እዚህ ቤት

@gazetaw


አገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም
ኢትዮጵያዊ ሆነን—የሚያግባባ አናጣም!

ዕወቂው ዐለሜ...!

ኢትዮጵያዊ መሆን—የውርስ እንቁጣጣ
በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ!

|ታመነ መንግሥቴ ውቤ—አባ ወራው|

ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል እና ጥበብ እናወጋለን!

ጀበናዋ ተጥዳለች! ፍንጃሎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም!

ክሕሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ።

ትውልድ

እዚህ ቤት

23 Oct, 05:22


የጎጃም "ፒያሳ"አለ🤔?

ኢትዮጵያ ውስጥ በመሐል ከተማ "ፒያሳ"የሚለው ቃል የሌለባቸው የቆዩ ከተሞች የጎጃሞቹ እንደሆኑ ሁለት ጎጃሜ ሰዎች አውግተውኛል።

በእኔም ጥናት ከደብረማርቆስ እስከ ሞጣ፣ከባሕር ዳር እስከ ደንበጫ "ፒያሳ"የሚባል መጠሪያ ያለው የከተሞች ክፍል አላጋጠመኝም።

በተለዬ ይህ ለምን ሆነ?

ባሕር ዳር አንድ ሰፈር በቅርቡ"ፒያሳ"በሚል ሥም የሚጠራ የአገልግሎት መሥጫ ቦታ ያለው ሰው ተመልክቻለሁ።

በጊዜ "ተው"ይባል!

ቢቢሲ በዚህ ጽሑፉ በሮማ ከተማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መንገድ ተሰይሞላቸዋል ይለናል።አንብቡለት።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

22 Oct, 13:18


ትግራይ "መዓረይ"

የእነ ሥሑል ሚካኤል፣የእነ ሰባጋዲስ፣የእነ ደጃጅ ውቤ ኃይለማርያም፣የእነ ካሳ ምርጫ፣የእነ አሉላ አባነጋ፣የእነ ኃይለማርያም ረዳ፣የእነ ኃዬሎም አርአያ አገር ትግራይ ኩራቷ ይደላኛል።

ዳንኤል ክብረት እና እሳቸውን የመሳሰሉ ጸሐፊያን ትግሪኛ ቋንቋ እና በቁጥር ያነሰ ግን በተቀራረበ የመልክ ምድር ላይ የሚኖር ሕዝብ የፈጠረላት ብሔርተኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ተወዳዳሪ የሌለው ነው ይሉላታል።

አሁን ግን በውስጧ የተፈጠረው ጎጠኝነት፣ጥቅም ያስተሳሰረው የወታደሮች በአዛዦቻቸው ሥር መቧደን፣ከከባድ ጦርነት በኋላ የሚያጋጥም ማኅበረሰባዊ መዛል እየፈተናት ነው።

የምወዳት አገሬ—ኢትዮጵያ አስኳል ለሆነችው ትግራይ ዛሬም የተጠና የማገገሚያ መፍትሔ ያስፈልጋታል።

"መዐረይ"የሚሉ ቆነጃጅት ያሏት ሌላ የኢትዮጵያ ክፍለ-አገር ታውቃላችሁ😀?

@Gazetaw

እዚህ ቤት

22 Oct, 08:29


"አፍንጫ መጎረድ
በዘር አለብን
ከንፈራችን ማር ናት
ትቀመስልን!"


ከዚህ በፊት የማላውቃት ግሩም ሥንኝ ናት🤔

@Gazetaw

እዚህ ቤት

22 Oct, 06:05


"በዚህ ሥፍራ ድሆች ከነመብታቸው አሉ፣ በዚህ ሥፍራ ሻጮች ሳይነሱ፣ ዞር በሉ ያልተባሉ ጉሊተኞችን ማየት ይቻላል። የአገልግሎት ክፍያ አምጡ ሳይባሉ ገብተው የሚወጡ... ከልጅ እስከ አዋቂ በሰማያዊ ተስፋ የሚመላለሱትን አየሁ። እየተሰጣጡ!

#ይሁን!"

ሙሉው በዐውድማ https://t.me/litjournalism/103088 ውስጥ በመምህራችን አብርሐም ፀሐዬ ተጽፎ-አለላችሁ

እዚህ ቤት

22 Oct, 05:31


በመርካቶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ከአምስት በላይ የባንክ ቅርንጫፎች ወድመዋል!

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

ትናንት ምሽት በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በተነሳው እሳት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ከአምስት በላይ የባንክ ቅርንጫፎች ወድመዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸማ ተራ ቅርንጫፍ ተቃጥሏል ያሉን አንድ የዐይን እማኝ፣ ሌላ ከአምስት በላይ ሕንፃው ላይ የነበሩ ባንኮች ወድመዋል ብለዋል።

አጋጣሚውን ተጠቅመው ዝርፊያ ሲፈፅሙ የነበሩ አካላት መኖራቸውም ተጠቁሟል።

እሳቱ በአንዳንድ ቦታዎች እስከ ጠዋት ድረስ አልጠፋም ተብሏል።

በቦታው ሲያለቅሱ እና ሲጮኹ ከነበሩ ባለንብረቶች መካከል የታሰሩ መኖራቸውንም ሰምተናል።

ይቀላቀሉን 👉 @zejournalist

እዚህ ቤት

22 Oct, 03:58


"...በእኛ ሞያ (በጋዜጠኝነት) ደባሪ ቀናት ከአስደሳቾቹ የሚለዩት በዕለቱ በሚከሰተው የዜና እና የመረጃ ክብደት ብቻ ነው።"

የፈራ ይመለስ፣ከተመስገን ደሳለኝ፣2008 ዓ.ም፣ገጽ-53

@Gazetaw

እዚህ ቤት

21 Oct, 19:13


#መርካቶ

[በታመነ መንግሥቴ ውቤ]


በኢትዮጵያውያን የዘመን ቀመር ሺህ ዘጠኝ መቶ 65 ዓመተ ምህረት ተሸላሚው ጸጋየ ገብረ መድኅን በኢትዮጵያው የገበያዎች ውቅያኖስ መርካቶ ተገኝቶ ታዘበ።

በዝነኛ ነበልባል ብዕሩ እንዲህ ሲል ከተበ፦

"አይ መርካቶ__
በቁሳቁስ ግሣንጉሱ
ለቱጃር የጥጋብ ቅርሱ
ለኔ ብጤም የቀን ጉርሱ
አባ መስጠት እጦት ቢሱ"

"መርካቶ ማለት የሰፊው ሕዝብ እና የአገር ተወላጁ ገበያ ነው።"የሚለው ጸጋየ ገብረ መድኅን ይህንን የአፍሪካ ገበያዎች አውራ"አባ መስጠት እጦት ቢሱ"ማለቱ ሃቅ መሆኑን ለመረዳት " ምናለሽ ተራ"እንታደም።

በመርካቶ ቀየ ድብድብ፣አባሮሽ "ያዘው ልቀቀው"እንጅ ፋታ አግኝቶ መደመም አይታሰብም።

ቢሆንም "ምናለሽ ተራ"ውስጥ የሌለ የለምና ፋታ በሌለበት አፍታም መደመም ግድ ነው።የደላቸው መሃል መርካቶ መፅሔት ገልጠው ቃላት ይለቅማሉ፣የሰለቻቸው ሁሉንም ትተው ጫት ይቅማሉ።



አፈ ታሪክ ስለ ምናለሽ ተራ እንዲህ ይላል፦
"በደርግ ዘመን ስኳርና ዘይት በመንግስት እጅ ነበሩ።ከደርጉ እኒህን ሸቀጦች ያገኙ በጉያቸው ድብቅ አድርገው መርካቶ የድሮው ቡና ተራ ለሽያጭ ተገኙ።ተቀባይ ነጋዴዎቹም በሹክሹክታ"ምናለሽ?"እያሉ መጠየቅና መግዛት ጀመሩ።በቃ ይሄው"የምናለሽ ተራ ምስጢሩ!"

መርካቶ የገበያዎች ውቅያኖስ ቢሆን ምናለሽ ተራ ደግሞ የገበያዎች ባህር ነው።በስሩ እነ ቡና ተራ፣ሸክላ ተራ፣ሸማ ተራ ሃይቅ መስለው አሉ።

በቡና ተራ እናቶች ሁሌም አቀርቅረው አረንጓዴውን ወርቅ ያሰማምራሉ።ቡና በመርካቶ የሚሸጥም የሚጠጣም ሃብት ነው።

እዚህ ቀና ብሎ ሰማይ ለማየት የሚሆን ፋታ የለም።ብረት መደብደብ፣ጎጆ የሚያህል እቃ መሸከም፣መጣር መጋር ነው።እናም ቡና እንደ ጉድ ይጠጣል።

ሸክላ ተራ ብቅ ላለም የቡናን ማዕረግ የምታስከብረው ጀበና እንደ እንቁላል በጭድ ስትጀቦን ይታዘባል።

በቃ መርካቶ ውስጥ ምን አለሽ ተራ የሌለ ምን ይገኛል?

በምናለሽ መንደር የሌለ የለምና ቤት ይጠባል።ከዕድሜው መርዘም የተነሳ አፈር የመሰለው ጣሪያ ከሆዱ የተረፈውን ግሳንግስ በላዩ ላይ ይሸከማል።

አይ መርካቶእንዲል ተሸላሚው
ምናለሽ ተራ ላይ ሕይወት በስምምነት ትተማለች።የውሻ ቡችላ የኤሌክትሪክ እቃዎች ተጠግነው ዳግም ነፍስ ከሚዘሩበት ሸራ ላይ "አገር ሰላም"ብላ እንቅልፏን ትለጥጣለች፣የመርካቶ አህያ የጫኗትን ትወስዳለች ታመጣለች!

ሕይወት በዚህ ቀየ እየመረረች ትጣፍጣለች!

የምናለሽ ተራ እናቶች ተራ ነጋዴዎች አይደሉም።የሰሩትን፣የለፉ የጣሩበትን እንጅ የገዙትን አይሸጡም።

እንሰትን ከጉራጌ ምድር አምጥተው ቆጮ እና ቡላ የሚባሉ ባህላዊ ምግቦችን በአደባባይ ይሰራሉ።

እንሰቱን እንደ እንጨት ታስሮ ለሚመለከተው ረብ የለሽ ይመስላል። በስልቻ ተከቶ ጊዚያትን ይፈጅና እንደ በረዶ ይነጣል።የዱቄት ለዛ እስኪኖረው በቢላዋ ተደጋግሞ ይቆራረጣል።ከዚያ ለመጋገር ብቁ መሆኑ ይረጋገጣል።

በምናለሽ ቀየ ይህ ስራ በነበረበት የሚረግጥ አድካሚ ሂደት ነው።ታቦተ ፅዮንን ሊፈልግ የመጣው ግርሃም ሃንኮክ እንደሚለው "ኢትዮጵያ በዘመናት ኑረት የማትለወጥ "መሆኑ ያሳዝናል።የኒህ መንፈሰ ጠንካራ ልበ ተራራ እናቶች ድካምም ለውጥ አልባነታችንን ይመሰክርብናል።
እዚህ አክርማ ተነክሮ በቀለም አጊጦ ያስዋበው ቀለምሻሽ የዐይን አዋጅ ይሆናል።ቆዳ እንደ ወረቀት ሲተጣጠፍና ሲቀረጣጠፍ አጃኢብ ያሰኛል።

የመርካቶ ባተሌ ሰርክ ይዳክራል፤ብረት ቀጥቅጦ አገር ይሰራል፤ወናፍ አናፍቶ እሳት ይፈጥራል፤በእሳት አግሎ ፌሮ ይገራል።

ግን ምን ይሆናል?

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ባለበት የሚረግጥ፣የአባቱን ወናፍ ያልቀየረ መሆኑ ያሳዝናል።
ፌሮ ብረትን ሲቆለምም መጠነኛ ዘመናዊ መሳሪያ የተጠቀመ ይመስላል።ቶርኖ ስራ የሚለው ነገር ግን አድካሚነቱ ያው ብረት ቅጥቀጣውን ያክላል።

በውቅያኖሱ መርካቶ ገበያ ፣በባህሩ ምናለሽ ተራ አዳፋ የለበሱት፣ከሕይወት ጋር ነግቶ እስከሚመሽ የሚታገሉት እናቶች ይተጋሉ፣ይፈጋሉ፤ለውጥ እምብዛም የለም።

በሌላ በኩል መርካቶ ለእንግዳ ሰው ጫጫታው ጭንቅላት ቢበጠብጥም፣አባሮሹ መንፈስ ቢያናውጥም፣ለለመደው አቤት ድባቡ ሲጥም?

ድማፃዊ አብዱ ኪያር፦

"መቸም የገባሁ ቀን፤ካገር ከመንደሬ
ደስታ ነው 'ሚሰማኝ ገና ሳየው
መርካቶ ሰፈሬ"
ሲል ያዜመው የመርካቶን ከባቢ አድገውበት ለሚያጣጥሙት ነው።


መርካቶ፦

"ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ተዘነጋሽ እንዴ? ኢትዮጵያ መሆኑ!
ሸገር አዲስ አ'ባ አንች ያለሽበት
ራጉኤል አይደል ወይ? የአንዋር ጎረቤት!"

ሲል ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሞ _ቴዲ አፍሮ ያዜመላት ነጭ፣ጥቁር፣አረብ፣አበሻ፣ሕንድ፣አርመን ወይ ባላገር ገዝቶ የሚሸጥባት፤ሰው በሰው ላይ፣ቤት በቤት ላይ፣ሸቀጥ በሸቀጥ ላይ ተደራርቦ የሚኖርባት "ምናለሽ?"ሲሏት"ሁሉም"የምትል የሁሉ አደባባይ ናት።

መርካቶ ሰፊ ነው።ውቅያኖስ! ጣሪያቸው አፈር በለበሱ ቤቶች ውስጥ ድንቅ የእጅ ጥበብ፣ምትሃት የሚመስል ትጋት አለ።

ልብ ያለው ሁሉ እኒያን ለፍቶ አዳሪ ኢትዮጵያዊያን በዘመናዊ መሳሪያ ደግፎ ከጥበባቸው ቢቋደስ አገር የሚሰራ አቅም አላቸው።ሥራቸው አድካሚ፣ገቢያቸው መናኛ፣ለአገር ምጣኔ ሃብት ያላቸው ድርሻ የማይተካ ነውና ይደገፉ፣ይታገዙ እንላለን።

ዛሬ የደረሰባቸው አደጋም የዚሁ ችግራቸው ቅጥያ ነው!

እዚህ ቤት

21 Oct, 17:17


የ"አዲመራ" ነገር

ያሬድ ነጉ ትናንትና ሚለን ኃይሉ ሥልክ እንደዘጋችበት ነገረን።ኤርትራም በኢትዮጵያ ላይ ሥልክ ዘግታለች።"አዲመራ"አከተመለት።

አዲስ አበባ ከተማ ሰሚት አካባቢ 20 ሜትር የሚባል ሰፈር አለ።እዚያ አንድ ኤርትራዊ ጠጉር አስተካካይ ደንበኛ ነበሩኝ።ኢትዮጵያን ዞረው እንደሚያውቋት ነግረውኛል።የጠጉር ቤታቸው ሥም "አዲመራ" ነበር።

ጋሸ ከሰሞኑ ተሰውረውብኛል።የአዲስ አበባ እና አሥመራ ግንኙነትም ቀዝቅዟል።የያሬድ ነጉ አዲመራ ዘፈንም ሰሚ የለውም።በሚለን ኃይሉ እና በያሬድ ነጉ መካከል የቀዘቀዘው ፍቅር ከኢሳይያስ አፈወርቂ እና ዐቢይ አሕመድ ፍቅር መቀዝቀዝ ጋር እንደሚገናኝ መጠርጠርም ይበጃል።

ያኔ ያሬድ ነጉ፦
"መቼ ይደክመኛል ለመመላለሱ?
ትኬቱን ልቁረጠው ሳይሞላ አውቶብሱ"


ብሎ ዘፍኖ ነበር።

ከአዲስ አበባ ተነስቶ አሥመራ የደረሰ አውቶብስ ዐየሁ ያለ አልገጠመኝም።የሰማዩ ባቡር የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሄው የአሥመራ በረራውን ተከልክሏል።

የእኛ ነገር ያሳዝናል።ነገራችን ሁሉ"የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ"ሆኖብናል።

አሁን "ዳሕላክ ላይ ልሥራ ቤቴን" የሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን "አዲመራ"ን ተክቶታል።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

21 Oct, 10:15


እጅግአየሁ ሺባባው ከደረጀ ኃይሌ ጋር

"...የ28 ዓመት ኮረዳ ናት።ገና ለጋ...ገና ቀንበጥ...ገና እሸት'...አዎ እንዲያ ናት ጂጂ ማለት።ተወልዳ ያደገችው ጎጃም ነው።ለያውም የጎጃም ባላገር ሆና...የጎጃም ሳዱሌ ተሰኝታ።"

ደረጀ ኃይሌ(የእኔው ባለውለታ፣ደጉ፣የዋሁ ቅኑ) ከእኔዋ የጥበብ ፈርጥ እጅጋየሁ ሺባባው ጋር ያደረገው የቃል መጠይቅ በ1994 ዓ.ም ኢትጶጵ መጽሔት ላይ ሲታተም በመግቢያው ያለላት ነው።

ሌላ አምሳ ዓመት ለልዕልታችን እመኛለሁ

@Gazetaw

እዚህ ቤት

20 Oct, 18:55


በነገራችን ላይ👇

1.ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር)_ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (የሃና ባለቤት)

2. ሀና አርዓያ ሥላሴ_ፍትሕ ሚኒስትር (የጌዲዮን ባለቤት)

3. ዮዳሄ አርዓያ ሥላሴ_የብሔራዊ መታወቂያ ዲጂታል ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር (የሃና ወንድም)



"የአንድ አፈር አፈሮች" እንዲል ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፥ የአንድ ቤት … ናቸው

እዚህ ቤት

20 Oct, 18:06


የሰንበት የመጽሐፍ ግብዣ

"ቢቡኝ ከሚባለው አገር የቢቡኝ ዘሮች አገራቸውን ሥለወደዱ ከወንድሞቻቸው ተለይተው ዜጋ ሆነው በገባርነት ይኖራሉ።...ቢቡኝ የመለሎ ልጅ ነው።ከተማውም ድጓ ጽዮን ነው።የአጎቱ የሰለሎ ልጅ አረፋ በቢቡኝ ወረዳ የወንዝ/ቀበሌ ሥም ሆኖ ይገኛል።"

ጥንታዊው የጎጃም ታሪክ፣አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ፣ገጽ 249 እና 264

መጽሐፉ፦

ሀ.ደብረ ማርቆስ ደርሷል።

ሁ.ባሕርዳር (አዳነ መጽሐፍ መደብር ዘንባባ ሕንፃ ሥር) ይገኛል።

ሂ.አዲስ አበባ ላላችሁ፦

1.ጸሐፊውን በ 0913308226  አግኙት።

2.አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ ባለቤት በሆነበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳቡ 1000211733296 ላይ የመጽሐፉን ዋጋ(ስድስት መቶ የኢትዮጵያ ብር) አስገቡለት።

ወዲያውኑ መጽሐፉ እንዲደርሳችሁ ይደረጋል ብሏል።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

20 Oct, 14:34


"በላያ በላያ በላያ በላያ
ትምጣ የአገሬ ልጅ
የወንዜ ቡቃያ...!"

እዚህ ቤት

18 Oct, 17:53


ላኩለት ለዚህ ሰው🤔

"ምነው በቅዳሜ ምነው በእሁድ ቢያርሱ
ከባለ ጠጋ ቤት ከሚመላለሱ ?

ደርሶ ማንጎራጎር ልማዱ ነው ድሃ
እየቀዘቀዘው የሚጠጣው ውሃ

አርሶ መራብና ተኩሶ መሳት
የሚያንገበግበው እንደ እግር እሳት!
"

@Gazetaw

እዚህ ቤት

18 Oct, 08:51


"የጎጃም ታሪክ ማለት የኢትዮጵያ፣የዓለም ታሪክ መነሻ...ነው።"ጥንታዊው የጎጃም ታሪክ፣አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ፣ገጽ-32

መጽሐፉ፦

ሀ.ደብረ ማርቆስ ደርሷል።

ሁ.ባሕርዳር (አዳነ መጽሐፍ መደብር ዘንባባ ሕንፃ ሥር) ይገኛል።

ሂ.አዲስ አበባ ላላችሁ፦

1.ጸሐፊውን በ0713361288  አግኙት።

2.አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ ባለቤት በሆነበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳቡ 1000211733296 ላይ የመጽሐፉን ዋጋ(ስድስት መቶ የኢትዮጵያ ብር) አስገቡለት።

ወዲያውኑ መጽሐፉ እንዲደርሳችሁ ይደረጋል ብሏል።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

18 Oct, 06:58


ጥንታዊው የጎጃም ታሪክ

አዲስ መጽሐፍ ነው።ጸሐፊው አበረአረፈዐይኔ አዳሙ ይባላል።የጎጃምን ታሪክ ከአዳም እስከ በላይ ዘለቀ ዘመን ጽፎታል።

የመጀመሪያውን ክፍል መጽሐፍ ለመግዛት፦

1.ጸሐፊውን በ0713361288 ያግኙት።

2.አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ ባለቤት በሆነበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳቡ 1000211733296 ላይ የመጽሐፉን ዋጋ(ስድስት መቶ የኢትዮጵያ ብር) ያስገቡለት።

ማስታወቂያው እንደ አስፈላጊነቱ ይደጋገማል።

@Gazetaw