Últimas Postagens de ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 (@bookshelf13) no Telegram

Postagens do Canal ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"
18,903 Inscritos
2,716 Fotos
24 Vídeos
Última Atualização 27.02.2025 06:07

O conteúdo mais recente compartilhado por ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 no Telegram


🎬🎬🎬

ዋልተር ኋይት ምስኪን የኬሚስትሪ መምህር ነበር። ከባለቤቱና ከልጁ ጋር ዝም ያለ ህይወት እየኖረ ገዳይ ካንሰር እንደያዘው ተነገረው። ሚስቱ ነፍሰጡር ናት። ልጁ የሰረብራል ፓልሲ ህመምተኛ ነው። እሱ ከሞተ ቤተሰቦቹ ምን ይውጣቸዋል? ማሰብ አለበት! ደግሞም ቶሎ የሆነ ነገር ማድረግ አለበት! ብዙ ገንዘብ ያስገኝ ብቻ። ይሄኔ አንድ ሰይጣናዊ ሃሳብ ብልጭ አለለት። የኬሚስትሪ እውቀቱ አስተማማኝ ነው። ታዲያ ለምን አደገኛ አነቃቂ እፅ አይቀምምም?!

ዋልተር ኋይት ቤተሰቦቹ ያስፈልጋቸዋል የሚለውን ወጪ አሰላ። የምግብ ፣ የህክምና ፣ የትምህርት ቤት፣ ሁሉንም ወጪ ከአመታት ቁጥሮቹ ጋር አዛምዶ ጥቂት መቶ ሺህ ዶላር መጣ። ይሄን ያህል ገንዘብ ካገኘ በኋላ ሜት ማብሰሉን ያቆማል።

ነገር ግን ዋልተር ኋይት ያልተረዳው ነገር ሰዎች ብዙ ገንዘብ ከቀመሱ በኋላ የበለጠ ብዙ ለማግኘት ይስገበገባሉ እንጂ አይጠግቡም። ዋልተር ኋይት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዶላሮች ሲያገኝ ሚሊየኖችን ተመኘ። ሚሊየኖችን ሲያገኝ ቢሊየኖችን ተመኘ። ቃል በቃል እንዲህ ይላል፦

"I'm not in the million dollar business. I'm in the billion dollar business."

የሰው ልጅ ስግብግብነት ማለቂያ የለውም። ይህ ስግብግብነት ዋልተር ኋይትን ሁሉንም ነገር አስከፈለው― ንብረቱን አጣ፣ ቤተሰቡ ተበተነ፣ ሁሉም ነገር ተነነ።

🎬🎬🎬

ብዙ ሰው ሞተ

አውሮፕላኑ ተከስክሶ ብዙ ሰው ሞተ

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ስለፎረሸ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ

ልጁ በድንገት ስለሞተች የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ፎረሸ

overdose ስለወሰደች ልጁ ሞተች

ዋልት overdose ወስዳ ከሞት ስትተናነቅ ዝም ብሎ ተመለከተ

Butterfly Effect ይሉታል። አንዷ የዋልት ግድየለሽነት አደገኛ የአውሮፕላን አደጋ ወለደች። Walt is bad. Very bad.

🎬🎬🎬

የ12 ወይም የ13 አመት ልጅ ቢሆን ነው። በአልቡከርኪ ጸሐያማ ሰማይ ስር ሳይክሉን እየነዳ ከከተማው ወጥቶ በበረሃማው መንገድ ብዙ ተጓዘ። ድንገት ግን ከመንገዱ ሶስት ሰዎች ገጠሙት።

3ቱ ሰዎች ዋልተር ኋይት፣ ጄሲ ፒንክማን እና ቶድ አልኩዌስት ነበሩ። እዚህ የተገኙት ለትልቅ የወንጀል ተግባር ነው። ዋልተር ኋይት ለሚቀምመው እጽ የሚሆን ኬሚካል ጭኖ በዚህ መንገድ የሚያልፍ ባቡር አለ። ግባቸው ይህንን ኬሚካል ማንም ሳያውቅባቸው መስረቅ ነው። ወደ ዝርዝሩ አንገባም።

ብቻ ባለ ሳይክሉ ትንሽ ልጅ ምንም አልጠረጠረም፦

"ሰላም" አላቸው።

ሁሉም ነገር የሆነው በሽርፍራፊ ሰከንዶች ነው። ቶድ ሁለቴ አላሰበም። አንዴም አላሰበም። ሽጉጡን አውጥቶ ተኮሰ። ዝምብም የገደለ አልመሰለውም።

ጄሲ ያየውን ማመን አልቻለም፦

"ምን ነካህ ሰውዬ?"

ቶድ ዘና ብሎ፦

"Shit happens"

ከመግደሉ በላይ መልሱ ያበግናል። አመላለሱ ያበግናል። ጄሲ በቦክስ ደረገመለት። ከሶስቱ መሀል ነፍስ ያለው ጄሲ ብቻ ነው።

እንግዲህ psychopath ብለን የምንጠራቸው እንደ ቶድ ያሉ ሰዎችን ነው። ምናልባት ምርጫ አጥተው ዋልትም ሆነ ጄሲ ልጁን ሊገድሉት ይችላሉ conflicted ሆነው። ከዛ በኋላም ጸጸቱ አይለቃቸውም። ወደ ሳይኮፓዞች ስንመጣ ታሪኩ ሌላ ነው። አይወዛገቡም፤ አይጸጸቱም። They have no empathy. እንደውም ሳይኮፓዞች በስሜትና በስነልቦና ኢቮልቭ ያደረጉ ራሳቸውን የቻሉ ሌላ species ሳይሆኑ አይቀርም።

🎬🎬🎬

አስተማሪና ተማሪ

አደገኛ እጽ አብሳይና አከፋፋይ

የዉድሮው ዊልሰን ማለቴ የዋልት ዊትማን ማለቴ የዊሊ ዎንካ🤣🤣 ማለቴ የዋልተር ኋይትና ጄሲ ፒንክማን ሃውልት በኒው ሜክሲኮ አልቡከርኪ

Breaking Bad - ጎግልን ርእሱን ወደ አማርኛ መልስልኝ ስለው "ሰበር ጉዳት" አለኝ። የክፋት ቁልቁለት/ጅማሬ/ ጉዞ የሚለው ያስኬድ ይሆን?!

እስቲ በዋልትና በጄሲ መካከል ምናባዊ ጨዋታ ቢደረግ ምን ይመስላል፦

ጄሲ፦ ዮ! ሚስተር ኋይት ሃውልታችንን እንዴት አየኸው?

ዋልት፦ ጉድ ነው ጄሲ! መነጽሬም አልቀራቸውም። ባርኔጣዬስ ብትል። ደግሞም ሃውልቱ የተሰራው ቤት ውስጥ መሆኑ ደስ ብሎኛል። አስበው ውጪ ቢሆን አደገኛው ሃይዘንበርግ የእርግብ ኩስ ማራገፊያ ነበር የሚሆነው። ባርኔጣዬን እንኳን አላደረግኩ።

ጄሲ፦ እኔ የምልህ ሚስተር ኋይት ለምን ሃውልቱን ሽጠን ተጨማሪ አደገኛ እጽ አናበስልበትም። እጻችን ዝነኛ ሆኗል። ፍላጎት ጨምሯል። ምርት አንሷል።

ዋልት፦ ጄሲ ይሄ መታሰቢያችን ነው አይሆንም። ገና ትውልድ በዚህ ያስታውሰናል። ቋሚ ምልክታችን ነው።

ጄሲ፦ አይ ሚስተር ኋይት ግትር ነህ። ግን ሃውልታችን ቢሰረቅስ?

ዋልት፦ ማን አባቱ ደፍሮን። እኔ ስራቂ እንጂ ተሰራቂ አይደለሁም። አደጋ አደርሳለሁ እንጂ አደጋ አይደርስብኝም። አሸብራለሁ እንጂ አልሸበርም። አደገኛው ሃይዘንበርግ እኔ ነኝ።

🎬🎬🎬

የጉስታቮ ፍሪንግ ቁጥር 1 ወርቃማ ህግ፦

"Don't go into business with crackheads."

ከሱሰኛ ጋር አታብር! ከሱሰኛ ጋር አትስራ! አየህ ሱሰኛ ባሪያ ነው። ሱሰኛ ጌታ አለው። ጌታው ሱሱ ነው። ገዢ ካገኘ ይሸጥሃል። ሱሰኛ ሱሱን ለሟሟላት እናቱን ከመሸጥ ወደ ኋላ የማይል ወራዳ ነው።

ሁሌም ሱስን ሳስታውስ ትዝ የሚለኝ የበእውቄ ግጥም ነው። ማእከላዊ ሃሳቡ እንዲህ ይላል፦

"ሁላችንም መኖርን የሚያክል ሱስ ተሸክመን ነው የምንዞረው"

🎬🎬🎬

ሃንክ ሽሬደር ጉስታቮ ፍሪንግን ጠርጥሮታል። ስለዚህ እንቅስቃሴውን የሚከታተል GPS tracker መኪናው ላይ ለመጥመድ ወሰነ። ከዋልት ጋር የጉስታቮ መስሪያ ቤት/Los Pollos Hermanos ተገኙ። ሃንክ መኪና ውስጥ ተቀምጦ ዋልት ትራከሩን ሊያጠምድ ሄደ። ይኼን ግዜ ጉስታቮ ፍሩንግ ድንገት ከች ይላል። ዋልት እጁ መንቀጥቀጥ ጀመረ፦

"እኔ አይደለሁም"

"አርፈህ ትራከሩን ግጠመው"

በነገራችን ላይ በብሬኪንግ ባድ ምህዋር ውስጥ ለኔ ትልቁ የፊልሙ ገፀባህርይ ጉስታቮ ፍሪንግ ነው። ብልጥ ነው፤ ብልህ ነው፤ የበታቾቹ ይታዘዙለታል፤ ያከብሩታል። ጠላቶቹ ይፈሩታል። የሚፈልገውን ያውቃል። ያንን ለማግኘትም ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል። መሞት ያለበት ሰው ካለ ያስገድለዋል። የአደንዛዥ እጽ ንግዱን የሚገዳደር ማንኛውም ነገር ያስወግዳል። የሚሰራው በመርህ ነው።

የሚያሳዝነው ይሄን የሚያህል ግዙፍ ስብእና በአንድ የሁለተኛ ደረጃ የኬሚስትሪ መምህር እጅ ይሞታል። ዳሩ Just because you shot Jesse James, don't make you Jesse James.

(በነገራችን ላይ የጉስታቮ ፍሪንግን ህይወት የሚያሳይ spinoff ሊሰራ ነው። የፊልሙ ርእስ Los Pollos Hermanos).

🎬🎬🎬

ሃንክ መጸዳጃ ቤት ተቀምጦ የዋልት ዊትማንን Leaves of Grass እያገላበጠ እንዲህ የሚል ተፅፎ ያያል፦

​“To my other favorite W.W. It's an honor working with you."

W. W. ደግሞ ማን ይሆን ብሎ መገመት ጀመረ።

Willy Wonka?
Woodrow Wilson?

በመጨረሻ ግን ግልጽ አለለት። W. W. እራሱ Walter White/ዋልተር ኋይት ነው። ይኼኔ ነው ሃንክ አገሩን ያመሰው ሃይዘንበርግ እራሱ ዋልተር ኋይት መሆኑ ወለል ብሎ የታየው።

© Te Di

ሰውየው ወንደላጤ ነው። ከስራ ሲመለስ ዳቦ ገዝቶ ቤቱ ልገባል። ይበላል። ዘውትር አመሻሽ በረንዳው ላይ ኳስ የሚጫወቱ ተንከሲስ ህፃናት አሉ። ለነገሩ ተንከሲስነታቸው ለጋብሮቫዊው ወዳጃችን እንጂ ለእኔስ ደግ ናቸው። ለምን ቢሉ። እነሱ ባይኖሩ ተረቴን ማን ያስውብልኝ ነበር። እላለሁ። እናም እነዚያ ህፃናት ልክ ዳቦውን ሊበላ ሲል ይመጣሉ ይቀመጣሉ። ቆርሶ ይሰጣቸዋል። ይበላሉ ይሄዳሉ። ከዚያም ነገ እየተጫወቱ ይመጣል። እነሱ ደግሞ ሊበላ ሲል ይመጡበታል። ያካፍላቸዋል ይሄዳሉ።

እነዚያ ህፃናት ጋቭሮቫዊውን አማረሩት። ለራሱ እንጂ ለእነሱ የሚሆን በጀትም አቅምም የለውም። ድንብሎ ዋስ የማይሆኑት ቅሪላ ለጊ ህፃናት ዳቦውን እየቀሙ ከጥጋብ ሜዳ ለጉት። ጨነቀው። አሰበ አሰበና አንድ ዘዴ መጣለት።
እንደተለመደው አመሻሽ ላይ ዳቦውን ማለቴ የሚበላውን ዳቦ አንከርፍፎ ሲመጣ ህፃናቱ ኳሱን ጥለው ተከተሉት። ዞር አለና የተገረመ በሚመስል አነጋገር እንዴ እዛ መታጠፊያው ጋ ዳቦ እየተሰጠ እናንተ ትራገጣላችሁ? ኧረ አፈር ብሉ! ምን አይነት ልጆች ናችሁ? ይሄኮ እርቧችሁ ይሆናል! » አለ።
ልጆቹ በአነጋገሩ ደንገጥ አሉ። የንግግሩን መዝጊያም ያዘነላቸው ለማስመሰል በመጣሩ የተቆረቆረላቸው መሰላቸው። ድጋሚ ሌላ ነገር ከመናገሩ በፊት ሁሉም በአንድነት ወደ ኋላ ወደመታጠፊያው የዳቦ እደላው ላይ በቶሎ ለመድረስ ሮጡ።

ጋብሮቫዊው ቤቱ ገባ። ዳቦውን ቆረሰ።በላ። ልጆቹ አልመጡም። ቆረሰ። አልመጡም። በላ አልመጡም። መንገድ መንገድ እያየ አላመጠ። ወይ ፍንክች። ሰውየው ደነገጠ። እንዴ ይሄ ነገር እውነትም ዳቦ እየተሰጠ ቢሆንስ ብሎ በሩን ቆልፎ እየሮጠ ወደ መታጠፊያው ሄደ። ስነ ተረቷ እስከዚህ ነች። ከዚህ በላይ አትለጠጥም። አንዳንዴ መኖራችን ውስጥ ቀልድ ሊገደን ጨዋታ ሊገዛን ሲያምረን የምናወጣት አይነት ካርድ ነች። ልክ እንደ ላጤው ጋብሮቫዊ አነሳሳቸው አንድን ግብ ለመምታት ይሆንና ጥቅል ጭብጡ እውነትን ያልተደገፈ ከዘመን የራቀ ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ ደግሞ ልልነትን በትረካ ሂደቶቹ ውስጥ ልንታዘብ እንቀርባለን።
ከህፃን እስከአዋቂ ይሰርቃል እንጂ የሚሰርቀው ለምን እንደሆነ አልተብራራም። ከመስረቃቸው ጀርባ ያለውን ድህነታዊ መልክ ከማሳየትም ይልቅ ጀብዳዊ ውሏቸው ላይ የተመላለሰ አይነት መፅሀፍ ነው።

ልልነት በወሪሳ ውስጥ

አንዳንድ የትረካ መስመሮች የተላበሱት ሀቅና ዚቅ የመፅሀፉን ጠቅላላ አንኳር ነጥብ አቅልለው አቅልለው ገለባ በማድረጋቸው የተዓማኒነት ጥያቄን እንድናነሳም ያደርጉናል። ለምሳሌ ያህል በገፅ 26 ላይ የምንመለከታት ባልቴቷ ወይዘሮ ጉዶ በሩን ቆርቁረው የሚጠይቁት ጥያቄ ለእኔ እጅግ የደከመ ለሳቅ ብቻ ያደላ እንጂ ሌላ መስሎ አልታየኝም። በገፅ 34 ላይም ተመሳሳይ ልልነቶችን እንመለከታለን።

ሌላው ልቦለድ ቢቻል የገሀዱን ዓለም ተምሳሌታዊ ቀለም ምናባዊ ሸማን አልብሶ ማቅረብ እንደሆነ ይታሰበኛል። ይህ ልቦለድ ማለትም ወሪሳ...
ከዚህ ብያኔ አኳያ የተጋነኑ አይጨበጤያዊ ትረካዎች በግልፅ የሚታዩበት ሆነው ላገኛቸው ግድ ሆኗል። ፀሀፊው እንዲህ ለዛና ፍሰቱ ውብ በሆነ መንገድ ፤ የቃላት መረጣውና የተባ ገለፃው መፅሀፉን ልዩ ቢያደርጉትም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የተሳኩ የማይመስሉኝ መጠነኛ ግድፈቶችን አስተውያለሁ። ይህም እንደዚህ ተብሎ ነበረ በሚል ንግግር ውስጥ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች አሁን ሲደረጉ መመልከት መታዘብ ይቻላል። ለምሳሌ በመፅሀፉ ውስጥ ሱሪውን አፍጦ እየጠበቀ አይኑን ለቅፅበት ጨፍኖ ሲገልጥ ጠፋበት ተረካ።

የሰረቀበትም ሰላቢ ወይም ረቂቅ አካል ሳይሆን ልክ እንደ እሱ ሰው ነው። አንዳንዴ አንድን ነገረ ጉዳይ ግነታዊ መርህ ለመስጠት የምንሄድበት ርቀት ቋሚ ብለን የያዝነውን እውነት ከማስካድ አይዛነፍም።ይህን ስል አንዲት የማህበራዊ ሚዲያ ቀልድ ትዝ አለችኝ። ቀልዷ የመርካቶን ምትሐተኛ ሌባን ተዓምራዊ ተግባር የምትገልጥ ሆና አግኝቻታለሁ። እነሆ ፦ ቻይና ናት አሉ ሌባን የሚይዝ ማሽን ሰራሁ ብላ ይፋ አደረገች። ያው አንድ ማሽን ሲፈበረክ ሙከራው የሚሞከረው በአይጦች አይደል። አሁን ግን አይጡ ራሱ ሌባው ነው። አለማችን ምን ያህል ሌባ እንዳላት ለማወቅ ማሽኑ በብዛት ሌባ ባላቸው ቦታዎች ዞሮ ዳታ መሰብሰብ ግድ ሆነ። እና ማሽኑ ጀርመን ሄደ 25% መዘገበ። አሜሪካ ሄደ 37% መዘገበ። ጣልያን ገባ 49% አለ። አፍሪካ መጣ ሊያውም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያም መርካቶ ገባ። መርካቶ ስንት ሌባ እንዳለ ከመናገሩ በፊት ማሽኑ ከነ ነብሱ ተሰረቀ!!

አንድ ልጨምርላችሁ።

ለምሳሌ እኔ በምንጅላቴ ዘመን በሬ ሲገዙ በግ ይመረቅላቸው ነበር። ብዬ የዛን ዘመን ደግነት ማጋነን ሲገባኝ በዚህ የኑሮ ውድነቱ በጠራራ ፀሀይ ብርድ ብርድ በሚያሰኝበት ፣ እንደታበደ ሁሉ ብቻ በሚያስወራበት ጊዜ ለፋሲካ በግ ገዝቼ ዶሮ ተመረቀልኝ ብል እዚህ አዳራሽ ውስጥ ያለ ሰው በሞላ ኮሌታዬን ጨምድዶ ይዞ ገቢያ ሜዳውን እንዳሳየው ሳያዳፋኝ የሚቀር አይመስለኝም።
ሆኖም ግን ይህ ይሁን እንጂ ይህ መፅሀፍ በብዙ ጥሩ ነገሮች የታጀበ ደንቅ ስራ ነው። ከነዚህም ውስጥ በለዛ የዛን ያህል ርቀት መሄዱ። በፈገግታ የተሰነዱ ውብ ተረኮች። ቀጣይነታቸው የማያጠራጥር የተዋበ ፍሰት። የገለፃ አቅሙም ከአንድ ስነፅሁፉ ላይ ከቆየ ጉምቱ ሰው የሚጠበቅ ድንቅ ስራ ነው። በጋራ የመኖር ባህል ውስጥ ሌብነት ክፉ ጠንክ እንደሆነ በስፋት ሲነገር እናደምጣለን። ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ ደግሞ ይህን ውሎ ቀልድ አልብሶ ከእምባችን ጀርባ ደማም ጥርሳችንን ሲጠራ እንመለከታለን። ልቦለድ ከማስተማርም ባለፈ ጥግ ደረጃ ጨዋታ መፍጠር መቻሉ ትልቅ ፀጋው ነው። ከቆየ የሀገራችን የነገስታት ታሪክ ውስጥ ልዩ አጫዋች ( ዚቀኛ ) የሚባሉ የኪነ ጥበብ ሰዎች መኖራቸው የሚታመን ቢሆንም በዚህም ነገራችን ሁሉ እንዳይሆን እንዳይሆን በሆነበት ጊዜ የሀዘን ሸክማችንን የሚያነሱልን የስነ ጥበብ ስራዎችና ሰዎች ሊኖሩን የግድ ነው።

ህመምን መኳል በራሱ ትልቅ ስነ ፅሁፋዊ ግብ ነውና!
ሌላው ቧልትን በተመለከተእጅግ አስደናቂ ቧልተኝነት በወሪሳ ውስጥ ነፍስ ዘርቶ ሲንቀሳቀስ እንመለከታለን። በአለም ፖለቲካ ውስጥ ረጅም ንግግር በማድረግ የሚታሙ ብዙ አሉ። አንዱ ስማቸው ያልተገለፀ አንድ የሩሲያ መሪ ሲሆኑ ሁለተኛው የሩሲያዊው መሪ የነብስ ጓደኛ የሆነው የኛው ጉድ መንጌ ነው። ቀልዱም በማዕከላዊ ኢላማነት ያነጣጠረው መንጌ ላይ ነበር። አንድ ስብሰባ ላይ ነው አሉ መንጌ ሆዬ ይሄንን ንግግር በስንት ዓመት አምሮት እንደተገኘ እንትን ካቀረቀረበት ቀና ሳይል ይነፋዋል። የተሰበሰበው ሁሉ ሰለቸ። ቀስ እያለ አንድ ሰው ሲወጣ ፤ ሁለት ሰው ሲወጣ ፤ ሶስት ሲል አራት ሲል አዳራሹ ባዶ ቀረ። ያኚ የሩሲያው ጓደኛቸው መቼስ ባለንጀርነት እዳ አይደል ሳይወዱ በግድ ቁጭ አሉ። መንጌ ይሄን ዲስኩር ይተፈትፈዋል። ቂጡን በሳንጃ ልቡን በቋንጃ አይነት ዝክንትል ወሬ ይዞ ጆሯቸውን አወላመጠው። ከአሁን አሁን ይጨርሳል ቢሉ ቢጠብቁ አሁንም እሱ ቂጡን በሳንጃ ልቡን በቋንጃ ላይ ነው። ታከታቸው። ምርር አሉ። ጠንከር ብለውም ጋሽ መንግስቱ አሉ። ቀና አለ ቆፍጣናው ማንም የለም። ወዳጃቸው ብቻ ቁልፍ ቢጤ ይዘዋል። አዳራሹን በአይኑ አስሶ ወደ እሳቸው ሲዞር « ሲጨርሱ ቆልፈው ይምጡ » ብለው የአዳራሹን ቁልፍ አስቀምጠው ወጡ።
መንጌን ለጨዋታ ካነሳን አይቀር ከወሪሳ ውስጥ በገፅ109-110 የገባችን ተረክ ብንመለከትስ?

“መንግሥቱ ኃይለማርያምን ያኳተነ(የሰረቀ) እኮ ነው" አለ

“ያኳተነ?"

« አዎ፣ ሰዓቱን ሰርቆታል! » መለሰ።

“የት?'' እንዲህ ያሉ ጨዋታዎች በእራሳቸው የሚያዝናኑ ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን ባለፉት ሁኔታዎች እየተዝናናሁ የነበረው በነፃነቴ እንደሆን ገብቶኛል፡፡ ይኸው ዛሬ ጭንቀት ሲቀርልኝ አፈልጋቸው ጀመር፡፡

“ፍል ውሃ፣ ማስፋፊያ ተደርጎለት ሲመረቅ መንግሥቱ እየተዘዋወረ ሲጎበኝ ልባሙ እስኪቀርበው ጠብቆ፡-
“የአምባ ልጅ ነኝ" ይለዋል"

"የአምባ ልጅ ነው እንዴ?'' ጠየቀ መንግስቱ

“አይደለም የአምባ ልጅ ጓደኛ አለው፡፡ ከሱ የሰማውን ይዞ 'አባታችን' ይለዋል፡፡ መንግሥቱ ደስ ብሎት ጠጋ ብሎ ያነጋግረዋል፡፡ ለካ መንግስቱ ፍል ውሃውን ሊጎበኝ ሲገባ ገላውን ታጥቦ ሰዓቱን ኮት ኪሱ ውስጥ አድርጎት ነበር፡፡ ልባሙ ሆዬ እያናገረ አኳተነው፡፡"

“ከዚያስ?”

“ከዚያማ መንግሥቱ የቤተ መንግሥት መግቢያ ወረቀት ሰጥቶት በቅርቡ መጥተህ እንነጋገራለን' አለው : : "

“ልባሙ ተቀብሎ ሽል' አለ፡፡ በነጋታው ምድረ አኳታኝ ይታፈስ ጀመረ፡፡ ስውር (ነጭ ለባሽ) ወሪሳን ባዶ አደረገው፡፡ ምንድነው ሲባል የመንግስቱ ሰዓት ጠፍቷል፡፡

“ልባሙ ይሄን ሲሰማ መንግሥቱ በሰጠው ወረቀት ቀጥታ ወደ ቤተመንግሥት ሄዶ ገባ፡፡ መንግስቱ ጋ ሲያቀርቡት 'አባታችን' አለው፡፡

“ልጄ' አለ መንግሥቱ፡ ልባሙ አቅፎት ከኋላ የተንጠለጠለ ኮት ኪሱ ውስጥ ሰዓቱን ከተተለት፡፡"

"እሺ"

“ምሳ ሰዓት ደርሶ ስለነበር መንግሥቱ ኮቱን ሲለብስ ከበደሙ እጁን ሲከት ሰዓቱ አለ፡፡ ስልክ አነሳና ወደ ህዝብ ደህንነት ደወለ፡፡

“ሃሎ ጓድ መንግሥቱ ነኝ' አለውና ሰዓቱን ስላገኘሁት ፍለጋውን አቁሙ አላቸው፡፡ ልባሙ ስልኩ ውስጥ ምን እንደተባለ አልሰማም ግን መንግሥቱ እየተገረመ

“ምን? አራት መቶ አርባ ሰባት ሰዎች ይዘን አራት መቶ አርባ አንዱ አምነዋል ነው የምትለኝ? በሉ ልቀቋቸው እናንተ ልጆች' ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡"

ከልቤ ሳቅሁ፡፡ ሳቄ ከልቤ ሲወጣ ደስ የሚል ስሜት እንደተካው ገብቶኛል፡፡ ምን እንደሆን ግን አላወኩም፡፡"

ከጠቀስናቸው ክፉም በጎም ጎኖቹ እንደተጠበቁ ሆነው የአንድን ሰው የቀን ውሎ የመባረክ አቅም ያለው ልቦለድ ነው። ታዲያ አንድ ደራሲ ከዚህ በላይ ምን ሊሰጠን ይችላል። እናመሰግናለን ማለት የአንባቢም የአባትም ነው። ህይወትን ምልዓት ሰጥቶ በተረት ውስጥ ማገማሸርም አንድ ሁነኛ ይዘት ነው። የወር ሰው ይበለን!

Reviewer :- © Sirak Wondemu is an associate editor at © Think Ethiopia

የዳሰሳ ርዕስ :- ዚቀኛው ወሪሳ ( የፈገግታ ፈለጎች )
የመጽሐፍ ርዕስ:- ወሪሳ
ደራሲ አለማየሁ:- ገላጋይ
የገፅ ብዛት:- 240 ገፅ፤ ሁለት ክፍልና 80 ንዑስ ክፍል
የህትመት ዓመት :- 2007
ዘውግ :- ልቦለድ
Rating ፦ 9.2

በሁለት ትንግርታም መንደሮች ማለትም ከወንዝ ወዲህ ማዶ ወሪሳ ከወንዝ ወዲያ ማዶ የአምጰርጵር ግዛት የሆነችውን እሪ በከንቱን ዋስ በማድረግ ልዩ ልዩ ገሀዳዊም ፈጠራዊም የህይወት መልኮችን ለመቃኘት የደፈረ መፅሀፍ ነው። መጽሐፉ የገሀዱን ዓለም በወከሉት ገፀ ባህሪያት አማካኝነት ጉርብትናን ፣ ልማዳዊ የጠባይ ግላጮችንና ሌላም ሌላም ነገሮችን በሰላ ብዕሩ ይዳስሳል። የእጅ አመል አዘቅት ሆኖ እስከአንገቱ ከዋጠው ወሪሳ አንስቶ የጠብ ፍቅር ተመን እስከሚታጣለት የአምጰርጱር መንደር እየተመላለሰ ማህበራዊ ትዝብቱን ፈገግታ በወለዳቸው የትረካ ስልቶች የሚያስቃኘን ነው። መጽሐፉ በአንደኛ ደረጃ የትረካ ስልት የተፃፈ ሲሆን ዋናውን ገፀ ባህሪ ነዋሪም ታዛቢም እያደረገ አንባቢውን ሲያስገርም ይታያል።

እንደመግቢያም እንደትውውቅም ከመፅሀፉ ገፅ 20-21 ጊዜን በማያሻማ መንገድ ጥቂት እንዝገን፦

« ቀጣዩ ገድል ከባልቴቷ ጋር ሲያወሩ የነበሩት አዛውንት ነው።
የተጠፈጠፈ ቆርኪ የሚመስሉት አዛውንት መሳፈሪያ እንኳን ሳይኖራቸው መርካቶ መሀል ሲንጠራወዙ ነው አሉ። አንድ ባላገር ቢጤ ይመጡና እኚያውን ሽማግሌ « አባቴ » ይሏቸዋል።

« ጌትዬ » ይላሉ በእሳቸው ዘዬ
ይሄ የእድር እቃ የሚሸጥበት የት ነው?
የድግስ ማለትዎ ነው?
አይ እድራችን የደረጀ የነበረ ነው። ዛዲያ እቃው ሁሉ በእድሜ ብዛት ነኩቶ አለቆብነ እሱን ለማስተካከል ነበር።
ኮርፖሌሽን ነዋ
የት ነው እሱ ደግሞ ?
እኔም ወደዚያው ነኝ። የድግስ እቃ ለመግዛት።
እንዋብ እንግዲህ
ይዘዋቸው የሄዱት ወደ አማኑኤል የአእምሮ ህሙማን ሆስፒታል ነበር። ካርድ የሚያወጡ ሰዎች ተሰልፈዋል።
« ይሄ ነው» አላቸው
« ድንቅ » አሉ
በሉ እንሰለፍ ለመሆኑ የቀበሌ መታወቂያ አለዎት?
የገበሬ ማህበር ነው።አይ የእርሶ ነገር ይሄ ለአዲስ አበባ ነዋሪ በቅናሽ የሚሸጥበት ቦታ ነው። ምን በጀኝ ይላሉ ዛዲያ
አይ በሉ ከእኔ ጋ አዳብዬ እመዘግብዎታለሁ። እዛች ይቆዩኝ። ምን ምን እንደሚፈልጉ ይንገሩኝማ። ነገሯቸው። ሦስት ብረት ድስት ...ሁለት ትሪ ... አምስት ጎድጓዳ ሰሀን።አርባ ኩባያ...
ንሱ ብሩን ይስጡኝማ አሉ። ሰጧቸው። ተቀበሉ። ባላገሩ ጥቂት ራቅ ብለው እንዲጠብቁ ነግረዋቸው አጭበርባሪው ብዙ ነው።ተማንም አያውሩ አዳፋ የለበሰ ሲያዩ ያጀበጅባሉ። »

ድንቅ

ወረፋው ደርሶ የመታከሚያ ካርዳቸውን በመታወቂያ አውጥተውላቸው ተመለሱ።ባላገሩን ጠርተው

«ንሱ ይሄንን ካርድ ይያዙና ነገ ጠዋት አስራ አንድ ሰዓት ላይ በከፈልነው መሰረት ዕቃችንን ተረክበን እብስ ነው። »
ወላዲቷ ከጭንቅ ለጭንቅዎ ትድረስልዎ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ።እግረ መንገዴን እንጂ ለእርስዎ ብዬ አልወጣሁ አልወረድኩ።ይልቅስ ነገ እዚህችው ይምጡማ። ተለያዩ። አዛውንቱ የወሬውን መጨረሻ እንዲያጠና አንድ የወሪሳ ወጣት ወደ አማኑኤል ሆስፒታል ላኩ። ባላገሩ አዛውንቱን ፈልገው ስላጡ የታካሚዎች ወረፋ ጠብቀው ገቡ። ካርዳቸው ታይቶ ለቃለ መጠየቅ ቀረቡ።
ለምን መጡ » ሀኪሙ ጠየቀ።

ከቴም ሳታውቁ ቀርታችሁ ነው? ይልቅስ ንሱ ስጡኝና ልሂድ። ሦስት ብረት ድስት..ሁለት ትሪ.. አምስት ጎድጓዳ ሰሀን፣ አርባ... »
ሀኪሙከኋላቸው የቆሙትን ነርሶች ጠቅሶ አስያዛቸው።የፊጥኝ ታስረው መርፌ ተወጉ። ወደ ህክምና... » ተሳቀ።» ይላል።
እጦት ያደቆነው መንደር በእጅ አመል ሲታመስ የምናይበት ዓለም ነው ወሪሳ!! በሰፈራ ታሪካቸው አይስማሙም። ባልቴቷ ወይዘሮ ጉዶ ታሪካችን የሚጀምረው በአጤ ምሊኒክ ዘመን ነው ስትል ሽማግሌው ሰው ደግሞ የለም የለም በአጤ ቴዎድሮስ ነው ይላል። የወይዘሮ የጉዶን መላምት ይዘን እንዝለቅ..!
መስራቹ አባ ወሪሳ ሀገር ያወቀው ሌባ የሚቀናበት ሌባ ነው።
ይህን ያዩት አጤ ምኒልክ « ተው አትረብሽኝ » አሉት። « ኤዲያ ደግሞ ወንድ ካልሰረቀ» አለ። ሁለቱ ተፋጠጡ እልቂት ከመምጣቱ በፊት ግን ጣልያን ጦሩን ወደ ኢትዮጵያ አዝምቶ ሊወረን መሀላቸው ገባ። ሀገር ካልተረጋጋ ሌብነት ስራ አይሆንም ብለው አባ ወሪሳ ጀሌዎቻቸውን አስከትለው በሙያቸው (በእጅ አመላቸው ) ኢትዮጵያን ለመጥቀም ጣሊያንን ለመዘየር ወረዱ።
አባ ወሪሳ አጤ ሚኒሊክን ከተከተሉ በኋላ ጣሊያኖች ግራ ተጋቡ። አስማት በሆነ ሁኔታ ወደቀኝ ለቅፅበት ሲዞሩ የነበረው ዕቃ ሁሉ ወዲያው ወደግራ ሲዞሩ የለም። ጉድ አሉ። ሀበሾች በጥንቁልና በሉን አይነት መገረም። ኋላ አባ ወሪሳ በእጅ አመላቸው ያደከሙትን ጣሊያን አጤ ምሊኒክ በጦር ገብተው አደባዪዋቸው። ከድሉ በኋላ አባ ወሪሳ ጀሌዎቻቸውን አስከትለው አንድቦታ ሰፈሩ። ይኸው አባ ወሪሳ ከሞቱም ከስንት ዘመን በኋላ ትውልዶቻቸው ይህንኑ ባህላቸውን ተግተው እንዳስቀጠሉት ነው።የሽማግሌውን ደግሞ እናንተ አንብቡት!

ተራኪያችን አማረኛ መምህር ሲሆን ፊት በአርሲ ነገሌ ኩየራ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማስተማር ቆይቶ በዝውውር ወደ አዲስ አበባ የመጣ ተንከራታች ነው። እንደአጋጣሚ ሆኖ ወሪሳ ሰፈር ገባ። አገባቡስ የወንድሙን ልጅ ፈለግ ተከትሎ እንጂ እንዲሁ በእጣ አይደለም። ተራኪያችን ተረት ወዳድ ክስተት አፍቃሪ ነው። እያንዳንዷን እርምጃ አስሮ የፈታው ተረት ውስጥ ነው። ተረት ስል ደራሲው አለማየሁ ገላጋይ በአንድ የስነ ፅሁፍ ውጤት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ተደርጎ የሚታየውን የሚት ፈጠራ ( አፈታሪክ ስነዳን ) በዚህ መፅሀፍ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ መፍጠር እንደቻለ ይሰማኛል። ምንም ከሆነ ባዶ የትረካ ጅምር በመነሳት አንድ ልቦለድ ሊሸከም የሚችለውን ፍሰታዊ የትረካ እግር ፣ ራሱን የሆነ ማህበረሰባዊ ቅርፅ ግንባታ ፣ ስነ ልቦናዊ ፍተሻዎችና መሰል ኪናዊ ውጤቶች በሰመረ ሁኔታ እንዲያሳካለት እንደረዳው እንመለከታለን። ይህ ማለት ምንድነው በልቦለዱ ውስጥ ሊሆኑ የገሀዱን አለም ሊመስሉ ይችላሉ ብሎ በገመተባቸው ስፍራዎች ሁሉ አዲስ ፈጠራዊ መነሻ ታሪኮችን አቁሟል። ይሄ ሰውዬ ፈጥሮ ያወራል እንደሚባለው አይነት ፈጥሮ የመሰነድ ትልቅ ብቃቱን በዚህ ዘመነኛ ስራው ላይ አሳይቷል።

እንደቅሬታና ጥቅል የመፅሀፉ ደካማ ጎን ወሪሳ በትንሽው ቢሆን ያጋባን የእጦት ህመም የለም የሚል ስሜት ይሰማኛል። በርግጥ እያንዳንዱን መልኮች ስንገለብጥ እንደመርግ የሚጫኑ ራሱም ደራሲው በመግቢያው ላይ « እንደእየሱስ በወንበዴዎች መካከል ተቸንክሬያለሁ » ቢልም። በህይወት ክረምቱ ውስጥ እንድንታዘብ የሚፈልገውን በር በልኩ ከፍቶ አሳይቶናል የሚል ግምት የለኝም። ለምን ቢሉ እያንዳንዷ በተራኪያችን ውሎ ውስጥ የምትከሰት ክስተትን በቸልታ መቀበል ይሁን በሚል ስንፍና መደምደም አይነት ተደጋጋሚ ውዴታዎች ይታዩበት ነበር። ይህ ደግሞ ምክኒያታዊነቱ ላይ ጥያቄ የሚያስነሱ ነጥቦችን ይጎትታል። ለምሳሌ የአንድ ጋቭሮቫዊ ገጠመኝን ለዚህ ምሳሌነት እንጠቀም።

እኛ ግን ማነን?

__ 👁 _

ከክርስቶስ ልደት አንድ ሺህ ዓመት በፊት (በአንድ ሺህ ዓመተ ዓለም ገደማ) በድንጋይ ላይ እንደተቀረፀ የሚታመን የእኛን በጣም ለግዕዝ የቀረበ የኋለኛ ሳባ ሆሄያት የያዘ የሰው ፊት ቅርፅ። በደቡብ አረቢያ የተገኘ።

ይህ ስለ እኛ ታሪክ ምን ይነግረናል?

የ3ሺህ ዓመት ታሪክ አለን የምንለው (አንዳንዶች ቀልድ የሚመስላቸው እንደሚያስቡት) ዝም ብሎ በዘፈቀደ የመጣ ነው?

እኛ ግን ማነን? ምን ነበርን? ደቡብ አረቢያ (የመን ሰላጤ) እና ሳዑዲአረቢያ ድረስ ምን ወሰደን? ሳዑዲን የመሠረቱት እና የቀድሞ መጠሪያዋን የሰጧት "አስር ህዝቦች" (Asir people) ማን ናቸው?

እኛ እውን ከየት የመጣን ነን? ወይስ የት ድረስ የተስፋፋን ነበርን? ምን ገጠመን? ለምን አነስን? ከዓለም ጋር የተሰፋ ታሪካችንስ እንዴት ጠፋ?

በዚያ ዘመን (ከሶስት ሺህ ዓመት በፊት) በረቂቅ ቅርፆች ይጫወቱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን የት ገቡ? እኛ ኢትዮጵያውያን በዓይን ላይ እና በክቦች ላይ ያለን ጥበባዊ መነደፍ ምን ይሆን ምንጩ?

ተመሣሣይ ሆሄያትን፣ ቅርፆችንና የሆነን መልዕክት ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ አጥብቆ የሚፈልግ መንፈስን አጥብቀው የያዙ የአክሱምና የዳማት፣ የአቡነ የማታ፣ የላሊበላ፣ የጢያና የሌሎችንም ጥንታዊ ጥበባዊ ቅርፆች በደቡብ አረቢያና በግብፅ ምድር፣ በሌሎች የአፍሪካ ምድሮችም ከተገኙ መሠል የጥበብ አሻራዎች ጋር አስተያይተን፣ መዝነን፣ አጥንተን መገኘት ብንችል... ስለራሳችን የሚነግረን ብዙ ነገር አይኖር ይሆን?

ማነው ግን እንዲህ ዓይነቱን ጥናት የሚሠራልን? ተቋም አለን ለመሆኑ? በሀገራችን ቅርሶችና ታሪኮች ላይ የሚያጠና? ለታሪካችን ባዳ፣ ለገዛ ሀገራችን እንግዳ፣ ለማንነታችን ባይተዋር ሆነን በአጭር ተመልካች ትርክቶች እየዳኽን የምንቀጥለው እስከመቼ ይሆን?

የትኛው ትውልድ፣ እና መቼስ ይሆን የራሱን ትልቅ ኢትዮጵያዊ ማንነት ይዞ ራሱን ፍለጋ የሚነሳው?

ግን እኛ ማን ነን?

አንድ ቀን እውነተኛ ማንነቱን የፈለገ፣ ያገኘ፣ እና የተጎናፀፈው ትውልድ ይኖረናል! ብዬ አምናለሁ!

አንድ ቀን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያችንን ይባርክ🙏🏿

መልካም ጊዜ!

© Assaf Hailu

ስለ አዳም መጽሃፍት "ከየትኛው ልጀምር" ለሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ
(ትንሽ መግቢያ) - ለመጽሃፍ ቀን!?!

ይሄ ጉዳይ የብዙ ሰወች ጥያቄ ስለሆነ ማመላከቻ ማዘጋጄት ሳይጠቅም አይቀርም፥፥ ለጊዜው ግን በጣም ጠቃሚ ያልኩትን ልዘርዝር ባጭሩ፥፥[My personal brief view(unedited draft)]

የአዳም የአጻጻፍ ስልት ከሌሎች የሚለይባቼው የራሱ ስልት አለው፥፥ስሙ ህጽናዊነት(Inter-connectivity) ይባላል፥፥ አዳም በአካዳሚክ ህይወቱ ጆግራፊን በከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያጠና እና የሰራ ሰው ነው፥፥ ይሄ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ ብዙ የተለያዮ ነገሮችን በአንድ ወይም ብዙ ቦታ ላይ አስቀምጦ ትርጉም የመስጠት መረጃ የመስጠት አቅም አለው፥፥ አሁን አለም ላይ ብዙ እየሆኑ ያሉ ዲሰራፕቲቭ ቴክኖሎጂወች በሙሉ ማለት ይቻላል ያለጆግራፌ እውቀት ምንም ናቼው፥፥ አዳም Symbolic representative የአጻጻፍ ስልትም አለው ፥፥

ብዙ ነገሩን ከጤፍ እና እንጄራ ጋር ሲምቦሊክ ሪፕረዘንቴሽን አሉት፥፥ አዳም ድርሰቶቹ እንጀራ ወጡ ገፀባህርያት፣የተለያዮ ኩነቶች፣ ገጠመኞች፣ ሌሎች ብዙ መነሸጦች ወይም ሞቲቮች እንደሆኑ በቃለ ምልልሱቹ ይነግረናል፥፥ያደርጋል፥፥

የአዳምን መጽሃፍ ከየት ልጄምር ሳይሆን በደንብ ሊያጣጥመው የፈለገ ሰው የሚከተለውን ቀድሞ ቢዘጋጅ መልካም ይመስለኛል፥፥

1/፩- Multidisciplinary reading(በይነ ዲሲፕሊን የአነባብ ዘዴ) በረዳት ፕሮፌሰር ቴድሮስ ገብሬ፣

2/፪- የኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ በፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ፣ [የኢትዮጵያን የሶስት ሽህ ዘመን ታሪክ አውትላይን(አክሱም፣ክርስትና፣እስልምና፣ዮዲት፣ዛጉየ፣ሰለሞኒክ ዳይናስቲ፣ኢማም አህመድ ኢብን፣የኦሮሞ ኤክስፓንሺን፣ዘመነ መሳፍንት፣የዘመናዊት ኢትዮጵያ አጼወች፣የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነቶች እና አንኳር ነገሮች አብሮ ማወቅ፥፥ መሰረታዊ የግሪክ ሚቲዮሎጂወቺን ማወቅ ጠቃሚ ነው፥፥

3/፫- የኢትዮጵያ ማህበረሰባዊ ታሪክ በፕሮፌሰር ፓንክረስት (የዶክተር የራስ ወርቅንም ስራወች እያቼው)፣

4/፬- ሙዚቃወች (በሀምሳወቹ፣በስልሳወቹ፣በሰባወቹ፣ሰማኒያወቹ ምርጥ የሚባሉ የሀገር እና የውጭ ሙዚቃወችን መስማት፣ [Consider them like ማጣፈጫ]

5/፭- Psycho-Analysis, Psychology, Philosophy መፈተሽ እና ማንበብ፣

6/፮- የስነ ስዕል፣ስነግጥም፣ቅርጽ፣እና የቀልም ቢያንስ መሰረታዊ እውቀት መጨመር፣

7/፰- በጣሊያን ወረራ ወቅት፣ጣሊያን ከወጣ በሗላ ያሉ ኩነቶችን ማወቅ (ፍቅር እስከ መቃብርን አላነበብኩም የሚል የለም ብየ ነው መቼም 🙂 )፣በሃይለስላሴ፣በ53 አመተ ምህረት መፈንቅለ መንግስት፣በ66 ዘመን በፊት የነበሩ የአይዲዮሎጂ ግርግሮች፣የአብዮት አካባቢ፣የደርግ ስርዕት ዘመን፣የኢህአዴግ መምጣት እና የብሄር ፓለቲካ ቢያንስ መረጃን ማወቅ ይገባል፥፥በወቅቱ የተጻፏትን ማንበብ፥፥[እነዚህን በተመለከተ የአዲስ አበባ Printing Press ያሉ መጽሃፍትን ጥሩ ናቼው፥፥ ቢያንስ ከBias በንጽጽር ነጻ ስለሆኑ በምሁራንም ታይተው ስለሚወጡ በየዘመኑ የተጻፏትን በጥቂቱ ማንበብ ተገቢ ነው፥፥

8/፰- አዳም የጽሁፍ ስራወቹን ለማስረዳት ቃለ ምልልስ አድርጓል፥፥ በተለይ ከረዢም ጊዜ በፊት ለአዲስ ነገር ጋዜጣ በጥልቀት መልስ ሰጥቶ ያውቃል፥፥ኢንተርኔት ላይ አይቼዋለሁ በቅርብ (I put it at the end) ፥፥ፈልጎ ማንበብ መልካም ነው፥፥እስከዚያው በዮቱዮብ ያሉትን ቃለ ምልልሶች መስማት ጥሩ ነው፥፥

9/፱ የአዳም ረታ fan pageጆች አሉ ፌስቡክ ላይ፥፥ እነሱን አባል መሆን እና መማማር፥፥37ሽህ ሰው አባል የሆኑበት Public Group አለ (Adam Reta) ብዙ ቀለል ያሉ ሀሳቦች ይንሸረሸራሉ፥፥ አባል መሆን እና መማማር፥፥(I put it at the end)

10/፲ የአዳም ጽሁፍ በጥንቃቄ የሚቀመሩ ናቼው፥፥ ባዮሎጂም፣ኬሚስትሪም፣ምህንድስናም፣ሂሳብም፣ፊሲክስም፣ሳይኮሎጂም፣ፍልስፍናም፣ጥበብም አብረው ይዋሃዱበታል፥፥ ለዚህ ነው "በይነ ዲሲፕሊናዊ" ዝግጂትም አነባበብ የሚፈልጉት(ከሁለት አይን እይታ በላይ ነገሮችን ለመፍተሽ መሞከር እንደማለት ነው)፥፥

እነዚህን ያላደረገ ሰው ወይ ጄምሮ ይተወዋል፣ወይ ጨርሶ ሌላ ስራውን አያይም፣ወይም ሳይገባኝ ጨረስኩ ብሎ ይነጫነጫል፣ወይ ደግሞ በትንሹ ይሆናል ሀሳቡን መረዳቱ፣ወይ ደግሞ ሲያስበው ሲያስበው ደክሞት ገና ሳይጄምረውም ሳያውቀውም ሳይሞክረውም ይተወዋል፣ወይ ሳይገባውም ሊወደው ይቺላል (ይሄ መብት ነው ፍቅር🙂ፍቅር አይጠላም )፥፥

ከላይ የተዘረዘሩትን ካደረጉ በሗላ ያለምንምን ቅደም ተከተል ብፌ እንደማንሳት ነው ከተፈለገ የአዳም ደርዘን ስራወች መርጦ መጄመር ነው፥፥ [የአዳምን ስራወች ከልብ ማጣጣም ከፈለግሽ መንገዱ ቢያንስ መጄመሪያው ይሄ ነው፥፥ አይ Short-cut ካሉ ግን በጸሃፊው እና ተከታዮቹ ሌላ መንገድ ይፈለጋል ብየ እጠብቃለሁ ወደፊት፥፥]

[በነገራቺን ላይ ይሄ የጠቀስኩት ቀለል ያለ መንገድ ነው እንጂ ስራወቹን የሚያመሳጥሩ፣የሚተነትኑ፣የሚያስተነትኑ፣ ሰም እና ወርቅ የሚያወጡ፣ብዙ በአዳም ስራወች ዘርፍ ከፍ ያሉ ሰወች አሉ፥፥ከእነሱም ምክር ቢጤ መውሰድ ይቻላል፥፥ለምሳሌም መድህን፣ተሻለ፣ጸዳለ፣ሙሉጌታ፣ኡሙ....... የሚባሉት ከብዙወቹ ጥቂት ምርጦቹ ናቼው፥፥]

====የሚከተሉትን ጥሩ መጄመሪያ ውይይቶች ናቼው፥፥====

መልካም ንባብ፥፥

© Yonas Solomon

ደስታን ያለቦታው አትፈልግ!
(Never looking happiness in the wrong place)
(እ.ብ.ይ.)

ብዙዎቻችን የምንፈልገውን ነገር ያለቦታው ነው የምንፈልገው፡፡ ትክክለኛውን ነገርም ይሁን ሰው በተሳሳተ ቦታ ውስጥ ማግኘት አይቻልም፡፡ በተንጋደደ አመለካከት የቀና ሃሳብ መፍጠር የሚቻል አይደለም፡፡ ይልቁንስ የተንጋደደውን አመለካከት በማጥናት፣ በመተንተንና በመመርመር የተንሻፈፈውን ሃሳብ ማስተካከል ይቻላል፡፡ ትክክሉ በትክክለኛው ቦታ ነው የሚገኘው፡፡ ጥያቄው ያለው ትክክሉ ምንድነው፤ ቦታውስ የት ነው የሚለው ነው፡፡ ሰው ይሄን ካወቀና መርምሮ ከደረሰበት የሚፈልገውን ነገር በተሳሳተ ቦታ በመፈለግ እድሜውን አይፈጅም፡፡ ወደትክክለኛው ቦታ በቀጥታ ይሄዳል፡፡

አዎ አብዛኛውን ጊዜ ፍቅርን የምንፈልገው ፍቅር የሌለበት ቦታ ነው፡፡ ትክክለኛውን ደስታ ለማግኘት የምንዳክረው ጊዜያዊ ደስታ በሚነገድበት ገበያ ውስጥ ነው፡፡ የዚህ ዘመን ንግድ ቋሚውን ደስታ ሸጦ ጊዜያዊው ደስታ የሚሸመትበት ነው፡፡ ግብይቱ ለነቃበት ጤናን ሸቅጦ በሽታን እንደመግዛት ያለ ነው፡፡ አብዛኞቻችን ጨርቃችንን ጥለን የምናብድለት ነገር የእውነት የሚያስደስተን አይደለም፡፡ የማይጠቅመንን ነው ደጅ የምንጠናው፡፡ የማይፈልጉንን ነው የምንፈልገው፡፡ ቋሚ ደስታ የማይሰጡንን ነው የምናሳድደው፡፡ የምንወደውንና የምናፈቅረውን ጠንቅቀን አናውቅም፡፡ የማንተማመንበት ነገር ላይ እምነታችንን እንጥላለን፡፡ ለአደራ ብቁ ያልሆነ ሰው ላይ አደራችንን እንጭንበታለን፡፡ የምንወደው በስሜት ነው፡፡ የምንታዘዘው ህሊናችንን አይደለም፡፡ አስበን አንወድም፤ መርምረን አንደሰትም፡፡ አዕምሯችንን ቅር እያለው፤ ህሊናችን ሳያምንበት ልባችንን አሳልፈን እንሰጣለን፡፡ ለአልፎ-ሂያጁ ደስታ ብለን ቋሚውን ደስታ መስዋዕት እናደርገለን፡፡ በደቂቃዎች ለሚረክስ ደስታ (Pleasure) በጤና የመኖርን ዘላቂ ደስታ (Happiness) እናጣለን፡፡ ‹‹ውሃን ከቀለብ፤ ጤናን ከገንዘብ የቆጠረው የለም›› እንዲል ብሂሉ፡፡

ብዙ ሰዎች እውነተኛ ደስታን (Happiness) ከጊዚያዊ ደስታ (Pleasure) ጋር ቀላቅለው ነው የሚያስቡት፡፡ በርግጥ ሁለቱም ስሜታቸው ይመሳሰላል፤ ነገር ግን በተግባር ለየቅል ናቸው፡፡ የሆነው ሆኖ በሁለቱ ስሜቶች ምክንያት ሰዎች ከጤንነታቸው እየተናጠቡ ከሰውነታቸው እያፈነገጡ ይገኛሉ፡፡ ሱስና ጭንቀት (Addiction and Depression) በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የነሱ ውጤቶች ናቸው፡፡ ሱስ የበዛ ጊዜያዊ ደስታን ከመፈለግ የሚመጣ ነው (Addiction – from too much pleasure )፤ ጭንቀት ደግሞ በቂ ደስታ በማጣት የሚከሰት ነው (Depression – from not enough happiness)፡፡ የስነ አዕምሮ ተመራማሪዎች እንደሚናገሩት ጊዜያዊ ደስታና ቋሚ ደስታ (Pleasure and Happiness) ዶፓሚን እና ሴሮቶኒን (Dopamine & Serotonin) ከተባሉ የስሜት አስተላላፊዎች (Neurotransmitter) ይመነጫሉ፡፡ ዶፓሚን (Dopamine) ጊዚያዊ ደስታን ሲሰጥ ሴሮቶኒን (Serotonin) ደግሞ ዘላቂ ደስታን ያመነጫል፡፡

አየርላንዳዊው ሰዓሊ ጆን በትለር ዪትስ (John Buttler Yeats)፡- ‹‹እውነተኛ ደስታ በጎነት ወይም ጊዜያዊ ፍንደቃ አይደለም፡፡ ደስታ ይሄ ነው ያ ነው አይባልም፡፡ እውነተኛ ደስታ እድገት ነው፡፡ ስናድግ ደስተኛ እንሆናለን፡፡ (Happiness is neither virtue nor pleasure nor this thing nor that, it is simply growth. We are happy when we are growing)›› ይለናል፡፡ ሰውየው የእውነተኛ ደስታ ምንጭ እድገት ነው ማለቱ ነው፡፡ እሱ እድገት የሚለው ቁሳዊ እድገትን አይደለም፡፡ ለእሱ እድገት ማለት መንፈሳዊና አዕምሯዊ እድገት ነው፡፡ እውነተኛ ደስታ ቁስ በማግበስበስ፤ ሀብት በማከማቸት፤ አስረሽ ምቺው በማብዛት አይገኝም፡፡ ደስታ ውስጣዊ ለውጥ ነው፡፡ ደስታ መንፈሳዊ እድገት ነው፡፡ ትላልቆቹ የዓለማችን የቢዝነስ ተቋማት ዓለሙን የሚሰብኩት ቁሳዊ እድገትን ነው፡፡ የሚፈበርኩት ቴክኖሎጂ መንፈሳዊ እድገትን የሚያበረታታ ሳይሆን ቁሳዊ ፉክክርን የሚያከርር ነው፡፡ ሕብረተሰቡ በየጊዜው ሕሊናውን የሚጋርድ፤ ልቡን የሚያጠፋ፤ አምሮቱን የሚያበዛ የእንቁልልጭ ማስታወቂያ ነው የሚለቀቅበት፡፡ ሶሻል ሚዲያው ሰውን ራሱን ዘንግቶ ሌሎችን ተከታይ ባሪያ እያደረገው ነው፡፡ ዙሪያችንን የከበበን ልቦናችንን የሚሰልብ፤ የማሰብ ሃይላችንን የሚያዳክም፤ ትኩረታችንን የሚቀማ ነው፡፡ ያላወቁ አለቁ ነውና በጊዜ ካልነቃን እናልቃለን፡፡

ወዳጄ ሆይ.... ፀጋዬ ገ/መድህን በማራኪ ስንኞቹ፡-

‹‹የማይነጋ ህልም ሳልም፣
የማይድን በሽታ ሳክም፣
የማያድግ ችግኝ ሣርም፣
የሰው ሕይወት ስከረክም፣
እኔ ለእኔ ኖሬ አላውቅም፡፡››

እንዳለው በማይመለከትህና በማይጠቅመህ ጉዳይ ውድ የህይወት ጊዜህን አታባክን፡፡ የሚገኝ ነገር ፈልግ፣ የሚነጋ ህልም አልም፤ የሚድን ቁስል አክም፤ የራስህን አረም ንቀል፤ እስቲ ለዋናው ራስህ መኖር ጀምር፡፡ ትክክሉን ነገር በተሳሳተ መንገድና ቦታ ለማግኘት አትድከም፡፡ ምናልባት የተሳሳተ ቦታ ከተገኘህ ስህተቱን አጥንቶ ለመለወጥ እንጂ ትክክሉን አገኛለሁ ብለህ አይሁን፡፡ ለጊዚያዊ ፍንደቃ ብለህ ቋሚውን ደስታህን አታስነጥቅ፡፡ ጤናህን ሸጠህ የህይወት ዘመን በሽታ አትሸምት፡፡ ደስታ ቢስ የምትሆነው የአዕምሮ ሰላም ስታጣ ነው፡፡ የአዕምሮ ሠላም ማጣት ገንዘብህንና አካልህን ከማጣት በላይ ነውና፡፡

ቸር ጊዜ!

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ፡

____
© እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
እሁድ ሕዳር ፳፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.

የተከፈለበት ማስታወቂያ!

ቶክን ሰፕላዩ ትንሽ ነው። ወደ ፊት ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያወጣ በብዙዎች ተገምቷል። ሊስቲንግ ፕራይሱ ከ0.05-0.1 ተተንቢዋል። እና ደስ የሚለው ደግሞ ሊስቲንጉ ለአንድ ወር ተራዝሟል።

👇👇

t.me/seed_coin_bot/app?startapp=1067310339

ባህራም ፈጠን፣ ፈጠን ብሎ እየተራመደ፣ ተካ ላይ ደረሰበት። ተካ ሁለቴ ቡጢ ቢሰነዝርበትም ፣ ባህራም ጎንበስ ብሎ አሳለፈው። እሱ ደግሞ በተራው፣ የተካን ጭንቅላት ከዛፍ ጋር አጋጨው ፤ ነፍሱ እስኪወጣ ደበደበው። ተካ በዚህ ድብደባ ሁለት የፊት ጥርሶቹን አጣ።ኒኮል እያለቀሰች ባትለምነው ሊገድለው ይችል ነበር። ከሁለት ሳምንት በኋላ ፣ ተካ የሰው ሰራሽ ጥርስ አስተከለ።

ጃምሺድና ልዑልሰገድ ደግሞ አሉ፤ ሁለቱም የኒኮል ውሽማዎች ናቸው። አብረው ቁማር ይጫወታሉ። ነገር ግን ጃምሺድ ፣ ልዑልሰገድ ከኒኮል ጋር መተኛቱን እንዲያቆም ጭንቅላቱ ላይ ሽጉጥ ደግኖ አስጠነቀቀው። ልኡልሰገድ ግን ይህንን ከቁብም ሳይቆጥር ቀጥታ ኒኮል ጋር ይሄድና ይተኛታል። ተመልሶ ጃምሺድ ጋር ይሄድና ይህንኑ ሲነግረው፦

" በጣም ወንድ ነህ" አለው። ነገር ግን ቀኑ አልደረሰምና የንዴት ሳቅ ስቆ አሳለፈው።

ለተወሰነ ግዜ ህይወት እንዲህ ቀጠለ። ጃምሺድ ከኒኮል ቀጥሎ የሚወደው ነገር ቢኖር ቁማር ነው። ደግሞ የሃብታም ልጅ ነው። ብሩን በየካዚኖው እየዞረ ይበትናል። ልዑልሰገድን ና ላዝናናህ ብሎ ሌላ ከተማ ይወስደዋል―እንደ ልብ ቆመሩ፣እንደ አሳ ጠጡ። በመጨረሻ ጃምሺድ በሁለቱም ራስ ቅል ውስጥ አንድ አንድ ጥይት አስቀመጠ።ከወራት በኋላ ፣ ጃምሺድ ቃሉን ጠብቆ የሉልሰገድና የራሱን ህይወት አጠፋ።

እቺ ከላይ ስትታይ የማትማርከው ኒኮል፣ የስንቱን ህይወት አመሳቀለች።

🤖🤖🤖

ትኩሳት የስብሃት ገብረእግዚአብሔር መፅሀፍ ነው።

አንዲት ገፀባህርይ አለች። ፈረንሳዊት ናት። ሲልቪ ትባላለች። ስብሃት ከጓደኛው ተመስገን ነጥቆ ጠበሳት። አንድ ቀን ወይን ቀማምሰው በስካር መንፈስ ሆና እንዲህ ትለዋለች፦

"ሴት አማልክት ናት። ለምሳሌ ያንን ጎረምሳ ተመልከት።
ፀጉራማ ደረቱን ተመልከት። ፈርጣማ ክንዶቹን ተመልከት
ለየትኛው አምላክ ነው የሚታዘዘው?! እኔ ግን በጥቅሻ ብቻ እጠራዋለሁ። ከኮሎኝ የበለጠ የተፈጥሮ መአዛው የኔ ነው። ጡንቻማ ሰውነቱ የኔ ነው። ለደስታዬ ላቡን ያፈሳል። እዚህ አለም ላይ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ሁሉ የኔ ናቸው። ቤቱን፣ ገንዘቡን፣ መኪናውን፣ ህንፃውን ማለቴ አይደለም። ይሄ ወንዳወንድ ጎረምሳ የኔ ነው። ውብ እና ዋጋ ያላቸው ነገሮች ሁሉ የኔ ናቸው። ታዲያስ ሴት አማልክት አይደለችም?"

🤖🤖🤖

አማንዳ

አማንዳ ወፍራም ናት። ድብልብል ፊት፣ ድብልብል ከንፈር፣ ድብልብል ሰውነት ያላት። ውብ ወርቃማ ፀጉሯን እና ሰማያዊ አይኖቿን ስብ ውጦት ፣ መልኳ ጠፍቷል።

ልዑልሰገድ ለመጀመሪያ ግዜ የተዋወቃት አንድ ፓርቲ ላይ ነው። ፓርቲው ላይ ሳይያዙ የቀሩት ሁለት ሴቶች ብቻ ናቸው። አንዲት ደቃቃ ሩቅ ምስራቃዊት እና አማንዳ። ሩቅ ምስራቃዊቷ በጣም ታምራለች፤ ነገር ግን ተመስገን አልጋ ውስጥ ትሞትብኛለች ብሎ ስለፈራ፣ አማንዳን አቅፎ ሄደ።

ከዚያ በኋላ አማንዳ እና ልዑልሰገድ አብረው በየቦታው መታየት ጀመሩ። ጓደኛሞቹ(ስብሀት፣ ባህራም፣ ተካ፣ ልኡልሰገድ ፣ ተመስገን) ቁጭ ባሉበት፣ አማንዳ እየተድበለበለች ትመጣለች ። ይኼኔ ተካ ልኡልሰገድን " በል፣ ይኼንን ሄደህ አንደባል" ይለዋል። ልኡልሰገድ በጣም እየተበሳጨ " ይኼን ተካ ግን አንድ ቀን እገለዋለሁ !" ይላቸዋል ለሌሎቹ።

ልኡልሰገድ ከሄደ በኋላ፣ ከአማንዳ ጋር እስከአሁን አብረው የቆዩበትን ሚስጥር እየገመቱ ይሳሳቃሉ።

" ልኡልሰገድ ድሮ የሚስዮን ተማሪ ነበር። ሚስዮኖች ደግሞ ግብረገብ ያስተምራሉ። ለዛ ይሆን?!" ይላል ስብሀት በበኩሉ ለራሱ።

ታዲያ ስብሀትና ልኡልሰገድ በጋራ የሚማሩት ኮርስ ነበራቸው። ስብሀት ልኡልሰገድን ፈልጎ ቤቱ ሲሄድ ብዙ ግዜ አማንዳን ያገኛታል። ሲያወሩ ለካ አማንዳ ከሰባው ሰውነቷ ስር ተወዳጅ ነፍስ ናት።

አሜሪካዊ ቤተሰቦቿም በጣም ሀብታም ናቸው።ታዲያ አባቷ ለአማንዳ የልደት ስጦታ ይሆን ዘንድ ውድ መኪና ይልኩላታል። መኪናው ግን ዘገየ። አማንዳ በዚህ በጣም ተናዳ ነበር። በኋላ ግን እንኳንም ዘገየ አለች። ምክንያቱም ልኡልሰገድ የቀረባት ፣ ለመኪናዋ ሳይሆን እሷን ብሎ መሆኑን አታውቅም ነበራ! ለስብሐት ይሁንን ሁሉ ስታጫውተው የዋህ ነፍሷን አየ፤ እንደ ታላቅ እህትም ወደዳት።

በዚህ መሐል ልኡልሰገድ ኒኮልን መተኛት ጀመረ። ሌሎች ምክንያቶችም ተደማምረው አማንዳ ወደ ሀገሯ ለመመለስ ተነሳች። በአውሮፕላን እየተጓዘች ሳትወድ የተለየችውን ልኡልሰገድን እያሰበች መነፋረቅ ጀመረች። አጠገቧ የተቀመጠው ሰካራም

" እንኳን! ፍቅረኛሽ ተለይቶሽ ነው! ማን እንደዚህ ተድበልበዪ አለሽ!" አላት።

የሰካራሙ ስድብ፣ እልህ ሆናትና ውፍረቷን ልትገላገለው ወሰነች። እንደአሰበችውም አደረገች። በመጨረሻ ሸንቃጣ እና ውብ ሆነች። በዚህ ውበቷ ልኡልሰገድን እንደምትማርክ አመነች ። አማንዳ ወደ ፈረንሳዊቷ ከተማ ኤክስ ስትመለስ ይህንን ተስፋ ሰንቃ ነበር።ነገር ግን በሕይወት አልደረሰችበትም ፤ ልኡልሰገድ ለዘለዓለሙ አሸልቦ ነበር።

※※※

ባህራም

ማኑ ባህራምን ወደ ኢራን ሊወስደው ፈረንሳይ ኤክስ ድረስ መጥቷል። በኢራን አብዮት እየተቀጣጠለ ነው። ለአብዮቱ ደግሞ ባህራም በጣም ያስፈልገዋል ።

ባህራም በበኩሉ መሄድ አይፈልግም። ትምህርቱን ቢያቋርጥ ችግር የለውም። ግን ኒኮል እርጉዝ ናት።

ይኸኔ ማኑ ስብሐት ጋር መጣ። ስብሐት ስለ ኒኮል ፣ ጃምሺድ እና ልዑልሰገድ ነገረው።

አሁን ማኑ ጠቃሚ ነገር አገኘ። በቀጥታ ኒኮል ጋር ሄደ። ማኑ አስፈሪ ገፅታ አለው። ግንባሩ ጠባብ ሲሆን ሰውነቱ ደም የሚዘዋወርበት አይመስልም። ማኑ ለኒኮል እንዲህ አላት፦

"ልጁ የጃምሺድ ወይም የልኡልሰገድ ነው ብለሽ ንገሪው።"

ኒኮልም ሳትወድ በግድ የተባለችውን አደረገች። ለባህራም ልጁ ያንተ አይደለም ብላ ደብዳቤ ፃፈችለት።

ማኑ የሚፈልገውን አገኘ። ከባህራም ጋር ወደ ኢራን ለመሄድ መዘጋጀት ጀመሩ።

🤖🤖🤖

የስብሐት ገብረእግዚአብሔር “ትኩሳት” ላይ አንብቤው የነበረ አንድ ድንቅ ታሪክ ድንገት ዛሬ ትዝ አለኝና ላጫውታችሁ ወደድኩ።

የልብወለዱ አብይ ገጸ-ባህሪ ባህራም ድንገት ትካዜ ይገባዋል፤ ተስፋ መቁረጥም ይጫጫነዋል። ልብወለዱን በአንደኛ መደብ የሚተርክልን ስብሐት ግን፡ ጓደኛውን ካለበት ድብርት መንጭቆ ለማውጣት ይህንን ታሪክ ይነግረዋል።
መቼቱ ኩባ ነው። ፊደል ካስትሮ ከወዳጅ ሀገር የመጣበትን ትልቅ እንግዳ በሀገሪቱ አራቱም አቅጣጫ እየዞረ ያስጎበኘዋል። ካስትሮና እንግዳው ሀገሩን እያካለሉ ደህንነቱ ብዙም ወደማያስተማምን አካባቢ ሊጓዙ ሲሞክሩ፡ የጦር መሳሪያ እስካፍንጫቸው በታጠቁ ታጣቂዎች መንገዱ ተዘግቷል። ካስትሮ እና አጃቢዎቹ ከመኪናቸው ወርደው የታጣቂዎቹን መሪ ያነጋግራሉ።

ካስትሮ፡ “እንግዳ እያስጎበኘሁ ስለሆነ መንገዱን ብትለቁልን”

ታጣቂው፡ “ለኛ ምንም አታስብልንም እንዴ?! አሁን የምትጓዝበት አቅጣጫ ጠላቶችህ እንደ ልባቸው የሚፈነጩበት ቦታ እኮ ነው። አንት ብትገደልና ብትሞት እኛንስ ምን ይውጠናል?”

በዚህን ግዜ ባህራም በአይኑ ሙሉ እምባ ግጥም አለ፦
“እንደዚህ አይነት ውብ ታሪክ ሰምቼ አላውቅም”
------------------------------------------------------------------------

ለህዝብ የሚያስብ መሪ ብቻ ሳይሆን ለመሪው የሚያስብ ሕዝብ, , ,??? ለኛ በጣም ሩቅ ነው!!! 😗

🤖🤖🤖

ስብሐት ገብረእግዚአብሔርና ሽታ

ትኩሳት፡ በደምሴ ጽጌ እና በሌሎች የስብሐት ወዳጆች እርማት ተደርጎበት በ1990ዎቹ መጀመሪያ ለህትመት ሲበቃና እኔም አግኝቼ ሳነበው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪና በአስራዎቹ አጋማሽ አካባቢ የምገኝ ጉብል ነበርኩ። እርማት ተደርጎበት እንኳን፡ ከእድሜዬ አንጻር pornographic የሚባል አይነት መጽሀፍ ነበር,,,,not anymore!

ትኩሳት ላይ አንብቤያቸው አእምሮ ላይ ተሰንቅረውብኝ ከቀሩት ከነባህራምና ሲልቪ፡ ከነጃምሺድና ልዑልሰገድ፡ ከአማንዳና ኒኮል ባሻገር፡ ስብሐት “ተካ” በሚል ስም የሚጠራው ገጸባህርይም ነበር። ተካ እራሱን የማይጠብቅ፡ ጸጉሩን የማያበጥር፡ ጥርሱንም የማይፍቅ ጀዝባ ነበር። ሴት የሚያገኘውም አንድም በጉልበቱ አስገድዶ፡ አልያም በገንዘቡ ሸርሙጣ ገዝቶ ነበር። ድንገት ግን ተካ ስርነቀል የሚባል ለውጥ ማሳየት ጀመረ። ጥርሱን መቦረሽ፤ ጸጉሩን ማበጠር፡ ክፍሉን ማጽዳት፡ ካልሲዎቹን ማጠብ ጀመረ። የልብወለዱን ታሪክ በአንደኛ መደብ የሚተርክልን ደራሲው ስብሐትም ”የዚህን ‘አብዮታዊ’ ለውጥ ምክንያት ካላወቅኩማ ምኑን ደራሲ ሆንኩት?!“ ይለናል። ”ወንድ ልጅ እንደዚህ አይነት የባህሪ ለውጦች የሚያሳየው ‘ሴት ሲያገኝ ነው’ “ ብሎም ይጨምርልናል።

ስብሐትና ሌሎች ጓደኞቹ፡ ተካ የጠበሳት ጀርመናዊት፡ ባለ ሙስታሽ(የከንፈር ጺም) እና አፍንጫዋም የማያሸት እንደሆነ እያነሱ ይሳሳቃሉ። በሐበሻ ተረትም ”ለአፈ-ግም አፍንጫ-ድፍን ያዝለታል“ እያሉ ይተርባሉ። ኢራናዊው ባሕራምም ሳቃቸው አስቀንቶት፡ በተሰባበረ ፈረንሳይኛው፡ ሐበሻውኛውን ተረት፡ እንደነገሩ በሚረዳው የባዕድ አፍ ይተረጉሙለት ዘንድ ይማጸናቸዋል።ተተርጉሞለት ሲያበቃም፡ በሳቁ ያጅባቸዋል።

በሌላ አውድና መቼት ደግሞ፡ ስብሐት ገብረእግዚአብሔርንና ሽታን ዳግም ከመጽሀፍት ገጾች መሐል አገኘኋቸው—ከ”ማስታወሻ“ ውስጥ። ስብሐት የአዲስ አበባን ”መዓዛ“ እንዲህ ይገልጽልናል፦ ”አዲስ አበባ ለኔ የትም ይስማማኛል—አፍንጫዬ አያሸትም!!!”

መቼም የአዲስአበባን ስም ያወጡት ጣይቱ ሰይጣን ሹክ ብሏቸው መሆን አለበት። እንደኔ ላለ የገጠር ልጅ አዲስአበባ ገነት መስላ ነበር በአእምሮዬ የምትታየው። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ለመጀመሪያ ግዜ አዲስን ስረግጣት ልክ አንድ ባልዲ ሙሉ መስሏችሁ ሃይላችሁን አሰባስባችሁ ስታነሱት ባዶ ሆኖ ብታገኙት የሚሰማችሁን አይነት ቅለት ነው የተሰማኝ። የዘመኑ ፖለቲከኞች አዲስአበባ ፣ ፊንፊኔ ፣ ሸገር ፣ በረራ እያሉ የሚሻኮቱት ነገር አይገባኝም። ለአዲስአበባ ተገቢው ስም "ቆሻሻአምባ" ተብሎ መፅደቅ አለበት😃😄

መች ለት የቆሻሻ ፍሳሽ መምጠጫ መኪና ላይ በትልቁ "ማር" ተብሎ ተፅፎበት አየሁ። በቃ አዲስ እንዲህ ናት። ስሟ ሌላ ተግባር ሌላ 😃😄

የአዲስአበባ ነዋሪ ከሆናችሁ ሁለት ምርጫ አላችሁ―በላያችሁ ላይ ሽቶ እየደፋችሁ መውጣት ወይም እንደ ስብሐት ታድላችሁ የማያሸት አፍንጫ ባለቤት መሆን😃😄

አዲስአበባ ቆሽሻለች። ከንቲባ ታከለ ኡማ ፓስፊክ ውስጥ ነከር አድርጎ ለቅለቅ ቢያደርጋት ጥሩ ነው😃😄

አለበለዚያ "ፊንፊኔ ኬኛ" የሚሉትን "ቆሻሻ የኛ" ከማለት ለይቼ አላያቸውም። ጤነኛ ሰው በቆሻሻ አይጣላም እንደ ተካ ጀርመናዊት አፍንጫ ድፍን ካልሆነ😃😄

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ትኩሳት ላይ ስለ አዲስአበባ እንደሚፅፍ አሁን ነው የገባኝ። በመጽሐፉ አዲስ አንድ ገፀባህሪ ናት። ስብሐት ሰውኛ አድርጓታል። አዲስአበባ ልክ እንደ ተካ ናት እራሷን አትጠብቅም፤ቆሻሻዋን አታስወግድም። ትጠነባለች። ታድያ በጥንብ መጣላት ነውር ነው። አፍንጫችሁን ጎርጉሩ አዲስን አፅዱ ከዛ ኬኛ ኬኛ እንባባላለን😃😄

🤖🤖🤖

አንድ ድሮ ያነበብኩት የስነ ልቦና መፅሀፍ እንዲህ ይላል፦
" ሰዎች በሚያወሩበት ወቅት ከሚያስተላልፉት መልእክት ፣ በንግግር/በቃላት የሚገልፁት ሐያ ፐርሰንቱን ብቻ ነው"

እንግዲህ የቀረው ሰማንያ ፐርሰንት፣ የፊት ገፅታ፣ የአካል አቋም፣ የእጅ እንቅስቃሴ ወዘተ ይሸፍናሉ ።
ታዲያ ይሄ 20/80 ጉዳይ ትኩሳትን ብሎም ባህራምን አስታወሰኝ።

ባህራም የፋርስ፣ ስብሐት ደግሞ የአቢሲኒያ ሰዎች ናቸው። ያገናኛቸው ፈረንሳይ ፣ የሚያግባባቸው ፈረንሳይኛ ነው። ታዲያ የባህራም ፈረንሳይኛ የተሰባበረ ነው። በእርግጥ ከጃምሺድ ይሻላል። የባህራም የቋንቋ ችግር የትምህርት ውጤቱ ላይ እንኳን ጥላውን እያጠላበት ፣ ባህራምን ሲያበሳጨው እናነባለን።

ነገር ግን ይህ የቋንቋ ችግር፣ ስብሐት የባህራምን ትልቅ ነፍስ ከማየት አላገደውም።ስብሐት ይህንን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦

" አንድ ሰው ከሚናገረው ነገር ተነስቶ ስለ አእምሮው ብቃት መናገር ይቻላል። ስለ ነፍሱ ለማወቅ ግን የአካል እንቅስቃሴውን፣ ፈገግታውን ፣ የአይን መርገብገቡን ወዘተ ማየት ያበቃል።"

ባህራም ኩሩ፣ በራሱ የሚተማመን ፣ ሩህሩህ መሆኑን ለመረዳት ለስብሐት ምንም አላገደውም ፤ ነፍስ ለነፍስ ተግባብተዋል!

ከሰው ስታወጋ የሚነግርህን ትተህ የማይነግር ህን ስማ ይላል አንድ ጥንታዊ ምሳሌ።

በፌስቡክ ስንነጋገር ሐያ ፐርሰንታችንን ብቻ ነው የምንገልፀው። በፌስቡክ መስታወት አጮልቆ የሌሎችን አእምሮ ማየት ይቻል እንደሆነ አንጂ ነፍሳቸውን ማየት አይቻልም። ማህበራዊ ሚዲያዎች በአጠቃላይ፣ ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰው ልጅ መስተጋብር እያጠፉ በሰው ሰራሽ ግንኙነት እየተኩ ይገኛሉ። ፌስቡክ ላይ የሚመሰረቱ ጓደኝነቶች ብዙም የማይዘልቁት ለዚሁ ነው። እዚህ ፌስቡክ ላይ ሐሳብ ለሀሳብ ትግባባ እንደሆነ እንጂ ነፍስ ለነፍስ አትተዋወቅም።

© Te Di