ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 (@bookshelf13)の最新投稿

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 のテレグラム投稿

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"
18,903 人の購読者
2,716 枚の写真
24 本の動画
最終更新日 27.02.2025 06:07

類似チャンネル

TIKVAH-SPORT
258,062 人の購読者

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 によってTelegramで共有された最新のコンテンツ


🦅 የሥነ — ግጥም ዘመነኛ መልኮች| overview
ባለንበት ዘመን ሥነ — ግጥም እያበበ ነው ወይስ እየሞተ?
🎈 Full Version | እሱባለው አበራ ንጉሤ

⨳ ሥነ — ግጥም ምንድነው?

የሰው ልጅ ከሥጋዊ ሥሪቱ በተጨማሪ መንፈሳዊ የኾነ ፍጡር ነው። ከሌሎች እንስሳት የሚለየውም በእዚሁ የመንፈሳዊ ሥሪት፣ አሳብና ስሜቱ ጭምር ነው። ስለዚህም የሰው ልጅ ፍላጎት በመብላት፣ በመጠጣት፣ በመዳራት ከሚገኙ ሥጋዊ እርካታዎች ይረቅቃል። ይህ ረቂቅ መሻት ደግሞ እርሱ ካለፈ በኋላ ለሚመጣው ቀጣይ ትውልድ ራስን በመግለጽና የኖረበትን የዘመን መንፈስ በመመርመር ለመተረክ በመትጋት ይገለጻል። ቃላት ተፈጥረው ለአፍአዊ ትርክት፣ ፊደላት ደግሞ ተፈጥረው ለሕትመትና ንድፍ ግልጋሎት ሲውሉ ይህንን የሰው ልጅ ነባር ፍላጎት ለሟሟላት ነበር። “ከሰው መርጦ ለሹመት፤ ከእንጨት መርጦ ለታቦት” እንደሚባለው ከቃላትም ደግሞ መርጠው ለሥነ-ግጥም ያውላሉ። ሥነ — ግጥም በአጭሩ የኖርንበትን የዘመን መንፈስ ለመግለጽ ያጨናቸው፣ ረቂቅ ስሜት የሚያጋቡ፣ ትርጉምና ውበትን አስተባብረው የያዙ የንዑድ ቃላት ስብስብ ነው ማለት ይቻላል።

⨳ ሥነ — ግጥም ለምን ይጻፋል?

አሜሪካዊው ገጣሚና ኀያሲ ዳና ጊኦያ ሥነ- ግጥም ከጥንታዊ የሰው ልጅ ኑባሬ፣ ዕድገትና ውስጣዊ ጉዞ ጋር ተያያዥነት ያለው የጥበብ ዘርፍ መሆኑን ያነሣል። ሥነ — ግጥም ሕልውናውም ከቅድመ ታሪክ (pre-history) ጊዜ አንሥቶ የነበረ ነው። የሰው ልጆች ታሪካቸውንና ጥበባቸውን በጽሑፍ መሰነድ ከመጀመራቸው በፊት የነበረ ኪነት እንደመሆኑ መጠን ሥነ ግጥም ለሰው ልጆች የህልውና ጉዳይ ነበር ማለትም ይቻላል። ነገሮችን ባሉበት ወይም በተከሰቱበት ሐተታዊ ኹኔታ እንደ ወረደ ለማስታወስ መሞከር ከባድ ፈተና ነው። የማስታወስ ክሂሎት እጅግ ተለዋዋጭና የማያስተማምን ነው። ስለዚህም ሰዎች ታሪካቸው፣ ባሕላቸው፣ እምነታቸው፣ ፍልስፍናቸው፣ ግላዊ ተመስጥዖና ኀሠሣቸው እንዳይጠፋና እንዳይረሳ ወደ ሥነ — ግጥምነት ያረቁታል፣ ያሻግሩታል። ሕይወታቸው በቃላዊ ሥነ ግጥም እየተነበነበ፣ እየተመደረከ መታወስ ይጠበቅበታል።

🦅

ጥንታውያኑ ሥነ — ግጥምን እንደ «Memory technology» ተገልግለውበታል። አሜሪካዊው ገጣሚ ሮበርት ፍሮስት «Poetry is a way of remembering what it would impoverish us to forget» ወይም «ሥነ ግጥም እንድንረሳ የሚያደርገንን የምናስታውስበት መንገድ ነው» በማለት ይናገራል። ስለዚህም ሥነ — ግጥም ለሰው ልጆች ከትውስታ ዝንጋኤ ጋር ትግል የሚገጥሙበት፣ ራሳቸውን ለመግለጽ የሚጣጣሩበት፣ ጀብዱን የሚተርኩበት፣ አማልክቱን የሚያመልኩበት፣ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት መንፈሳዊ ጸጋና መሣሪያቸው ነው። የሆሜር Iliad፣ Odyssey፣ የህንዶችን Mahabharata፣ የዳንቴን Divine Comedy፣ የጆን ሚልቶን Paradise Lost መሰል ጥንታዊ የገድል (Epic) ሥነ — ግጥም ድርሳናትን፣ እንዲሁም ከብሉያት ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ትንቢተ ዕዝራ፣ ትንቢተ ሕዝቅኤል፣ መዝሙረ ዳዊት፣ መጽሐፈ መክብብ፣ መጽሐፈ ኢዮብ ያሉትን በአብነት ማቅረብ እንችላለን።

🦅

ባሕልን ከዝንጋኤ ከመከላከል ባለፈ ሥነ-ግጥም የቃላትን ኃይል ለማጠንከርና ጉልበት ለመስጠት ይውላል። ገብረክርስቶስ ደስታ በመንገድ ስጡኝ ሰፊ ያላለቀ መግቢያው “አብዛኛውን ጊዜ ቃላት በግጥም ተቀርጸው በሚገቡበት ጊዜ ከትርጉማቸው በላይ አልፈው ተርፈው ይሄዳሉ” ይላል። ግጥም ከዝርው ይልቅ ለሰው ስሜትና ውስጣዊ ጆሮ ቅርብ ነው። በፕሮፖጋንዳ ያልዘመተው በሽለላና ቀረርቶ ይነሣል፤ በምክር ያልተገሰጸው በጥበባዊ ሥራ “እሺ” ይላል። እንዲሁም ግጥም ሀገራዊ ብልሽቶችን ለመታገል፤ ማኅበራዊ መበስበሶችን ለማረቅና የእኩልነትና የፍትሕ ድምፆችን ለማስተጋባት ጥቅም ላይ ውሏል።

🦅

በዓለም ላይ የነበሩ ትላልቅ አብዮቶችና ንቅናቄዎችን ከፊት ሆነው የመሩት ጠመንጃ ካነገቱ ተዋጊዎች ባልተናነሰ መልኩ ገጣሚያን ነበሩ። የጥቁሮችን የሰብዓዊ መብት መገፈፍ ወይም “Civil right movement” እንደ Maya Angelou, Nikki Giovanni, Margaret Walker, June Jordan ያሉ እንዲሁም፣ በተለያዩ የዓለም ጥግጋቶች የሕዳጣንን መበደል ይፋ አውጥተው ድምፅ የሆኑት ገጣሚያን ናቸው። ከእዚህም ባለፈ ብዙኅን ተስፋ ባጡበት፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አስተዳደሮች በተንኮታኮቱበት ወቅት ተስፋ እንዳለ በመንገር፣ ገብተው የወጡበትን ጨለማ በማመላከት ተስፋ የሰጡ፣ ኑሮን ያስቀጠሉ፣ የሕይወትን ሽታ ያሳዩ ባለቅኔዎች ናቸው።

🦅

በእኛም ሀገር “አዝማሪው ምን አለ?” ይባል ነበር። ነገሥታቱ የሕዝቡን ትርታ በአዝማሪዎች በኩል ያደምጡ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። በ1960ዎቹ የአብዮቱ ትውልድ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና በመኳንንቱ ፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድፍረት ይቀርቡ የነበሩ የኮሌጅ ቀን ሥነ — ግጥሞች የትግል እንቅስቃሴው አንድ መልክ ናቸው። ከዚያ ባሻገር በተለያዩ የደስታ፣ የችግርና የመከራ ጊዜያት በቃል የተሰናኙ ጥንታዊ ግጥሞችን ለትውስታ ብንከልስ ሥነ — ግጥም የህልውና ወይም የ«Necessity» ጉዳይ እንደሆነ እንረዳለን።

🦅

ባለመሰንቆ የገዘገዘው፣ ባለበገና የደረደረው፣ አባ ውዴዎች በአራራይ ያንጎራጎሩት ሥነ — ግጥም ልባች ድረስ ዘልቆ መንፈሳችንን ያነቃቃዋል። ያስተክዘናል፣ ያሳስበናል። ዘመን ያሳልፋሉ እንጂ፣ ጊዜ አያልፍባቸውም። የባለቀረርቶና የሸላይ የስንኝ ጉልበትና ዘራፋቸው በሰላም ሀገር ያዘምታል። ፍርሃትን አባርሮ ወኔን ያስታጥቃል። በአጠቃላይ የ “Dead poet society” ገጸ ባሕርይ የሆነው “John Keating” እንደሚለው “We read and write poetry because we are members of the human race” ግጥም የምንጽፈው የሰው ልጅ በመሆናችንና ከዚህ ተላላፊ እዳ ነጻ ልንሆን ባለመቻላችን ነው።

⨳ ዘመነኛ የሥነ — ግጥም ተግዳሮቶች

ባለቅኔ በዕውቀቱ ስዩም በኗሪ አልባ ጎጆዎች መክፈቻው «ግጥም የህያው ስሜቶች ምስክርነት እንደሆነ እናምናለን፤ ምናባዊ መገለጥ እንደሆነ እናምናለን፤ ለአባቶቻችን የአብዮትን ሰይፍ የሚስል ሞረድ፣ ለእኛ ፍለጋ /ኀሰሳ/ መሆኑን እናምናለን፤ ያልተንዛዛ ለቅሶ፣ ያልቆረፈደ ተረብ፣ ያልተዝረከረከ ፍልስፍና መሆኑን እናምናለን» ሲል ያውጃል። ከዚህ አንጻር ተነሥተን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተገጠሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ሰሌዳና በመጻሕፍት ሰፍረው ያነበብናቸው፣ የሰማናቸውና የተመለከትናቸው አብዛኛዎቹ ሥነ — ግጥሞች ከውስጣዊ መቃተት የመነጩ፣ መረሳት ስለሌለባቸው የተጻፉ፣ በጊዜ የማይደበዝዙ፣ ውበትና እውነትነታቸው እያደር እየገዘፈ የሚሄዱ ግጥሞች ናቸው ወይ? የሚለውን ጥያቄ የመመለስ የቤት ሥራ ይጠበቅብናል። ኀያሲ አብደላ እዝራ ለኤፍሬም ስዩም ኑ ግድግዳ እናፍርስ ለተሰኘ መጽሐፉ ባሰፈረው ድኀረ ቃል ላይ «ግጥም ስሜትን ለማፍካት፣ በሆነ ጉዳይ ለመብሰክሰክ፣ በውበት ለመደመም፣ ቢቀር ቢቀር በቋንቋው ንዝረት ለማገገም ይነበባል። አንብበነው እውስጣችን የሚፈነዳ፣ ለንዴት አሳልፎ የሚሰጠን፣ ለባይተዋር ነፍስ ሆነ ለሌላው ጉዳይ እንድንቆረቆር፣ ከህሊናችን እሚላወሰው በጣም ጥቂት ነው» በማለት ያጸናል።

🦅

አንዳንድ ጊዜ የሚጻፉም ሆኑ በመድረክ የሚቀርቡ ሥነ — ግጥሞች “ተመልካች ምን ዓይነት ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሥነ ግጥም ቢቀርብለት ይወዳል?” በሚለው ላይ ሊመረኮዙ ይችላሉ። በብዛት ርእሰ ጉዳያቸው ምን ላይ ያመዝናል? የገጣሚያኑ አቀራረባቸው፣ ድምፅ አጠቃቀማቸውና ተክለ ቁመናዊ እንቅስቃሴያቸው ማንን ይመስላል? ይህን መንገድ ለምን መረጡ? የጥበብ ቅኝቱ ገበያ ተኮር ሲሆን ገጣሚውም ሆነ ሥነ — ግጥሙ ይከሽፋል። ኀያሲና ገጣሚው ሰሎሞን ዴሬሳም በዘበት እልፊቱ መስከንተሪያው “ግጥምን የሚያረክሰው ያንዳንድ መስመሮች መበላሸት ሳይሆን፣ የሀሳብ ወይንም የስሜት ሀቅ ማጣት ወይንም ለገጣሚው ባይተዋር መሆን ነው።” በማለት ያጸናል። በዕውቀቱ ስዩምም «ገጣሚ ያላረገዘውን የማያምጥ፣ ያላማጠውን የማይወልድ፣ ያልወለደውን የእኔ ብሎ የማይጠራ እንደሆነ እናምናለን» ሲል ከሰሎሞን ጋር ይተባበራል።

🦅

ሥነ — ግጥም እንደ ሃይማኖት አንድ ወጥ ድንጋጌና ብያኔ የለውም። ስያሜው አቃፊ ቃል (umbrella term) ነው። ነገር ግን በባሕሪው የክዋኔ ጥበብ (performative art) እንደመሆኑ መጠን ራሱን በተለያየ መደብ፣ ቅርጽና አቀራረብ ሊገልጥ ይችላል። በዚህ ላይ የድኅረ ዘመናዊነት ጣጣ ሲጨመርበት ቀኖናዎች ፈርሰው ይበልጥ ለብያኔና ለዳኝነት ያዳግታል። ሆኖም ከያኒው ምን በአጉል ፈሊጥ ቢራቀቅ፣ በጄ ብሎ ቅጽር ቢነቀንቅ፣ ከፍ ሲልም ቢያፈርስ በሥነ — ግጥም ምንነት ዙሪያ መግባቢያዎች አሉ። ያን ልብ ማለት ያስፈልጋል።

🦅

በሀገራችን እንደ ጃዝ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ተቀናብረው የምንመለከታቸውና የምናደምጣቸው አብዛኛዎቹ የመድረክ ሥነ — ግጥሞች፤ በባሕላዊ የመሰንቆ፣ የክራር፣ የበገና ዜማ መሣሪያዎች ሲዜሙ ካደመጥናቸው ዘመን አይሽሬ ሥነ — ግጥሞች ጋር ለማነጻጸር ያለ አጃቢ ሙዚቃ ብናደምጣቸው ለጆሮ ይሰንፋሉ፣ ለልብ አይመቱም። ከዚያ በመለስ ይህ ልምምድ በራሱ ምጣኔ ያለውን፣ ቤት የሚመታውን (rhyme)፣ ሥልተ ምት (rhythm)፣ ቅርጽ (form)፣ እና መሰል ባሕርያት ኖረውት ምልዑ የሆነው ሥነ ግጥም፣ ካለሙዚቃ መሣሪያ አጀብ ለዓይን፣ ለጆሮና ለልብ የማይሞላ ተደርጎ እንዲሣል እያደረገ ስላለመምጣቱ መጠናት ይኖርበታል። እንዲሁ በአስደሳች ጥራት (quality) ታትመው የተሸጡ የሥነ — ግጥም መጻሕፍት፣ ቢያንስ በአንድ ዘለላ ሥነ — ግጥማቸው እንደ ዝርዉ ሥነ — ጽሑፍ፣ እንደ ወግ (essay) ላሉ ለሌላ የሥነ — ጥበብ ዘርፍ መቆስቆሻ ሆነው ሲጠቀሱ የማንሰማው ለምንድነው?

⨳ ሕትመትና ሥነ — ግጥም

እዚህ ጋር ደግሞ ወረድ ያልን እንደሆን ሌላ ተቃርኖ ያጋጥመናል። ወደ ወቅታዊ የሕትመት ገበያው እና የመጻሕፍት ግብይት ያመራን እንደሆነ ሥነ —ግጥም በአሳታሚያንም ሆነ፣ በአንባቢያን ዘንድ እየተገፋ እንዳለ እናስተውላለን። እጃችን ላይ በተከታታይ የገቡ መጻሕፍት በገጣሚያኑ አሳታሚነት የሕትመትን ብርሃን ያዩ ናቸው። ገጣሚያኑ የደከሙበትን ያህል እንደማይነበቡና እንደማይሸጡ ቢያውቁም የነፍስ ጥሪያቸውንና መቃተታቸውን ለማስታገስ ሲሉ የጻፉትን በግላቸው ተበድረውም ቢሆን የሥነ — ግጥም ሥራቸውን ያሳትማሉ። ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ላሳተመው የኮሌጅ ቀን ግጥሞች ስብስብ በጻፉት መግቢያ ላይ ሥነ — ግጥም የጻፍ ጻፍ ግፊት፣ በተለያዩ ምክንያቶች እውስጣቸው ሰርፆ ፋታ በነፈጋቸው፣ ለዚህ ግፊት መልስ ለመስጠት ሲሉ በሚያሰናኙ ገጣሚያን እንደሚጻፍ ይጠቁማሉ።

🦅

ከሕትመት ገበያው እና ካለመነበብ አንጻር ካየነው ሥነ — ግጥም ለጊዜው እየሞተ ያለ ይመስላል። ለአንድ ጸሐፊ ካለመነበብ በላይ ሞት የለም። ሆርሄ ሉዊስ ቦርሄስ “This craft of verse” በተሰኘ መጽሐፉ ኤመርሰን ዋልዶ ጠቅሶ ከመጻሕፍት ንባብ ጋር በተያያዘ እንዲህ ጽፏል፦ “a library is a kind of magic cavern which is full of dead men. And those dead men can be reborn, can be brought to life when you open their pages.” የሥነ — ግጥምም ሆነ ሌሎች መጻሕፍት በፊደልነታቸው ደረቅ ሲምቦሎች ናቸው፣ ትርጉምና እስትንፋስ የሚዘራባቸው መነበብ ነው።

🦅

የግጥም ንባብ ቢዳከምም፣ አድማጭና ተመልካች ግን አለ። በአንጻሩ ይህ ከመጻሕፍት ንባብ ጋር በተያያዘ እንደ ሕዝብ ጆሯችን ለማድመጥ እንጂ ዓይናችን ለማንበብ እንዳልሠለጠነ በከፊል ሊነግረን ይችላል። የሀዲስ ዓለማየሁ ፍቅር እስከ መቃብር ይበልጥ ዝነኛ ያደረገው መነበቡ ሳይሆን በወጋየሁ ንጋቱ እየተተረከ በራዲዮ መደመጡ ነው። ሀዲስ ዓለማየሁ በራሳቸው አንደበት “ወጋየሁ ከመተረኩ በፊት ቆይቷል ፍቅር እስከ መቃብር በገበያ ላይ። ግን እርሱ ካስተዋወቀው በኋላ ነው ያን ያህል ተወዳጅነትን ያገኘው።” በማለት ይመሰክራሉ። በሌላ አንጻር ቀደም ባሉ ዓመታት ለሥነ — ግጥም የነበረውን ወርቃማ ጊዜ በዓይነ ኀሊናችን ብንቃኝ፣ “ታዲያ የግጥም አፍቃሪያኑ አሁን ላይ እንዲቀዛቀዙ ያደረጋቸው ምክንያት ምንድር ነው? በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎችና መድረኮች ሥነ — ግጥም ሲታደም የምናየው ምዕመን ለምን የሥነ — ግጥም መጻሕፍት ለገበያ ሲበቁ ጠብቆና ተሻምቶ ሲገዛ አናገኘውም?” ብለን መሠረታዊ ጥያቄ እንድንጠይቅ ያነሣሣናል።

⨳ ሥነ — ግጥምን ወንዝ ማሻገር

በዚህ መሃል እጅግ የነጠሩ፣ እንኳን ለእኛ ለቀሪውም ዓለም በተለያየ ቋንቋ ቢተረጎሙ የሚተርፉ ሥራዎች በደጋፊ በማጣትና በማስታወቂያ እጥረት እስከጊዜው ድረስ ተደብቀዋል። አሁን አሁን በተለያዩ ክፍትና የኦንላይን መድረኮች ላይ በእንግሊዘኛ የሚቀርቡ የሀገር ልጆች የሥነ — ግጥም ሥራ ቢኖርም፣ ይህም በግል ጥረት የሚደረግ እንቅስቃሴ እንጂ ከጀርባ ድጋፍ አቅራቢ አካል ያለው አይደለም። እነዚህን ሥራዎች ገልጦ በማንበብና በማስተዋወቅ፣ ብሎም ሥነ — ግጥም ላይ የተጋረጡ ተግዳሮቶች ላይ እየተወያየ መፍትሔ የሚሰጥ የገጣሚያን ኅብረት የለንም። በራሳችን ቋንቋም በዓለም አቀፍ የሥነ — ግጥም መድረኮች ላይ እንድንወዳደር እና እንድንሳተፍ ጥሪ ለማቅረብ የሚሻ አካል ቢኖር ይሄን ጥሪ የሚሰማ ጆሮ ያለው አንድ ተቋም አለመኖሩ ያስቆጫል።

⨳ ሥነ — ግጥምና የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች

በኢንተርኔት ላይ መሠረታቸውን የጣሉ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች (applications and platforms) መዳበር የዓለምን ገጽታና የሰው ልጆችን ዕጣታ ፈንታ ሙሉ ለሙሉ ቀይሮታል። በሁሉም የሕይወት እና የሙያ መስክ ነገሮች እንደ ድሮ አይደሉም። ይህ ለውጥ እጅግ ወግ አጥባቂ (conservative) የሚባሉ ክፍለ ዓለማትን ሳይቀር የተወደረ ክንዳቸውን እንዲያጥፉ፣ በባሕል ጦርነት እየተሸነፉ እንዲሄዱ እያደረገ ይገኛል። ኢንተርኔት የዓለምን አንድ መንደርነት ወይም ግሎባላይዜሽንን እውን የሚያደርግ፣ አይቀሬነቱን ያስረገጠ እጅግ ኃይለኛ መሣሪያ ሆኗል። ደጅን ዘግቶ፣ ተገልሎና ለሌላው ዓለም ባይተዋር ሆኖ መቀመጥ እምብዛም የሚቻል አይደለም።

🦅

በሀገራችንም ያሉ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ተጽዕኖ ሲዘወር የምናየው ነው። በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ያሉ ወቅታዊ (contemporary) ከያኒያንም ከዚህ የቴክኖሎጂ በረከትና መርገም ተካፋዮች ናቸው። የትኛውም የሥነ — ጽሑፍ ሰው በዘመኑ ካለ ክስተት ራሱን ለማግለል ቢጣጣርም፣ ፈጽሞ ግን ማምለጥ አይችልም። ለብቻው ሌላ ዓለምና መሸሸጊያ ደሴት የለውም። በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የከባቢው ሰለባ ነው። በሀገራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለሚታየው የሥነ — ግጥም ጥበብ እና ሕትመት መነቃቃት በግልጽ በሚታይ መልኩ የፌስቡክ መተግበሪያ ጉልህ አስተዋጽዖ አለው። አሁን አሁን ደግሞ ቲክቶክ ያፈራቸው ገጣሚያንም አሉ።

🦅

ቀስ በቀስ እየከሰሙ እስከሚሄዱ ድረስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሥነ — ግጥም አብዮትና መድረኮች ተፋፍመው ነበር። ሥነ — ግጥም ከፒያሳና ከብሔራዊ የጥበብ ገዳም ወጥቶ በተለያዩ የአዲስ አበባና የክልል ከተሞች ተሰይሟል። ከዚያም ግዛቱን በማስፋት በመንፈሳዊ ተቋማት ሳይቀር ጉባኤ እስከማዘርጋት ደርሷል። ሆኖም ባለንበት ዘመን ሥነ — ግጥም ከመልካም ዕድል እና ከአስጊ ተግዳሮት ጋር የተጋፈጠ ይመስላል። ሥነ — ግጥም እንደ አንድ የጥበብ ዘርፍ እያበበ ነው ወይስ እየሞተ? ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን።

🦅

ከላይ በተጠቀሰው በአዝመራው መስፋት፣ በገበያው መድራት የመዘነው እንደሆነ ህልውናው አይካድም። በየጊዜው ከአዳዲስ ገጣሚያንና የሥነ — ግጥም መጻሕፍት ጋር እየተዋወቅን ነው። ማኅበራዊ ሚዲያ የአንድ ነገርን እሴት የምንለካበትን መለኪያ ቀይሮታል። የሥነ — ግጥም ይዘቶችን (content) ዋጋ የምንለካው ባገኙት እይታ (view)፣ በተወደዱበት (like)፣ በተጋሩበት (share)፣ ደግመው በተለጠፉበት (repost) መጠን ነው። ከዚህ አንጻር ካየነው በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ላይ ከፍተኛ የዕይታ መጠን ያስመዘገቡ የሥነ — ግጥም ከያኒያንና ይዘቶችን እንታዘባለን። ታዳሚያን በነጻና ገንዘብ እየከፈሉ የሚገቡባቸው የሥነ — ግጥም ዓለማዊ (secular) እና መንፈሳዊ ጉባኤያትም ወምበራቸው ጦሙን አድሮ አያውቅም። በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ መድረኮች ዝና በማትረፍ የተሸጡ፣ ከአንድ ዙር በላይ የታተሙ በጣት የሚቆጠሩ የሥነ — ግጥም ሥራዎችም ያጋጥሙናል።

🦅

ነገር ግን እነዚህ ውጤቶች በሙሉ ልብ የሚወሰዱ የሥነ — ግጥም እሴት እውነተኛ መለኪያዎች ናቸው ወይ? ተደማጭነትን በማሳደድ የተጻፉ አይደሉም? ማኅበራዊ ሚዲያ ቅኝት (Algorithm) ካልነቁበትና ተጠንቅቀው ካልያዙት ጠልፎ ጣይ ነው። ከያኒው ከሕዝቡ በፊት የሚቀድም ሳይሆን የተከታዮቹን ትርታ እያየ ገበያው ወደነፈሰበት እንዲነፍስ የማድረግ ጠባይ አለው። በእንዲህ ዓይነት ወጥመድ ለሚወድቁ ገጣሚያን ጸጋዬ ገብረ መድኅን በእሳት ወይ አበባ መግቢያው ብሮኖውስኪን አስታክኮ “በኪነ ጥበብ የተሰጥዖ ግዳጁ ተዳክሞ ተጭለምልሞ ነፍሱን ሲያሳድፍና የስሙን ጩኸት በምጥ በማስተጋባቱ ብቻ ዕለታዊ ተደማጭነትን እንደ ጥቅም ሲቃርምና ሲዘርፍ ግን ‘ያማ የኪነቱን የእውነታ አቅጣጫ ስቶ ብዕሩንም አሳተ ማለት ነው” ይላል።

🦅

ሌላኛው ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሣው ተግዳሮት ወደተነሣንበት የሥነ — ግጥም መፍቻ ይመልሰናል። የሰው ልጅ ከሥጋዊ ሥሪቱ በተጨማሪ መንፈሳዊ የኾነ ፍጡር ነው ብለናል። ግጥም ተፈጥሯዊ ሥሪቱ መንፈሳዊ ሲሆን ሥጋን ለማገልገል ሲውል ግን ጥንቃቄ ይፈልጋል። ምክንያቱም የግጥም ውበት የሚጓደለው ለሥጋ ሲባል ይህንን መንፈሳዊ ጥበብ አመቻምቾ ማቅረብና መሸቃቀጥ ሲጀመር ነው። በቀደሙት ዘመናት “court poets” የሚባሉ ለሕይወት ዘመን በገዢዎች የሚቀጠሩ ገጣሚያን ነበሩ፤ የእነዚህ ገጣሚያን ሥራም እግር በእግር እየተከታተሉ ገዢዎቹን ማሞገስና እንጀራ መብላት ነው። እንጀራ አጉራሻቸውን፤ ድርጎ ቆራሻቸውን ላለማስቀየም ሲሉ ከግጥም መንፈሳዊ ጠባይ በተቃራኒው በመሄድ በአድርባይነት ያገኙትን ሲቃርሙ ይኖራሉ። ቅኔያቸው “ካለው ተወለድ ወይ ካለው ተጠጋ” ይሆንና ረብ ያለው ሥራ ከማበርከት ይልቅ የጊዜን ፈተና የማይቋቋም ወገቡ የተመታ ጎታታ የቃላት ድሪቶን ሲያጭቁ መኖር ይሆናል። በዚህ መልኩ ያጣናቸው ብዙ ባለተሰጥዖዎች የሚያስቆጩ ናቸው። እዚህ ጋር ሮበርት ፍሮስትን መጥቀስ ያዋጣል፦ “poetry is a condition not a profession”

🦅

ሥነ — ግጥም ንዑድ ክቡር ቤተ መቅደስ ቢሆን ገጣሚ ደግሞ ካህን ወይም ነቢይ ነው። “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለእዳ” አይቀበለውም” ነውና ገጣሚያንም የግጥምን መልክ ወደቀድሞ ቁመናውና ሀቀኝነቱ ለመመለስ ትልቅ ሥራ ይጠበቅባቸዋል። እነዚህንና በዚህ ጽሑፍ ያልተዳሰሱ ተግዳሮቶችን ከግምት አስገብተን ሥነ — ግጥም ባለንበት ዘመን እያበበ ነው ወይስ እየሞተ? ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው አንድም በተስፋ ያበበ፣ ሁለትም በድርቀት የተመታ መንታ መንገድ ይሆናል።

Cc ፡ Yohanes Molla, Theodros Atlaw

© Esubalew Abera Nigussie

"ታላቁ ሙዚቀኛ ከያሬድ ትምህርት ቤት ጀርባ ከአልጋው እንደ ተነሳ በእንቅልፍ ልቡ ለመጀመሪያ ፒያኖ ሲነካ የወጣው ድምፅ 'ጉዴ !' ነው .....
የድንግልና መዝገብ ጠባቂ መልአክ ደብተሩን አውጥቶ ኢትዮጵያን ፈልጎ አዲስ አባን ፈልጎ ጨርቆስን ፈልጎ የልጅቷን ስም ሰረዘ ....ከስሟ ፊት ለፊት በግዕዝ 'ጉዴ!' ብሎ ፃፈ....
አገልጋዩ፡ 'ምን ላድርግ?' ሲለው
'እጃቸውን ወደ እኔ አቅጣጫ ሲዘረጉ ብታይ እንዳላየ ሁን፣
ሲጮሁ ብትሰማ እንዳልሰማ ሁን፣
ተበሳጭተው ቢነዱ፣ ጢሳቸው እዚህ ቢሸትህ ያላሸተትክ ሁን፣
ብትችል የሞተ ምሰል፣
ይሄን ሁሉ ያልኩህ ካልሆነልህ ራስህን ከሰማይ ወደ ምድር ጥለህ እግሬ ተሰብሮ ታምሜአለሁ ብለህ ተኛ፣ ገባህ ከርፋፋ? '" ገጽ 321

"የሚያምር መኝታ ቤት ነው:: አልጋ ላይ ገፍቶ ጣለኝ አለ አይደለ በጣም ሳይሆን ዐይኖቼን በፍርሃት ጨፈንኩ:: አልቅሽ አልቅሽ አለኝ፡፡ የስሜት ሞገድ አስሮኝ የሆነች ምክንያት በደንብ የማትገባኝ በትንሽ ቀዳዳ……… ጩልቅ ብላ ገብታ…….የቀዳዳዋ ጠባብነት ወይኔ እማዬ ምንድነው እያልኩ አለ አይደለ በቃ ሐብቴን ላጣ እንደሆነ...…እግሮቼ መሃል ተጨብጦ እንደቆየ ሽልንግ የሚሞቅ ለስላሳ ነገር ይጫነኛል። እሱ ፊቱ በወዝ ተሸፍኖ ይለፋል፡፡ አለ አይደለ ዓይኖቹ ፈጠው ነበር፡፡ ዓይኖቹ ሲፈጡ በቃ እንዲህ ይፈጣሉ ቧ ምናምን፡፡ ዓይኖቼ ፈጠው የሚያዩት አንድ ቦታ ነው… እዛ ኮመዲኖ አለ እዛ አንድ ቴፕና አንድ የተከፈተ ካሴቱ የወለቀ ጥቁር ወክማን አለ እዛ ግድግዳ ላይ ሬክላም አለ………የሚያስፈራ መነፅር ያደረገ ሰውዬ እሱ ላይም 'ተርሚኔተር' የሚል ፅሑፍ ያለበት…..የልጁ የግራ ጡቱ ጫፍ የዛገ አስር ሳንቲም ይመስላል፡፡ ወደ ጆሮዬ ያጎነብስና 'ነፅዬ' 'ነፃነትዬ' ይለኛል:: ደረቱ ላይ ከመሃል አንድ አራት ፀጉሮች አሉ፡፡ የፈራሁት ደረሰና ጮኸኩ፡፡ የፈራሁት ነገር እንደ ሆነ ገባኝ፡፡ ስጮህ አፌን በእጁ ያዘኝ አንጎሌ በተከታታይ በተለያዩ ሰዎች ምስል ሞላ፡ እማማና እማማ(ጋቢ ለብሳ ለፀጉሯ ውሃ ሳፈስላት: ውሃው ቀይ ነው) ክርስትና እናቴ ዘውዲቱ (ስትጎነጉነኝ፡ ጣቶቿ ብርማ ይሆናሉ) በር የከፈቱልን አሮጊት እንኳን አልቀሩም(እሳቸው 'አንቺ ልጅ! አንቺ ልጅ ' ይሉኛል):: በአፉ አፌን ዘጋኝ፡ አፉ ውስጥ ጮኸኩ፣ ከዛ በቃ ያለሁበትን። ረሳሁ። " ገጽ 322

***እያንዳንዱን ትርክት ብዘረዝር ደስ ባለኝ። ግን አሰልቺ እንዳይሆን ስለፈራሁ እዚህ ላይ ላብቃ። ሰባቱንም ትርክቶች በጣም ወድጂያቸዋለሁ። እንደተለመደው ኦ አዳም ከማለት በቀር ሌላ ምንም ማለት አልችልም። በመጨረሻው ታሪክ የመጨረሻ አንቀጽ እንሰነባበት...

"የቀልሽ ልጅ የካሌብ ዐይኖች ከኤምሲ ሃመር አይበልጡም? ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ከውስጥ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለችው ማርያም ከዚያች አቴቴ የበለጠ ማን እህት አለኝ.. ሐሩሩ ቢያስጠማኝ ቄጤማ መሃል እንደ ጣኦስ አጎንብሼ በአፈር ያማረ የለገዳዲን ቢሻን እጠጣለሁ…….. ቢርበኝ ከእናቴ መዳፍ ብልቅጥቅጥ ያለ ፈንድሻ እዘግናለሁ………… ሴትነቴ ቢገፋፋኝ የቀልሽ ልጅ ምን አለኝ…... በዐይኖቹ ሁሌ ባቶቼን እምጣ እምጣ እምጣ እንዳደረጋቸው ነው..... ይሄ ቡዳ. የሚያላምጥ ያላምጠውና…... " ገጽ 337

© Art of Tigest

"ፖለቲካ ነፍሳቸው ከጠፋና ሕልማቸው ከተዳፈነ አንዳንድ የዕድሜ እኩያዎቼ ጋር አነፃፅረው ጉዞዬ ብዙ ጀብዱ የሌለው 'ምስኪን' እንደ ኾነ ሁሉ ሊነግሩኝ የሚፈልጉ 'አራዳ ነን' ባዮች ይኖራሉ፡፡ ያልገባኝን አድርጌ አላውቅም፡፡ ለምሳሌ ማርታ ሚስቴ የሆነችው አውቄአት ነው:: ያገባኋት ባልቻ ለመማር ሰባተኛ ክፍል ከገባሁበት ጊዜ ጀምሮ ስለ እሷ በቂ መረጃ ሰብስቤ ነው:: በቂ ጥናት አድርጌ ነው:: (ገና ስወዳት ልጅነቷን ለማማለል...… አየለ ጋና ካስተማሩኝ ጅምናስቲክ ጥቂቶቹን፣ ከስንታየሁ ሳህሌ አክሮባቶች ቀላል የሆኑትን ሁለቱን ሳር ሜዳ ላይ ወስጄ አሳይቼአታለሁ፡፡ በዚህም ተማርካለች) (ልኡል መኮንንም ስማር ዘጠነኛ ክፍል ጎኔ የምትቀመጠውን የፀሐይ ለገሰን ጠይም ውበት አየሁ፡ ማርታዬንም ከእሷ አወዳደርኩ፣ በዚህም ጠይሞች የሚጋሩት ረቂቅነት ገባኝ) ከሁሉ ከሁሉ ደ'ሞ የበለጠ አፍቅሬአት ነው፡፡ ከቤቷ ተነስታ አቶቡስ ማቆሚያው እስክትደርስ ቂጥዋን ምን ያህል ጊዜ ግራና ቀኝ እንደምታወዛውዘው ቆጥሬአለሁ፡፡ ሳታየኝ እንዳለሁም ሳልነግራት ከኋላዋ ተከትዬ፡ ያን አስገራሚ የጎረምሶችን ፊት የጠፋ አረማመድ ስቆጥር ጊዜዬን በከንቱ ያበላሸሁና ልቦናዬ የተሰረቀ መስሏቸው የሳቁብኝ በኋላ ፖለቲከኛ የሆኑ 'የነቁ' ወዳጆቼ ነበሩ፡፡ ፖለቲከኛ ለምን እንደሆኑ፣ እንዴት እንደሆኑ፣ ምን እንደሚያውቁ፣ በዝርዝር ምን እንደሰሩ አሁን ስጠይቃቸው የሚናገሩት ነገር ባዶ ሊሆን ምንም አይቀረው…….. ከዚህ ዓረፍተ ነገር ቀጥሎ እንዳለው ቦታ ፡
~~~~~~~~~~~~~~ ለመሆኑ ማርቲ ስንት ጊዜ አወዛወዘችው ያን ነገሯን? ሁለት መቶ አርባ ሰባት ጊዜ። አንድ|–ግራ፡ ሁለት|–ቀኝ። እንዲያ እንዲያ እያለ። " ገጽ 234

"ከአለማየሁ ጋር ስንበላ የምሳ ቦታ የምመርጠው እኔ ነኝ ......ብዙ ጊዜ ሜዳ ላይ መብላት እወዳለሁ:: ሜዳ ላይ ዐይኖቼን የሚስቡ ነገሮች አያለሁ:: የክፍላችንን አንድ ተማሪ አይና ስለእሱ አወራለሁ ኳስ ሲጫወቱ አያለሁ ዘሎ ለመግባትም ይቀርበኛል:: መማሪያ ክፍል ውስጥ የምንበላ ከኾነ ግን ብዙ ጊዜ የምሳ ሰሐኑን ማየት አለብኝ ይሄም ምርጫ ሳላቋርጥ ያከከ እጁን እንዳይ ያስገድደኛል፡፡ ከአለማየሁ ጋር ስበላ በማይገባኝ ምክንያት ትዝ የሚለኝ የእናቱ የውስጥ ሱሪ ነው:: ማሰብ አፍራለሁ………ግን በአይነ ሕሊናዬ እንደ ዜፔሊን ጥየራ በስድስት ኪሎ ሰማይ ላይ እየተንሳፈፈ ሲመጣ አየዋለሁ………መርካቶ ላይ ጥላሞቱን ይጥላል………ሕዝብ ወደ ላይ እያንጋጠጠ ያጨበጭባል………ወደ ቢሾፍቱ እየተንሳፈፈ ያልፋል… የአየር ሐይል ፋንቶም ጀቶች ደብድበው እስኪጥሉት………ስድ ፅላሎቴ ሳቄን እንዳያመጣው ቶሎ ዐይኖቼን ስገልጥ የማየው ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ሁለት አጥቆች ያህል የተተከሉትን፣ ተተክለው የሚፈተፍቱትን እከክ የፈሰሰባቸውን የአለማየሁን ቀኝ እጅ ጣቶች ነው፣ አመድ የመሰለ የዘመዴ የአምባር መዋያ ነው አንዳንዴ የማስበው ሐጢያቴ ገብቶት እናቱን እየተበቀለ ይመስለኛል......" ገጽ 253

"አባቴ ጴንጤ እናቴ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ነበሩ። የሚገርመኝ አባቴ ጴንጤ ሆኖ የሚበላው በግ ትልቅነት በከባድ ከፆሙት ከጎረቤቱ ኦርቶዶክሶች መብለጡ ነው:: አንዳንዴ መፅሐፍ ቅዱሱን በእጁ ይዞ እያራገበ 'እኔና እናትህ በአንዳንድ ነገሮች እንለያያለን' ሲለኝ ማሰብ እገደዳለሁ……..ምክንያቱም ቢያንስ 'ክርስቲያን' የሚለው ባያገናኛቸው ሆድያን' የሚለው ወይም በቀጥታ ቃል 'ዱለታውያን' ሳያገናኛቸው አይቀርም በሚል……..ግን አልናገረውም)" ገጽ 269

"ውስጥ ሱሪዬን ተደጋግሞ አጥር ላይ ሲዘረጋ ካየ አባቴ፡ 'አጥር ላይ አታስጣ አላልኩህም! ተላላፊ መንገደኛ መዥረጥ አድርጎብህ ይሄድና ጉድህ እንዳይፈላ!' ይለኛል። በልቤ 'ይሄን ቀና ብሎ አይቶ እንኳን የተመኘ የተረገመ ነው' እላለሁ። አንዳንድ ጊዜ ከሃሳቦች የበለጠ እነሱን ተሸክመው የሚመጡት ቃላቶች ያበሳጨኛል። ለምሳሌ 'መዥረጥ' ማለት ምን ማለት ነው? ቃሉን ስሰማ ፍጥነት ይታየኛል፡፡ ቃሉን ስሰማ ቆራጥ ጎታች ይታየኛል። ቃሉን ስሰማ ለዓይነሕሊናዬ የሚነበበው ሊሰየም የማይችል ብሌን ፈታኝ ውልብታ ነው። የውስጥ ሱሪዬ እንኳን በርጥቡ ይቅርና ደርቆ ለመሸከም ሁለት ሰዎች ኋላና ፊት ኾነው በትከሻቸው ላይ አጣና አጋድመው እዚያ ላይ ___አስተኝተውት ነው:: 'መዥረጥ' የተሰኘው ቃል ለውስጥ ሱሪዎቼ አይሰራም)" ገጽ 271

*** (ከሽልንጓ) የመጨረሻዋ የቀበሌ 01 ድንግል የወደድኳቸው አንቀፆች...

"ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ግን አላውቅም:: አንዳንድ ጊዜ ሳቁን ብቻ አስባለሁ:: ዝም ብሎ ሲስቅ ሲስቅ ሲስቅ:: ፊቴን ትራሴ ውስጥ እቀብርና በትላልቅ ጥርሶቹ ሲስቅ አስበዋለሁ:: አንዳንዴ አጣጥለዋለሁ... ጥርሱን እንኳን አይፍቅም እያልኩ አለ አይደለ በልቤ። ከዛ ሲስቅ ግን ሀይኖቹ ሲጨፈኑ ልቤ ይነዝርብኝና ፊቴን አዞራለሁ:: ከዕንብርቴ በታች ለሰስ ያለ እሳት ይነሳል. ይህቺ እሳት ድንገት ብታፈተልክ በሚያሳዝንና በሚያሳፍር መልክ ሰደድ ሆና የምታቃጥለኝ ይመስለኛል:: ወሬውን አስቁሜ ትቼው ቤቴ መግባት እፈልጋለሁ፡፡ ራሴን እየገፋፋሁ ያልጨረስኩትን የማድ ቤት ስራ እያሰብኩ እራሴን እየገፋፋሁ አለ አይደለ ቢላውን አላጠብኩትም፡፡ የሽንኩርቱን ልጣጭ አልሰበሰብኩትም:: የቡታውን እሳት ከፍ ካላደረኩት የድንቹ ወጥ ለራት አይደርስልኝም :: የመሳሰለ………እቤት ከገባሁ በኋላ ደ'ሞ የማስበው አብርሃምን ነው፡፡ አለ አይደለ ወሬውን፡፡ ከዛ ራሴን ለምን ትቼው መጣሁ ምናምን እላለሁ፡፡ ከዛ የማስበው እየተጫወተ የነካካኝን ቦታ ነው.....እጄ ጋ ምናምን…….ጭኔ ጋ ምናምን…….ከዛ ሲነካኝ የወረረኝን ነገር፡፡ ልቤ ደጋግሞ እየፈሰሰ ደጋግሞ ሲሰበሰብ ምናምን..." ገጽ 294

"ድንግል' የሚባለው ነገር ሁልጊዜ ለዐይን የሚከሰት 'ያልጀመሩ' ወጣት ልጃገረዶች እግሮቻቸው መሃል ተሸክመው የሚዞሩት ለጋ ቅቤ ውስጥ እንደተነከረ ሁሉ የሚያብለጨልጭ ደቃቃ ድቡልቡል የክትፎ ስጋ ይመስለዋል፡፡ ይኼም ቀን ያለ ዕለት በዕድለኛ ወይ በደፋር ወንዶች ጣልቃ ገብነት በየአልጋው ላይ፣ በመንገዱና በየወንዙ ዳር የሚጣል፡፡ ይህን ድቡልቡሌ ነገር--በደምና በጅማት ዕድሞ ውስጥ የተጀጎለ ሳትጠብቅ ሳትጠረጥር ማውለቅ አለበት...." ገጽ 299

"በጠለለ ማታ በአልኮል የነደዱ ወይዘሮዎች በሳቅ እየፈረሱ………ጎረምሳው ላብ በላብ ነው እንደ ወጠጤ ፍየል ይሸታል ወጠጤው:: በቀዝቃዛ ማታ ከጥላዎች ፈቀቅ ብሎ የድፍን ጨረቃ ብርማ ወዝ እሱ መደብ ሆኖ የምታየው የጎረምሳው እጅ ትልቅ ነው……ትልቅ ጥቁር ነው………ደም ስሮቹ ወፋፍራም ናቸው:: ከፊት ለፊቷ ቀሚሷን በቀስታ አንስቶ ወይ በልፊያ መሃል በሃሳዌ እምቢ አንደበት ስታገረገር ግን ሳይቆይ የመሳሳም ትንፋሽ ነው……የሆነ ነገር ጉሮሮዋ ውስጥ ሲሰነቀር ትደነቃለች ትደነቃለች ፍርሃትም ፍርሃቷም…... አንዱ ጆሮዋ ወደ ማ'ድቤቱ አቅጣጫ ኮቴ ሊሰማ መንገድ ላይ እንደ ቅጠል ያርፋል፡፡ ፊቷን በእጆቿ ሸፍና ለሩብ ሰዓት የሚያንቀጠቅጣት እንግዳ ስሜት እስኪበርድላት እየጠበቀች፡፡ ከውስጥ ሱሪዋ ጠል ይረግፋል በሚያዘግም ፀጥታ::"ገጽ 311

ከካርታ ላይ በቀላሉ በራሳቸው በዜጎቹ ምሬት መሰረዝ ሊፈፀም አይችልም? በየቀኑ የምናያቸው አልባሌ የመሰሉት ቅናትና ምቀኝነት (የኤቲክስ ፈላስፎች ማስተር ኢሞሽንስ” ይሏቸዋል) ረቀቅ ባለ ስልት ስማቸው ግን ሳይጠራ በሆነ ቁም ነገር በመሰለ የፖለቲካ አጀንዳ ስር ቢዋቀሩስ? ቢዘገይም አገር ማጥፊያ ሞተር እንዲሆኑ ቢቀመሩስ? እናቴ እየተራገመች መሞቷ ምናልባት ምንም ማድረግ ካለመቻሏ ጋር የተያያዘ ሆኖ ይሆን? ውድ ፍትህ ካልተገኘ በርካሽ አቅመ ቢስ እርግማኗና ፍልስፍናዋ ለመገላገል?" ገፅ 128-129

“መወለድህ ትዝ የሚልህ ስታፈቅር ነው:: በጣም ሲከፋህም ትዝ የሚልህ መወለድህ ነው:: የመጀመሪያው እንዳትሞት፣ የሁለተኛው ቶሎ ለመገላገል፡፡ አንድ ነገር በሕይወቴ አድርጌአለሁ:: እርግጠኛ ነኝ: ባይረባም አንድ ሰው ወድጄ ነበር፡፡ አቤት አዲስ አባን እንደ ወደድኳት መሬቷን በርከክ ብዬ መሳም ነው የቀረኝ፡፡ ሃብት አልፈለኩም፡፡ እሱ አብሮኝ ካለ ምን እንደምበላ ትዝ ብሎኝ አያውቅም፣ ይኼው አላህ ምስክሬ ነው:: እሱን ለማስደነቅ ሹመትና ዶክተርነት ሌላ ምናምን አልነበረም:: ሺህ ዶክተር ብትሆን የሚያያይዝህ ፍቅር ከሌለ ሜዳ ላይ የምትቀሩት አንተ፤ መድሃኒት፤ ገንዘብና ጀርም ናችሁ።" ገፅ 129

***የአዳምን 'በለስ' የሚለውን ትርክት አንብቦ ዘፍጥረትን በተለመደው አይን ማየት በጣም ከባድ ነው። እጅግ በጣም ያስደነቀኝ፣ ፍልስፍናው ያስገረመኝና ያዝናናኝ ትርክት ነው። የአዳም የፈጠራ ጥበቡ ወደር የለውም። እግዚአር አዳምን ነበር ዘፍጥረትን ጻፍ ብሎ ማዘዝ የነበረበት የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ ብዬ አምናለሁ። 🙂 እስቲ እንዳይሰለቻችሁ ዘለል ዘለል እያልኩ የጣመኝን አንቀጾች ላሳያችሁ..

***በለስ

***ዛፏ

"ከነዚህ ሁሉ መሳጭ ተክሎችና አነሁላይ የተፈጥሮ ጣዕመ ዜማዎች ዘልቃ የምትታይ የሐመልማልና የቀለም ድምብል የመሰለች፣ የቅጠሎቿና የፍሬዎቿ ሕብረት ዐይንና ልብ የሚስብ ዛፍ አለች። ከሌሎቹ መለየቷን ለማሳየት ዐይነት ሳይሆን አይቀርም ዙሪያዋን በአትክልተኛ የተከረከመ የመሰለ ሪም አለ፡፡ ዛፏ ከላይ እስከታች ዐይን በሚማርኩ እና ጠረናቸው በሚመስጥ ፍሬዎች ከአመት ከአመት ትሸፈናለች። ከዚህች ዛፍ ፍሬዎች ግን ማንም በፍፁም ለቅሞ እንዳይበላ እግዜር በተባለ በዋናው ሐላፊ ተከልክሏል፡፡" ገጽ 136

***የሰይጣን ጥያቄዎች ...

"ሰይጣን ጠላቱ እግዜር ፍፁም ዓለም ፈጥሮ እንደማያውቅ ከረዥም ጊዜ የኑሮ ልምዱ ይረዳል፡፡ እነዚህም 'ሰው' የተባሉ ፍጡራን ፍፁም አለመሆናቸው ከሌሎች መላዕክት የበለጠ ይገባዋል፡፡ ሲጀመር የእግዜር ጓደኛው አገልጋዩና አማካሪው አልነበር? የጓዳ አዋቂ ነው:: እግዜር እኒህ አዳምና ሔዋንን የማይጐልበት አትክልት ቦታ ውስጥ አስቀምጦ ጥያቄ የማይጠይቁ፣ የማያጉረመርሙ፣ ተቃራኒ, ጐን የሌላቸውና የማይጋጭባቸው እንስሳት አስተኔዎች ፈጥሮ ፍፁም የሚታዘዝለት አለም አቀናብሮ ከልሏል:: ይኼ ፍርሐት ነው:: ሰይጣን ከቀድሞ ልምዱ እግዜር የረቀቀ ፈሪ እንደሆነ ያውቃል፡፡" ገጽ 138

"ሁሉን ነገር ሰጥቶ የዚህቺን አንድ ዛፍ ፍሬ መከልከል ምን ይባላል? የሰይጣን የመጀመሪያ ጥያቄ ይኸቺ ነበረች… ለምን? ደብቆ ከፈጠራቸው በኋላ ስለዛፏ መኖር ሰዎቹ ካልተናገሩ ወሬውን ማን ወደ ውጭ አወጣው? መቼም ዐይን ከሌለ የሚታይ ነገር አይሠራም፡፡ ሆድ ከሌለ የሚበላ ነገር አይፈጠርም፡፡ ስለዚህ ሰይጣን በዚህ ፍፁም በሆነች ገነት ውስጥ አንድ የጐደለ ነገር እንዳለ ገባው:: የጐደለውን ነገር ለማወቅ ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ እግዜር 'ፍጡሮቼ በእኔ አምሳል የተቀናበሩ ፍፁም ናቸው' ብሎ ጉራ ቢነፋም ነጭ ወሬ እንጂ ፍፁም እንዳልሆኑ ከበለስ ዛፍ እዚያች ገነት ውስጥ መተከል በቂ ግንዛቤ ማግኘት ችሏል፡፡ ሰይጣንን ብልህ ያደረገውና በሰማይ ቤት ያስጠላው ከቃል” ይልቅ ድርጊት! የድርጊት ያለህ! ማለቱ ነው፡፡ በቀላል አማርኛ ሆድ ሰርቶ፣ የሚበላ ፍሬ አበጅቶ፣ እነዚህን ጎን ለጎን አድርጎ፣ 'አትብሉ' ማለት ያ ፈተና ነው:: ወሬውስ በራሱ በአምላክ የተበተነው በተዘዋዋሪ እነዚህን ሰዎች የሚፈትን ከይሲ ፍለጋ ሊሆን አይችልም?" ገጽ 139

****ወይ ሶፍያ...

"ኦ! አስታርቴ ኦ! ዛር! ኦ! ሶፍያ! ውብ ሶፍያ፡፡ ተጓዥ፣ ሒያጅ፣ ሰጤ ዛር ሶፍያ:: ሠይጣንን እስከ አሁን የሚያበሽቀው እሷን ማጣቱ ነው፡፡ ለአዳም ከሔዋን በፊት መጀመሪያ ለሚስትነት ወይም ለደባልነት የተመደበችለት ሴት ዛሯ ሶፍያ ነበረች፡፡ የገነትን እድሞ የረበሸች፡፡ የሰበረች፡፡" ገጽ 139

"የእግዜር ችሎታውና ድክመቱ ትዕግስቱ ነው:: ትዕግስት ያበዛል:: ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን ብቻ ያበዛዋል:: ሶፍያ ስትሳሳት በዝምታ እያየ ስህተቷን ይቆጥራል:: ወይም ምናልባት እንደሚወራለት ያህል ወደ ፊት የሚመጣውን ነገር አያውቅም:: ገማች ነው። የፈጠረው ፍጡር ወደ ፊት ምን እንደሚመስል፣ ወይም ወደምን/ ማን እንደሚለወጥ አጥርቶ መገመት አይችልም:: በሰማይና በምድር የሚወራለት አሉባልታ ግን ዛሬንና ነገን ይፈጥራል እየተባለ ነው:: ሰይጣን እግዜር ስለወደፊቱ የሚያውቋው ነገር አንድ በጣም ብልህ የሆነ ሰው ከሚያውቀው የተለየ እንዳልሆነ ይጠረጥራል፡፡ አብሮት ኖሮ አይቶታል:: ለምን ስለ ሰይጣን ስለራሱ መሸፈት ቀድሞ አልተረዳም? ወይስ ደም የማፍሰስ ፍላጎት ከአልፋው አድሮበት ነው? ትዝ ይለዋል ሰይጣን በመጀመሪያው የአመፅ ጦርነት ዕለት ከሰባተኛው ሰማይ ወደ ምድር የመላዕክት ደም እንደ ዝናብ ለአርባ ቀናት እንደወረደ፡፡ እዚህ ያስደርስ ነበር? ቢሳሳት 'ድክመቱን አውቄ ያደረኩት ነው' ብሎ ለማስወራት መፈለጉ ካልሆነ ለሌላ ለምን ተአምር ነው?::" ገጽ 141

***እባብ ገነት ውስጥ...

"ታዲያ ቦታው እኩልነት ያለበት ቢመስልም በረቀቀ መልክ ስሙ የማይጠራ የተንሰራፋ ተዋረድ አለ፡፡ አንዱ ማስረጃ የእባብ ችግር ነው:: እባብን አስቀያሚ በመሆኗ ገነት ውስጥ ከጉዳይ የሚጥፋት የለም፡፡ ይኼ እኩልነት ነው? አዳምና ሔዋን ያልዳበሱት አብረው ያልተኙት ያላጫወቱት እንሰሳ ገነት ውስጥ የለም:: እሷን ግን ለሰላምታ እንኳን ዞር ብለው አይተዋት ወይም አጢነዋት ኣያውቁም:: ከገላዋ ክፍሎች የሚያምሩት በውብ ቀያቴ ላባ የተሸፈኑት አራት እግሮቿና ለጥ ያለው ለስላሳ ቀስተዳመና የመሰለው ባለቀለም ሰፊ ሆዷ ናቸው:: እግዜር ደ'ሞ ላባዎቹን እግሮቿ ስር፣ ሕብረ ቀለሟን ሆዷ ላይ ስላደረጋቸው ሥራ ፈቶ አጐንብሶ የሚያይላት፣ ዐይቶም 'ይኸቺ እባብ ለካስ ቆንጆ ናት' የሚላት አይኖርም፡፡ እባብ የአዳምንና የሔዋንን ስሜት ለመፈተሽ አንዳንድ ቀን መተላለፊያ መንገዳቸው መሐል በጀርባዋ ተንጋላ የሚያማምሩ እግሮቿን ወደ ሰማይ ዘርግታ ስትጠብቃቸው እንዲህ እያዩአት እንዲህ አተኩረው እያዩአት 'ከየት መጣ?' ብለዋት ያልፋሉ፡፡ ይኼ ቸለልታ ያበሽቃታል፡፡ አትነክሳቸው ነገር፡ አትጮህባቸው ነገር፣ አትለማመጣቸው ነገር…..." ገጽ 146

***የአዳም በለስ ላይ ሰይጣን በእባብ ውስጥ ሰርጾ ሔዋንን ለመጀመሪያ ግዜ ሰላምታ የሰጣት በኦሮምኛ ነው... "አካም" ነው እኮ ያላት። ይኸው....

"ሔዋን ጥቂት እንደቆየች ከዛፉ ውስጥ የሚንኮሻኮሽ ነገር ሰማች፡ ለማየት ድምፁን የሚፈጥረው ነገርና ፍጡር ምን እንደሆነ ለመረዳት ወዲያ ወዲህ አየች:: ከዚያ ካልጠበቀችበት አቅጣጫ ባልጠበቀችበት ጊዜ ከዛፉ ላይ፡
«አካም!» አለ…….የሚያምር እኩያ የሌለው ውብ የሆነ ድምፅ:: ሰላምታውን ልትመልስ ሔዋን ዙሪያ ገባዋን አየች:: በቅርቧ ማንም የለም:: በውሃ የተጠመቀ ፊቷን እያለበች ከዝላይዋ ያገኘችውን ደስታ ስታጣጥም: «የምታምር ዛፍ ናት አይደል?» አለ ያው የሴት ይሁን የወንድ የሚያምታታ ውብ ድምፅ «ማነው?» አለች ሔዋን «እኔ ነኝ. በድምፅ እንኳን አታውቂኝም?» አለ እባብ፡፡ «ኸረ እኔ እንጃ» «ይገርማል በጣም ይገርማል» «ምኑ ይገርማል?» አለች ሔዋን «እኔን አለማወቅሽ» አለች እባብ፡፡ «ሳላይህ እንዴት አውቅሃለሁ?» አለች ሔዋን «በድምፄ፡ በአንደበቴ፡ ዝናዬን አልሰማሽም?» «አልሰማሁም» «ይኼ እኰ ነው የኛ ነገር» «የማን ነገር?» «እዚህ ገነት የምንኖር»" ገጽ 155

***ሔዋንን በለሱን እንድትበላ ካደረጋት በኋላ አዳምንም እንድታበላው ያግባባበት መንገድስ...

"አዳም ከበላ በኋላ አንድ ላይ ስትሆኑ ከምታገኙት ደስታ ትንሽ ባስተዋውቅሽ እወዳለሁ»
«ምን ደስታ ይኖራል ሌላ? እንደዚህ የሚያስፈራ እንዲሆን አልፈልግም» «እስክትለምጂው ነው:: የፍሬዋ ቅመምና ጣፋጭነት ለምላስ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ሰውነትን ነው የሚሰማው፡፡ አይደለም እንዴ? ይኼን እንኳን አልነግርሽም። ከነዚህ የሰውነት ክፍሎች እግሮችሽ መሐል አሁን ድረስ ፀጉር ተሸፍኖ ያለው የገላሽ ክፍል አንዱ ነው:: ይኼ የገላሽ ክፍል ከማንኛውም የሰውነትሽ ክፍል የበለጠ ፍሥሐ የሚፈልቅበት ነው:: ፍሬዋን ከመብላትሽ በፊት ይሰጥሽ የነበረው አገልግሎት አንድ ብቻ ነበር፡፡ ከአሁን በኋላ ሁለትና ሦስት አገልግሎት አለው:: እስኪ ዳብሺና እይው»
«እ… እ… ፈራሁ፡፡ እምቢ» «አትፍሪ………እሱን እንዲነኩልሽ የምትለምኝበት፣ የምትለማመጭበት ጊዜ ይኖራል:: ካፈርሽ ተይው:: ነገር ግን አዳም ሲመጣና ፍሬዋን ከበላ በኋላ ለእሱም ቢሆን ለአንቺ የጠቆምኩሽን የአካላታችሁን ቦታ ብትፈታተሹ ጥሩ ነው:: ደስታ እዚያ ውስጥ ነው………» ገጽ 160

"ስሙ እናንተ የምታውቁት ሰለ ገነት ነው:: ፈጣሪያችሁ ስደተኛ አድርጓችኋል:: ለስደተኛ አዝናለሁ:: ከምታውቁት ዓለም ወደ ማታውቁት ዓለም ነው የመጣችሁት:: የጉልበተኛ ደካማ ያጠቃውን ስደተኛ የሚያደርግ ነው:: በአካል የሚያሸሽ ነው:: አይደለም? በረሃብ ብትሞቱስ? ጥሩ አይደለም:: ስለራሳችሁ አታውቁም:: ስሚ ሔዋን መነፋረቅሽን አቁሚና አንድ ነገር ልጠይቅሽ? ገላሽን ለምን ሸፈንሽ?” ሔዋን እንደመመለስ በእሳቱ የተጠበሰ እጇን እያርገበገበች ወደ ባሏ በማፈር ጠጋ ብላ ተቀመጠች፡ «ስለአፈርሽ ሌላ ምክንያት የለውም፡፡ ለምን አፈርሽ? ማፈር ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? እህቴ ሆይ ማፈር በራስ አለመደሰት ማለት ነው:: በራስ ላለመደሰት የማታምኚው ሰው መኖር አለበት:: ማለት ሌላው የሚያይሽ ዐይን የማታምኚው መሆን አለበት፡ እኔን አታምኚኝም የሚገርመውም አዳምንም አታምኚውም፡፡ ምንድነው አለማመን? እሱን አሁን ለመግለፅ ከባድ ነው:: ብችልበትም አይገባሽም። በቀላሉ በሚገባሽ ልግለፅልሽ፡ አሁን በማድረግ ላይ ያለሽውን ማፈርና መሸፋፈን ለምን የምታደርጊው ይመስልሻል? ጡት ስላለሽ፡፡ እግሮችሽ መሐል በፀጉር የተሸፈነ የሆነ ነገርም አለ፡፡ አዳምስ ለምን ታፍራለህ?» «ሐጢያቴ፡፡ ትዕዛዝ አለማክበሬ» አለው «ወሬኛ፡ ወግ ትችልበታለህ፡፡ እሱን አላልኩህም፡፡ ገላህን ለምን በቅጠል ሸፈንከው? ኮባ ስወረውርልህ ቀልበህ ታችህን አይደለ የጋረድክበት፡፡ ለምን አናትህን አልጋረድክበትም?» ዝም አለ፡፡" ገጽ 169

"«እግሮችህ መሐል ምርጥ የስጋ ቁራጭ አለ፡፡ እሱ ያሳፍርሃል:: ማፈር አይገባችሁም:: ከገነት ስትወጡ የተሰጣችሁ ሽልማት ነው:: ዶሮው እስኪበስል ድረስ እንዴት እንደ ምትገለገሉበት አሳያችኋለሁ. ........................................................................................................................,,,..,,,............,,,,................,.................
ከዚህ በኋላ አንቺም ትፀንሺያለሽ። ልጅ ትወልጂያለሽ፡፡ ጌታችሁ ከገነት ሲያባርራችሁ «ምጥሽን አከብደዋለሁ» ሲል ነበር፡፡ ምን ማለቱ እንደሆነ ለራሴም አይገባኝም፡፡ እግዚአብሔራችሁ ምነው ያልተፈተነ አዳዲስ ተንኰል የሚፈጥረው?»
«እንደሱ አትበለው»አለ አዳም በቁጣ፡፡ «ምን ልበለው?»
«ትእዛዝ ስላፈረስን መቀጣት አለብን» «ታዲያ ይሔ ሁሉ ምነው አዳም? ከገነት ተባረራችሁ፣ ሞትን ተሰጣችሁ፣ ወሲብ ሰጣችሁ…………እሱም ጣፍጦ እንዳያልቅ ልጅ ሰጣችሁ:: ልጅ ሲሰጣችሁ ምጥ በተባለ መንገድ፡፡ ግን ምጥ ሲከብድ ምን እንደ ሚመስል ራሴ አላውቀውም፡፡ አይገርምም? ይኼ ሁሉ ፋይድ ለምንድነው? ገና ለገና አንዲት ፍሬ ተቀመሰችና ምን ይጠበስ?» ገፅ 170

***አይ አዳም .. ዘፍጥረት ላይ ጤፍን ያስተዋወቀ ጀግና።

"አዳም ሔዋንን አየና ፍላጎቷን አጢኖ በአወንታ ራሱን ነቀነቀ። እሱ ፊት ለፊት…… ሁለቱ ከኋላ ከኋላ እየተከተሉት ኰረብታውን ትቶ ወደ ሜዳ ወረደ፡፡ ብዙ ተጉዘው አንድ አምባ ላይ ደረሱ፡፡ አምባው ላይ እንደ ወጡ ታች ታቹን ፊት ለፊታቸው በአረንጓዴ የውሐ ማዕበል የተጥለቀለቀ የመሰለ እጅግ ሰፊ ሜዳ አዩ፡፡ ሦስቱም ፈዘው ያን ሲመለከቱ ቆይተው ሠይጣን ሣል ሣለና እጁን ወደ ሜዳው ዘርግቶ ፡ «ይኼ የምታዩት ሜዳ ላይ የበቀለው ዛሬ ጠዋት የበላችሁት የበለስ ልብ የተሰራበት ነው»
«ሣር አይደለም?» አለ አዳም፡፡ «ይመስላል………ስሙ ጤፍ ይባላል. ..አያምርም?…..ኑ ላሳያችሁ......» ገጽ 176

***ሰይጣን አቤልና ቃየል መሃል ጠብ ሲጭር..

***እግዜር ዘፍጥረት ላይ ሳይነግረን የረሳውን ነገርስ? ደራሲያችን አዳም የአቤልና የቃየልን እህት ስም ማን ነበር ያላት? ኩል ውሐ? በምን ነበርስ የተጣሉት?

"ሰማኸኝ አንተ የበኩር ልጅ…….ለመሆኑ ከኩል ውሐ ጋር ከተኛህ ስንት ጊዜህ ነው? ሁለት ወር? ሴትህ ከታናሽ ወንድምህ ጋር እንደምትተኛ ታውቃለህ? አንተ እርሻ ቦታህ ከአፈር ጋር ስትታገል እሱ ጠቦት ይዞ እየመጣ………የአንተን ስንዴ ዳቦ እየበሉ ሲጠግቡ ተደብቀው የሚሰሩትን አይተሃል?» ገጽ 179

***አዳም እንጀራና ፍርፍርን ዘፍጥረት ውስጥ ጨምሮ ሰይጣን በለጋ ቅቤና በርበሬ የተሰራውን ፍርፍር ሲጎርስ ያሳየንስ ነገር?

" «እም………እም……ሲያዩት ያምራል……….ለመሆኑ ይኼ የፈጠራ ሥራችሁን ስሙን ማን አላችሁት?» አለ እየሳቀ ቀና ብሎ፡፡ የእንጀራውን ጉብታ ነካካና ከላዩ ጣል የተደረገውን ሐር የመሰለ ቁራጭ አንስቶ ከስር የተወሸለውን ነገር በዓይኖቹ አጠና፡፡ ከቁራሹ እንኩሮ ስር በበርበሬ የደመቀ ለጋ ቅቤ ውስጥ የተነከረ ትንሽ የፍርፍር ክምር አየ፡፡ ከቆመበት ዛፍ ስር እጁ መሐል ካስቀመጠው ሸክላ ሰሐን ላይ ጢስ ሲነሳ አየ፡፡ ወደ አፍንጫው ወስዶ በቀስታ አሸተተው:: ቀና ብሎ ወደ ዋሻው አየ፡፡ ሁሉም አፍጠው ይታዘቡታል:: በይሉኝታ ከእንጀራው ቆርሶ ከፍርፍሩ ክምር በአውራ ጣቱ ንዶ በእንጀራ ጠቀለለና ጎረሰ፡፡" ገጽ 183

***ከሁለት ተኩል የውስጥ ሱሪዎች ለአዲስ አበባ የወደድኳቸው አንቀጾች..

"'ይህቺ ሴት ስሟን ነገረችህ?'
'ሎሚ ሽታ ይባላል'
'እህ!………ጠይም ረዥም ሴት?'
'አዎ''
ስለ እሷ ሲያወሩ ዝናዋን ሰምቼአለሁ፡፡ የሰው ባልና ጎረምሳ ማባለግ ነው አሉ ስራዋ፡፡ እያፋታች ታገባለች፣ ከዛ ትፈታለች:: የምታገባው ደሞ ከእሷ በእድሜ የሚያንሱትን ነው…..የሃብታም ልጅ ናት አሉ…….አብዮት እንኳን አልነካትም። ቅፅል ስሟ ማን እንደሆነ ታውቃለህ?'
'ማን ነው?'
'በለስ' ነው የምትባለው። እግዜር ለማሳሳቻ ነው ያስቀመጣት። " ገጽ 278-279)
(አራተኛው የአዳም ትርክት 'በለስ' ይባላል... ንክኪው ገርሞኝ ነው:)

ገዳምን እንደገና በመጨረሻው የአዳም ትርክት ውስጥ ነጻነት በምትባለው ገጸባህሪ እይታ ውስጥ እናገኝዋለን።

"የለም ብቻ የማያጋጥም…….አለ አይደለ እንደዚሁ እሁድ እሁድ መርካቶ እሄዳለሁ:: የምገዛው ነገር ባይኖርም ከሠፈር ያርቀኛል እና ነገሮች አያለሁ:: በመንገድ ብዙ ነገር አያለሁ ታክሲ ውስጥ ብዙ ነገር አያለሁ:: አውቶቡስ ውስጥ ብዙ ነገር አያለሁ:: እና አንድ ቀን ጉድ አየሁ፡፡ ያውም የሚያሳዝን:: የክርስትና እናቴን ልጅ ጋሼ ገዳምን መርካቶ አስፋው ሆቴል በጀርባ ከዛች ቁሌታም ሎሚሽታ ጋር ተከታትሎ ሲገባ፡፡ መጀመሪያ ለብቻቸው ያሉ ያልተያዩ መስሎኝ ነበር፡፡ ግን ሰዎች አንድ ሰፈር ሆነው እየተዋወቁ ተከታትለው ሲሄዱ እንደማይተዋወቁ ዝም ሲባባሉ ትንሽ የሆነ ነገር ያስጠረጥራል አይደል፡፡ ደ'ሞ የእሱ እየተገላመጠ ማየት:: ጠርቼው ሰላም ልለው ምንም አልቀረኝም ነበር መጀመሪያ፡፡ ሳያዩኝ ተከተልኳቸውና እዛ ሆቴሉ ግቢ እውስጥ እጅ ለእጅ ተያይዘው አየሁዋቸው:: እጤ ዱብ አለ፡፡ ተደበርኩ፡፡ ለማንም አልነገርኩም፡፡ ሚስቱ ማርታ ይሄን ብትሰማ ወይ እሱን ወይ ራሷን ትገላለች፡፡ አዘንኩ፡፡ ከዛ ትንሽ ሳስብ ማርታስ እንዲህ ጀምራ እንደሆነስ አልኩ፡፡ ልክ በዚያች ደቂቃ ይሄን ባየሁበት ጊዜ ስንት መከዳዳት አዲስ አባ ይሰራል? አልኩ:: ማርታ በጣም ቆንጆ ሴት ናት። ዛሬ እንኳን አራት ወልዳ በመንገድ ስታልፍ ጎረምሶች ወሬአቸውን አቁመው ዞር ብለው ያዩዋታል:: የሚከዷት አትመስልም:: ግን ስለ መከዳዳት ሳስብ ብዙ ብዙ የማላውቀው ነገር ቢኖርስ ብዬ ራሴን አረጋጋሁ......" ገጽ 332

***እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው በጣም ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። መጽሐፉ ሙሉውን በዚህ መልኩ የተሳሰረ ነው። ስለዚህ እኔ አንባቢውን የምመክረው በያንዳንዱ ትርክት ላይ የተጠቀሱትን ገፀ ባሕሪያት መጻፍ እና ልክ እንደ puzzel መጨረሻ ላይ ማገጣጠም። የሕዳግ ማስታወሻዎቹ ሁሉም ዕንቁ ናቸውና የጥሞና ንባብ ይጠይቃሉ።

***ሌላው እጅግ በጣም የገረመኝ (the concept of a story within a story) ነው።
የኤፍሬምን አባት ታዋቂ ሰዓሊውን መስኮት ገረሱን ካልተሳሳትኩ በለስ ከሚለው ትርክት በቀር በእያንዳንዱ ታሪኮች ውስጥ ሲንሸራሸር ታገኙታላችሁ። በእያንዳንዱ ትርክት ውስጥ በጣም በሚገርም መንገድ አኗኗሩ፣ ደራሲ ጓደኛው ስብሃት፣ ፍላጎቱ፣ ፍልስፍናው፣ አባትና እናቱ፣ መልኩ፣ የወደፊት ሚስቱን ሲተዋወቅ፣ የሳላት ሴት እና አሟሟቱ ሳይቀር ቀስ እያለ እየተገለጠ ይመጣል። This intricacy is like a story within a story. I am in awe of Adam’s way of creating a fully complete story about one man through other stories.

***ስለዚህ እዚህ መጽሐፍ ላይ በጣም የወደድኩት ገጸባህሪ መስኮት ገረሱን ነው። ይህ ገፀ ባሕሪ ራሱን የቻለ ለሱ የተመደበ ትርክት የለውም። በመጀመሪያው ትርክት ላይ እንደዋዛ ብቅ ብሎ ከዛ ግን በእያንዳንዱ ትርክት ውስጥ ማንነቱ እየተገለጠ ይሄዳል። አዳም ሰባት የተለያየ ታሪክ ፅፎ ትርክቶቹን በማይረብሽ ሁኔታ ይህንን fixed ገፀ ባሕሪ በእያንዳንዱ ታሪክ ውስጥ እንዴት እንዳንሸራሸረው ስናይ it is mind blowing! የመስኮት ገረሱ ፍልስፍና እና አኗኗር ራሱን የቻለ በእነዚህ ሰባት ትርክቶች ውስጥ ህያው የሆነ ስምንተኛ ታሪክ ነው።

ሰዓሊ መስኮት ገረሱ አለማየው ሌንጮ ከተባለ አርታኢ ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ከዚህ ታሪክ ሕዳግ ላይ አንብቦ መስኮት አዳም የፈጠረው ገፀ ባሕሪ ሳይሆነ እውነተኛ ኤክስፐርት መስሎት ያልተደናበረ ካለ ውሸት ነው። አዳም አሳማኝ የሚመስሉ ምናባዊ ማጣቀሻ መፃህፍት የፈጠረ ጀግና መሆኑ የገባኝ ከብዙ ድንብር በኋላ ነው።

***መስኮት ገረሱ...

በልጁ በኤፍሬም ትርክት ውስጥ ..

"ቤቴ ተመልሼ ለበዓል የተዘጋጀ መዓት ቅባት ያለው ዶሮና በግ ወጥ ነከነክሁ፡፡ ጉርሻዬ……ትሪ ዳር ቆሞ ሳየው ጥላ የሌለው የኮካኰላ ጠርሙስ ይመስላል፡፡ አባቴ መስኮት በአበላሌ እየተበሳጨ 'ጉርሻህ እኔን ያክላል፡ ስለዚህ ስታጎርሰኝ መጠኑን ትንሽ አድርግልኝ' ይለኝ ነበር፡፡ አባቴ የታወቀ ሰዐሊ ነው(የታወቀ' ስል አፍራለሁ):: እናቴንና ጉርሻዋን መውደዱ ምክንያት ሆኖ የስዕል 'አጣጣል' ጥበቡ እንደተለወጠ ደጋግሞ ሲናገር ሰምቼአለሁ፡፡" ገጽ 15

***መስኮት ገረሱ ከአለማየው ሌንጮ ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ የተውጣጡ እኔን የመሰጡኝ የህይወቱ ፍልስፍናዎች..

አሌ(አለማየሁ ሌንጮ)፡ በአሁኑ ወቅት አንተ የምትከተለው የአንተን አባባል ልጠቀምና የብሩሽ አጣጣል ዘይቤ ተነካናኪ ይባላል፡ ተነካናኪ ምን ማለት ነው?
መገ(መስኮት ገረሱ)፡ ተነካናኪ የአጣጣል ፈርጅ በሌላ ሰሙ ቅርባዊነት ይባላል፡፡ በአገራችን የባህል አሳሳል የበላይነት ቦታ ያላቸውን ዐይንና ፊትን በተለይ ዐይንን በሌሎች የስሜት ሕዋሳትና ብልቶች ቀስ በቀስ መተካትና ቢቻል እኩል ለማድረግ የሚሞክር የአሳሳል ዘይቤ ነው:: በባህል ስዕሎቻችን ዐይን ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ዐይን ማለት ርቀትና ሃሳባዊነት ሲሆን፤ የየቀኑ ኑሮአችን ግን የቅርብ፣ አፋአዊና ተነካናኪ(የሚነካና የሚነካካ ውህደት የሚያሳዩበት) ነው:: ተነካናኪ የሚለው ፅንሰ ሃሳብ የመጣው ከዚህ ነው(ባለቤትና ተሳቢ/ ሳብጀክትና ኦብጀክት ሐተታዊ በሆነ መልክ ሲዋሃዱ)፡፡ (………………………)ባህላዊ ስዕሎቻችን በርቀት የስሜት ሕዋስ(ዐይን) የተመሰጡና በማሰብ ስርዐት ላይ የተመሰረቱ ናቸው:: የማቅረብ የስሜት ሕዋሳትን (የመንካት፣ የማሽተት፣ የመቅመስ) ኮስተር ባለ መልክ አጥንተን ቀድሞ ያዛባነውን ውክልና(ሬፕሬዘንቴሽን/ representation) ለማስተካከል መጣራችን ያረካኛል። ወደዚህ ሃሳብ እንዴት መጣሁ? (……………………………)ሐላፊነቱ የባለቤቴ የበረካ ነው፡፡ የአንድ ደራሲ ወዳጄ ጎረቤት ነበረች፡፡ ገና ከመጀመሪያ ሳውቃት እንደ ሌሎች ዜጎች 'ድንክ ነው' ብላ በመናቅ ሳታገለኝ እቤቷ አስገብታ 'ተቀመጥ፡፡ ምን ልጋብዝህ?' አለችኝ። (……………… )በውበቷ ተማርኬ ነበር፡፡ ገና ሳያት ፍቅር እንደ ያዘኝ ገብቶኝ ነበር፡፡ ምንም መመለስ አልቻልኩም፡፡ 'የሚበላ ትፈልጋለህ?' አለችኝ:: መልስ አልነበረኝም።(ሳቅ) 'ምሳዬን አልበላሁም…… ኩላሊት ጥብስ ልበላ ነበር፣ አብረኸኝ ትበላለህ? ልስራ?' አለችኝ፡፡ ቆንጆ ስትጋብዝ እምቢ ይባላል? አይባልም:: ካልክ ወንጀል ነው:: ማን ነው/ናት በደንብ የማያውቀውን/የማታውቀውን 'ተቀመጥ' ብሎ/ብላ ኩላሊት ጥብስ የሚጋብዝ/የምትጋብዝ? 'እሺ' አልኩ፡፡ በግማሽ ሰዐት ሁሉ ደረሰ፡፡ ኩላሊት ጥብሴን አንዴ እንኳን በእጄ ሳልነካ እንደ ትንሽ ልጅ እሷ እያጎረሰችኝ ጠግቤ በላሁ:: (…)ስሰናበታት ያጎረሰኝ እጇን ከነለበሰው መረቁ አገላብጬ ሳምኩት፡፡ ጣቶቿ ዛሬ ድረስ ለእኔ የፍቅር ምንጮች ናቸው:: ቅርባዊነት ወይም

ተነካናኪ የመጣው ከዚያን ቀን በኋላ ነው:: የዚህ የኪነጥበብ ረድፍ ምንጩ ፍቅር ነው:: በመተሳሰብ ስለ መነካካት ነው::
.... የዚያን ዕለቱ ጉርሻ አንዳንድ መሰረታዊ የሆኑ ግን ችላ ያልኳቸውን ነገሮች እንዳጤን አደረገኝ፡፡ መጀመሪያ ጉርሻ ምንድነው? አልኩ:: ቀላል ጥያቄ ነበር:: መልሱ ግን ሰፊ ነው:: ( ....) ይሄን በሚመለከት ለበለጠ ማብራሪያ ነቢዩ ጎበናን ብታነብ ደስ ይለኛል:: ጉርሻ የሚያቀራርበን ነው:: በጉርሻ ዐይኖቻችን የፈጠሩት ዕርቀት ይጠፋል:: በኋላ እንዳየሁት መጎራረስ ወደ ወሲብ የሚጠጋ ኢትዮጵያዊ ድርጊት ነው:: በማዕድ ዙርያ እንዲቀመጥ የተገደደው ተከፋፍሎ ግለሰብ የሆነው ቡድንና ማህበረሰብ በሚዘረጋው የበላተኛ እጅ ድልድይነት ይቀራረባል፡፡ 'አብረን በልተን' ሲባል እውስጡ ከባድ የጉርሻ ይዘት አለ፡፡ ጉርሻ አገናኝ አቀራራቢ ድርጊት ነው:: (……………………..) ሌላም ዝርዝር ረድፍ አለው፡፡ በርበሬና ሚጥሚጣ በመብላት ሂደት ውስጥ ዜጋ ያልበዋል፡፡ በዚህም በእያንዳንዱ እንጀራ ሰበከት ላይ የአብሮ በላተኛችን የወዝ አሻራ ይታተማል። ይሄ አስገራሚ የሆነ ግላዊ ማህተም ያለው(እያንዳንዱ ሰው የራሱ ከማንም ግለሰብ የሚለየው የጣት አሻራ ስላለው) የተቀናበረ ድራማ በሚጠጋ 'ማጉረስ' ተብሎ በተሰየመ ድርጊት ማሕበራዊ ቅንጅት ይከናወናል፡፡ በጉርሻ ድርጊት የግልና የማህበራዊ አላማዎች ሳይጋጩ ይቀርባሉ። (…………………) ይሄ ሁሉ አማካይ ወደ ሆነው ብልት ወደ አፍ ያመጣናል:: ጉርሻ በአፍ መግባት አለበት፡፡ የጉርሻ አጉራሽና ጎራሽ የሚረካከብበት ታላቁ ቀዳዳ አፍ ነው:: ለሕይወት የሚያስፈልገው ምግብ የሚገባበት፣ ቋንቋ የሚሰራበትና ሰዎች በራሳቸውና በሌላው መሃል ያለውን ልዩነት የሚያጠቡት ወይም የሚያሰፉት(ሃሃሃሃ) በአፍ ነው:: አፍን ሴቶችና ወንዶች የሚጋሩት ቀዳዳ ነው: ይሄ ግንዛቤአችንን ጠንካራ ሁለንተናዊነት ይሰጠዋል፡፡ ጎራሽ አፉን ሲከፍት አጉራሽ ሕይወት እንደሚሰጠው አምኖ ነው። እኔና አንተ፣ አንተና አንቺ …ወዘተ በስምረት ውስጥ የሚጠፉበትና 'እኛ' የሚሆኑበት ነው:: የቦታ ዕርቀት የሚወድምበት ነው (...) አብረው ተቀምጠው ሲበሉ የማይጎራረሱ ሃበሾች ቁጥራቸው ከበዛ ኢትዮጵያ የምትባል እንደሌለች ወይ በመለወጥ ላይ እንዳለች ምልክት ነው:: ይሄ የሚያሳየን አንድ ቅራኔ የባህል ሕልውናችን ውስጥ እንደተከሰተ ነው:: አንዳንድ በቅርብ መወለድ የጀመሩ ልምዶቻችንን እዚህ ባጭሩ እንድጠቅስ ይፈቀድልኝ:: እዚህ አዲስአባ ውስጥ አንዳንድ ቦታ እንጀራ በቢላ ሲቆረስ እናያለን፡፡ ይኼን በቢላ የመቁረስ ባህል የጀመረው ማን ነው? ለምን ጀመሩ? እንጀራን በቢላ መቁረስ እንጀራን ወደ ዳቦ ለማውረድ መጣር አንደሆነ አልተረዱም? የእኛ ትልቁ ችግራችን ዕውር ኮፒ አድራጊዎች መሆናችን ነው:: ፈረንጅ ዳቦ ሲቆርስ ዐይተን ከዛ ያን በጭፍን ያለ ጥየቃ ያለ ትንታኔ ተበደርን፡፡ የዚህ ችግር በራሳችን ማመን አለመቻላችን ነው:: በራሱ የማያምን ሕዝብ ወደ ባርነት የሚጓዝ ነው:: ተነካናኪ የስዕል አጣጣል ንቅናቄ አላማው ባያያዛችን ባሮች መሆን ባይቀርልንም የመሆኛ ጊዜውን የማዘግየት ነው:: ቢያንስ ስለ ራሳችን እያወቅን ራሳችንን በቁጭት እየነቀነቅን ወደ መቃብር እንድንወርድ ነው:: ( ....) ለመሆኑ እንጀራ ለመቁረስ እጅ አነሳትና ነው ቢላ የመጣባት? በእንግሊዘኛ ኦቨርኪል (overkill) ይባላል፡፡ ዝንብ ለመግደል ታንክ ስታወጣ ማለት ነው:: እንጀራ ቢደርቅ እንኳን አይፈነክትም፡፡ እንጀራ ጥፊ እንኳን አይሆንም፡፡ ምኑ ሰይፍ ያስመዝዛል? ግን እንጀራ አገር ያቆማል። ይሄ አያኖ የሚያምር ነው:: አሁን አሁን ወደ ሕብረተሰቡ በደንብ የቀረብኩ ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሶሻሊስት ሪያሊዝም ነው ይላሉ፡፡ የምስላቸው ሰዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ያለበትን የገባበትን እላይ የጠቀስኩትን ቀውስ ለመፍታት መሞከር ነው ስራዬ፡፡ ግለኛነትም አይደለም፡፡ የእኔ ሕይወት ለሌላው ምሳሌ ነው:: በሁለት በኩል የተቧደኑትን የስሜት ሕዋሳት አንድ ለማምጣት ነው ሃሳቤ፡፡” ገጽ 15-16

***ለትንሽ ደቂቃዎች ቆም ብላችሁ ሕዳጉ ላይ ያለውን ሙሉውን የተነካናኪ ፍልስፍናው ላይ ማውጠንጠኑ የሆነ ደስታን ይረጫል። እዚህ ቃለምልልስ ላይ ባለቤቱን ባርካን የሆነ ደራሲ ጓደኛው ቤት እንደተዋወቃት ይነግረናል። የትኛው ደራሲ ቤት የሚለውን ለማየት እዚሁ መጽሐፍ ላይ የስብሐት ጢም የሚለው የአዳም ሁለተኛ ትርክት ውስጥ መስኮት ገረሱ ደራሲው ጓደኛው ስብሐት ቤት ባርካን ሲተዋወቅ እናያለን። ገጹን እጠቁማለሁ እባካችሁ ራሳችሁ አንብቡት። ገጽ 74

***የስብሐት ጢም የሚለው ትርክት ላይ መስኮት ድንክ እንደነበረ ገጽ 64፣ ስለ አባቱ ገረሱ እና እናቱ ስንዱ ገጽ 43-44 ወዘተ ወዘተ.. ተጠቅሷል። መስኮት የተገለፀባቸው ገጾች .. ገጽ 29, 43, 44, (45 ሕዳጉ ውስጥ), 46, 63, 64, 65, 74, 79, እቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ ላይ ገጽ 113, 114, (125 ሕዳግ ውስጥ), ለድልህ የሚለው ትርክት ላይ ገጽ 211, (212 ሕዳግ ውስጥ), 227, 228, ሁለት ተኩል ሱሪዎች ለአዲስ አበባ የሚለው ትርክት ላይ ገጽ 235, 258, 259...ሽልንጓ የመጨረሻዋ የቀበሌ 01 ድንግል ላይ ገጽ 334 እና 335 ውስጥ የመስኮትን አሟሟት እንሰማለን። በለስ ከሚለው ትርክት በቀር መስኮት በእያንዳንዱ ትርክት ውስጥ ስለሚመጣ አንባቢው እያንዳንዱን ትርክት እያጤነ ቢያነብ የመጽሐፉን ጥልቀት ይረዳዋል። (በትርክት ውስጥ ያለ ሌላ ትርክት አለ ለማለት ነው። ) ኦ አዳምዬ ያስብላል።

***መስኮት ገረሱ በሱና በደራሲ ገብሬ ገብርዬ መሃል ስለተፈጠረው አለመስማማት ሲጠየቅ የሰጠው መልስ በጣም አስደምሞኛል።

***እዚህ ቃለምልልስ ላይ (ሰዓሊ መስኮት ገረሱ ቀይ ሌሊት የተባለ ልብወለድ ከጻፈው ደራሲ ገብሬ ገብርዬ another fictional character ጋር ያለውን ልዩነት ያብራራበት መንገድ በጣም ይመስጣል። ገብሬ ገብርዬ ስብሃት ይሆን እንዴ? ቀይ ሌሊት ልብወለድ የስብሃት 'ትኩሳት' ይሆን እንዴ? (ትኩሳት ከመባሉ በፊት የቀይ ኮከብ ጥሪ ተብሎ ሊሰየም ነበር ይባላልና ..እርግጠኛ አይደለሁም:) ግን እንዲህ ስል የራሴ ቅዠት ነው እንጂ አዳም ያለውማ ...
"እነዚህ ልብወለዶች ውስጥ ያሉት ገፀባሕርያት በሙሉ ምናብና ሃሳብ የወለዳቸው ናቸው:: በአንዳንዶቹ ውስጥ የሚያጋጥሙን የታዋቂና የሚታወቁ ግለሰቦች ስም መግባት ጊዜን በሚመጥ ነው ድባብ ለማጀብ የተሰራ ኪነታዊ ጥረት እንጃ, ሌላ ዳራ የለውም:: ከዚህ ውጭ የተቀረው 'ድብን' ያለ ልብወለድ ነው:: ከግለሰቦች ታሪክ ጋር መመሳሰል ድንገት ቢከሰት የአዳም ሳይሆን 'የእዝጌር' ስራ እንደ ሆነ ይቆጠር። በተጨማሪም ከድርሰቶቹ ጋር እንደ መግለጫና እንደ ማብራሪያ በሚቀርቡት ሕዳግ ማስታዎሻዎች(ሕማ) ውስጥ (አ) ማለት አርታኢ(ደ) ደራሲ ማለት እንደሆነ አንባቢ እንዲያውቀው ይሁን፡፡ አረ"

***ቃለ ምልልሱ ይህን ይመስላል

አለማየሁ ሌንጮ - "ባለፈው ሁለቱ ኤግዚቢዥኖችህ በ '18' እና 'እንደገና 18 በተባሉት ውስጥ ሁለት ሴቶች እንደ ሞዴል ተጠቅመሃል፡፡ እንዳየነውም በተለያየ ደረጃ እነዚህ ቆነጃጅት ገላቸውን ያላዩናል፡፡ ታዲያ የአንዳንዱ ግልፅነት በቅርብ ይታተም ወይስ 'አይታተም አየተባለ ከሚያከራክረን ሁለት ምዕራፎቹን በመፅሔት ካነበብነው ከደራሲ ገብሬ ገብርዬ 'ቀይ ሌሊት' ልብ ወለድ ጋር የሚያመሳስሉት አሉ፤ አንተ ግን በሌላ ቃለ መጠይቅ 'አይመሳሰልም' እንዳልክ ሰምቼአለሁ፡፡ ብታብራራልን፡፡

መስኮት ገረሱ: በቀይ ሌሊትና በ18ቶች መሃል ያለው ልዩነት የዕውቀትና የፐርፎርማንስ ነው:: ቀይ ሌሊት ግልፅ የወሲብ ቋንቋ ይጠቀማል፡፡ ይሄ በአገራችን የተለመደ አፃፃፍ አይደለም፡፡ ስላልተለመደ ኋላ ቀር ነን ማለትም አይደለም፡፡ ከባድ የስለላና የጭቆና ስርዐት ባለባቸው አገሮች የዚህ ዐይነት የወሲብ ግልፅነት አለ። እንደውም እንዲኖር ይገፋፋል:: ስለዚህ ግልፅ የወሲብ ቋንቋ ማስክ ማለት ጭምብል ሊሆንም ይችላል፡፡ 'ግልፅ' የሚለው ቃል የተራማጅነት ወይም የቀዳሚነት ምልክትም አይደለም:: ወይም 'እንደ ወረደ' ማለት ኩመካ ነው:: ማንም ስነፅሑፍ በአርትኦት ጎዳና ነው የሚያልፈው(ግብታዊ' የተባለ- ድርሰቶች እንኳን ከመነበባቸው በፊት በአታሚ/በአርታኢ 'ይነካካሉ')፡፡ ቀይ ሌሊት መዋቅር ያለው ልቦለድ ነው:: መዋቅር እንደ ወረደ አይመጣም፡፡ ቅንነት ቢርበንም እዚህ ድረስ አንሸወድም፡፡ 'እንደ መጣልኝ ፃፍኩት ብሎ ሽወዳ የለም፡፡ እንደወረደ የሚመጣው ያለቀ መዋቅር እግዜር ሲሰራው ብቻ ነው:: እኔ አጠቃላይ ማህበራዊ ሁኔታን ነው የማየው፣ የሴትና የወንድ ብልት ብቻቸውን ቦታ የላቸውም:: በቅዱስ መፅሐፍ ከወሲብ በፊት ጉርሻ ነበር። በለስን መብላት፡ አስፈሪውና ሰው የተነፈገው ዕውቀት ነበር፡፡ ያን ስጦታ መጠቀም አለብን፡፡ የእኔ ስዕሎች ጥናቶች ናቸው:: አላማዬ ዕውቀት የመሰብሰብ ነው:: ቀይ ሌሊት የውሰት ድርጊት ወይም ኮፒ ፐርፎርማንስ ነው:: ( ) ለምሳሌ በእኔ አንድ ስዕል 'ከቁርስ በፊት' በተባለው በጎን የተሳለች ሴት አለች፡፡ ይህቺ ሴት የውስጥ ልብሷን ታወልቃለች ወይም ትለብሳለች፡ ውስጥ ልብሷ ሳይሸፍናት በፊት በጨረፍታ ግልፅ ባልሆነ መልክ የአፍረቷን ፀጉር እናያለን፡፡ ከሴቷ አጠገብ (foreground) አንድ ሰውዬ ራቁቱን ተኝቷል፡፡ የምናየው ግን ከወገቡ በላይ ነው:: እዛ አልጋ ላይ ምን ይደረግ እንደነበረ ወይም ምን ሊደረግ እንደ ታቀደ ነጋሪ አንፈልግም:: በተለያየ መጠን እናውቃለን፡፡ ሁለቱም የስዕል ኤግዚቢዥኖቼ 80 በመቶ የዚያን ጊዜ ወዳጄ ከነበረችው ዛሬ ባለቤቴ ከሆነችው በረካ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው:: መነሻዬ ናት፡፡ ዕውቀትና ጥናት ነው:: ቀይ ሌሊት ግን ፐርፎርማንስ ነው:: የገብሬ ገብርዬን ቀይ ሌሊትን ከማንበብህ በፊት የእኔን ስዕል ማየት አለብህ።" ገጽ 17

"አሌ፡ ሃሃሃሃ ከገብሬ ገብርዬ ጋር በዚህ ምክንያት አልተስማማችሁም ይባላል:: ምን የማያስማማ አለ? ስዕልህ በቴክኒክ ጠንካራ ቢሆንም ወግ አጥባቂ ነህ ይባላል፡፡
መገ: ዕውቀት ይቅደም ነው ያልኩት:: ያውም ሰፊ ዕውቀት:: ከአትኩሮት ጠባብነት እንውጣ ማለቴ ነው:: ከደቃቃዊነት (minimalism) ወይም አሹራዊነት (ከአስሩ አንዱን ብቻ ማየት) ለመሸሽ ነው:: በሌሎች አገሮች እዚህ ቀይ ሌሊት ዐይነት ስራ ከመድረሳቸው በፊት ታላላቅ ስራዎች ተደጋግመው ተሰርተዋል፡፡ ድልድዩ አልተገነባም፡፡ ለምሳሌ ስለ ቅኔ ብዙ እናወራለን ግን ስለ ቅኔና ስለ ግጥም የተፃፉ የጥናት ነገሮች አሳየኝ:: አባባሌ ገባህ? በግዕዝ ብዙ አቀኛኘት እንዳለ እንሰማለን እነዛን ወደ አማርኛ አሸጋግረናል? ምንስ ይመስላሉ? ትልቅ ታሪክ አለን ይባላል፡፡ እንደዚያ የሚል ሕዝብና ምሁር በተክለፃድቅ መኩሪያ ሁለት ሶስት መፅሐፎች ብቻ አይቆምም፡፡ ዕውቀቱ የለም፡፡ ወይም ይሄ ዕውቀት የተባለው ነገር ማብራሪያ ሊሰሩልን ባልቻሉ ጅምላ አውሪዎች ቁጥጥር ስር ነው:: ስዕል ቢያንስ ከፅሁፍ የተሻለ ሁኔታ ላይ ነው ያለው:: ሰዐሊዎች ድልድዩን እየሰሩ ነው:: ዘሪሁን፣ እስክንድር ድልድይ ሰሪዎች ናቸው ከሌሎችም ጋር ሆነው አዲስ ፓራዳይም(የአመለካከት ዕቅድ) እያበጁ ነው፣ ስነጽሑሀፍ ግን የለንም። ምናልባት ዳኛቸው? ምናልባት ፀጋዬ:: በአማርኛ ተፅፎ በእንግሊዘኛ ሂስ የሚሰጥበት ዓለም ነው እኮ ያለነው:: ንቅናቄ የለንም፡፡ ደብዛዛ ነገር ነው:: ያለትም ስለ ፍልስፍናቸውና ስለ ቴክኒካቸው ሳይነግሩን፣ ሳያስተምሩን እንዳያልፉ ነው የምፈራው:: ስለዚህ ለእኔ ´ቀይ ሌሊት' ጋሪ ነው ከፈረሱ የቀደመ:: በማህበራዊ የድርጊት አለም ውስጥ ተስተካካዩ ምሳሌ የተማሪዎች ንቅናቄ ይመስለኛል:: ቀይ ሌሊት የተማሪ ንቅናቄ በጋለበት ሰሞን መፃፉ የመመሳሰሉ ምልክት ይሆን? የአገሪቷን ሕብረተሰብ የምትለውጠው 'ጭቆና' በሚል ካልተጠናና ካልተብራራ ፅንሰሐሳብ ወይም ኮንሴፕት ተነስተህ አይደለም: እዚህ ፕላኔት ላይ ጭቆና ያሌለበት ቦታ የለም፡፡ የበለስ በይዎች ዝርያ ነን፡ ግን ያለህበትን ማወቅ አለብህ፡፡ ምንድነው ጭቆና? ኋላ ቀርነትስ? ምን ዓይነት ባህል አለን? ጠላታችን ማን ነው? የጠላታችን ጠባይ ምን ዓይነት ነው? ከዚህስ ጋር ተያይዞ የመንግስታችን ጠባይ ምን መምሰል አለበት? ቋንቋችንስ? ቋንቋችን ውስጥ ምን የተደረገ ነገር አለ? የውስጣችን የባህል ሲነርጂ ምን ይመስላል? የባህል ውርሰት ጥናቶች አለ ወይ? ከውጭው ዓለም ጋር የምንቀራረብበት ሊቃዊ መንገድ ምንድነው? ወዘተረፈ ጥያቄዎች ብዙ አልተመለሱም በጥናት ማለቴ ነው ...
አሌ ፡ - 'ቀይ ሌሊት ን ጥናት ነው የሚሉት አሉ
መገ፡ አይመስለኝም። በድርጊት ጀምሮ በድርጊት ያልቃል:: ባለታሪኮቹ ፈረንጅ ሊሆኑም ይችላሉ:: ካመሱትራን ያነበበ፣ ዘ ፐርፊዩምድ ጋርደንን ያነበበ ወይም ሄነሪ ሚለርንና አናይንስ ኒን ያነበቡ፣ ማርኪ ደ ሳደን ያነበበ የሚያመጡት ነው:: ሜካኒስቲክ ነው:: እንደኛ ባለ አግላይና መራጭ፣ እንደገና ኋላቀርና ጎጠኛ ሕብረተሰብ ጥናት ይቀድማል፡፡ በመጀመሪያ ቢያንስ ቢያንስ በጥንት ጊዜ የነበረውንና የረሳነውን ምሉዕ ዕውቀት እዚህ ማምጣት አለብን፡ እስኪ ዘርአያዕቆብን እናጥና። 18 ወደ'ዛ በትንሹ ይመልሰናል፡፡ ስለዚህ ለእኔ ጉርሻ ቀላል ድርጊት አይደለም:: በመውደቁና በመነሳቱ ውስጥ ጨለማና ብርሃን አያለሁ:: የባህሌን መውደቅና መነሳት አያለሁ:: ጉርሻ ለእኔ እንደ ሐይማኖት ቀኖና ነው::" ገጽ 19
*****
***አሁን ደሞ የመሰጡኝን የቃላት ውበትና የስነጽሁፍ ጥልቀት ልጥቀስ...

***መች ትመጣለህ?) ከምትለዋ አጭር ታሪክ የወደድኩትን አንቀጾች ላካፍላችሁ። እንዳላበዛባችሁ ስለፈራሁ የአዳምን የአጻጻፍ ስልትና የቃላት ውበት ለማሳየት ብዙ ማለት እየቻልኩ ይህ ጽሁፍ አሰልቺ እንዳይሆን ራሴን ቆጥቤያለሁ።

"ኰረሪማን ገና ሳያት የወደድኳት ጠይም ናት፡ ነጭ ጉርድ ካናቴራ ለብሳ፡፡ ቀይ አጭር ሽንሽን ቀሚስ ለብሳ፡፡ ጡቶቿ ያለመያዣ ብይ ብይ ( መስለው:: የዕውነት ይሁን የውሸት ደቃቃ የወርቅ ቀለም ያላት ድምብል አንገቷ እርግብግቢት መሐል አቁራ::....የቀጠኑ ክንዶቿ……. ትላልቅ ሊስቁ የፈለጉ ዓይኖቿ (ግን እናቷ እንዳይስቁ እንዳይገላምጡ እንዳያተኩሩ የከለከለቻቸው)…….በዚያ ላይ በችኰላ እንደተሠራ ሁሉ የተልቆሰቆሰ ጉንጉኗ