ቤሬ ሐር
HANDMADE ETHIOPAN SILK
ኢንተርፕራይዙ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የሚገኝ ሲሆን የሐር ትሎችን ከማራባት ጀምሮ ጨርቅ ሆኖ እስኪወጣ ድርስ ሂደቶችን ጠብቆ የሚሰራ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ድርጅት ነው፡፡ የሚያመርታቸውን የሐር አልባሳትን በአርባ ምንጭና በአዲስ አበባ ከተማ በጥራት ተደራሽ በማድርግ ላይ ያለ ድርጅት ነው፡፡
የቤሬ ሐር ኢንተርፕራይዝ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ገለታ ሐይሉ እንደተናገሩት ስራውን ከመጀመራቸው በፊት በዕህል ንግድ ላይ ተሰማርተው እንደነበርና በአንድ ወቅት ሳይንስና ቴክኖሎጅ ምርምር ከመልካሳ ምርምር ማዕከል በራዲዩ በሐር ልማት ዙሪያ ሲተላላፍ በመስማት ወደ ስራው እንደገቡ ያስታውሳሉ፡፡
ድርጅቱ በ1997 ዓ.ም በ200 ካሬ ሜትር ቦታ፣ በ600 ሺህ ብር ካፒታልና በአምስት የሰው ሐይል እንደተጀመረ የሚናገሩት ስራ አስኪያጁ በወቅቱ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት አሁን ያሉበትን የመስሪያ ቦታ እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የሐር ክሩን ብቻ በማምረት ለሚሸምኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሲሸጡ እንደነበርና አሁን ላይ ባካበቱት ልምድ የራሳቸውን ዲዛይነርና የሽመና ባለሙያዎችን በመቅጠር ያለቀለት በእጅ የተሰሩ የሐር ልብሶችን በማምረት ለገበያ እንደሚያቀርቡ አቶ ገለታ ተናግረዋል፡
የሐር ክር ለቀዶ ጥገናና ለፓራሹት መውረጃነት አገልግሎት ላይ ሲውል ልብሱ ደግሞ የሰውነትን ሙቀት በመቆጣጠር ምቾት የሚሰጥ እንዲሁም ፕሮቲን ያለው በመሆኑ በዓለም ደረጃ እጀግ ተፈላጊ ምርት አድርጎታል ያሉት ስራ አስኪያጁ በኢትዮጵያ በሐር ልማት ላይ የተሳተፉ ባለሀብቶች የሉም ብለዋል፡፡
የስራውን ሁኔታና የዘርፉን አዋጭነት ለማስገንዘብ ቤሪ ሐር ልማት ድርጅት እንደ አንድ የምርምር ተቋም ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝና ከስራው ስፋት አንጻር በራሱ ማሳ ላይ የሚያመርተው ምርት አልበቃ ብሎት በአካባቢው ያሉ 200 አርሶ አደሮችን በማሰልጠን ምርት እንደሚወስድ አብራርተዋል፡፡
የሐር ምርት በውጭ ሐገር ደረጃ ካለው ተፈላጊነት አንጻር ኤክስፖርት ለማድረግ ፍላጎት ቢኖርም በምርት አቅርቦት፣በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሐይል፣ ፋይናንስ፣ የቦታና የማሽን አቅርቦት ችግር ምክንያት በስፋት ኤክስፖርት ማድረግ እንዳልተቻለና እነዚህ ችግሮች የሚቀረፉ ከሆነ በስፍት በማምረት የውጭ ገበያውን መቆጣጠር እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
ቤሬ ሐር ኢንተርፕራይዝ ከ80 በላይ ለሚሆነ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን አጠቃላይ ካፒታሉም ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ነው፡፡
👉አድራሻ፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ኤርፖርት 800 ሜትር ገባ ብሎ ና አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ መድሐኒዓለም ገልፍ አዚዝ 1ኛ ፎቅ
☎️ ስልክ፡- 09 77 07 85 15
🌐 BER HAR፡- በማለት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮች ማግኘት ይችላሉ