ካሳቫ የተባለው ስራስር በእንጀራ ላይ ተጨምሮ እንዲሸጥ ተፈቀደ‼
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድሃኒት ባለሥልጣን ካሳቫ የተባለው ሥር በእንጀራ መልክ እንዲቀርብ መፈቀዱን አስታውቋል።
ካሳቫ የስራስር አይነት ሲሆን፤ በተለይ በደቡቡ የሀገሪቱ ከፍል ምርቱ በብዛት ይገኛል።
የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ ስሙ ካዛቫ የተባለ ሥር ከምግብ ምድብ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ከእንጀራ ምርት ጋር ተቀላቅሎ ለምግብነት እንዲቀርብም መፈቀዱን ተናግረዋል።
ነገር ግን ይህን ተገን በማድረግ ሌላ ባዕድ ነገር የሚቀላቅል ስለማይጠፋ በተቻለ አቅም የቁጥጥር ሥራ ይሠራል ብለዋል።
የካሳቫ ተክል ከፍተኛ የካርቦሀይድሬት መጠን ያለው ሲሆን በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ነው።
ካሳቫ የስኳር በሽታን፣የልብ በሽታን እንዲሁም የህዋስ እርጅናን/cell aging/ እንደሚከላከል ሳይንሳዊ ጥናቶች ያሳያሉ።
ካሳቫ ተክል መነሻው ከመካከለኛው አሜሪካ ሲሆን ወደ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባው በፈረንጆች 1558 በፖርቹጋሎች ሲሆን ተክሉን በማብቀል ከአፍሪካ ሀገራት ኮንኮ ቀዳሚዋ እንደሆች ታሪክ ያስረዳል።
አሁን በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት በስፋት የሚመረት ሲሆን በሀገራችንም በደቡብ ኢትዮጵያ በስፋት ይመረታል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter