Последние посты አዲስ ሪፖርተር - NEWS (@addis_reporter) в Telegram

Посты канала አዲስ ሪፖርተር - NEWS

አዲስ ሪፖርተር - NEWS
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
37,413 подписчиков
10,211 фото
227 видео
Последнее обновление 01.03.2025 12:34

Похожие каналы

Ethiopian Press Agency/አማርኛ /
29,456 подписчиков
Abyssinia Media - አቢሲኒያ ሚዲያ
17,896 подписчиков
Ethiopia Commodity Exchange
7,923 подписчиков

Последний контент, опубликованный в አዲስ ሪፖርተር - NEWS на Telegram


የአማራ ክልል የ102 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ያስፈልጋል

የአማራ ክልላዊ መንግሥት፣ በአውሮፓዊያኑ 2025 ለሰብዓዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች 102 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ትናንት ከዓለማቀፍ አጋሮች ጋር በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ መግለጡን ዶቸቨለ ዘግቧል።


ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ አሁንም በሚካሄደው ጦርነት ሳቢያ 6 ሺሕ154 ትምህርት ቤቶች እንደወደሙ የክልሉ መንግሥት በመድረኩ ላይ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።


የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ በክልሉ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዕርዳታ ፈላጊ ሕዝብ እንደሚገኝም በመድረኩ ላይ ገልጧል ተብሏል።

ከአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ሰብዓዊ ዕርዳታ ያገኙ የነበሩት ዋግኽምራ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ባኹኑ ወቅት ዕርዳታው እንደተቋረጠባቸው ኮሚሽኑ ማስታወቁንም የዜና ምንጩ ዘገባ አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

በመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከ3,700 በላይ ሠራተኞቹን ከሥራ አሰናበተ

በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው ከሰም የስኳር ፋብሪካ፣ በክልሉ እየተከሰተ ባለው ለወራት የቀጠለ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይፋ ባደረገ በወሩ፣ ከ3,700 በላይ ሠራተኞቹን ከሥራ ማሰናበቱ ታወቀ።
በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው በካምፕ የተጠለሉ 3,750 ቋሚና ጊዜያዊ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች፣ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባልጠበቁት ሁኔታ ከሥራ ተሰናብተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣ ሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ፡፡ ፕሬዝደንቱ ከኮሚሽነሩ ባንኮሊ አዶዬ ጋር አህጉሪቱ በገጠሟት ፈተናዎች በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ባሉት ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ጥልቀት ያለው ውይይት ማድረጋቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ሲናገሩ ‹‹ምእራባዊያን አፍሪካን የእርስ በእርስ ጦርነቶች ማእከል አድርገው የሚገልፁት በጦርነቶቹ መሀል ጣልቃ ለመግባት ነው›› ማለታቸውን ያስታወቁት አቶ የማነ ይህንን ድርጊት አሳፋሪ በማለት መግለፃቸውንም አስረድተዋል፡፡ ‹‹እንደአለመታደል ሆኖ የአፍሪካ ህብረት እነዚህ አሰራሮች ለማስተካከል እርምጃዎችን መውሰድ አልቻለም›› ያሉት አቶ ኢሳያስ የአፍሪካ ህብረት ጦርነቶችንና ግጭቶችን ለመቆጣጠር ጊዜና ጉልበቱን ከሚያባክል ይልቅ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ማድረግን ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ማሳሰባቸውን አቶ የማነ አስረድተዋል፡፡

ፕሬዝደንት ኢሳያስ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ ‹‹የአፍሪካ ህብረት ያሉበት መዋቅራዊ ድክመቶች ከውጭ ጣልቃ ገብነት ጋር ተዳምረው ድርጅቱ የአፍሪካዊያንን ምኞትና ፍላጎት እንዳያሟላ እንቅፋት ሆነውበታል፡፡ የሚያሳዝነው ደግሞ የአፍሪካ ህብረት አይሆንም የማለት አቅም በማጣቱ የተወሰኑ አገራት ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚያደርጉትን ጥረት ቀጥለውበታል›› ያሉ ሲሆን በእሳቸው እይታ የአፍሪካ ልማት ምን መምሰል እንዳለበትም ማብራሪያ እንደሰጡ አቶ የማነ ገልፀዋል፡፡

በተለይም የሱዳንንና የሱማሊያን ጉዳይ በተመለከተ ሀሳባቸውም መግለፃቸውንም አስረድተዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ለኤርትራ ቴሌቪዥን በሰጡት አጭር መግለጫ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በሱዳንና በሱማሊያ ጉዳይ የተሰጣቸው ገለፃ ጥልቅና በሳል መሆኑን ተናግረዋል ብለዋል አቶ የማነ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

♨️ እንኳን ደስ አላችሁ ለመላው ስራ ፈላጊ ኢትዮጲያዊያን!
  -----------------------------------
Make Money Online In Ethiopia 🇪🇹

           በቀን 3000 ብር የሚከፍል ዌብሳይት

15,000- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት  እና በልምድ

🔺የትምህርት አይነት: በተለያዩ ዲፓርትመንቶች
🔺የስራ ልምድ: በ 0 ዓመትና በልምድ
🔺 የቅጥር ሁኔታ: በቋሚ ቅጥር
🔺 ብዛት: 15,000+ በላይ
🔺ደሞዝ:  በቀን 3000 ብር
 
🛑 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ  ስራውን ይጀምሩ

⁉️ ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon ይክፈቱና

      👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇
                        👇👇👇👇
https://reportervacancy.com/make-money-online/

--------Follow Our Website--------
                     👇👇👇👇👇👇
         https://reportervacancy.com

----------Join Our Telegram-------
                               👇👇👇👇👇
     https://t.me/reporter_vacancy

መንግሥታቸው የውጭ እርዳታ ለመቀነስ መወሰኑን በመቃወም ስልጣናቸው የለቀቁት የብሪታንያ ሚንስትር

የብሪታንያ የዓለማቀፍ ዕርዳታና ልማት ሚንስትር አነሊሴ ዶድስ፤ መንግሥታቸው የውጭ እርዳታ በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ መወሰኑን በመቃወም ትናንት በፍቃዳቸው ከሥልጣን ለቀዋል።

ሚንስትሯ የዕርዳታ በጀት ቅነሳው በዓለም ዙሪያ በምግብና ጤና ድጋፍ ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል በማለት ተቃውመውታል።

ሚንስትሯ ከሥልጣን የለቀቁት፤ ጠቅላይ ሚንስትር ኬር ስታማ የአገሪቱን የመከላከያ በጀት ለመጨመር ሲሉ የውጭ እርዳታ በጀታቸውን መቀነሳቸውን ይፋ ባደረጉ ማግስት ነው።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት 0 ነጥብ 5 በመቶ የነበረውን የውጭ ዕርዳታ በጀት ወደ 0 ነጥብ 3 በመቶ ነው የቀነሱት።

ብሪታንያ በአውሮፓዊያኑ 2023 ብቻ 19 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ሰጥታለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

ትራምፕ ዘለንስኪን “አሜሪካን አላከበርክም" ሲሉ፤ ዘለንስኪ ዋይት ኃውስን ጥለው ወጥተዋል

የአሜሪካው ፕሬዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ በዋይት ኃውስ ያደረጉት ውይይት ያለ ምንም ስምምነት ተጠናቋል።

ዘለንስኪ ወደ ዋይት ኃውስ ያቀኑት በውድ ማእድናት ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ስምምት ለመፈራረም ቢሆን፤ ሁለቱ ወደ ክርክር እና የቃላት ግጭት አምርቶ ያለ ምንም ሰምምት ተጠናቋል።

ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ጋር የጦፈ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው ውይይታው የተቋረጠው።

በዋየት ኃውስ በኦቫል ፅህፈት ቤት በነበራው ቆይታ ዶናድ ትራምፕ ቮሊድሚር ዜልኒስኪን “አክብሮት የጎደለው ባህሪ” ከሰዋል።

በንግግራው ወቅትም ትራምፕ ዘሌንስኪን “በሚሊየኖች ህይወትና በ3ኛ የዓለም ጦርት ቁማር እየተጫወትክ ነው” ብለዋል።

ዘለንስኪ የሰለም ስምምነት ለመፈረም ዋስትና ያስፈልገናል ማለታችውን ተከትሎም፤ ትራም ዘለንስኪን ያለህ አማራጭ ስምምነቱን መፈረም ነው ካልሆነ አሜሪካ ከዚህ ትወጣለች ሲሉም ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ዘለንስኪ በሰላም ውይይቱ ዙሪያ ካለመግባባታቸውም ባሻገር "ለሰላም ስትዘጋጅ ተመለሰህ ና" ብለዋል።

ይህንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ዋይት ሀውስን ጥለው የወጡ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ሊያደርጉት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫም ተሰርዟል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

ምርጫው የእርሶ ነው !

"ባንክ ሲቆጥቡ 7% ወለድ ያገኛሉ
የአያት አክሲዮን ባለቤት ሲሆኑ ግን በግማሽ ያተርፋሉ"

በ2016 ዓ.ም ብቻ

❇️የ100,000 ብር የአያት አክሲዮን ድርሻ ያላቸው 45,020 ብር አትርፈዋል

❇️የ1,000,000 ብር የአያት አክሲዮን ድርሻ ያላቸው 450,200 ብር አትርፈዋል

❇️የ2,000,000 ብር የአያት አክሲዮን ድርሻ ያላቸው 900,400 ብር አትርፈዋል

❇️የ5,000,000 ብር የአያት አክሲዮን ድርሻ ያላቸው 2,251,000 ብር አትርፈዋል

❇️የ10,000,000 ብር የአያት አክሲዮን ድርሻ ያላቸው 4,502,000 ብር አትርፈዋል

❇️ከተመዘገቡ ከ1 ወር ጊዜ ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ ስለሚሆኑ  ከ112,500 ብር ጀምሮ ፈጥነው በመመዝገብ የ8 ግዙፍ ድርጅቶች ባለቤት በመሆን በቶሎ የትርፍ ተካፋይ ይሁኑ

❇️ ትርፋማ የሆነውን የአያት አክሲዮንን ለእርስዎ ፣ ለታዳጊ ልጅዎ  ፣ ለቤተሰብዎ እና ለወዳጅ ዘመድዎ በስጦታ ያበርክቱ

❇️ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ባላችሁበት ወይንም በወዳጆቻችሁ በኩል የአያት አክሲዮን ባለቤት መሆን ትችላላቹህ

☎️ ለበለጠ መረጃ
0912024560 በቀጥታ 
በቴሌግራም 
ወይንም  በዋትሳፕ ይደውሉ 

ከጠ/ሚ አብይ ሶማሊያ ጉዞ በኃላ አሜሪካ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

ትናንት በሶማሊያ ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ የሞርታር ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ አሜሪካ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣች፡፡

በኬንያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በትናንትናው እለት በሞቃዲሾ በሚገኘው አደን አዲ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተደጋጋሚ ጥቃት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ አሜሪካዊያን በዚያ አየር ማረፊያ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል፡፡

ሌላ ማስታወቂያ እስከሚወጣ ድረስ በሱማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአየር ማረፊያው ከመጠቀም እንዲቆጠብም አሳስቧል፡፡

በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድን የያዘው አውሮፕላን ሞቃዲሾ ከመድረሱ በፊት አየር መንገዱ አካባቢ 11 ጊዜ የሞርታር ጥቃት መፈፀሙንና አንዱ ኤርፖርቱ ውስጥ ማረፉን፣ከቱርክና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ውጪ በረራ መከልከሉንና በርካታ የሞቃዲሾ መንገዶች መዘጋታቸውን ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

1446ኛው  የረመዳን ወር ነገ  ቅዳሜ የካቲት 22 ይጀመራል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺህ ብር ያስቀጣል

በአዲስ አበባ ተግባራዊ የሚደረግ የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ ይፋ ሆኗል።
የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብን መተላለፍ የሚያስከትለው ቅጣት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በባህሪው አደጋኝነት የሆነ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በወንዝ ዳርቻ ያሰወገደ ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር ይቀጣል፣

ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ወንዝ ላይ የጣለ ግለሰብ 500 ሺህ ብር ይቀጣል

ፍቃድ የወሰዱም ሆነ ሳይወስዱ ፍሳሽን ቀጥታ በወንዞች ዳርቻ ሲያስወግዱ ቢገኙ 100 ሺህ ብር ይቀጣሉ፣

በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺህ፤

የፈሳሽ ማጣሪያ ሳይኖር በወንዝ ዳርቻና አካባቢ ተሽከርካሪ ማጠብ 400ሺህ ብር፤

ሙሉ ቅጣቱ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter