‼️በሸማ ተራ የተነሳውን የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ነው።
ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻዉን በመርካቶ ሸማተራ አየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በንግድ ሱቆች ላይ የተነሳዉን የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ርብርብ እያደረጉ ነዉ።
አካባቢው የተጨናነቀ እና ለተሽከርካሪ አስቸጋሪ በመሆኑ እሳቱን በፍጥነት ለመቆጣጠር አስቸጋረ አድርጎታል ሲሉ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።
የአደጋ ገዜ ባለሙያዎች እና ተሽከርካሪዎች በስፍራው ከሚገኘው ቅርንጫፍ በተጨማሪ ከሌሎች ቅርንጫፎች መላካቸውን ለማወቅ ተችሏል።
👀 https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia