Amharic Poem❤️ @amharicpoem1222 Channel on Telegram

Amharic Poem❤️

@amharicpoem1222


ግራ የገባዉ ሰው ምንኛ ታደለ
ቀኝም ሆነ ግራ ያልገባው ስንት አለ

Amharic Poem❤️ (Amharic)

በቀንም ወሬዎች መዘርጋት የገባዉ ሰው ወዲህ መመስረት ማቅረብ እና እንቅስቃሴ እናስከታለን። የግራ ቋንቋ ነፃ የሚታወስ ዜናዊ ጉዳይ ስለ ትምህርት እና ትምህርት መነሻ ውጤታማ ርዕስ እና አባላት ማለት በተለያዩ እና ተጠቃሚ ቅናት እባኮት ሁሉ።nnግራ የገባዉ ስንት ማወከብ አለ? የታፈነ ይሆን? አሉት? እና ወደ ተለዋዋጮች ታይት እንዳይጠቀምልን እለምንሃለሁ። @amharicpoem1222 በጀርነቱ ከሠው ምንኛው በፊት ወደ እውነትና ሕይወት ምልክት ያደረገው የገባዉ ግራ ስንት ነው። እንዴት ተጠናክሮ ሰውየሀው ሚስጥራት እና ስለዚህ የሚሆነው የአሮጊት ቋንቋ እንጂ የምናምራብዘው ቋንቋ ሊተማመን ነው።nnበመሰረታዊ ትምህርት እና ትምህርት አገልግሎት በሓዙ እና እልፈዋን ክፍት ሃሳቦችን ከእሱም ፊልሞች በቀዳዳ ሰነ አድራሻ ባላቸው ሰዎች ሲያመልክ። እንደሠላሳላሚ ለተለያዩ ቅናት በተጀመረ ጣሪያዎች እና ትምህርት ያዳብሩ ወደገላገል የሚዝናበት ነገር እንሄዳለን።nnይህን ያረጋግጡ እርምጃውን ለማሳየት ለማክበር የምንጠቀምበት በዚህ እርምጃ ሥነሳት ይከብረዋል።

Amharic Poem❤️

04 Nov, 15:27


""""""""""ስሚኝ""""""""""""


ስሚኝ የኔ ቆንጆ

ከአምላክ ያልሆነን፣ ደስታን አታሳጂ
ክብርሽን ጠብቀሽ ፣ በማስተዋል ሒጂ

እኚህ ውብ ቀኖችሽ፣ ዛሬ እምቶኖሪያቸው
ልክ እንዳንቺ ሁሉ፣ ማህፀን አላቸው

ከዓመታት በኋላ ፣ ይወልዳሉ መንታ
ያንዱ ስም ፀፀት ነው ፣ ያንዱ ስም ትዝታ።


/የዛሬ እርጉዝ ቀኖችሽ ነገ ላይ ምን እንዲወልዱልሽ ትፈልጊያለሽ? መራር ፀፀት ወይስ ውብ ትዝታ፤ ምርጫው ያንቺ ነው።/

#life #couple #Amharicpoem #peom


@Amharicpiem1222

Amharic Poem❤️

29 Oct, 20:14


""""""""'መንግ__ስተ 🤐 ሰምያት"""""""


እዩዋት እዪዋትማ
መንግሥተ ሰማያት፡
በባሕር መካከል፡ በአጥማጅ የተጣለች
በዓይነት በዓይነት፡ ዓሣዎች የያዘች
መረብ ትመስላለች፤»

ብሎ በምሳሌ ፡ ነግሮን ነበር ጌታ
እንኳንም የመጣሽ
ሚስጥሩ በሙሉ፡ ስናይሽ ተፈታ።

አዎ እህም_": እህ
መንግስተ ሰማያት፡
በደጎች ቀናነት፡ በጻድቃን ልመና
ጅማትሽ ሳይደድር፡ ቋጠሮሽ ሳይፀና
እኛኑ ለማጥመድ፡ ገና ከመጣልሽ
ስንቱን መልካምና፡ የረከሰ ለየሽ?

ተውጦ ድምፃቸው
ለስልሶ ቆዳቸው
ዓሳ ከመሰሉን፡ ከእባቡ ከጊንጡ
በስውር መርዛቸው ፡ ሊነድፉሽ ሲያወጡ
ባንቺ የተነሳ ስንቱ ተጋለጡ?

እህ

መንግስተ ሰማያት ፡ ታናሺቱ መረብ
ደፋ ቀና እያሉ፡ በዓሦቹ ወረብ
ከሚያዜሙት መሀል፡ ያጠመድሽው ዓዞ
ሲበጥስሽ አይተን፡ በጥርሱ ገዝግዞ

ከአውሬነቱ ጋር ፡ ባንቺ ተዋውቀናል
የይምሰል ሀዘኑን፡ እንባውን ንቀናል
ከእንግዲህ በኋላ፡
ያንቺ እድል ቢጠምም፡ የዘርሽ ይቀናል።

እህ
መንግስተ ሰማያት ፡
Kingdom of heaven፡ የሰውነት ወንፊት
በክብር ስትቆሚ፡ ካበጀሽ ጌታ ፊት
በምኞት በሀሳብ፡ ድርጊት በወሬ
ላቆሰለሽ ፀላይ፡ ለነከሰሽ አውሬ
Heaven መንጓለያ ፡ መረብ ነሽ ለክሱ
የጣልሽው ነውና ፡ የሚፋጨው ጥርሱ።


#heaven. #peom #Amharic.

#Share

@Amharicpoem1221

Amharic Poem❤️

12 Oct, 11:31


""""'''''''''''''''''';;;;;;;""""""""""""

መንታ ነው ፍጥረትሽ
_______


ተገለጠ ዕቶኑ
ተከፈቱ ዓይኖችሽ ብርሃን አዘነቡ፤
ቀለማት አቅርረው ውበትን አነቡ፣
ጋረዱት ኮከቤን
ብርሃን አጠሉበት
ኩራዜን በማሾ አደናገዙበት፡፡

ክንዶችሽ አቀፉኝ
አቅፈው አባበሉኝ
አባብለው አስተኙኝ
ውጋቴን ነጥቀውኝ
ቁስሌን አዘናጉኝ
ከሰመመን ጀርባ
እሾህ ላይ ሊያነቁኝ
ቁርንጮ ሊያለብሱኝ
በማቅ ሊፈትጉኝ፡፡


ሰጠሽኝ ጨለጥኩት የፍቅርሽን ጽዋ
ባንድ የተቀመመን ማር እና ግራዋ፡፡

ምን ይሆን ፍጥረትሽ
ጥንድ የሆነ መንታ፤
ከቃልሽ ያልጠፋ ብስራት እና መርዶ
ዋይታን እልልታ፡፡

ያልቃሾች ሙሾ ነሽ
የዕድምተኞች ጨዋታ
የሐሴት ርችት የሐዘን እሩምታ፡፡

እህ ሁለት ግራ🐐🐐


#Twinslife #poem #Amharic #ethiopia

@Amharicpoem1222

Amharic Poem❤️

29 Sep, 15:02


"""""""""""""""""""🤔🤔🤔"""""""""""""""""""

የሰው ልጅ አትናቁ
ሰው እንዴት ይናቃል

ቁንጫ እንኳን ባቅሙ
ሱሪ ያስወልቃል

እህ 🤔

#Man #Poem #Amharic #ግጥም

@Amharicpoem1222

Amharic Poem❤️

21 Sep, 10:33


""""""""""""""😭😭😭😭"""""""""


ብንሔድ ይሻል መሰል
ብንሰነባበት
መፍቻ ውል የለውም የኑሮው መጫኛ
ውስብስብ ተቋጥሮት

ፈጣሪም እራሱ

አንዱን ለደስታ አንደኛውን ለሀዘን
አንደኛውን ፈዋሽ ገዳይ ሌላኛውን

አድርጎ ይፈጥርና - ደግ አባት አደለ
በዚህ ምድር ስትኖር......
አንድ ቀን ሳይደላህ በል ኑረው ይልኻል እያንከለከለ

ምን ቆሽቷ ቢቃጠል
ያች ምስጉን ነፍስ በርሱ የተረገመች

አንተ ሰማይ ሆነህ ስትቀልድ በሰው
እናትህ ነደደች ማረርን ቅመሰው

ብላ የገጠመች


እህ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭


11/01/2017

#Cray #Sad @Amharicpoem1222

Amharic Poem❤️

19 Sep, 21:10


ከጠላው ልጠጣ
እስኪ ስካር ይንካኝ
በገላሽ ስሸነፍ
በጌሾው ላመካኝ
አንሶላውን ሽጡት
ከአልጋው ወርጃለሁ
ከዳጃፍ ቁጭ ብዬ
ማለም ለምጃለሁ

እግዜርም አንዳዴ መች ፍትህ ያውቅና
ለኔ ፍርሀት ሰጠኝ ለእሷ ግን ቁንጅና


#love #man #Amharic #Poem


@Amharicpoem1222

Amharic Poem❤️

09 Sep, 20:13


"""""""""ደግ ቀን ቶሎ ና """"""""""


ክፉ ቀን ተወገድ፤ ተወገድ
መልካም ቀን አሁን ና
የታገልከኝ ይብቃ - እኔም ልበል ዘና
መጪው ጥሩ ሆኖ - በሀሴት ልፅናና

የዕረፍት ጓዝህን
ይዘህ ከተፍ በላ
መልካም ቀን በል ናልን ይሰጠን ተድላ

ህመም በዚያ ውጣ፤ ውጣ
ጤና በዚህ ግባ
አንዴ ልረፍብት፤ እንጀቴ አይባባ
ምትህ አሽቆጥቁጦኝ
ቢያሻህ በመዳፍህ ሲያሻህ ባይበሉባ

ክፉ ቀን ቶሎ ሒድ - መልካም ቀን ቶሎ ና
ይኸው ብዙ ዘመን - ጎድተኸኛልና

ዛሬ ና- አዎ ና
መልካም ጌዜ ሆይ ና
ክፉ ጊዜ ሆይ ሒድ
መንገዴን አታግድ

መጥፎ ቀን በረህ ሒድ- መልካም ቀን በረህ ና
የዓዲስ ዓመት ተስፋ ውስጤ ገብቷልና


መጪው አዲስ ዓመት ያቀዳችሁት ሁሉ የሚሳካበት እንዲሆንላችሁ Amharic Poem ትመኝላችኋልች።



እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
መልካም አዲስ ዓመት

#newyear #best #ethiopia #poem


@Amharicpoem1222

Amharic Poem❤️

31 Aug, 08:40


እርሳስ እድሜ ሁላ...

መቅረጫ ሀገር ውስጥ - ገብቶ እየዞረ
እቀረፃለሁ ሲል - ያልቃል እያጠረ።

ቢቀርፁት ቢቀርፁት - መዶልዶሙ ላይቀር
መቅረጫ በሚሏት - በእርሳሶች ሀገር
ማስተካከል ሳይሆን - መቅረፅ ነው ማሳጠር።




Thank You for 1k Subscribers


#Nation #Pencil #Amharicpoem

@AmharicPoem1222

Amharic Poem❤️

18 Aug, 16:33


,...................,
.....................

በልብሽ  አስበሽ
የኔን ልብ ለመስበር
እግርሽ ከኔ ርቆ ወደሌላ ሲበር
እመኚኝ ፍቅሬ ሆይ
ላለቅስ ይቅርና ሳቅ ሊገለኝ ነበር

የሚል ግጥም
ሰጥቼሽ ከቤቴ እንደገባሁ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ
አንገቴን ቀብሬ ቁጭ ብዬ አነባሁ

አየሽ!

መለየትሽ ቢያመኝ ሆዴን ቢያላውሰው
ምን ላርግ ወንድ_ልጅ ነኝና
ባደባባይ ስቄ ቤቴ ነው የማለቅሰው!


ይሁና



#Love #Men #Poem #Amharic


@Amharicpoem1221

Amharic Poem❤️

08 Aug, 11:46


ቀላል ነው ............በመልካሙ ታደሰ

በተወጋ እግር ላይ የሾለ እንጨት መስደድ
በወደቀ ሰው ላይ ተዝናንቶ መራመድ

ወይም በሰው ግብዣ ውድ ነገር ማዘዝ
አንድም በአውሮፕላን ቢዝነስ ክላስ መጓዝ

ድሮ ልጅ እያለን ዶክተር ብለን ማለም
በሌለ መዳኒት ህምተኛን ማከም

ቀላል ነው

የወደቀ ዛፍን በመጥረቢያ መቁረጥ
የተዘጋጀን ጁስ በስትሮ መምጠጥ

አንድም ፖለቲካን ቁጭ ብሎ መተንተን
ያለምንም ስራ የተገኘን ገንዘብ ዝም ብሎ መበተን

ምርጥ ሰው እያሉ ለሰዎች ማሽቃበጥ
ልብና ህሌናን በአንድ ጊዜ መሸጥ

ቀላል ነው


#Simple #Peom #Amharic


@Amharicpoem1222

Amharic Poem❤️

30 Jul, 08:23


እግዜርም ሲጨክን
ሰው በሰው ሲከፋ
ተፈጥሮም ሲጣላን አየን ጋሞ ጎፋ

መሬቱም ሲከዳ
በንፁሃን ዓለም
ከነፍስ ይማር ወዲያ
የሚገኝ ቃል የለም   😭😭😭


#Gamogofa

@Amharicpoem1222

Amharic Poem❤️

19 Jul, 18:28


እይ ሰው ........


ክቡር የሰው ፍጡር - በሃሳብ ነጎድጓድ
ይወጣል ይወርዳል
ሲያሻው አውሬ ሁኖ - አራዊት ያለምዳል ።

አንዳንዴ ደግሞ -ቅዱስ መላክ መስሎ፣
በሬውን ያርሰዋል -ቢላዋውን ስሎ።

ታድያ ይሄን ፍጡር -አምላኩ ሲቀጣው፣
ከገነት አውጥቶ -መሬት ፈጠፈጠው።

እናም ይሄ ፍጡር -በአምላኩ ታርጋ፣
እንደመጣ ሁሉ -ይሄዳል እሱ ጋ።

አንድም ወይ ይፀድቃል- አንድም ወይ ይቀጣል
ከፈጠረው ጌታ -ወደየት ያመልጣል ???

#Man

መልካሙ ታደሰ

@Amharicpoem1222

Amharic Poem❤️

03 Jul, 07:39


ስማኝማ………….

መስመርህን (ምሕዋርህን) ሳትለቅ እንደ ፀሐይ አብራ::
የዚያን ጊዜ ሌሎች…….
“ባንተ ዙሪያ ይዞራሉ ልክ እንደ ተራራ
ከፈለግህ እንደ ውኃ ሁን
ሁሉም ጥማቸውን ለማራስ ከአንተ ዘንድ ይመጣሉ
ሲቦጫጭቁህ እንደ መሬት ቻይ ሁን
በኋላ ተጠቃለው ከስርህ ይመጣሉ::


የዓለም ሕዝብ በሙሉ ክፉ ቢሆን አንተ መልካም ሁን:: በተቃራኒው የዓለም ሕዝብ በሙሉ መልካም ከሆነ አንተም መልካም ሁን:: የሌላው ክፋትም ይሁን ደግነት አይመለከትህም:: ሁሌ መልካም ሁን:: ምክንያቱም መልካሞች ሞልተዋል:: ያላገኘሃቸው እኮ በውሎህ ምክንያት ነው:: እነርሱ ጋር መቀላቀል የምትችለው መልካም ስትሆን ብቻ ነው:: ስለዚህ ደግ ሁን:: በዚያው ጽና:: ሳታውቀው ደጋጎች መሃል ላይ ትገኛለህ::


@Amharicpoem1221

Amharic Poem❤️

03 Jun, 06:49


…………………..
…………………..

ለሰው ነውር ሆኖ
ተደርጎበት ክልክል
ምንድነው መተከዝ
ምንድነው መቀምጠል

ወንድ አይደለህ እንዴ
እንዴት ታለቅሳለህ
ቆፍጠን በል እንጂ ምን እንዳህ አረገህ

እየተባለ አድጎ
ያን ልማድ አድርጎ

ብሶቱን ሀዘኑን
ውጋቱን ሸሽጎ
ብዙ ወንድ ይኖራል
ከፍቶት እንዳልከፋው - እንባውን ዋጥ አርጎ!


#Man
@Amharicpoem1221

Amharic Poem❤️

22 May, 06:04


......✍️ልቧ ላይ ፡ የሆነ የከረመ ጠባሳ አለ መሰለኝ ፡ በቀልዶቼ ደስ ብሏት ከሳቀች በኋላ ፡ መልሳ በሀሳብ ጭልጥ ትላለች። እስሯ ቁጭ ብዬ ፡ እንዳልነበር ፡ አንድ ላይ ትረሳኛለኝ።
........ እጄን ትከሻዋ ላይ አሳርፌ ፡ በለሆሳስ ፡ አይን አይኗን እያየሁ ፡ ''መክሊቴ ''ስላት በድጋሚ ፡ ከገባችበት ቅዠት ትወጣና፡ ......''አቤት '' ትለኛለች።
..........................
ይሄ ነገሯ እያደር ተላምጄዉ ነዉ መሰለኝ 🙄፡ ከጓደኞቼ ጋር ቁጭ ብዬ ፡ እየተጫወተን ባለንበት ሰዓት ፡ እነሱ ከት ብለዉ ሲስቁ ፡ እኔ ለማልቀስ ይዳዳኛል ፡ አልቅስ አልቅስ ይለኛል ።.... ....ምክንያቱም ከእነርሱ ጋር ሆኜ የማስበዉ ፡ ስለሷ በሀሳብ መዋለልና መተከዝ ነዉ ፡ ፍቅር ማለት መተሳሰብም አይደለ ?.......ሀዘኗን ማጥፋት  ባልችል እና ደስተኛ ባላደርጋትም ፡ቢያንስ ዘለቄታዊ ትካዜና ድብርቷን ተካፍዬላታለሁ ።

@Amharicpoem1221

Amharic Poem❤️

21 May, 07:42


ጠብቂኝ አልመጣም.......

ከቀጠርሽኝ ቦታ ሂጂ ተገተሪ፣
ዛፉን ተጠልለሽ ግራ ቀኝ አማትሪ....

......ጠብቂኝ አልመጣም........

..አላፊ አግዳሚዉ ይጠቋቆምብሽ፣
የመንደሩ ዉርጋጥ ከበዉ ይሳቁብሽ፣
የተጠለልሽዉ ዛፍ አይቶ ይታዘብሽ....

.......ጠብቂኝ አልመጣም.........

...የእጅ አይበሉባሽን፣አስሬ አገላብጭዉ፣
ጉንጭሽን ሳብ አርገሽ፣ጊዜዉን ገላምጭዉ፣
በቀኝ መዳፍሽ ሰዓቱን አጋጭዉ....

.....ጠብቂኝ አልመጣም....

...በስንጣሪ እንጨት መሬቱን ቆፍሪ፣
ዉር ዉር ሚለዉን መኪና ቁጠሪ።
እሱ ሲሰለችሽ ጎርደድ ጎርደድ በይ፣
ግንባርሽን ይዘሽ አንጋጪ ወደላይ...

ጠብቂኝ አልመጣም......

ሀሩሩ ከሞቀሽ ጃኬትሽን አዉልቂዉ፣
በሁለት እጆችሽ ወገብሽን እነቂዉ፤
በቀኝ በግራ እግርሽ መሬቱን ደልቂዉ፣
ቀጥሮ መጠበቅን ህመሙን እወቂዉ....

....ጠብቂኝ አልመጣም.......

..የሚል ደብዳቤየን ከቀጠሮዉ ሰአት አስቀድሜ ፅፌ፣
እየጠበኩሽ ነዉ ከቀጠርሽኝ ቦታ ግንዱን ተደግፌ።
አያስችለኝ.....


#Tebkign

@Amharicpoem1221

Amharic Poem❤️

19 Apr, 07:51


ሰሚኝማ ልመርቅሽ


ስሚኝ እና ልመርቅሽ
አንዴ ልብሽን ክፈቺው
ተስፋሽን እንደ-ምኒልክ ደኩላ
ቀንድ ያቆንድሸው
ጠላቶችሽ የኮሬብ እሳት ይፍጃቸው
ችግርሽ በአዜብ ነፋስ ይበተን
ስቃይሽን የናጌብ ውሀ ይውሰደው

አምላክ የኪሩቤልን ክንፍ
ከትከሻሽ ያኑርልሽ
የሱራፈልንም ክንፍ
ለእግሮችሽ ይግጠምልሽ

ዳሩ ግን ግን አንቺ
አግር አለሽ መወገጃ
ችግር መውጫ መራመጃ
እንጃ!😔

#Lemerkesh #Poem

@Amahricpoem1221

Amharic Poem❤️

15 Apr, 07:09


...............👇

ካሰብከው ለመድረስ🏃‍♀️
ካቀድከው ለመቆም🕴️
ህልምህን ተከተል እርግማኑን አክስም

መንገድህን ስትይዝ
ብትደናቀፍም ላትወድቅ ተግተርተር
መስተዋትህ ሆኖ ነገህን ሊያሳምር
ሁሌም ካንተ ጋር ነው ቸሩ እግዚአብሔር🙏🙏🙏


#Pray #Peot


@AmharicPoem1221

Amharic Poem❤️

10 Apr, 03:38


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።

መልካም በዓል❗️

😍@Amharicpoem1221

Amharic Poem❤️

05 Apr, 05:29


ከመሞት ባተርፋት ....


አገሬን ጫኑልኝ ይዣት እጠፋለሁ
ልባችሁ ሲረጋ፣
ቀልባችሁ ሲሰክን፣
የበታችነት ስሜት
ቆርጦ ሲተዋችሁ፤
እመልሳታለሁ።

#Ethiopia

@Amharicpoem1221

1,178

subscribers

32

photos

4

videos