ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 (@bookshelf13)の最新投稿

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 のテレグラム投稿

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"
18,903 人の購読者
2,716 枚の写真
24 本の動画
最終更新日 27.02.2025 06:07

類似チャンネル

Tikvah-University
317,092 人の購読者
Capitalethiopia
16,593 人の購読者

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 によってTelegramで共有された最新のコンテンツ


እና ኦ! ጠይምነቷ: የቀሚሷ በጨዋታ መሃል ከኋላ ፊኒር አባባልና ከዛም ስር ሰርቄ የማያቸው(ዘራፍ ዓይነ ሌባው) ጠይም ወዛም ጭኖቿ………አላፈቀርኳትም ግን በዓይኔ በብሌኑ ገባች፡፡ ጠይም ጦር፡፡" ገጽ 8

"መኝታቤቴ ውስጥ ነው ብዙ ጊዜ የምቀመጠው:: መኝታቤቴ ማድቤቱ አጠገብ ነው:: ማድቤቱ መንገድ ዳር ነው:: መንገድ ዳር ሆነህ ብታፏጭልኝ እሰማለሁ»

ሒድ እንግዲህ! አለ ተገራሚ፡፡ በልቤ በዚህ ዘመን የዚህ ዓይነት ነገር ይደረጋል? አልኩ «ሦስቴ አፏጭልኝ» አለች

ይታያችሁ ከመሽኮርመምና ገመድ ከመዝለል ሌላ ምንም አታውቅም ያልኳት ልጅ ስለፉጨት ጠቃሚነት አንድ ነጥብ ብጉራም ዕውቀቴ ላይ ጨመረችልኝ፡፡ ጠንቅቄ የማውቀው ፉጨት የጎል ኪፐራችንን ነው.... አቀብለኝና እኔ ልለጋው' ሲለኝ:: ከዚያ ሆኖልን የተገናኘን ቀን...

እኔ ኋላ ኋላ፣ እሷ ፊት ፊት። እዛ እዛ የሚያይ መስዬ እዛች ሚኒ ቀሚስ ስር የማላውቀውን ሁለመናዋን እየጎመጀሁ፡፡ ከአፏ ላይም ለሆነ ማታ የሚሆነኝ ቅዠት ልለቃቅም፡፡" ገጽ 11

"የፋሲካ ትርጉም ፍፁም የመብላት ነው:: ከተክሎች እስከ እንስሳት የሚበሉበት ነው። አንዳንዴ እንደ እኔ ዓይነት ሞላጫ ወይም የመሰለው፣ እንደ ኮረሪማ ዐይነት የዋሕ ወይም የመሰለች የፌሽታ ሜኗቸው ላይ ልጃገረድ መሳምና መሳሳም የመሳሰለ ቢጨምሩበትስ?" ገጽ 15

***እዚህ ታሪክ ላይ ኮረሪማ ኤፍሬም ሲያፏጭላት ለምን አልወጣችም? ለምን ስምምነታቸውን አላከበረችም ብዬ ሳሰላስል ነበር። ነገር ግን በሌሎች ትርክቶች ውስጥ ብዙ ጊዜ ኮረሪማን የምናገኛት የሆነ የወፍ ደዌ ይዟት ታማሚ ሆና ነው። ስለዚህ ታማ ይሆን ያኔ ያልወጣችው? አላውቅም። በመጨረሻው ትርክት ውስጥ ግን ኤፍሬም የተሳካለት ይመስላል። ምክኒያቱም ነጻነት የተባለችው ገፀ ባሕሪ ኤፍሬም እነ ኮረሪማ ቤት እንደ አየር ሲገባና ሲወጣ አይቼዋለሁ ትላለች። I guess በዚህ ትርክት ውስጥ the happy ending happened። እንዲህ ነው አዳም ትርክቶቹን ያስተሳሰራቸው።

***በጣም ከወደድኩት ትርክት ከእቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ ደሞ የመሰጡኝ አንቀፆች እነዚህ ነበሩ።

"ረዳቷ ነሽ' ስለተባልኩ ለድምፅዋና ለግልምጫዋ እንድቀርብ ከእሷ ብዙ እርቄ ተቀምጬ አላውቅም (በማላውቀው ምክንያት አንዳንዴ ስጠጋት ብትነጫነጭም) ሁልጊዜ ስርስሯን ነው የምሄደው! ስርስሯን። የታዘዝኩትም እንደዚያ እንድራመድ ነው። እንደ እንቅፋት። ወይ ምን ልበል እንደ ውሻ። ተከናንበን ስንጓዝ ግራና ቀኝ ተመልካች የሚያስበ ልጅና እናት እንደሆንን አድርጎ ነው:: ሎሚሽታ በጣም ረዥም ሴት ናት። ደልደልም ያለች ናት። እኔ ትራፊዋ እመስላለሁ:: እሷ ከሰማይ ብትወረወር እና ብትሰባበር ደቃቃዋ ተፈናጣሪት እዛ ቦይ ወድቃ የምትገኝው እኔ ነኝ። ማሪያምን። መጀመሪያ ጨዋ መስላኝ ነበር አጃቢ ስትፈልግ:: በኋላ በኋላ ሳይ ለካስ ባሏ ያልበቃት የውሸት ዓይኖቿን የደፋች ቅሪ ናት፡፡ ያገባች ጋለሞታ።" ገጽ 42

"ባለቤቴ ጠበቃ ስለሆነ ነገር ሲጥልና ሲያነሳ ጠዋት ከቤት የወጣ የሚመለሰው ሲመሽ ነው፡፡ እሱን ራት አብልቼ፤ አልጋ ላይ አስተኝቼ፣ ከእኔም ነገር ጉዳይ ካለው እሷን አደራርጎ፣ ስለፍትሐ ብሄርና ስለወንጀለኛ መቅጫ እያሰበ ወይም እያለመ ይተኛል፡፡ ጎኑ ተጋድሜ ገና ሳገባው አደርገው እንደነበረ ሁሉ ሆዱን እዳብስለታለሁ፣ ችፍ ያለ ቅንድቡን በአመልካች ጣቴ እካክክለታለሁ፣ በጀልጃላ ውስጥ ሱሪው ስር እጄን አስገብቼ ፀጉር የፈሰሰበት ጭኑን እነካካዋለሁ:: ከደስታ ይልቅ ውስጤ የሚሰማኝ አነጣጥሬ ያለመውደዴ ቁጭት ነው:: ታዲያ ወደ ውጭ እሱ እንዳይሰማኝ አድርጌ እተነፍሳለሁ፤ አተነፋፈሴን ከሰማኝም የፍቅር ስራው ያረካኝ ለመምሰል በወዛም ፀጉር የተሸፈነ ፊቱን አፌን ከፍቼ እስምለታለሁ፡፡" ገፅ 87

"ታዲያ ለቅሶ ቤት እንዳየኝ (እኔም እንድታይ ፊት ለፊቱ ሄጄ ተጎለትኩ) ትክ ብሎ አፉን ከፍቶ ሲያጠናኝ ቆየና ሰላምታ ሰጠኝ………ከአምስት ዓመት በፊት:: ቤቴ በአሮጌ ፔጆው ሸኘኝ፡፡ ለስድስት ወር አብረን ወጣንና ለመጋባት ወሰንን:: አያችሁ ሰው ጣዕሙ እንደ ከረሜላ የሚያልቅ አልመሰለኝም:: ሁለት ዓመታት መጠጥኩት። በትልቅ አፌ አስገብቼ አንገላታሁት፡ ትልቅ ክንዴ ላይ አስቀምጬ እኔ ልጅት ወንድነቱን ተፈታተንኩት:: በከፊል ሽክላ በከፊል ጭቃ በሆነች ቤቱ ከዳር እዳር ዘለልኩባት፡፡ አንድ ጠዋት ስነቃ ብዙ ያለፍኳቸው፣ ያልኖርኳቸው መልካም ነገሮች እንዳሉ ሊያሳየኝ ነው መሰለኝ እግዜር አስናቀን አምጥቶ ፊቴ ገተረው:: ገበያ መሃል ጣልያን እድሞ ፒያሳ አሳዶ የተከተለኝ ዕለት ዞር ብዬ ሳየው ጥቁር ረዥም ፊቱ (አንዳንዱ ያልገባው 'ሞጋጋ' የሚለው)፣ ሰማይ የነካ የመሰለው ሎጋ ቁመናው አብረከረከኝ:: የአለባበሱ ጥራት፣ ትላልቅ ዓይኖቹ ውስጥ የሚንቦገቦገው የፈላ ስሜት መረጋጋቴን አበለሻሽው፡፡" ገፅ 189

"ሳቅሁባት:: ሁሉ አገርሽም እኔም ቁንጅናችንን ልጅነታችንን በትክክል ያልተጠቀምንበት ጅሎች ነን:: እኔ ብዙ ፍቅር ሳላገኝበት ራሴን ስቆጥብ፤ እሷ ደ'ሞ ላገኘችው ወዲያና ወዲህ ስትወረውረው፡ እኔ የማያስፈልግ ውድ ነገር ራሴን አድርጌ ስቆጥር፣ እሷ እንደ ርካሽ ነገር ለአላፊ አግዳሚ ሰጥታው:: ለእሷ የመዝናናት ነጻነት የሰጣት ለእኔስ ያልሰጠኝ ማነው?" ገጽ 93

"'ሴት ነኝ አየሽ:: በትምህርት ነፃ አልወጣም:: እዚህች አገር በትምህርት ነፃ አይወጣም: በትምህርት ብቻ ነፃ የወጣ የለም፡፡ ሕይወት አሁን ነው:: በልጅነት ነው ጨዋታ:: ሴት ሆነሽ ሁለት ነገር፤ ዋና ዋና ነገር ያስፈልግሻል፡፡ ቢቻል ሦስት:: ወሲብ መስጠት፣ ቁንጅና፣ ትምህርት፡፡ በአጭሩ ሸርሙጣ፣ ቆንጆና ምሁር መሆን፡፡ አለበለዚያ የትም አትደርሺም፡፡ ሽርሜነትን ጀማምረሽ አቁመሽዋል፣ ምሁር አይደለሽም፣ ቁንጅናሽ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ይጠፋል፡፡ ይጎልሻል፡፡ አንዱን ብቻ ከሆንሽ ይጎልሻል። ወንዶች ወይም ገዢዎችሽ እንድትሆኚ የሚፈልጉትን መሆን አለብሽ፡፡ ሴት ለማን ተሰራች? ለወንድ፡፡ ቆንጆ... ሽርሙጣ……..ምሁር። ሦስቱን በአንዴ አጠቃለሽ መያዝ፡፡ እንደ እኔ መኪና መንዳት ትፈልጊያለሽ? ነጠላ ተከናንበሽ ከሠፈር ሉዘሮች ጋር ስትዳሪ ልታረጂ ነው? ነቃ በይ፡፡ ቆንጆ ነሽ። ሽርሙጣ ነሽ፡፡ በቀላሉ ካናሳ ፖለቲከኛ ጋር አገናኝሻለሁ……..ከፈለግሽ፡፡ ይኼ ሁሉ የምታየው ብዙው የማይረባ ሰው ነው:: ይሉኝታ አይያዝሽ፡፡ ኢትዮጵያ ሺት ነገር ሆናለች። ትዳር ይፈርሳል በየቦታው………እንደ እኔ አይነቶች 'አፍርሱ' የተባልነውን እናፈርሳለን፡፡ ሻል ያለ ፈልጊ 'ጎጆ መውጣት' ምናምን ሲሉ ቃሉ ራሱ አያስቅም? እ? ሂሂሂ 'ቪላ መውጣት' 'መኪና መውጣት' አይሉትም እንዴ?… ሂሂሂሂ…………የምትኖሪው አንድ ጊዜ ነው……..አስናቀ ምንድነው? የሆነ ባርያ ነገር (አውጥታዋለች እኮ) ወንድ ላሳይሽ? ያለው? የሚያበሉ የሚያጠጡ፣ የሚተኙ፣ የሚያለብሱ:: ማሳደር የሚችሉ:: መኪናቸውን የሚያውሱ፡፡ ሳይቆጥቡ የሚያሰክሩ:: ከፈረንጅ እስከ ተቃጠለ አበሻ አሳይሻለሁ:: የእኔን ልብስ ተዋሺና አንድ ቀን እንውጣ ትምህርት ቤት ደርሶ አለማያ ከመሄዴ በፊት…….አያይዤሽ.....»
'በይ እግዜር ይርዳሽ እቴ' አልኳት በልቤ፡፡ እግዜር የማይረዳው ዓይነት ሰው የለ)" ገፅ 97

"መምሸት እንደጀመረ አስናቀ ቤት በረንዳ ላይ ሆኜ ታደሰ በፔጆው እየተሳበ ቤቱ ሲገባ እየሁት፡፡ እስናቀ ጎኔ መጥቶ ተቀምጦ ወደ ታች ያያል:: የቀኝ እጁ መዳፍ በውስጥ ልብሴ ስር ጡቴ ላይ እንደ ሙቅ ጎጆ ያርፋል፡፡ ከተከፈተ አፌ የሚወጣው ማንንም የማረከ ሞዛርት ነው:: ታደሰ እቤቱ ገብቶ ምን እንደሚያደርግ በሃሳቤ አወጣለሁ አወርዳለሁ:: ማድቤቴ፣ ያቺ የብረትድስት፣ ጠዋት እሱ ፊቱን ሲታጠብ የምጭራት የክብሪት ሳጥን ድምፅ: ሳላቋርጥ የምተኛባት ሶፋ:: የመኝታ ቤቴ ትልቅ መስታወት፡፡ አስናቀ አንገቴን ይልሳል፡፡ በጆሮዬ የወንድ ቀረርቶውን ይሰዳል:: ውስጤ የሚፋጅ ሐምሌ ነው:: ምላሱ ቅባት የነካ መቀነት ነው ታጥቄው የማድር:: እንደ ሚወደኝ ይነግረኛል:: የማንሾካሾኩ ግለት ሊገለኝ ነው:: ሁለመናዬ ይከፈታል፡፡ ጠበቃው ባሌ ደንገዝገዝ ባለው ምሽት ያቺ ልጅ ቤት ሲሄድ አየዋለሁ:: ተንከራፎአል:: የደከመው ይመስላል፡፡ የምንኖረው አንዴ ነው:: ነገ ሞት ይመጣ ይሆናል፡፡ የሚሞትበትን የሚያውቅ አለ? የለም:: በጭኖቼ መሃል ግለቴን የሚቀናቀን ቅዝቃዜ ይፈሳል.....የአስናቀ አውራጣትና አመልካች ጣት ጡቴን ይቆነጥጣሉ፡፡ በቦዙ ዓይኖቼ(የቦዙ ይመስለኛል) ወደ ቤቴ ሄጄ ተመለስኩ:: ወደ አስናቀም መጥቼ ወደ ቤቴም ሄድኩ:: ተመላለስኩ፡፡ ትዝታና አስናቀ እየነዱኝ፡፡ አስናቀ እየነዳኝ፡፡" ገፅ 101

“ታደሰ እባላለሁ፡፡ የወይዘሮ ሎሚ ሽታ የሰማንያ ባሏ ነኝ፡፡ እናቴ 'ታደሰ' ብላ ስትጠራኝ የአባቴን ትንሳኤ ወይም አዲስ መሆን መመዝገቧና መመኘቷ ነበር፡፡ ስም ያቅዳል እንጂ ፈፃሚው ፀባይ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የእኔ የሕይወቴ መስመር የተቀየሰው ገና ከእናቴ ማሕፀን ስወጣ ነው:: አባቴ ከጠፋበት የድንቁርና ጎዳና እንዲመለስ ስሜን ማስተማሪያ ልታደርግበት 'ታደሰ' ትበለኝ እንጂ እሱ የተማረም የተመራመረም የሚመራመርም አልነበረም፡፡” ገጽ 106

"የአባትህ አንጎል ታውቃለህ፤ ይኼ የጫማ ፈለግ ሳያቋርጥ እንደሚቀበል የቦካ የሐምሌ የጭቃ መንገድ እሱን ነበር……… ከእኔ ከምወደው ሚስቱ የበለጠ የጠላ ቤት ወሬ ያመነ 'አጋንንት ነው!' ይላሉ:: 'እንዴት አንድ ሰው በአጭር ጊዜ ሰካራም ይሆናል ያው አጋንንት ካልሆነ?' ይላሉ፡፡ አጋንንት ፍቅርህን የሚሰብር ነው:: ፍቅርህን ከወሬ የበለጠ የሚሰብር ምን አለ? መጠራጠርን እየዘራ፣ አለመግባባትን እያመከረ። አጋንንት በትክክል ታላላቅ ቂላዋትን የምታሰባስብ ወሬ ናት....." ገጽ 106

"ትናንት በመንገድ ሳልፍ አንዷ የተናገረችው በጆሮዬ ገብቶ እስከ አሁን ሲከነክነኝ፡፡ መሳደቧ እኮ ነው፡፡ አንዱን 'አንተ ሂትለር!' አለችው:; በአገሬ ክፉ ጠፍቶ ጀርመን እሄዳለሁ? ደደብ ናት፡፡ ራሷን ያላወቀች ያልደረሰባት:: ሂትለር ምን አደረገኝ? ሂትለር ለእኔ ውብ ነው:: ግራዚያን ይሻለኛል። እሱስ ምን በደለኝ? ባዕድ አይደሉ እንዴ? አብረውኝ ኣልበለ አብረውኝ አልጠጡ፡፡ አብረውኝ ባንዲራ ይዘው አልቶንጠለጠሉ፡፡ እንጀራ ከቆጮ ሕብስት ከአንባሻ ሽሮ ከክክ አልተሻሙኝ:: ሂትለር ብሎ ነገር:: እነዚህ ጀርሞች፣ እነዚህ መርዞች ቆመህ በወገንህ መሳቂያ ያደርጉሃል:: ለምን ትስቃላችሁ? ብትል አይገባቸውም፤ አህያ ምን ይገባዋል? አህያን ብትገለብጠው፣ ብትጠብሰው፣ ብታለብሰው፣ ብታስተምረው፣ ብታበጥረውና ብታሰክረው ያው አህያ ነው:: ለምን ይስቃሉ? እጠይቃለሁ፡፡ አህዮች ሆይ ለምን ትስቃላችሁ? ትዳሬ ፍቅሬ በመፍረሱ? አየህ! እኔ ላይ የሠፈረው ጀርም እስኪይዛቸው ነው፡፡ እሱ እንዲደርስባቸው እፀልያለሁ፣ ቢገባቸው:: ቤቴን እያፈረሱ ያልገባኝ መስሏቸው አፍጥጠው 'ቤቱ እንየው‛ ብለው ይመጡና ስለ ዲሞክራሲ ጥሩነት፣ ስለ መንግሥቱ ሃይለማርያም መጥፎነት ያወሩኛል፡፡ ማነህ አንተ? እላለሁ:: ማነህ አንተ? ማነህ አንተስ? መለኪያዬ ረቂቅ አይደለም አየህ፡፡ ከባድ ነው ግን፡፡ ቤቴን እያፈረሱ ንጉሥ ያማሉ:: አወናካሪዎች፡፡" ገፅ 120

"ዕውነት የሚባለው ነገር ከምናየው፣ ከማናየው፣ ከምናምንበትና ከማናምንበት የተቀመመ መሆኑን መረዳት የሚያስፈራራ፣ በትንሹም ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አለው:: አይደለ? በማንፈልገው 'ተበዳይነታችን' ውስጥ ባናወራውም የራሳችን ተሳትፎ ይኖርበታል:: ምንም ብንክድ አወዳደቃችን ውስጥ የኛ ሃሳብ በማይታይ መልክ አፍሮ ተቀምጦአል ('እዚህ ምን አደርጋለሁ?' እያለ)፡፡ ሌሎች ድርጊት ውስጥ ያለው ማጥፊያ ሴራ በእኛ የታበየ የቂሎች ሳቅና ድጋፍ የታጀበ መሆኑን እንስተዋለን፡፡" ገፅ 123

"ፊቷ ሞታም ያዘነ ይመስላል (ሁሌ ያዘነ ፊት እንደነበራት ትዝ አለኝ)፤ ወደ ጎን ወደ መሬት የምታይ ይመስላል (መሞቷ ያሳፈራት ዐይነት)፣ ግራ እጇ ከጋቢው ወጥቶ አየር ላይ አምላክን እንደሚለማመጥ የገረጣ መዳፉን ወደ ሰማይ አድርጎ፡፡ የደረበችውን ጋቢ ከላይዋ ሳነሳ ከስር የሙሽራነቷን ቬሎ ቀሚስና ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ አይ የነበረውን የአባቴን ኮትና ሽሚዝ እንደለበሰች አየሁ:: ሁሉንም በስርዐት ለብሳለች:: ነጭና ጥቁር አዝሙድ ፀጉሯን ታጥባ ተጎንጉናለች፡፡ ጉንጉኗን ሳምኩት፣ ከግንባሯ ከፍ ብዬ፡፡ እንዲህ ተጠንቅቃ አታውቅም:: ወጣት መሰለች:: በእነዚህ የውሰት ጨርቆችና (አንዱ ከራሷ፣ ሌላው ከፍቅረኛዋ ልጅነት) የሙት ፀጥታዋ ውስጥ እናቴ ቆራጥ መሆንዋን አየሁ:: ከዚህ የበለጠ ስር ነቀል ነገር አለ? ፈራኋት::" ገፅ 123

"ሬሳዋን ሳየው ከሌላ ጊዜ የበለጠ ደስተኛና የተዝናናች መሰለችኝ:: ለአፍታ በዝርዝር አቅዳ ራሷን ያጠፋች መሰለኝ፡፡ ጭንቅላቴን ደረቷ ላይ አድርጌ። ልቤ እስኪችል አለቀስኩ፡፡ ሞትን በሚገርም መልክ ጣፋጭ የሚያደርጉ ሸረኞች ምን ያህል የሚገርሙ ናቸው?" ገፅ 124

"ለመሆኑ ዐይንና ገንዘብ የሚለዋወጡበትን ሂሳብ ማን ይሰራዋል? ከአንድ ጤነኛ ዐይን የማገኘው ደስታ ምን ያህል ብር ያወጣል? ትክክል ልውውጥ መሆኑን በምን እንለካለን? በየአገሩ ብቻ ሳይሆን በየዳኛው ዓይነት የተለያየ ፍርድ አይኖርም? ሐሙራቢ 'ዓይን ያጠፋ ዓይኑ ይጥፋ' ብሎ ሲወስን እጅግ ትክክለኛ ፍትህ ይመስላል፡፡ ሆነ ብሎ አንድ ዓይኔን ያጠፋ በገንዘብ ቢቀጣ ቀጥሎ ዕውር መሆኔን ተመኝቶ የቀረችዋን ዓይኔን 'ገንዘብ ከፍዬ ማጥፋት እችላለሁ' ብሎ እንዲያስብ አያደርገውም? እናቴ ምሥራቅ ሙያዬ ዳኝነት የሆነ ልጇ ቆሜ እየሄድኩ ተበድላ ያለ ፍትሕ ስትሞት አየሁ አይደል?" ገጽ 127

"እንደው ለመሆኑ የእናቴና የአባቴ ፍቅር በዚህ ዓይነት ዘዴ መፈራረሱ አገር አይጎዳም? እናቴ 'በእኔ የሕይወት ቀዳዳ ብትገባ አገርህን ታገኛታለህ ስትል ይሄን ማለቷ ነበር እንዴ? አገር መናድና ሰላም ማደፍረስ የሚፈልጉ ሰዎች ተደራጅተው በዚህ ዓይነት ስልት ብዙ ግለሰቦችን ካለሙት ግብ እንዳይደርሱ ኣድርገው ማበሳጨት አይችሉም? የእነዚህ ግለሰቦችስ መበሳጨት ለአገሪቷ እድገት የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ አያሰናክለውም? መንፈሳቸውንስ አደፍርሶ ተስፋ አያስቆርጣቸውም? ለሁላችንስ ያስቡ የነበሩትን ሰዎች የተማረሩ ግለኞች አያደርጋቸውም? ያገባናል የሚሉትን ሰዎች 'ምን አገባን' እንዲሉ አያደርጋቸውም? ይሄ ባይሆን በምሬት 'የመጣው ይምጣ' ብለው ከሁሉ ለመራቅ ከአገር ሊሰደዱ አይችሉም? መሰደዳቸውንስ አንዳንድ ፖለቲከኞች ራሳቸው አባራሪዎቹም ሊሆኑ ይችላሉ) 'ዲሞክራሲ በመጥፋቱ ነው' ብለው በመንግስት ሊያመሃኙ አይችሉም? እንበል እንዲህ ዓይነቱ የማስተጓጎል ኪነት ቢቀናበርና ለረዥም ጊዜ ቢሰራበት ብዙ ግለሰቦችን የግል ችግር በመሰለ ነገር ነጥሎ በማውጣት ኣፍዞና አደንዝዞ የአገር ሕልውናን ማውገርገር አይቻልም? ብሎስ አገርን

(እስቲ እንወያይበት)

እቴ ሜቴ ሎሚሽታ... ኦ አዳም!

እቴሜቴ ሎሚሽታን አንብቤ ስጨርስ የተሰማኝን ስሜት በቃላት ለማስፈር በጣም ከብዶኝ ነበር። ውስብስብነቱ ያስደመመኝ መጽሐፍ ነው። አንባቢዎች በተለየ መልኩ የእቴሜቴን የሕዳግ ማስታወሻዎች ጥልቅ ትኩረት ሊሰጡበት ይገባል ብዬ አምናለሁ።The entire book, It is beautifully intricate.

ግን በመጀመሪያ መግለጽ የምፈልገው እዚህ ስር የማጋራችሁ ከመጽሐፉ የተውጣጡ አንቀጾች ላይ የመጽሐፉን የገፅ ቁጥሮች ጽፌያለሁ ቢሆንም እኔ የተጠቀምኩት የ2001 ህትመትን (it might be first edition) ስለሆን እናንተ ከያዛችሁት ገጽ ጋር ላይስማማ ይችላል። ሌላው የዚህን ጽሑፍ ርዝመት አይታችሁ አትደናገሩ። ይህንን በንክኪ ለእናተ አካፈልኳችሁ እንጂ አዳምን በጣም ስለምወደው ትንታኔው ለራሴ እንዲጠቅመኝ እንደማስታወሻ ለመገልገል ነው።

ይህንን መጽሐፍ አንድ ግዜ አንብቤ ተረድቼዋለሁ የሚል ሰው ካለ ለማመን እቸገራለሁ። ይህ መጽሐፍ በሚያምሩ ሃምራዊ ቀለማት ያሸበረቀ ውስብስብ የሆነ በቴክኒክ ያበደ ረቂቅ ሥዕል ነው። እየተነበበ ሲሄድ ውበቱና ጥልቀቱ እየጎላ የሚሄድ፣ እያንዳንዷን የእንቆቅልሹን ጥግ በይበልጥ በመረመርን ቁጥር የበለጠ የምንደመምበት፣ ባሰላስልንበት ቁጥር፣ የበለጠ ግልጽ እየሆነ እየሄደ ማራኪነቱና ውበቱ ማለቂያ የሌለው መጽሐፍ ነው። ሕዳጉ ላይ የተዘረዘሩትን ቃለ ምልልሶች እና ማስታወሻዎች ስናነብ አዳም የጠቀሳቸው ማጣቀሻ መጽሐፍት እውነት እስኪመስሉን ድረስ የተጭበረበርንበት መጽሐፍ ነው። እኔ በሚገባ ተደነጋግሬ ነበር። ገጽ 15 እስከ ገጽ 19 ላይ ያለውን ሕዳጉ ላይ የተገለጸውን የታዋቂ ሰዓሊውን የመስኮት ገረሱን ቃለምልልስ አንብቤ ስጨርስ ከመስኮት ጋር የመጀመሪያ ትውውቄ ስለነበር በገሃዱ አለም ውስጥ ያለ እውነተኛ ሰዓሊ መስሎኝ ነበር። ስለ መስኮት ገረሱ ብዙ ከማለቴ በፊት እስቲ በቅድሚያ የመጀመሪያው ታሪክ ላይ ትንሽ እናውጠንጥን።

መች ትመጣለህ? የሚለው የመጀመሪያውን ታሪክ ስናይ አፍ የሚያስከፍቱ በጣም ብዙ የሚማርኩ ውስብስብነቶችን እናያለን። ውስብስብ የሚለውን ቃል በአዎንታዊ መልኩ ነው እዚህ ጽሁፍ ላይ የምገልጸው። የሚተሳሰር፣ የሚወራረስ እና ብዙ 'ተነካናኪ' ነገር አለው ለማለት። አሁን የማሳያችሁ ጥቂት አንቀፆች እዚህ ሰባቱም ትርክቱ ላይ ያሉት ገፀ ባሕሪያት እንዴት በተለያዩ ታሪኮች ውስጥ በሌሎች ሰዎች እይታ ውስጥ ታሪካቸው ሲቀጥል ነው። ይህ በጣም ያስደምማል። አንድን አጭር ታሪክ አንብበን ጨርሰን ተደመደመ ስንል በሌላ ከታሪኩ ጋር ምንም ግንኙነት በሌለው ልዩ ታሪክ ውስጥ ገጸ ባሕሪው ሞቶ ሲቀበር እንደርሳለን። (መስኮት ገረሱ ገጸ ባሕሪ የተጸነሰው መጀመሪያ ታሪክ ውስጥ ሲሆን መሞቱን የምንሰማው 7ኛው ታሪክ ውስጥ ነው) ወይ ደሞ የአራት ልጆች አባት የሆነው ገፀ ባሕሪ የተሳካ ትዳር ላይ እንዳለ ታሪኩ ተደምድሞ ግን በሌላ ታሪክ ላይ ይህን ገፀ ባሕሪ ሲማግጥ ያሳየናል። (ገዳም የማርታ ባል ከሎሚሽታ ጋር 7ኛ ትርክት ላይ እጅ ከፍንጅ እንደተያዘው) እረ ኡ ኡ ኡ አዳም ቴክኒኩ ያሳብዳል ለማለት ነው። እስቲ እንዲህ እንዲህ ያሉትን ትስስሮችና ንክኪዎች ከመጀመሪያው ታሪክ ብቻ ተነስተን በምሳሌ ላሳያችሁ።

(መች ትመጣለህ?) እዚህ ትርክት ላይ ሁለት ዋና ገጸ ባሕርያት ይገጥሙናል። አፍቃሪ ኤፍሬም እና ተፈቃሪ ኮረሪማ። ከዛ የኤፍሬም አባት ታዋቂ ሰዓሊ መስኮት ገረሱን እንተዋወቀዋለን። (ተነካናኪ የሚባል የብሩሽ የአጣጣል ስልት የሚጠቀም ሰዓሊ... የአዳምን አጻጻፍ አይነት እንበለው? እዚህ መጽሐፍ ላይ ትርክቶቹ ተጀምረው እስኪደመደሙ የማይነካኩ ገፀ ባሕሪያት የሉምና።

መጀመሪያው በጣም በጣም የደነቀኝ (The character’s time traveling ability) እያንዳንዷ ገፀ ባሕሪያት በተለያየ አጋጣሚ በተለያዩ ሰዎች ይታያሉ። Adam is allowing us to see the characters in other stories in the lens of other peoples perspective. ኦ አዳም ያስብላል። It is mind blowing.

ለምሳሌ አዳም እነዚህን ሁለት ገፀ ባሕሪያት ..ኤፍሬምና ኮረሪማን "(ሽልንጓ) የመጨረሻዋ የቀበሌ 01 ድንግል" በተሰኝው የመጽሐፉ መጨረሻ ታሪክ ውስጥ ነጻነት የተባለችው ገፀ ባሕሪ የኮረሪማና ኤፍሬምን ትውስታዋን from her perspective ገጽ 334 ላይ እንድትገልጽ አድርጓታል።

"እናቷ እትዬ ቀለመወርቅ እንደ ፈረንጅ እያደረጋት እምቢ ብላ ኖራ ኖራ አሁን ለኮረሪማ የሀበሻ የወፍ መድሃነት ልትሰጣት ነው እና ትንሽ ከባድ ነው ቤቷ ሄደሽ እርጂያት ምናምን አለችኝ እማማ... መታመም ከጀመረች ስንት ጊዜዋ እና ደ'ሞ አንድ ኤፍሬም የተባለ ልጅ ወዷት ከአጠገቧ አይለይም፡፡ ቤቷ እንደ አየር እየገባ ይወጣል፡፡ ሽመልስ ይማር ነበር፡፡ በዐይን አውቀዋለሁ፡፡ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን የወጣቶች ምናምን ተጠባባቂ ተብሎ በቃ ያነጅባል፡፡ ሲያነጅብ ያስቃል አለ አይደለ አያፍርም ድርቅ ያለ ነው ....ግን ይስቁለታል፡፡ ኮሚክ ነው ምናምን ይሉታል፡፡ ገጽ 334

ኮረሪማን ሌላ ቦታም እናገኛታለን። 'ለድልህ' የሚለው አምስተኛው ታሪክ ላይ። እዚህ ታሪክ ውስጥ እናቷን ቀለመወርቅን፣ አባቷ ሲራክን እንዲሁም ወንድሟ ካሌብን የመተዋወቅ እድል እናገኛለን።

"ካሌብ መኖሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ከቤቱ ፊት ለፊት ሳሩ ያለቀ መሬት መሃል በእርጅና ጥቁር የሆነ ኩርሲ ላይ ተቀምጧል:: ፊት ለፊቱ ያለው የኮረኮንች መሬት ላይ የሰሌን አንሶላ ተዘርግቶ ቃሪያ ተሰጥቶበታል:: «ቃሪያውን እይልኝ የሠፈር ዶሮ እንዳይጭረው» ብላው እናቱ ፀሐይ እንዳይጎዳት ከራሷ በላይ ባለ አበባ የቀጭኔ ዣንጥላ ፏ አድርጋ መርካቶ ከሄደች ቆየች፡፡ እህቱ ኮረሪማ ጋቢ ተከናንባ ፊት ለፊት በረንዳ ላይ ሸራ አልጋ ዘርግታ ከወፍ በሽታዋ እያገገመች ጋደም ብላለች:: ፊት ለፊቷም ትንሽ የእንጨት ጠረጴዛ ላይ ውሐ በፕላስቲክ ኩባያ ተቀምጦላት አልፎ አልፎ ያን እያነሳች በትጋት ትመጣለች፡፡ እሱ በግራ እጁ የደራሲ ገዳም ማርታን የጠፋ ቀለበት የተሰኘ ልብ ወለድ ባመልካች ጣቱ አልቦ ይዟል።" ገጽ 193, 194

በዚሁ ‘መች ትመጣለህ' የሚለው መጀመሪያ ታሪክ ውስጥ ደሞ በሶስተኛው ታሪክ ‘እቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ’ ውስጥ ገና ወደፊት የምንተዋወቀው የሎሚ ሽታ ባል ጠበቃው ታደሰ በማንገምተውና በማናስተውለው መንገድ መኪናውን አቁሞ ሲንገዋለል እናስተውለዋለን። Basically what I am saying is that the characters of Adam’s time travel to the past and future so easily. የሎሚ ሽታን ባለቤት ታደሰን በኤፍሬም እይታ ስናየው ይህን ይመስላል።

“ታዲያ ኰረሪማ ቤት ግንብ ሥር ቆሜአለሁ:: እወዲያ ወደ ግራ የሚያልፍ አሮጌ ፔዦ ተሰብሮ ሞተሩ ይጨሳል:: ባለቤቱ ጠበቃው ታደሰ ፍቅረ ስላሴ ነው፡፡ የሚጠብቀው ነገር እንዳለ ሁሉ ወገቡን ይዞ ወዲያ ወዲህ ይላል:: ያቺ ቁሊ ሚስቱን ሎሚ ሽታን ጎረቤታችን አስናቀ ወስዶበታል ይላሉ፡፡ አንዳንዱ ሲበሳጭ (በመኪናው ይሁን በሚስቱ) ዝም ብሎ ወገቡን ይዞ ወዲያ ወዲህ ይላል፡፡ ሌላው ወዲያ ወዲህ የሚለው መንገደኛም ፋሲካን ያሳለፈ እይመስልም፡፡ ትንሽ መጥገብ እንኳን አይፈለቅቀውም እንዴ? ከኰረሪማ ቤት ድምፅ እሰማለሁ:: የድንች ጥብስ ይሸተኛል፡፡ ፋሲካው አልቆ በምኔው ድንች ውስጥ ገቡ? በሀሳቤ የተንገለጠጠ የከሰል ፍም

ላይ ድንቾች ከነጥብቋቸው ሲድበለበሉ ታየኝ:: ሦስት የእኔን ቡጢ የሚያካክሉ ድንቾች:: አንድ በጥልቅ ተጠብሳ የጠቆረች፣ አንድ የተጀመረች ገና ቢጫነቷ ያልጠቆረ፣ ሦስተኛዋ አንድ ጐኗ የጠቆረ:: ኮረሪማ ለባብሳ ተቀምጣለች።" ገጽ 21

በሶስተኛው 'እቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ' በተሰኝው ትርክት ውስጥ የታደሰ ሚስት ሎሚሽታ ከባሏ ውጪ ከጎረቤቷ አስናቀ ጋር እየማገጠች ጠበቃው ባሏን ታደሰን በፔጆው እየተሳበ ቤቱ ሲገባ ታየዋለች። መጀመሪያው ታሪክ ላይ ኤፍሬም በብስጭት ሲንገዋለል ያየውን ይሄን ጠበቃው ታደሰን ሚስቱ ሎሚ ሽታ በሶስተኛው ትርክት ውስጥ ይህን በመሰለ ሁኔታ የብስጭቱን መንስዔ ትነግረናለች።

"መምሸት እንደጀመረ አስናቀ ቤት በረንዳ ላይ ሆኜ ታደሰ በፔጆው እየተሳበ ቤቱ ሲገባ እየሁት:: አስናቀ ጎኔ መጥቶ ተቀምጦ ወደ ታች ያያል። የቀኝ እጁ መዳፍ በውስጥ ልብሴ ስር ጡቴ ላይ እንደ ሙቅ ጎጆ ያርፋል:: ከተከፈተ አፌ የሚወጣው ማንንም የማረከ ሞዛርት ነው:: ታደሰ እቤቱ ገብቶ ምን እንደሚያደርግ በሃሳቤ አወጣለሁ አወርዳለሁ፡፡ ማድቤቴ፣ ያቺ የብረትድስት፣ ጠዋት እሱ ፊቱን ሲታጠብ የምጭራት የክብሪት ሳጥን ድምፅ:: ሳላቋርጥ የምተኛባት ሶፋ:: የመኝታ ቤቴ ትልቅ መስታወት:: እስናቀ አንገቴን ይልሳል፡፡ በጆሮዬ የወንድ ቀረርቶውን ይሰዳል:: ውስጤ የሚፋጅ ሐምሌ ነው:: ምላሱ ቅባት የነካ መቀነት ነው ታጥቄው የማድር:: እንደ ሚወደኝ ይነግረኛል:: የማንሾካሾኩ ግለት ሊገለኝ ነው:: ሁለመናዬ ይከፈታል:: ጠበቃው ባሌ ደንገዝገዝ ባለው ምሽት ያቺ ልጅ ቤት ሲሄድ አየዋለሁ:: ተንከራፎአል፡፡ የደከመው ይመስላል:: የምንኖረው አንዴ ነው:: ነገ ሞት ይመጣ ይሆናል:: የሚሞትበትን የሚያውቅ አለ? የለም:: በጭኖቼ መሃል ግለቴን የሚቀናቀን ቅዝቃዜ ይፈሳል…….የአስናቀ አውራጣትና አመልካች ጣት ጡቴን ይቆነጥጣሉ፡፡ በቦዙ ዓይኖቼ(የቦዙ ይመስለኛል) ወደ ቤቴ ሄጄ ተመለስኩ፡፡ ወደ አስናቀም መጥቼ ወደ ቤቴም ሄድኩ:: ተመላለስኩ:: ትዝታና አስናቀ እየነዱኝ፡፡ አስናቀ እየነዳኝ::" ገፅ 101

እዚሁ 'መች ትመጣለህ?' የሚለው ትርክት ላይ ሌላ ገና ወደፊት "ሁለት ተኩል የውስጥ ሱሪዎች ለአዲስ አበባ" በሚለው 6ተኛ ታሪክ ውስጥ የምንተዋወቀውን የማርታን ባለቤት ደራሲ ገዳምን በብዕር ስሙ 'ገዳም ማርታ' ተብሎ የህዳግ ማስታወሻ ውስጥ 'ዝንደዳ' ስለሚለው ቃል ሲያብራራ እናገኝዋለን።

"በደራሲ ገዳም ማርታ ከተፃፈው መፅሐፍ ተመዞ የወጣና በዚያን ሰሞን ፋሽን ሆኖ ሲጠቀስ የነበረ ቃል:: 'መዘንደድ' ማለት 'ዘንዶ' መሆን ማለት ነው፡፡ ዘንዶ በገዳም አባባል በልቶ ጠጥቶ የሚተኛ ማለት ነው:: 'ዝንደዳ' በጭራሹ አገርን መርሳት፣ ለአገር የሚችሉትን አለማድረግ፣ ግን የአገሪቷን ምግቦች እያሳደዱ በመብላት በዛ ብቻ ዜግነትን ለማሳየት መጣር ማለት ነው:: ገዳም 'መዘንደድ‛ ከሀዲ መሆን ነው ይላል፡፡ ገዳም በአባቱ ስም አይፅፍም፡፡ 'ገዳም አባተ' ተብሎ ከመጠራት፣ የባለቤቱን ስም እንደ አባቱ ስም አድርጎ ገዳም ማርታ' መባልን መርጧል፡፡ በዚህ ምክንያት ሳይሆን ይቀራል ገዳም ገፀ-አስቀያሚ ቢሆንም ብዙ ሴት አንባቢዎች የነበሩት? ገዳም መፅሐፉ አንድ ምዕራፍ ውስጥ እንዲህ ይላል፡ '…..የምናደርገው ነገር ቢኖር የልኳንዳ ስጋ በርካሽ ገዝተን እምብርታችን እስኪ ፈርስ እሱን በልተን በየአልጋችን መውደቅ ነው:: የዚህ ድካም ሲያልፍ እሷና እኔ፣ እኔና እሷ ይቀጥላል፡፡ እሱና እሷ ይቀጥላል፡፡ ጠላት መጥቶ በር አንኳኩቶ አገራችንን ቢወስድ አንሰማም:: ይሄን 'ዝንደዳ' እለዋለሁ።'
(ከ ገዳም ማርታ የጨርቆስና የአገርሽ ዛንታ፡ ግልፅ ደብዳቤ ለአዲስ አባ ጃሌዎች 1978 ኩሉ አሳታሚዎች፡፡" ገጽ 19-20

ገዳም የሚፈጠርበት ሰባተኛው ታሪክ ላይ ገና ሳንደርስ ገዳምን ብዙ ቦታዎች ላይ በተለያዩ ሰዎች እይታ ስር እናገኝዋለን።
ኮረሪማና ወንድሟ ካሌብ "ለድልህ" የሚለው ታሪክ ላይ ስለ ገዳም ምን አሉ?

" «ምን ታስባለህ?» አለች እህቱ « እ……………እዚህ ልብ ወለድ ውስጥ ስለአለችው ባለታሪክ» ዋሻት::
«ደራሲው ገዳም እኰ እዚህ ሰፈር ያለው ነው »
«ማን ነገረሽ?…………እንዴ? ይሄ የማርታ ባለቤት? አትይኝም?»
«አዎ»
«እም.... »
« ምነው?»
«ምንም:: ደራሲ መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡ ደ'ሞ ነው እንዴ?» የአባቱ ስም ማርታ ? «የሚስቱን ስም ነዋ! የብዕር ስም ዐይነት………» «አባቱ እንዳይገሉት» «ሂሂሂ………አንተ ሲቪል ኤንጂኒየሪንግ ምናምን በል አርቱን ለእኔ ተወው......» «ጉረኛ.....»
«ሂሂሂ…...ሁሁሁ»
ከተጋደመችበት እያማጠች ቀና ብላ ውሐ ጠጣች፡ ዓይኖቿን ጨፍና የሚያስብ መሰለች፡፡ የሕመሟን ቁርጠት ይሁን ውጋት እያዳመጠች እንደሆነ ይገባዋል፡፡" ገጽ 195

ስለገዳም እና ማርታ የሚዳስሰው ሰባተኛው ትርክት ላይ ደሞ የኮረሪማ እና የካሌብ አባትና እና እናት ቀለመወርቅ እና ሲራክ በገዳምና ማርታ እይታ ውስጥ ምን እንደሚመስሉ እናያለን።

""……«እኔ ሌላ አሪፍ መፅሐፍ እሰጥሻለሁ» መፅሔቱ አጓጓኝ:: «ምን ትሰጠኛለህ?» «'ሞንተ ክሪስቶ ካውንት' የተባለ በጣም አሪፍ መፅሐፍ አለኝ»
«እንግሊዘኛ ነው አማርኛ?» እንግሊዘኛ ማንበብ እንደማትወድ አውቃለሁ:: ለምን እንደምትጠይቀኝ እንጃ::
«ከእንግሊዘኛ የተተረጐመ ነው:: በጣም ደስ ስለሚል እኔ ሁለቴ ነው ያነበብኩት። ማን እንዳዋሰኝ ታውቂያለሽ? የጋሼ ሲራክ ባለቤት»
«ቀለመወርቅ? እሷ ሰው አታናግርም አይደለ? አንተ ሰው ይወድሃል»
«ከመርካቶ ስትመጣ ሜክሲኮ አውቶቡስ ስጠብቅ አገኘችኝ:: ሊፍት ሰጠችኝ:: መፅሐፉ መኪናው ውስጥ ከኋላ መቀመጫ ላይ ነበር:: ሳገላብጥ አየችና 'ከፈለግህ ወስደህ አንብበው' አለችኝ:: ማን እምቢ ይላል…….ከዛ ሠፈር ስንደርስ ዕቃ ስታወርድ ጠረጴዛና ወንበር ገዝታ ነበር ማስገባት እረዳኋት»
«እና ለኩሊነትህ መፅሐፍ ይከፈለኝ አልክ?» «ምናለበት ደሞ አንቺ ቀናሽ…...» «ምንድነው የምቀናው?»
«ልጃቸው ጩጬ ነው አይደል እንግሊዘኛ ነው የሚያነበው ከአሁኑ»
«ሲራክ ነው ሰላምተኛ…….እሳቸው ደስ ይሉኛል:: ሚስቱ ግን.... ትንጠባረራለች»" ገጽ 265

ይህ ብቻ ሳይሆን ገዳም ሶስተኛዋ ታሪክ ላይ የምትገኝውን ሎሚሽታንም አግኝቷታል። በእሱ እይታ ሎሚሽታ ይህን ትመስላለች..

"(እንዲህ የሴት ጭን የሳበኝና የማርታን የልጅነት ጊዜ አቅርቦ ያስጨነቀኝ አጋጣሚ ነበር፡፡ አንድ ቀን በቶሎ ቤቴ ለመግባት ታክሲ ተሳፈርኩ። የአንድ ሰው ቦታ ብቻ ነበር፣ ከኋላ፡፡ ገብቼ እንደተቀመጥኩ፣ ከጎኔ የነበረች ስሳፈር ልብ ያላልኳት አንዲት ሴት ሰላም አለችኝ፡፡ ፊቷ ማርታን የሚመስል ነገር አለው:: መልሼ ሰላም ካልኳት በኋላ፡ 'የጠፋ ቀለበት የተባለው መፅሐፍህን አንብቤው ደስ ብሎኛል። ባለቤቴ ነው የነገረኝ የዚህ ሠፈር ሰው እንደሆንክ:: ሎሚ ሽታ እባላለሁ' አለችኝና በወርቅና በብር የሚንቦገቦግ ቀኝ እጇን ዘረጋች፡፡ በቸልታ ጨበጥኩና፡ 'በጣም ደስ ብሎኛል ደስ ስላለሽ አልኳት፡፡ ዝርዝር አልነገረችኝም፡ ከመሃል እንዲህ እያወራችኝ ዐይኖቼ በድንገት በግማሽ የተራቆቱ ጭኖቿ ላይ አረፉ። "ገጽ 276

ሎሚ ሽታ በማርታ እይታ ..

ጂጂ የራሷን ህይወት ይሆን የምትተርከው? በዚህ የሐሩር ጉዞ ውስጥ በእውን አልፋ ይሆን ጂጂ? ወይስ የማንን ህይወት፣ የማንን ታሪክ ነው በዚያ የስሜት ጥልቀት የምታንጎራጉረው? እንዴትስ እንዲህ ጠልቃ ተሰማት? ...

እንዴትስ እነዚያን ዲቴይሎች አወቀች? እንዴት እንዲህ እስከ አጥንቷ ዘልቆ ተሰማት? ለምንስ በራሷ ስም "እኔ" በሚል ፈርስት ፐርሰን ትተርከዋለች? በእውን የራሷ ታሪክ ነው? ወይስ የእህቷ? የገነት ሽባባው? በእውነቱ አላውቅም።

በመኪናው መንገድ መኪናው ዘለቀ
አሁንም ቅድምም ያ በላይ ዘለቀ
ከበላይ ዘለቀ ከተሰቀለው
ሺፈራው ይሻላል ሶማ የገባው
አያ በለው በለው፣ በለው እንዲያ
ያገሬ ልጅ ነው፣ በለው እንዲያ...

የእጅጋየሁ ሽባባውን ድምፅና የእንጉርጉሮ ኃይል የተላበሱት፣ የገነት ሽባባው አይረሴ እንጉርጉሮዎች ናቸው። ሁሌም ሳስባቸው፣ ሳስታውሳቸው እኖራለሁ። አሁንም ሙዚቃው አብሮኝ አለ።

በፈቃድ እጅን ሰጥቶ፣ ተበልጦ፣ ያለ ትግል በባላንጣ እጅ ከመሞት። ታግሎ፣ ሸፍቶ፣ ባገርህ ደን ውስጥ፣ በሕዝብህ፣ በወገንህ፣ በሰርዶህ መሐል፣ በጀግንነት ቆመህ መሞት፣ የበለጠ ክብር ነው። የምትል ይመስለኛል ገነት ሽባባው በበኩሏ።

እነዚህ የጀግንነት ማርዘነቦች። እነዚህ አርበኛ ልጆች። እነዚህ ልባችንን በማይረሳ እንጉርጉሮ ያቀለጡ ልቦች እጅግ ይደንቁኛል። አፀደ ወይን ናቸው። የነፍስ ማረፊያ። የነፍስ ምግብ። መከፋትህን፣ ብሶትህን፣ ትዝታህን፣ መብሰልሰልህን ርቀህ የምትጠለልባቸው ምኩራቦች ናቸው። የችግር ቀን መፅናኛዎች። የነፍሳችን ሶማዎች።

ፈጣሪ ጂጂዬን ባለችበት መልካሙን ሁሉ በረከት ያዝንብላት የኢትዮጵያ አምላክ! ዳግም ፀድቃ፣ አብባ፣ በሙዚቃችን ሠማይ ከፍ ብላ በእንጉርጉሮዎቿ ልባችንን እንድትዳብስ እመኛለሁ። እናፍቃለሁ። ይናፍቀኛል የጂጂ ሁለመና። የጂጂ ከነፍስ ጋር የታሸ፣ የተዛመደ፣ ውብ ቃና።

ሙዚቃዋ አብሮኝ ላለው ለገነት ሽባባውም ፈጣሪ ነፍሷን በገነቱ ሥፍራ እንዲዲያኖርላት፣ ዕረፍቱን እንዲያበዛላት እመኛለሁ።

የጥበብ አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ።

🎼🙏🏿

© Assaf Hailu

የጂጂ እህት፣ እና የጂጂ ብቻዊ ዓለም
_____

(ከነፍስ የፈለቁ እንጉርጉሮዎች)

"ከበላይ ዘለቀ ከተሰቀለው
ይሻላል ሺፈራው ሶማ ከገባው
አያ በለው በለው በለው
ያገሬ ልጅ ነው..."

እያለች ስታንጎራጉር ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማት ጂጂ መስላኝ ነበር። ድምጿ ቁርጥ የጂጂን ነበር። ተማሪ ነበርኩ።

ከብዙ ጊዜ በኋላ ነበር ጂጂ ሳትሆን፣ የጂጂ እህት መሆኗን፣ ስሟም ገነት ሽባባው እንደሚባል፣ ኬንያ ውስጥ ራሷን አጥፍታ ህይወቷ እንደተቀጠፈ የሰማሁት። በጣም ነበር ልቤ የተነካው።

ምን ገጥሟት ይሆን? ለምን? ደሞ ጂጂም ራሷ ያኔ ኬንያ ነበረች። አብረው ይኖሩ የነበረ አልመሠለኝም። እንዲያውም የጂጂ ታላቅ መስላኝ ነበረ።

ነገር ግን ኋላ አንድ ዕለት ጂጂ ስለዚህች እህቷ ስትጠየቅ የተናገረችው ቃል ታናሽ እህቷ እንደነበረች አረጋገጠልኝ። ጂጂ ከተናገረችው በቃሌ የማስታውሰው እንዲህ የሚል ቃል ነበረበት፦

"የእኔን እግር ተከትላ ወደ ሙዚቃ መግባቷ፣
ምንም እንኳ የኛ ህይወት አስቸጋሪ ነው አየሽ?
ያውም በሰው ሀገር ፈተና ይበዛዋል፣ የእኔን ፈለግ
እንድትከተል ባላበረታታትም ግን ብዙ ጓደኞች
አፍርታ ነበረ፣ ጥሩ ነበረች፣ ሙዚቃም ፊልምም
ይቀርፁ ነበር፣ እና ግን ባልጠበቅኩት፣ ባላሰብኩት
ሰዓት አጣኋት፣ አጠገቧ ሆኜ ብጠይቃት፣ ብረዳት፣
ለዚያ የዳረጋትን ብሶትና ጭንቀት ብካፈላት፣ እንዴት
ደስ ባለኝ፣ ሁሌም ይቆጨኛል፣ አልቅሼም
አይወጣልኝም፣ ካጠገብሽ ትናንት አብራሽ የነበረች
ታናሽ እህትሽን ድንገት ዛሬ መነጠቅ በጣም ከባድ
ነው፣ ለመቀበልም ከባድ ነው፣ የሁልጊዜ የእግር-
እሳቴ ነው..."

በ90ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሌላዋ የጂጂ ታናሽ እህት ሶፊያ ቲቪ ላይ ቀርባ የእህቷን የጂጂን ዜማ ስታንጎራጉር የሰማናት ሁሉ በቤተሰቡ ውስጥ ባለው የሙዚቃ ተሰጥዖና በጣም የሚመሳሰል ድምፅ አለመደነቅ አልቻልንም ነበር።

ያቺን በጂጂ አንደበት ስታንጎራጉር የሰማናትን የጂጂን እህት ከነቁንጅናዋ፣ ከነድምጿ ከዓይን ያውጣሽ ብለን መረቅናት በየፊናችን። የአኔድ ሰሞን መነጋገሪያችንም ሆና ነበር።

በአንዱ ቀን ላይ፣ ደብረብርሃን ለሥራ ሄጄ በነበረበት አንድ ወቅት (በ1997 ዓመተ ምኅረት ገደማ)፣ አንድ ድሮ ድሬዳዋ ላይ "ተሃድሶ" ከሚባሉት የኦርቶዶክስ አዘማኝ ነን የሚሉ ወጣቶች መሐል ሆኖ የኅብረት ዝማሬ ያስቀረፀ፣ ታሪከኛና ጉደኛ ወዳጄ ብርሃኑ መንግሥቱ አንድ አዲስ ሲዲ ይዞልኝ መጣ እየፈነደቀ።

ምንድነው? አልኩት። ቃል አላባከነም። የሲዲውን ላስቲክ ቀደደና፣ በሽፋኑ የውስጥ ገፅ ላይ ፊርማውንና ስሜን፣ ቀኑን አኑሮበት "ይሄ ያንተ ድርሻ ነው፣ የእኔን ለራሴ ገዝቼያለሁ" ብሎ የራሱን ከማይለየው የቆዳ ቦርሳው አውጥቶ አሳይቶኝ እየሣቀ ሄደ።

እንዲህ ነው ብሬ🤩😊። ሲዲውን ተቀብዬ አየሁት። የሶፊያ ሽባባው አዲስ መዝሙር። የጴንጤ መዝሙሮች። እንዴ ባንዴ ከዘፈን ወደ መዝሙር? ምን ችግር አለው?

የጂጂ እህት ነች። ትታወቃለች። አሪፍ ፕሮሞሽን ትሆንላቸዋለች። በዚያ ላይ ልቅም ያለች ቆንጆ። የብዙ ሰውን ቀልብ ትስባለች። ስሟንና ዝናዋን፣ ታለንቷን አይተው ቀልበዋታል ማለት ነው። ፕሮቴስታንቶች። ("ተቃዋሚዎች"😀🥰)።

ስናዳምጠው ከረምን። እውነቱን ለመናገር ለክፉ አትሰጥም ነበረ። እኔ ግን ከመዝሙርነቱ በላይ በሶፊያ ውስጥ የማዳምጠው የጂጂን አይረሴ ቃና ነበር።

ብዙም አትቆይም። የጂጂ አፍላ የሙዚቃ ወራቷ ነበር። ጂጂያችንም እያከታተለች ተወዳጅ ዜማዎቿን አንቆረቆረችልን። አንዳንዴ ሳስበው እኛ የምናየው ዜማዎችን ነው። የድምፅን ውበት ነው። የስንኞችን ጥልቀት ነው። የሙዚቃን መሠናኘት ነው።

ግን የማይታይ፣ የማናስበው፣ ነገሬ የማንለው፣ የሰውልጅ ጥልቅ የብቻው ጭምት የልቡ ምት ደሞ አለ። ከሚፈነድቀው የሙዚቃ ምት ባሻገር፣ አርቲስቱ ገልጦ የመያሳየው የራሱ የተጠራቀመ የህይወት ብሶት አለ። ነዲድ የጓዳው ብቻዊ ሀዘን አለ። አብሮት የሚኖር፣ የሚከተለው፣ ለእኛ የማይነግረን፣ ከድምፁ ጀርባ የተሸሸገ አንዳች የህይወት ፀፀት፣ አንዳች የኑሮ ሸክም አለ።

ለእኔ የጂጂ ህይወት እንደዚያ ይሆንብኛል። እንደዚያ ይመስለኛል። ባሰብኳት ቁጥር የዜማዎቿ እንጉርጉሯዊነት አንጀቴን ያላውሰዋል። በጣም ጥልቅ በሆነ የስሜት ነዲድ ከታሸ ዜማዋ፣ በትዝታ ከበሰለ፣ ከተብሰለሰለ ስንኟ ባሻገር አንዳች ዓይነት ተካዥ፣ ናፋቂ፣ ተብሰልሳይ እንጉርጉሮ አለ ከጂጂ ሙዚቃዎች ጋር አብሮ ኩልል ብሎ የሚንቆረቆር።

ሳስበው ምናልባት ይሄ ተካዡና አስተካዡ በውስጠት አዋቂ በሙዚቃዋ ውስጥ የምናደምጠው አንዳች የስሜት ድባብ ይሆን.. ብዙዎቻችን ልብ ውስጥ ሰተት ብሎ የሚገባውና በማናውቀው መልኩ እንድንወዳት የሚያደርገን? እያልኩ ሁሉ እጠይቃለሁ።

ጂጂ እንጉርጉሮን ታውቅበታለች። ምናልባት በአንቀልባ ከምትታዘልበት ዕድሜዋ ጀምሮ ስትሰማው ያደገችው ተከትሏት የኖረ ድምፅም ይሆናል።

ዛሬ አላውቅም። ያኔ ግን ባገራችን እናቶች ያንጎራጉሩ ነበር እኛ ስናድግ። ማንጎራጎር ደግሞ ዜማ ብቻ አይደለም። ስንኝ አይደለም። የሆነ ብቻዊ ቅዳሴ ነው። ከውስጥ የሚወጣ ነፍስን የማርጊያ ቅኝት ነው።

በእንጉርጉሮ ውስጥ አንዳች የአምሰልስሎት ኃይል አለ። እንጉርጉሮ የአፍ ሳይሆን የልብ ነው። የሥጋ ሳይሆን የነፍስ ድምፅ ነው። ራሱን የቻለ ሜዲቴሽን ነው። "ትራንስ" ነው።

ካለህበት ኑሮ፣ ከገባህበት ስሜት፣ ከተጫነህ ድብርት ውስጥ ፀጉርህን እያሻሸ፣ ቁስልህን በቀስታ እየዳበሰ፣ እያባበለ ወደ ስክነት ዓለም የሚወስድህ በዜማ የታሸ የነፍስ መጓጓዣ ነው የኛ እንጉርጉሮ። ጂጂ ያ የእንጉርጉሮ ኃይል አላት። የነፍስን ጥያቄ በዜማ አውጥታ ማንጎራጎርን ታውቅበታለች።

አባ ዓለም ለምኔ ለእኔ እንጉርጉሮ ነው። የማያረጅ ውበት እያለች ጂጂ አባይን ስታዜምለት ዜማዋ ከአባይ በላይ ይሆንብኛል። ከነፍስ የተጨለፈ ሰማያዊ እንጉርጉሮ ነው።

አባይ ወዲያ ማዶ አንዲት ግራር በቅላ፣ ልቤን ወሰደችው ከነሥሩ ነቅላ... እያለ ሲነግረኝ ትዝታው ገደለኝ...። የማይታመን እንጉርጉሮን ነው የምትለቀው ጂጂ። በዘመናይቱ የኢትዮጵያችን የሙዚቃ ሠማይ ላይ እንጉርጉሮን ከፍ አድርጎ በሁለመናችን ላይ የሠቀለ፣ ያነገሠ፣ እንደ ጂጂ የሚያውቅበት ሰው መጥራት ይቸግረኛል።

ቀደም ሲልም ባሉት የቁጥር አንዷ የጂጂ አልበም ላይ ብሶትን አዘል ዜማዎችን ማግኘት ከባድ አይደለም። ካገር ርቀው በማያውቁት ባዕዳን እጅ ተመሪ ሆነው በሣህራ በረሃ ስለሚያቆራርጡ፣ ስለሚሰደዱ ሰዎች ጂጂ ያንጎራጎረችውን ዜማ ስሰማ ሁልጊዜ ውስጤ በጥልቅ የሀዘን ስሜት ይንቦጫቦጭ ነበር።

ጂጂ የምታዜመው ስለማን ነው? በበረሃ እየመሩ የሚወስዱትን ደላሎች በአንድ ቦታ ላይ "የሰው አዞዎች" ትላቸዋለች። በወንዙ ውበት ተማርከህ ልትዋኝበት ስትገባ፣ ያልታሰበ መቅሰፍቱን ይዞ እንደሚጠብቅህ አይምሬ አዞ አድርጋ ነው የምታቀርባቸው።

የበረሃውን መከራ የምትገልፅበት መንገድ በራሱ ያስገርመኝ ነበር። በዚያው አልበም ላይ ያገሬ ፀሐይ፣ ፀሐይ፣ ውጪ በወገኔ ላይ... እያለች የምታዜምበት አንድ የሙዚቃ ሥራ አላት።

ያንን ባለችበት አንደበት በዚያው አልበም ውስጥ የሣህራ በረሃዋን ፀሐይ የምትገልፅበት መንገድ ግን የራሷን የህይወት ጉዞ፣ የራሷን የስሜት ድባብ፣ የራሷን የውስጧን ስቃይ የተከተለ ነው። ከውብ ጌጥነት ወደ አቃጣይነት፣ አክሳይነት የሚሸጋገረውን የፀሐይዋን ግለት በብሶት እንጉርጉሮ ትገልፀዋለች የሣህራ ፀሐይ፣ መቋቋም አቃተኝ ሐሩሩን እያለች።

የተከፈለበት ማስታወቂያ!

ውሸት ነው ሲባል…Notcoin ከፈለ … Pixelverse የፍንጥር ሰጠ … Avacoin መላ በጠሰ…Dogs ጨላ አንበሸበሸ። Hamster እና Cats ትንሽም ቢሆን ሰጥተዋል። ስሙኝ። ትርፍ ጊዜያችሁን እርባን በሌለው ነገር ላይ ከምታጠፉ ቴሌግራም ላይ በኤርድሮፕ ገንዘብ ስሩበት። አንድ ነገር አለ። በጣም የሚጠቅም ወይም ቅድሚያ የምትሰጡት ስራ ወይም ተግባር ካለ ግዜያችሁን እዛ ላይ ማዋል ይገባል። ምንም ጥያቄ የለውም። ነገር ግን በዋዛ ፈዛዛ ሚባክን ካለ ግን ቢያንስ እዚህ ላይ ቢውል መልካም ነው። ምንም ግንዛቤ የሌለው ቅድሚያ ስለክሪፕቶ ወይም ኤርድሮፕ ጥናት እንዲያደርግ ይመከራል። ከዛ የተመቸው ይስራ ያልተመቸው ባላየ ይለፈው። አሁን ምጋብዛችሁ። የተረጋገጠ ቶን ከፋይ Airdrop ነው!

Ton ማለት የቴሌግራም መገበያያ ገንዘብ ነው። በወቅታዊ ምንዛሬ 1 Ton = 5 dollar አከባቢ ነው። ጓደኞቻችሁን በመጋበዝ ብቻ Ton ማግኘት ትችላላችሁ። ይሄ ከሌላው የሚለየው minimum withdrawሉ 0.1 ton መሆኑ ነው። ከዛ Verify በሆነ የTelegram Wallet በኩል የሰራነውን Ton ወደ ብር በቀላሉ ቀይረን ማውጣት እንችላለን። ይሄም 100% እውነት ነው። መልካም አዲስ ዓመት! ጆይን ለማለት…

👇👇👇

https://t.me/AblyBot/join?startapp=ref1067310339

የትምህርት ነገር

… …

የትምህርትን ሥርዓት በማሻሻል ብቻ በትምህርት ረገድ ለውጥ ማምጣት አይቻልም፤ ብቻ የምትለዋን አስምሩባት። መልካም የትምህርት ሥርዓት አቅርቦቱን እንደሚያሻሽለው ጥርጥር የለውም። በትምህር ፍላጎት ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ግን ውስን ነው።

ሰው ለምን ይማራል? ለምንስ መማር አለበት?

ይህን ጥያቄ መመለስ የትምህርት ፍላጎትን ለመረዳት ወሳኝ ነው። ትክክለኛው መልስ ሰው ለመሆን የሚለው ነው፣ ምሉዕ ሰው። ትምህርት ሰው ራሱን ፈልጎ የሚያገኝበት ጉዞ ነው። በዚህ ሂደት ከተፈጥሮ፣ አካባቢው፣ መሠሉ እና ሁለንተና ጋር ያለውንና የሚኖረውን መስተጋብር ይረዳል። ይህ ነበር የትምህርት ዕሴት መሆን የነበረበት።

በዚህ ረገድ፣ ትምህርት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አበርክቶ አልነበረውም ባይባልም፣ እጅግ ውስን ነው።

ከዚህ ይልቅ የትምህርት ፋይዳ፣ ከሥራ ቅጥር ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው። ትምህርት ልጆች በቀጣይ ህይወታቸው ኑሯቸውን የሚመሩበትን ገቢ ለማግኘት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ማስጨበጫ መሳሪያ ሆኖ ቆይቷል። ይህ እንግዲህ ውጤታማ ከሆነ ነው። በዚህ ረገድ የኛ ሀገር ትምህርት ውራ ነበር ማለት ይቻላል። ከትምህርት ይልቅ አጫጭር ስልጠናዎችና የሥራ ላይ ልምምዶች የላቀ ዋጋ አላቸው።

ሌላኛው የትምህርት ፋይዳ የስብዕና ግንባታ ነው። አነሰም በዛ የሀገራችን ትምህርት ለዚህ ዓላማ ጠቀሜታ ሲሰጥ ቆይቷል።

… …

የትምህርት አሥርዓት መሻሻል የተሻለ የትምህርት አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል። ፍላጎትንም በተወሰነ ደረጃ ያበረታታል፣ ራስን የመፈለግ፣ እውቀትና ክህሎት የማስጨበጥ እና ስብዕናን የመገንባት ሚናውን በአግባቡ ስለሚወጣ።

ብዙ ሰው ግን ልጆቹን የሚያስተምረው የወደፊት ህይወታቸው መልካም እንዲሆን በማሰብ ነው። ይህ ደግሞ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ ነው።

መንግስት ዋነኛ ቀጣሪ በሆነበት እና የቅመስፈርቱም ብቃት ባልሆነበት ሁኔታ የመማር ፍላጎት ይገታል፣ እውቀትና ክህሎትን የመሻት ጉጉት ይዳከማል።

ዜጎች በነፃነት በኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚሳተፉበት ዕድል በጠበበበት ሀገር፣ ሰዎች ለትምህርት የሚሰጡት ዋጋ ይቀንሳል። በነፃነት የማሰብ፣ የመኖር፣ የማምረት እና የንብረት ባለቤት የመሆን መብቶች በሚደፈጠጡበት አገር፣ እውቀትና ክህሎት ዋጋቸው ይኮስሳል።

… …

ምን ለማለት ነው?

አጠቃላይ የአገራችን ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ሥርዓት ሳይስተካከል፣ ትምህርትን ማሻሻል የማይቻል እንኳ ባይሆን እጅግ ከባድ ነው።

© Ja Liberty

የተከፈለበት ማስታወቂያ!

በInvitation ብቻ የዶላር ሽልማት። ለ500 ተወዳዳሪዎች በየ15 ቀኑ የሚሸልም። ከ500$ እስከ 10$። በውድድሩ eligable ለመሆን ከናንተ ሚጠበቀው ዋሌታችሁን ኮኔክት ማድረግ፤ በቻላችሁት መጠን ሰው መጋበዝ፤ ታስክ ስሩና 100k coin መሰብሰብ። በቃ አለቀ። አሁን ባለው ውድድር 6 ሰዎችን ብቻ invite ብታደርጉ ደረጃው ውስጥ ትገባላችሁ። 6ኛው ዙር ትናንት ነው የተጀመረው ከ15 ቀናት በኋላ ያበቃል።
ለመጀመር…

👇👇👇

https://t.me/cherrygame_io_bot/game?startapp=r_1067310339

የተከፈለበት ማስታወቂያ!

HOT ከካቲዝን የሚበልጥ ኤርድሮፕ ነው። አንድ ካት ሊስት ሲደረግ አንድ ዶላር ነበር። እናም ቻናሎች ላይ ግን በተደጋጋሚ ቢለቀቅም በተደጋጋሚ ስለሱ ቢወራም ብዙዎቻቹ እየሰራቹት አይደለም።

አንድ HOT ፕሪማርኬት ላይ 10$ ገደማ ነው። ትኩረት ሰጥታቹ ሥሩት።

Storage ሲሞላ በየ 6 ሰአቱ እየገባቹ ክሌም ማድረግ ነው። Boost አድርጉ። ባገኛቹ ሰአት Storage የሚለው ውስጥ በመግባት Boost ማድረግ ትችላላቹ።

በተጨማሪም ታስኮችን ስሩ ሰው ጋብዙ።

ያልጀመራቹ መጀመር ለምትፈልጉ

👇👇👇

https://t.me/herewalletbot/app?startapp=9438338