Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

@ethionegarii

#NewsaboutEthiopia & the #Horn
ይህ የቴሌግራም ቻናል ትኩስ ዜናዎች፣ አዝናኝ መረጃዎች፣ ትንታኔዎች እና የስራ ቅጥር ማስታወቂያ የሚቀርብበት ነው።

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ አድርገው ቤተሰብ ይሁኑ።

http://youtube.com/@ethionegari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

22 Oct, 14:29

የእሳት አደጋውን ተገ አድርገው የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎች ተያዙ
          
ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ/ም ምሽት በመርካቶ ሸማ ተራ የተከሰተውን የእሳት አደጋ እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት  መድረሱንም ገልጿል፡፡     

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

22 Oct, 08:10

አዲስ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች

በተለያዩ የስራ መስኮች የወጡ የNGO ስራዎችን በዝርዝር ለመመልከት እና ለማመልከት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://ethionegari.com/2024/10/22/latest-ngo-jobs-in-ethiopia-9/

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

22 Oct, 07:57

ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ጭማሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሙሉ ዕወቅና ለመስጠት ሲያስከፍል የነበረው 200 ብር ቢሆንም ከትናንት ጀምሮ ግን 30ሺህ ብር ማድረጉን አስታወቀ፡፡

በመቶኛ ሲሰላ - ከ150% በላይ ነው፡፡

ቦርዱ ባወጣው መግለጫ ለሀገር አቀፍና ለክልላዊ ፓርቲ ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት ለማግኘት ያስከፍል የነበረው 100 ብር ሲሆን ከትናንት ጀምሮ ግን በአንድ መቶ ሀምሳ ዕጥፍ (150%) ጨምሮ 15ሺህ ብር አድርሶታል፡፡

የሙሉ ዕወቅና ክፍያ 200 ብር ሆኖ እስከትናንትናው ዕለት ድረስ ቢቆይም እዚህም ላይ የ150% ጭማሪ በማድረግ ቦርዱ 30ሺህ ብር አስግብቶታል፡፡ 30 ብር የነበረው የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ ደግሞ በአንድ መቶ ስድሳ ስድስት ነጥብ ስድስት በመቶ (166.6%) አሻቅቦ 5ሺህ ብር ሆኗል፡፡

ቦርዱ ለዚህ ጭማሪው በየጊዜው መሻሻል እንደሚያስፈልግ በማመኔ ነው ይበል እንጂ ዝርዝር ጉዳዮቹን አልገለጸም፡፡

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

21 Oct, 20:51

የእሳት አደጋውን መቆጣጠር ተችሏል - አዳነች አቤቤ

መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል።

የእሳት አደጋዉን በቁጥጥር ስር በማዋል ርብርብ  ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳትና መንስኤዉን በማጣራት ቀጣይ ለህብረተሰቡ እንደሚገለፅም ከንቲባዋ ጠቁመዋል።

ምሽት 1 ሰአት ገደማ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከ4 ሰአት በላይ ጊዜ የወሰደ ሲሆን ይህም የሆነው በአከባቢው የመንገድና ሌሎች አመቺ ያልሆኑ ጉዳዮች ምክንያት ነው ተብሏል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

21 Oct, 17:05

የራይድ ታክሲ ተጠቃሚ በመምሰል ሾፌሮችን ሲገድሉ የነበሩ አራት ግለሰቦች በሞት ተቀጡ

የታክሲ ኮንትራት በመጥራት ሹፌሮችን በመግደል ተሽከርካሪ ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በተለያዩ ጊዜያት አሽከርካሪዎችን  ራቅ ወዳለ ስፍራ እየወሰዱ በመግደል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር  ስር ውለው በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በአዲስ አበባ ገላን ክፍለ ከተማ፣ በሳሪስ እንዲሁም በቢሾፍቱ መኖሪያቸውን ያደረጉት ቴዎድሮስ ብርሃኔ እና  እዩኤል ቴዎድሮስ እንዲሁም በሌላ በኩል ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ  የተባሉት ግለሰቦች  ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ በመመላለስ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር  የሸገር ከተማ አስተዳደር  ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ዓቃቢ ህግ አቶ ሚዴቅሳ አጋሩ  ተናግረዋል።

አራት ግለሰቦች ከግል ተበዳዮች በኮንትራት በመውሰድ ከዋናው መንገድ ውጪ በማስውጣት የአሽከርካሪዎቹን ህይወት በማጣፋት ተሽከርካሪዎቹን ይዞ በመሰወር  ለተለያዩ ጋራዦች እና  ግለሰቦች በመሸጥ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር ተገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ:- https://bit.ly/3Y95f3w

#ethiopia #Deathpenality

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

21 Oct, 12:57

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለፃል- ትምህርት ሚኒስቴር

በርካታ ጥያቄ እየቀረበበት የሚገኘው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ ጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ምላሽ ሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ በኦፊሻል የፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መረጃ "በ2016 የ12ኛ ክፍል  ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለፃል " ብሏል።

ይህንን በመገንዘብ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

21 Oct, 07:57

ኦብነግ ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ራሱን አገለለ

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ድርጅት አሳታፊነትና ግልጸኝነት ስላላየሁበት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊነት እራሴን አግልያለሁ ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በሱማሌ ክልል የገዢው ፓርቲ መዋቅር ተሳታፊዎችን የሚለይበትና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽ የሚያፍንበት ህገ-ወጥ አሰራር መዘርጋቱን የሚገልጸው ፓርቲው በዚህ ሂደት ውስጥ በምክክር መሳተፍ ረብ የለሽ ነው ሲልም ገልጾታል፡፡

ይህ አግላይ አሰራር አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቋቋመበትን አላማ የሚጥስ ነው ሲልም በምክክር ኮሚሽኑ ሂደት ላይ ጥያቄ አንስቷል፡፡

ፓርቲው ከሱማሌ ክልል ውጪ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳሱ የታጠቁ ሃይሎች ባልተሳተፉበት ሁኔታ እንዴት የምክክር ሂደቱ ሊሳካ ይችላል ሲልም በጥያቄ መልስ አንስቷል፡፡

በቀጣይም ሁሉን አቀፍ የድርድር መድረክ እስካልተዘጋጀ ድረስ በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደማይችልም ጠቁሟል፡፡

ኦብነግ በ2010 ዓ.ም ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ለማድረግ ከፌዴራሉ መንግስት ጋር ስምምነት አድርጎ መግባቱ አይዘነጋም፡፡

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

19 Oct, 17:38

የጥቅምት ወር የደመወዝ ክፍያ በአዲሱ ስኬል እንደሚሆን ተገለፀ

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የጥቅምት ወር የደመወዝ ክፍያ በአዲሱ በተሻሻለው የደመወዝ ስኬል መሰረት መሆን ይጀምራል ብለዋል።

ለዚህም በቂ ዝግጅት ከመደረጉ በላይ የአፈፃፀም መመሪያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

አዲሱ የደመወዝ ስኬል በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንደሚሆን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

19 Oct, 16:32

በመቄዶኒያ አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅት የእሳት አደጋ ደረሰ

በአዲስ አበባ አያት በሚገኘው የመቄዶኒያ አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅት፣ ዛሬ ከሰዓት  በኋላ የእሳት አደጋ ማጋጠሙ ተሰምቷል፡፡

አዲስ በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘው ህንፃ ስር ተነስቶ ነበር የተባለው የእሳት አደጋ፣ ስላደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።

የእሳት አደጋው ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀ ጥረት፣ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተነግሯል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

19 Oct, 16:21

አዲስ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች

በተለያዩ የስራ መስኮች የወጡ የNGO ስራዎችን በዝርዝር ለመመልከት እና ለማመልከት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://ethionegari.com/2024/10/19/care-ethiopia-latest-ngo-job-openings/

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

19 Oct, 16:08

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር የዩናይትድ ብሬንትፎርድን አሸነፈ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ስምንት በመካሄድ ላይ ሲሆን ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ከብሬንትፎርድን አስተናግዷል።

2ለ1 በተጠናቀቀው በዚህ ጨዋታ አሊሀንድሮ በጋርናቾ እና ራስሙንድ ሆይሉንድ ጎሎችን ለማንችስተር አስቆጥረዋል።

የአርሰናል እና በርንማውዝ ጨዋታ ከቀዲቃዎች በኋላ ይካሄዳል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

#football

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

18 Oct, 15:10

በጫሞ ሀይቅ ላይ በደረሰ የጀልባ አደጋ 14 ሰዎች የገቡበት አልታወቀም

አደጋው የደረሰው ትላንት ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ነው።

ከኮሬ ዞን አቡሎ አርፋጮ ከሚባል አካባቢ ሙዝ ጭኖ ሲመለስ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሐይቅ ሰምጦ ከተሳፈሩ  16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ መገኘታቸውን የጋሞ ዞን  ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙት እና ገጽታ ግንባታ ድቪዥን  ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ፣ በጀልባው ላይ ከነበሩ 16 ሰዎች ሁለቱ በጀርካን ላይ ተንሳፈው የተረፉ ሲሆን 14ቱ ባለመገኘታቸው ፖሊስ በፍለጋ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የጀልባዋ ተሳፋሪዎች በሙሉ ሙዝ ለመጫን ከአርባምንጭ ዙሪያ አካባቢ የሄዱ ናቸው።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

18 Oct, 12:41

በኢትዮጵያ ከሞቱ ሰዎች ኩላሊት እንዲለገስ የሚፈቅድ ህግ እንዲዘጋጅ ተጠየቀ

ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ከስድስት ዓመት በፊት የተዘጋጀ ቢሆንም እስካሁን መልስ እንዳላገኘ የኩላሊት ህመምተኞች ማህበር ተናግሯል፡፡

የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ የኩላሊት ልገሳን ከቤተሰብ ውጭ እንዲለገስ የማይፈቅደው የኢትዮጵያ የጤና ህግ  እንዲሻሻል ቢጠየቅም መልስ አለማግኘቱ ችግር እንደሆነ ተነግሯል።

በቅርቡ በተወካዮች ምክር ቤት የጤና ህጎች ረቂቅ አዋጅ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ስለ ኩላሊት ልገሳ የሚያወራው ህግ ግን እስካሁን እንዳልቀረበ  በኩላሊት ተካሚዎች ማህበር በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ገልጸዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://bit.ly/3BNWVil

#ethiopia #Kidneyhealth #organtransplant

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

18 Oct, 08:21

ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚሁ መሰረት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር፣ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር፣ ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ፦ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል።