ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
ችግር ውስጧን ሚረዳላት
ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
የአይኗን እንባ ሚያብስላት
ለጠየኳት ጥያቄዎች
ምንም ነበር መልሰ ቃሏ
ብዙ እንደሆነች ግን
ይናገራል ፊት አካሏ
ብቻ...ዝም ብላለች
ታስታውቃለች ሆድ ብሷታል
ታስታውቃለች እንደከፋት
ቆንጆ መልኳን ተመልክቶ
ማን ይሆን ሰው ደርሶ የገፋት
ደረቅ ብሏል ውብ ከንፈሯ
አላገኘም አንዳች እህል
ቀዝቀዝ ብሏል የእጇ መዳፍ
ምን ሁናለች እቺ ጉብል
ቀና ብላ እያየችኝ
ዘረገፈች የአይኗን እንባ
ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
ነጠላ እጇን ተከናንባ
እንዲህ ነው እያለች መናገር ባትችልም የውስጧን አውጥታ
ብዙ አውርታኛለች ከኔ ጋራ ሳለች ቃሏን በዝምታ
ይገርማል አንዳንዴ
ቃላት ሳይደረደር ምስክር ሳይጠራ ሀቀኛ ሳይለካ
ብዙ ሳንናገር በዝምታ ብቻ ቃል ይወጣል ለካ!
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan