤ ካልሆነም ዝም ያለ ቤት ይኾንና የጠዋት ፀሐይ ይጮኽበታል። እኔ የነበርኩበት ካፌ ግን የማሕሙድ አሕመድ 'ትዝታ ' ተከፍቷል። እዳዬ! እሱን እያደመጥኩ ግን እሌኒ ዘለቀ ትዝ አለችኝ። እሌኒን ተከትሎ ደግሞ የማስተርስ መመረቂያውን የሚሠራ ጓደኛዬን አስታወስኩ። የመመረቂያ ስራውን ይዘት ሳስብ 'ደይ-ድሪሚንግ' መከራ እንደሚያበላው ሰው በሌለሁበት፥ ባልዘለልኩበት ስሳቀቅ፥ ሲደብረኝ ተገኘሁ።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በትዝታ ስልት እሌኒን ለመጎተት የሚያበቃ የስራዋም፥ የእሷም ምንም ግንኙነት አልነበረኝም። ግን ሰዎች የሌሎችን መልክ ያውሱኛል። ከሕዋስ ጋ ውል በሌለው ቀለምና ባሕርይ እንደወደዱት ወድዶ፥ እንደናፈቁት ናፍቆ መገኘት ከዚያ ኋላ እዳ ኾኖ ከላዬ ይቆያል። እሌኒን ማስታወስ ከጓደኛዬ የተሰጠኝ ነው ለማለት ነው(በተገናኘን አጋጣሚዎች ሁሉ ስራዎቿን ሳታነሳ አታልፍም... ስራዎቿን ለሳምንት እንድነካም ተፈቀደልኝ...መመለሴን እንዣልኝ!)። እሌኒ፤ 2021 ላይ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ ስለ ስራዋ ውይይት ባደረገች ጊዜ የማሕሙድን ሙዚቃ ለሰኮንድ ካስደመጠች በኋላ ስለሙዚቃው ባወራችው አሟሽተን ይሕችን አንቀጽ እንዝለል (አፈር ይቅለላት እሌኒን)"...The song refers to both the loss of form and the loss of content. I don't have you; therefore, I don't have memory, or don't have memory, therefore I don't have you." ያለችበትን ተውሼ፥ እሷን በሌለችበት ይዤ 'ረታታለሁ።

ተከትሎ ትዝ ያለኝ ዠለስ ደግሞ በቅርቡ የወጡና ድጋሜ ታርመው በተሰራጩ የሕይወት ታሪክ መፃሕፍት፥ ማስታወሻዎች (memoirs ) እንዲሁም ጥናታዊ ስራዎችን፤ በተመሳሳይ ሁኔታና የጊዜ አጽቅ ውስጥ ከታተሙት ነፃ የፈጠራ ልቦለዶችም (literary fiction ) ኾነ በዘውጋዊ ልቦለዶች (genre fiction) ምድብ ከሚገኙ ከተወሰኑ ስራዎች ጋ በንጽጽርና ጎንለጎን ከኾነ ዲስፕሊን አኳያ በማጥናት ነው ማስተርሱን እየሰራ ያለው።

ሌላ ሌላውን ትቼ የቴሲሱን ይዘት በቀጥታ ስለማይነኩ፤ ከስራው ውጤት አንፃር ወይም ከእኛ ግምት አኳያ አንዳንድ ጥያቄዎችን አንስተቼ መልሱን አብረን ብንገምትስ?
( ከሁለቱ የአጻጻፍ ዘውጎች )

° የኑሮ እጅግ ውስብስቡን ትልም ዝርጋታ በመረዳት ረገድ የትኛው ዘርፍ የተሻለ እኛን ይጠጋናል? ፥ 'ርቀቱን አጥብቦ ቢችል ከማህበረሰቡ ጋር በእኩል የኑሮ እና የህይወት ክንድ የተደቆሰ፥ ከገመናው ጋ የቆረበ፥ በዘመኑ ያለውንና የነበረውን ንቁ ሕይወት በንዝህላልነት ሳይተው መተንተን የቻለው ዘርፍ የትኛው ነው?

° የማኅበረሰብ ሥነ-ልቡናዊ ገጽታን የተሻለ ግልጽ፥ በደንብ የተብራራ የሚያደርጉት፥ ምንም ቢጽፉ የሚሰምርላቸው ያሕል ክሂላን ኾነው የተገኙት በየትኞቹ መደብ ያሉት ይኾናሉ? ምናምንና ወዘተ... የሚለውን ማሰብ ለእኔ ትንሽ አስቸገረኝ።

ነፃ እንድትሆን በመመኘት "ኪነት ዳኛ የላትም " ሲሉን፤ የላትም! ብዬ ተቀብዬ ነበር። ለእኔ ግን የላትም ሰም ነው፤ ወርቁ "የራሷ ደንብና መመሪያ አላት" ማለቴ ነው። ስማቸውን በስራዎቻቸው መቀጸል በሚፈልጉ 'ነፃ' ሰዎች መካከል መገኘት ብዙ ጊዜ ነፃነትን ለመለማመድ አቅሙንም ድፍረቱንም(ደፋር ሁላ!) ከየትም ከየትም አግኝተው፤ የራሳቸውን ግላዊ ምዘና(subjective evaluation) ቁልጭ አድርጎ የማስቀመጥ ግዴታቸው ላይ ሲደርሱ As the well known ደብተራ state it "ጳራራም ፓራራም! " ማለት ብቻ ወጋቸው ይኾናል። ያናድዳሉ!

እና በዚህም የተነሳ አንዳንድ ጓደኞቼ እየተግደረደሩ፥ አንዳንዴ ደግሞ በግልጽ " አንድ መቶ ሦስት የፈጠራ ልቦለዶችን ከማንበብ አንድ የማዕማር መና ሰማይን አርቲክልና መፃሕፍት መገረብ የተሻለ ወደ 'ራስ ያቀርባል" ይላሉ። ቢጠኑ፥ ቢነጻጸሩ የማያሳፍሩ ትልቅ የፈጠራ ስራዎች መኖራቸውን የሚክዱ አይመስለኝም። ሊክዱም አይችሉም—ገላጋይና፥ ረታን የት ይደብቋቸዋል። ይርጋ ገላው፥ ጳውሎስ ሚኪያስ፥ ተከስተ ነጋሽ፥ መሳይ ከበደና የመሠል ሰዎች መጣጥፎችን ማገላበጥ ግን የተሻለ... የተሻለ የፀሐፊን ሉዐላዊነት ለመረዳት ትዕምርት ኾነው መቆም መቻላቸውን በጀብድ ነው የሚያወሩት። ሲጀመር የንፅፅር ሜዳ ላይ ለመቅረብ ተመሣሣይ ሜዳ ላይ የተገኙ አይደሉም። ብትሉ እኔም ከእናንተ ጎን ነኝ።

"እነዚህ ሰዎች ሲጽፉ፥ ኀልዮት ሲቀምሙ፤ የሚጽፍ ሰው የሚኼደው መንገድ፡ የተሻለ የሥርዓተ አምልኮ መመሪያ አሚነ-ስብከት ፍለጋን እንዳልሆነ በግልጽ ያስተምሩናል። የሚኼደው ሁሉንም መምህራንና ትምህርቶችን በመተው፤ ያላነጣጠረውን ወይም በተቃራኒው— ያለመውን ግብ ብቻውን ለመምታት፤ አሊያም ደግሞ ለመሞት መወሰኑን ማረጋገጥ እንዳለበት ይነግሩናል " ባይ ናቸው። እነዚያኞቹ ግን ትንታግ ምላስ ብቻ። በአንዳንዶቹ ትንታግ ምላስ ደግሞ፣ ዘመኔን ሙሉ ልቤ ሲላስ ነው የፈጀው። መቼም ብዕር ለማለት እኔም እናንተም ደፍረን አንናገርም።

ጓደኞቼ በምን ስርዋጽ ወደ'ዚህች ዘርፈ-ቢስ ጨዋታ ገቡ? እንጃ! ግን ጥናቱን እያደረገ ስላለው ወዳጄ ነገር ስመለስ፤ በቀጥታ የስራውን ኦርቢት ከመንካት ድጋሜ ሆን ብዬ ልዝለለውና፤ ትኩረት አድርጎ ከሚያየው አንደኛው ንዑስ ርዕስ "ትዝታ፥ ትውስታ... " በአማርኛ ሥነ-ፅሑፍ ውስጥ፤ በተለያዩ ዲስፕሊኖች መካከል እንዴትና በምን ሁኔታ ተገለጸ? ምናምን የሚል ነው። 'ትዝታ'ን ወደ አካዳሚ ዲስኮርስ ካመጡ ሰዎች መካከል ደግሞ አስቀድሜ ያነሳኋት እሌኒ ዘለቀ(ፕ/ር ) እና ዳግማዊ ውብሸት(ፕ/ር ) ናቸውና፤ ስራቸው መዳሰሱ አይቀርም የሚል ያልተረጋገጠ ግምት አለኝ። ሌሎች ቢኖሩም፡ ቢያንስ ሁለቱን ማስታወስ በቂ ነው።

የእሌኒ ዘለቀ "ትዝታ"ን 'Ethiopia in Theory' የሚለውን መፅሐፍ ለማዘጋጀት እንደ ሜትዶሎጂ የመጠቀሟን አቅም፥ መግፍኤና፥ ውበት ከየትኛው የፈጠራ ስራ ጎን ለጎን ሊጠቀስ ይችላል? የሚለውን ማሰብ አያሳቅቅም? ተሳቅቄ፥ ተጦልቤ ቀኔ አለቀ እኮ! እኔ እራሴ ከማለቄ በፊት ወደ ሙዚቃው ይዘት 'ራሱ ለመመለስ እሌኒን በግርድፉ "ትዝታ"ን እንደ ሙዚቃዊ ዘውግ እና እንደ term መጠቀሟን ማሰብ ይሻላል። ማሕሙድ አሕመድ
« ትላንትናን ጥሶ ዛሬን ተንተርሶ
ነገንም ተውሶ፤ አምናንም አድሶ
ይመጣል ትዝታሽ ጓዙን አግበስብሶ።
(...)
ትዝታ ነው አሉን የሐሳብ መርከቡ
ማራገፊያውማ እኔ ነኝ ወደቡ...» ሲል፤ እሌኒ ደግሞ

የተከፈለበት ማስታወቂያ!

በሶስት ቀኑ ከ6M በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራት ችሏል። እንደ $DOGS ነው እየተባለ ገና ካሁኑ ሰፊ ተቀባይነት ማግኘት የቻለ Airdrop ነው። እንደ ሌሎቹ Airdroፖች በየጊዜው ታብ፣ ታብ ሚሉት ጣጣ የለውም። ታስክ ሲኖር ብቻ ገብቶ መስራት ነው። ይሄም ከዶግስ ጋር ያመሳስለዋል።
👇👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=Wl0TPCIS