Mulugeta Anberber

@mulugetaanberber


ፈጣን መረጃ እንዲሁም ለዕለታዊ ክንውኖች ወዳጅ ይሁኑ❗️

ዜናው ጥሩም ይሁን፤ መጥፎ እነግራችኋለሁ፡፡


መረጃ ለመላክ @Mulugetaanberberrrr

Mulugeta Anberber

22 Oct, 17:24


የድል ዜና

በሸዋሮቢት ከተማ አቅራቢያ አስፋቸውና ዋንዛ በተባሉ ቦታዎች ላይ በተጣለ የደፈጣ ጥቃት የጠላት ብልፅግና ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።

በአረመኔው አብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና ሰራዊት ወታደራዊና የፖለቲካ አመራሮችን አጅቦ  ለማሳለፍ ሲሞክር በተወሰደበት የደፈጣ እርምጃ መደምሰሱ ታውቋል።

በተወሰደው የደፈጣ እርምጃ የሰራዊቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ከእነ አጃቢዎቻቸው እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን በጠላት ሃይል ላይ ትልቅ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ኪሳራም ደርሶበታል።

የደፈጣ የተካኑት አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ደሳለኝ ነጋሽ ብርጌድና አንበሳው ብርጌድ በጋራ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት የብልፅግና ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምክልል ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ስንታየሁ ደመቀ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነፃነት አንደበት !

https://t.me/ethio251media

Mulugeta Anberber

22 Oct, 15:45


https://youtube.com/live/lO5ASsQKQE0?feature=share

Mulugeta Anberber

22 Oct, 14:37


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ወገራ ከተማን ተቆጣጠረ!

በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ በፋኖ ዋና እሙሃይ እየተመራ ወገራ ከተማን ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም መቆጣጠሩን የብርጌድ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ መምህር ፋኖ አገሩ ታዲያ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

ከሁለት ቀን በፊት በተካሄደ ውጊያም የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ናሁሰናይ ብርጌድ ንስር ሻለቃ ከራስ ደጀን ብርጌድ በጋራ ጥምረት ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም 18 ሙት፣ 25 በላይ ቁስለኛ በማድረግ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታቱን የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ናሁሰናይ ብርጌድ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ መምህር ፋኖ አገሩ ታዴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

የአብይ አህመድ አገዛዝ በፋኖ ከፍተኛ ምት ሲደርስበት ንጹሃንን ታርጌት ያደረገ ግድያ እየፈፀመ እንደሆነ ተገልጿል።

ዝርዝር ጉዳዮችን "በ251 ዛሬ" ዝግጅታችን ይጠብቁን።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media

Mulugeta Anberber

22 Oct, 13:50


ሰበር ዜና

የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ኃይል አምባ ጊዮርጊስ ላይ ድባቅ ተመታ!

በአርበኛ ሀብቴ ወልዴ የሚመራው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ቴዎድሮስ ብርጌድ አሳምነው ሻለቃ፤ በፋኖ ወርቁ ዘገዬ እየተመራ አምባ ጊዮርጊስ ከተማ ዘልቆ በመግባት በርካታ ጀብዱዎችን መፈፀሙን ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ኢትዮ 251 ሚዲያ አረጋግጣለች።

አምባ ጊዮርጊስ ላይ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያ የጠላት ኃይል ከፍተኛ ኪሳራ ሲደርስበት አማራ በመሆናቸው ብቻ የታሰሩ ንጹሃንን እስር ቤቱን በመስበር ማስፈታት መቻሉን ኢትዮ 251 ሚዲያ አረጋግጣለች።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ቴዎድሮስ ብርጌድ አሳምነው ሻለቃ የጠላትን ኃይል ድባቅ የመታችው ሲሆን ከተማ ላይ የነበረው የብልጽግና ሰራዊት የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው እየፈረጠጠ ካምፕ መግባቱን የጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር አመራሮች ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጸዋል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media

Mulugeta Anberber

22 Oct, 12:49


የአዲስ አበባ ሕዝብ፤ አታጋይ ድርጅት በማጣቱ ወይስ የብልጽግና አገዛዝ ተስማምቶት ነው በዝምታ የቆየው? ትንታኔው መልስ አለው።

https://youtu.be/cv0FiJUjHEI?si=xJXSIX0htREgD2pz

Mulugeta Anberber

22 Oct, 09:16


ሰበር ዜና!

ወልደያ ከተማ ላይ የአገዛዙ ሰራዊት በደፈጣ ተመታ!

ወልድያ ዙሪያ አሳምነው ክፍለጦር እያደረገ ያለው ተጋድሎ የቀጠለ ሲሆን ባህር ዳር መውጫ አፍሪኬር አካባቢ ጠላት ኬላ የሚያደርግበት ቦታ ላይ ደፈጣ በማድረግ የጠላት ኃይል ድባቅ መመታቱን የአማራ ፋኖ በወሎ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ አበበ ፈንታው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገለጸ።

የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ወታደር በደረሰበት ጥቃት ጠላት አምስት ሙትና ስድስት ቁስለኛ ያነሳ ሲሆን በወልድያና በሳንቃ በኩል ሁለት ዙ23 በማምጣት በዘፈቀደ እየተኮሰ ሲሆን ቃሊም መግቢያ አቦ ቤተ-ክርቲያን አካባቢ ሁለት እናቶችን በከባድ ሁኔታ ማቁሰሉን ገልጾ፤ አንደኛዋ እናታችን ወዲያውኑ ማረፋቸውን ፋኖ አበበ ፈንታው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

አገዛዙ አሁን ላይ ወደመጣበት የሸሸ ሲሆን ወልድያ ከተማ ተረጋግቶ መቀመጥና ስራ መስራት ስላልቻለ ራያ አላማጣ ያስቀመጠዉን ተጠባባቂ ቀይ ቆብ ለባሽ ፈርጣጭ ሰራዊቱን ዛሬ ያስገባ መሆኑን አረጋግጠናል፤ ቢሆንም ግን የሚያመጣው ለውጥ ስለማይኖር ተጋድሎዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የሕዝብ ግንኙነቱ ፋኖ አበበ ፈንታው ለጣቢያችን አስታውቋል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media

Mulugeta Anberber

22 Oct, 08:43


ታላቅ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ!
በ16 ከተሞች!

Mulugeta Anberber

21 Oct, 16:44


https://www.youtube.com/live/YoJ2ANjzCJc?feature=shared

Mulugeta Anberber

19 Oct, 19:23


ለ12 ቀን ሲካሄድ የነበረውን ስብሰባ ሙሉ ለሙሉ ስከታተለው ነበር። እናም በተስፋ መቁረጥ ደምደውታል!

የመጨረሻ ውሏቸው፦
የስብሰባ አዳራሽ- አድዋ 00 ሙዚዬም

ውሎ ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን!

ጠ/ሚ እስካሁን የሰነበቱባቸውን የ10 ሰነዶችን ዋና ዋና የሚላቸውንና አዳማ ያቀረበውን ቪዲዮ ሙሉ ሳይሆን ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያ ሲነሱ የነበሩትን ጉዳዮች ተቆርጦ እንዲቀርብ ተደርጓል። ከተቆረጡት ንግግሮች መካከል (ኤርትራን እንደጋዛ) በዚሁ ውስጥ አጠቃላይ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታ አንስቷል። ከአንሳቸው ነጥቦች መካከል "አመራሩ የፅንፈኛ ምሽግ ናችሁ፣ እናንተ ሰርታችሁ ለውጥ አታምጡ፣ የሆነ ነገር ሲነገራችሁ አንገት መነቅነቅና ከንፈር መምጠጥ ሆኗል ስራችሁ" ብሏቸዋል።

ቀጥሎም "አጠቃላይ እኛ አሁን ባለው ሁኔታ ከንጉሱ ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ ድርስ በምስለኔ እንጅ ሶማሌ በራሱ ተወላጅ ክልሉን መርቶ አያውቅም፣ አፋር በራሱ ተወላጅ ተመርቶ አያውቅም፣ ክልሎች አሁን ያላቸውን ያክል ነፃነት ኖሯቸው አያውቁም።" እያለም ቀባጥሯል። ታሪክ ስለማያውቅ ከዚህ የተለዬ ሊናገር አይችልም።

#ስለDiplomacy፦ ዙሪያችን ብዙ እድገታችንን የማይወዱ በክፉ አይን እየተመለከቱን ነው። የባህር በር ጥያቄ ጉዳይ ነገም የማንተወው ጉዳይ ነው ብሏል። በቪዲዮ ላይ ባለፈው ናዝሪት ላይ በተካሄደው ስብሰባ ኤርትራን እንደ ጋዛ እናደርጋታለን ያለውን ቆርጠውታል።

አብይ አህመድ ከፋኖ ጋር እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ምንም ያለው ነገር የለም፤ ግን ንግግሮቹ ሁሉ የተስፋ መቁረጥ ይመስላል።

#####################

ከአብይ አህመድ ማጠቃለያ በመቀጠል ከንቲባ ተብዬዋ በአካል መጥታ የስራ መመሪያ ልሰጥ ነው በሚል ደስኩራለች።

በንግግሯም "እናንተ የምንሰራውን ስራ ጠላት ሲያራክሰው እያያችሁ ምንም አይመስላችሁም፣ እኛ ከተማዋ እየቀየርናት ነው፣ ማንም ቢጮህ እኛ ከጉዟችን የሚያግደን ነገር የለም።" የሚል እረጅም ሰዓት ወስዳ እጅና እግር የሌለው ማጠቃለያ ነበር።

በንግግሯ ተስፋ መቁረጧን መረዳት ችያለሁ። አዳነች ከተናገረቻቸው ነጥቦች "እስኪ የምር ብልፅግና ሁኑ፤ መጀመሪያ እናንተ የምር መሆን ብትችሉ የሚያቅተን ነገር የለም፣ ሌብነት ተንሰራፍቷል። አሁን ባለው ሁኔታ ተቋማዊ ሌብነት ባይኖርም ከወዲሁ ማስተካከል ካልቻልን ወደ ተቋማዊ ሌብነት መሄዱ አይቀርም። በየቡድኑ ስለ ሌብንት ብዙ አንስታችኃል ግን ማነው ሌባው? ማነው የእጅ መንሻ የሚቀበለው? ለምን መታገል አቃታችሁ ብላ ጥያቄውን ወደ ተሳታፊው መልሳዋለች።" ቀጥላ ግን ይሄኛውን ከላይ ያነሳችውን ነጥብ የሚያፈርስ ሀሳብ ሰንዝራለች። ይህ ሀሳብም እንዲህ ይላል:- "ፊርማ አትፍሩ እኛ የኮሪደር ልማቱን ለማፋጠን ስንል አንዳንድ አሰራሮች ላንጠብቅ እንችላለን፤ የፋይናስ አሰራር እንጠብቅ ካልን በአሰብነው ጊዜ መጨረስ አንችልም፤ ስለዚህ የወረዳ አመራሮች በእኛ በኩል የመጣ ከሆነ 'ለለውጥ' ስለሆነ ያለምንም ፍርሃት የሚፈረም ነገር ካለ አትሸማቀቁ ፈርሙ እኛ ሀላፊነት እንወስዳለን" ብላለች።

ከፋኖ ጋር እየተደረገ ስላለው ጦርነት አለቃው አብይ አህመድ የፈራውን ሀሳብ እሷ አንስታዋለች።

"አማራ ክልል የተፈጠረውን ችግር ማስተካከል ያልቻልነው፤ ሕዝቡ በተግባርም በአመለካከትም የፋኖ ተባባሪ ስለሆነ ነው እንጅ ከመከላከያ አቅም በላይ ሆኖ አይደለም።" ብላለች።

አጠቃላይ የሁለቱም ማጠቃለያ በተስፋ የተሞላ ሳይሆን በተስፋ መቁረጥ የተደረግ ማጠቃለያ ነው ያደረጉት!

ስብሰባው ሲጠናቀቅ ተኝተው የነበሩት ተቀስቅሰው ወደ ቤታቸው ሂደዋል!

አንበርብር!
https://t.me/Mulugetaanberber

Mulugeta Anberber

19 Oct, 17:39


📌የኢትዮ ቴሌኮምን ሼር በተመለከተ (Boycott)

1ኛ. ኢትዮ ቴሌኮም የብር እና የዶላር ምንዛሬ በገበያ ትይዩ እንዲደረግ ከመወሰኑ ቀድም ብሎ የነበረው ጠቅላላ ዋጋ 80 ቢሊየን ብር ነው ተብሎ ነበር። ዶላር 100 ቤት ሲገባ ሁላችንም በግማሽ እንደደኸየነው ኢትዮ ቴሌኮምም ዋጋው ወደ 40 ቢሊየን ይወርዳል ማለት ነው። እሺ በጦርነት የወደመበትን ንብረት፣ አገልግሎት ባልሰጠባቸው ቦታዎች ያጣውን ገቢ ምናምን እንተወውና 20 ቢሊየን ጨምረንለት 100 ቢለየን ብር ዋጋ እንስጠው።

የቴሌኮሙ 10 ከመቶ ድርሻ 30 ቢሊየን ነው ከተባለ ጠቅላላ ዋጋው 300 ቢሊየን ነው ማለት ነው። ይህ የተጋነነ ዋጋ (Overvalued) ወይም ማውጣት ከሚችለው በላይ ነው ማለት ነው። የ10 ብር እቃ በ1ሺ ብር መግዛት ከፈለግህ መብትህ ነው።

2ኛ. ኢትዮ ቴሌኮም በጣም ከፍተኛ እዳ ያለበት ተቋም ነው። ይህን ያክል እዳ ካለበት ተቋም ሼር መግዛት ካዋጣህ ምርጫው የአንተ ነው።

3ኛ. ኢትዮ ቴሌኮም ቬር ሸጦ የሰበሰበውን ብር ምንድነው የሚያደርገው? ተቋሙን ያዘመንብታል? ወይስ መንግስት የጦር መሳሪያ እንዲገዛበት ይሰጣል? የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት። መልሱ ብሩ ለጦር መሳሪያ ግዢ እና ሰዎችን በማፈናቀል ስልታዊ የዲሞግራፊ ለውጥ ለማድረግ እየተሰራ ባለው የኮሊደር ልማት ይውላል የሚል ነው። ህዝብህን ለመግደል ለሚውል ተቋም ገንዘብህን ካፈሰስክ ከገዳዮች አትለይም። መብቱ ግን የአንተ ነው።

4ኛ. የቴሌኮም ዘርፉ በአደገኛ ሁኔታ እየተቀየረ ነው። ኢንተርኔት ከስፔስ ላይ መግኘት ተችሏል። ከሳተላይት ኢንተርኔት የሚሰሩ ስልኮች እየተመረቱ ነው። ይህ ለውጥ አሁንም ገመድ የሚዘረጋውን ኢትዮ ቴሌኮም ያከስሩታል። በዚህ ፍጥነት ይራመዳሉ ተብሎ ስለማይታሰብ የሚያዋጣህን አንተ ታውቃለህ።

5ኛ. ኢትዮ ቴሌኮም ብዙ ገንዘብ ያባክናል። ኢቨንት ይወዳል። በሚሊየኖች ብር ለአላስፈላጊ ወጭዎች ይከፍላል። በዚህ አመት እንኳ ለኢሬቻ ብቻ የከፈለው ብር ከፍተኛ ነው። ለጥገና፣ ለመኪናና የቢሮ ኪራይ ወዘተ ብዙ ገንዘብ ያወጣል። በጨረታ የሚሰራው ሿሿ እንዳለ ሆኖ። ይህንን ወጪ እየቀነሰ እንደማይሄድ እርግጥ ስለሆነ የሚያዋጣህን አንተ ታውቃለህ።

https://t.me/Mulugetaanberber

Mulugeta Anberber

19 Oct, 15:43


https://x.com/251media/status/1847663428468355291?s=46

Mulugeta Anberber

19 Oct, 15:11


ሰበር ዜና!

በዛሬው ዕለት ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም የአገዛዙ ሰራዊት ከአዲስ ዘመንና ከእብናት ኃይሉን አግተልትሎ በአንቦ ሜዳና አካባቢው ወረራ ለመፈፀም በሌሊት ጀምሮ በተለያዩ አቅጣጫዎች እንቅስቃሴ ቢያደርግም በጀግናው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር አንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ተመክቶ መመለሱን የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

ከአዲስ ዘመን አቅጣጫ የተነሳው የጠላት ሀይል በተለያየ አቅጣጫ በማስፋት ከበባ ሊፈፅም  ቢሞክርም ብራ በተባለው አካባቢ ደፈጣ ይዞ የቆየው የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር የአንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ነበልባል ሻለቃ ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ወደመጣበት አስፈርጥጦ ልኮታል ሲል ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለጣቢያችን ገልጿል።

የጠላት ሀይል ከላይ የጀት ሀይል በማንሳፈፍ በምድር ዲሽቃና ሞርተር አግተልትሎ ቢገባም በአናብስቶቹ የሊቦ ፋኖ ተመትቶ የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ አክሎ ገልጿል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media

Mulugeta Anberber

19 Oct, 07:33


📌ድርብርብ ኃላፊነት አለብን!

ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ሕይወታችን የሰቀቀን ነበር፡፡ አማራ በመሆናችን እንዳንዶቻችን ከአማራነታችንም በተጨማሪ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች በመሆናችን ፋሽስታዊው ቡድን ዛሬ አፈነን፣ ነገ አፈነን እያልን ነበር የሰቀቀን ህይወት የምንገፋው፡፡ ያም ሆኖ ብዙዎቻችን ከመታፈን አላመለጥንም፡፡ ዛሬ ያለነው ስደት ላይ ነው፡፡ ስደት ጥሩም ባይሆን እንደ ኢትዮጵያ እታፈናለሁ ብለን ብዙ የምንሰጋበት አይደለም፡፡

ስለሆነም ድርብርብ ኃላፊነት አለብን፡፡ አንድም የሕልውና ትግል ላይ ለሚገኘውና በየእለቱ በድሮን ለሚጨፈጨፈው ሕዝባችን ድምፅ መሆን፡፡ ሁለትም በፋሽስታዊው ቡድን ታፍነው በየማጎሪያ ቤቱ ለሚገኙት ውድ ወገኖቻችን ድምፅ በመሆን አለም አቀፉ ማህበረሰብ ያለንበትን ሁኔታ እንዲገነዘብና ጫና እንዲያደርግ መታገል፡፡ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ሊያደርግ የሚችለውና የእኛን ሁኔታ በትክክል ሊገነዘብ የሚችለው በበጎ አድራጎት መልክ ሳይሆን እኛ በታገልነው መጠን ነው፡፡

ስለሆነም በውስጣችን ሊኖሩ የሚችሉ ጥቃቅን የአካሂድ ልዩነቶችን ወደ ጎን ብለን ለሚሰቃየው ሕዝባችን ስንል የመተባበርና በአንድነት ፀንተን የመቆም ግዴታ አለብን፡፡

በውጭ ሀገራት በየዩኒቨርሲቲው በትምህርት ላይ የምትገኙ የአማራ ልጆችም በውጭ ቋንቋዎች መፃፍና ስለ አማራ ሁኔታ ማስረዳት ይጠበቅባችኋል፡፡ ቢቻል ቢቻል ያላችሁበትን ዩኒቨርሲቲ ተጠቅማችሁ የጥናት ኮንፈረንሶችን ማዘጋጀትም በጣም ትልቅ ነገር ነው፡፡

በተባበረ ክንድ የምናደርጋት እያንዳንዷ የየእለቱ ጥረታችን ፍሬ አላት፡፡ ከያዝ ለቀቅ ወጥተን ጸንተን ስናታገል ምን ያክል ውጤት እንደምናመጣ እያየነው ነው፡፡

እንበርታ‼️

https://t.me/Mulugetaanberber