የአማራ ክልላዊ መንግሥት፣ በአውሮፓዊያኑ 2025 ለሰብዓዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች 102 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ትናንት ከዓለማቀፍ አጋሮች ጋር በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ መግለጡን ዶቸቨለ ዘግቧል።
ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ አሁንም በሚካሄደው ጦርነት ሳቢያ 6 ሺሕ154 ትምህርት ቤቶች እንደወደሙ የክልሉ መንግሥት በመድረኩ ላይ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።
የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ በክልሉ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዕርዳታ ፈላጊ ሕዝብ እንደሚገኝም በመድረኩ ላይ ገልጧል ተብሏል።
ከአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ሰብዓዊ ዕርዳታ ያገኙ የነበሩት ዋግኽምራ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ባኹኑ ወቅት ዕርዳታው እንደተቋረጠባቸው ኮሚሽኑ ማስታወቁንም የዜና ምንጩ ዘገባ አመልክቷል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter