BikuZega - ብቁ ዜጋ

@bikuzega


ልጆች በአካል፣ በአእምሮ፣ በስነ-ልቦና እንዲሁም በማህበራዊ ህይወታችው ብቁ ና ተወዳዳሪ ትውልድን ሆነው እንዲያድጉ ማስቻል።

Follow us on:
www.facebook.com/ethiobikuzega
www.twitter.com/BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

21 Jan, 00:24


የሕፃናት እድገት ላይ ወሳኝ ከሆኑት ነገሮች አንዱ መንፈሳዊ እድገት ነው። ልጆችን መጸለይን ማስተማር በህወታቸው ውስጥ ትልቅ ሚና አለው። ከሃይማኖታዊ ትርጉሞቹ ባሻገር፣ ጸሎትን መረዳት ልጆች ለአጠቃላይ ደህንነታቸው እና ለግል እድገታቸው የሚያበረክቱ ጠቃሚ የህይወት ክህሎቶችን ይሰጣል።

ልጆችን ስለ ጸሎት ማስተማር ለምን አስፈላጊ ነው?
♦️ከ ፈጣሪ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠነክሩ
♦️ስሜታቸውን እንዲገልጹ እድልን ይከፍታል። ይህም በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ጽናትን ይሰጣቸዋል።
♦️ስለሌሎች እንዲያስቡ፣ ርህራሄን እና የማህበረሰብ ስሜትን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።
ጸሎት እንደ ደግነት፣ ታማኝነት እና ምስጋና ያሉ ዋና እሴቶችን ያጠናክራል፣ ይህም ልጆች ጠንካራ የስነምግባር መሰረት እንዲያዳብሩ ይረዳል።
♦️ልጆች እራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ እና እራሳቸውን እንዲያውቁ ይረዳቸዋል።
♦️ልጆችን በአዎንታዊ እይታ የህይወትን እርግጠኛ አለመሆን እንዲመሩ ይረዳቸዋል።

ወላጆች፣ አስተማሪዎች እና ተንከባካቢዎች፣ ልጆች ጸሎትን ከህይወታቸው ጋር እንዲያዋህዱ መምራት እንችላለን። ቀጣዩ ትውልድ በጸሎት ልምምድ ጥንካሬን፣ ዓላማን እና ግንኙነትን እንዲያገኝ እናበረታታ።

ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው (ጠቅላላ ሀኪም እና ሁለንተናዊ የህጻናት እድገት ባለሞያ)

Join 👇🏻

telegram:- https://t.me/currrrrrr99

Tik tok:- https://www.tiktok.com/@dr.tumim.getachew?_t=8mDNslc442P&_r=1

Facebook:- https://www.facebook.com/Drtumim?mibextid=LQQJ4d

BikuZega - ብቁ ዜጋ

21 Jan, 00:13


በቆስጣ ፣ በካሮትና በዶሮ ስጋ የሚዘጋጅ ለልጆች ምሳ ለት/ቤት የሚቋጠር

ግብዓቶች ለ2 ልጆች


▪️150 ግራም የዶሮ ሥጋ አጥንቱ የወጣ
▪️2 መለስተኛ ካሮት
▪️4 ቅጠል ቆስጣ
▪️½ ቀይ የፈረንጅ ቃሪያ ከተገኘ(በ 1 ቲማቲም መተካት ይቻላል)
▪️1 አነስተኛ ቀይ ሽንኩርት
▪️2 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት (እንደአስፈላጊነቱ )
▪️ሩብ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል
▪️1 የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ሮዘማሪ ቅጠል
▪️ቁንጥር ጨው
▪️ቁንጥር ቁንደ በርበሬ
▪️ሩብ የሻይ ማንኪያ እርድ
▪️2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
▪️ውሃ እንደአስፈላጊነቱ

አዘገጃጀት
▪️የዶሮ ስጋውን አጥቦና ጠፈፍ ሲል በስሱ መክተፈ
▪️አትክልቶቹን በሙሉ አጥቦ ከትፎ ማዘጋጀት
▪️ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርቱን ልጦ መክተፍ
▪️ቆስጣውን ግንዱንና ቅጠሉን ለየብቻ ከትፎ ማዘጋጀት
▪️መጥበሻ ወይም ድስት በመካከለኛ ሙቀት ለኩሶ ዘይት
▪️መጨመርና የዶሮ ስጋውን ቡናማ እስኪሆን መጥበስ

▪️ካሮቱ፣ ዝንጅብል፣ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርቱንና የተከተፈውን የቆስጣውን ግንድ አከታትሎ ጨምሮ እርዱን መጨመርና ለ 5 ደቂቃ ያክል መጥበስ

▪️እንደአስፈላጊነቱ ውሃ ጠብ ማድረግ አስከትሎም የቆስጣ ቅጠሉን፣ ቃሪያውን ( ቲማቲሙን)ና ሮዘማሪ ቅጠሉን ጨምሮ ቀጣይ 3 ደቂቃ ማብሰል

▪️በመጨረሻም በጨውና ቁንዶ በርበሬ አጣፍጦ ከምድጃው ማውጣት
▪️በአትክልትና በዶሮ የተዘጋጀውን ምግብ በተቀቀለ ሩዝ፣በመኮረኒና በፓስታ ማቅረብ ወይም ለት/ቤት መቋጠር ይቻላል።


ማሳሰቢያ ፡
- ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት እጃችንን በደንብ መታጠብ ይኖርብናል፣
- የምንሰራበት ቦታና የምንጠቀምባቸው እቃዎች ንጹህ መሆን አለባቸው።


@BikuZega #HealthyCooking

BikuZega - ብቁ ዜጋ

21 Jan, 00:01


ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ የነበረን ውይይት እንግዳችን ካቅም በላይ በሆነ ችግር ስለገጠመው ወደ ሚቀጥለው አርብ ያዘዋወርነው መሆኑን በታላቅ ይቅርታ እናስታውቃለን። እናመሰግናለን።

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:59


ልጆች እንዴት ማጥናት አለባቸው፣ በትምህርታቸውስ እንዴት ጎበዝ መሆን ይችላሉ?

ልጆቾዎ በትምህርት ውጤታማ እንዲሆኑ እና ውጤታማ የአጠናን ዘዴ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ?  ከአቶ በረከት ያኪም ጋር ተማሪዎች እንዴት ጎበዝ ተማሪ መሆን እንደሚችሉና ውጤታማ የአጠናን ዘዴ ማጥናት እንዳለባቸው የምንወያይ ይሆናል።

በዚህ ፖድካስት ላይ የጋበዝነው በትራንስፎርሜሽናል አመራር ማስተርስ ያለው አቶ በረከት ያኪም ሲሆን በዚህ ፖድካስት ላይም በሰፊው በብዙ ርዕሶች ላይ እንወያያለን እናንተንም እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

ተጋባዥ
▪️አቶ በረከት ያኪም

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ


🗓 አርብ መስከረም 24
ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast

@BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:50


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሣችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

መልካም የመስቀል በዓል!
Happy Meskel Holiday!


ጅምላዞን ትሬዲንግ

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:45


ልጆች የስክሪን ጊዜ

ልጆች  እንዳይረብሹ ስልክ፡ ታብሌት መስጠት፡ ቴሌቪዥን መክፈት እከንደመፍትሄ  የሚታየው በሁሉም ሰው ቤት ሆኗል።የስክሪን ጊዜ በልጆች በእድገታቸው ላይ ያለው ተፅዕኖ ምንድን ነው? ጥቅሙስ ምንድን ነው? በምን አይነት መልኩ እንፍቀድላቸው?

የስክሪን ጊዜ ምን ማለት ነው?

የስከክሪን ጊዜ ማለት ህፃናት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ማለትም እንደ ቴሌቪዥን ስልክ ታብሌት ኮምፒውተር ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ ማለት ነዉ ።

ለምን ያህል ሰአት ይጠቀሙ?

- ከ 2አመት በታች ለስክሪን መጋለጥ የለባቸውም!
- ከ2-5 አመት ከ1 ሰአት ያልበለጠ በወላጅ የተመረጠ !
- ከ6-17አመት  ከ2 ሰአት ያልበለጠ በወላጅ የተመረጠ!

የስክሪን ጊዜ ሲጨምር ጉዳቱ ምንድን ነዉ ?

- የቋንቋና የንግግር ብቃታቸው ይቀንሳል
- የትምህርት አቀባበል ብቃታቸው ይቀንሳል
- ጨረሩ የአይን ጉዳት ሊያመጣ ይችላል
- የእንቅልፍ ሰአት መዛባት
- ስሜትና እራስን መቆጣጠር አለመቻል
- ወጣ ያለ ባህሪ ማሣየት
- የአመጋገብ ስርአት መስተጓጐል
- የሰውነት እድገትና ክብደት ላይ ተፅእኖ ይፈተጠራል
- አእምሮአቸው ላልዳበረበትና መረዳት ለማይችሉት የተለያዩ ነገሮች ይጋለጣሉ።

በቂ የስክሪን ጊዜ ጥቅም ምንድን ነው?

- ለትምህርታቸው እንደ አጋርነት ያገለግላል።
- ለወደፊቱ በ ቴክኖሎጂ ላይ ፍላጎት ላላቸው ልጆች ብዙ እውቀት ያስጨብጣል።
- በአንዳንድ "Game" ጫዋታዎች የተለያዩ ችሎታዎችን እንዲያዳብሩ ይረዳል።

እንዴት እንቆጣጠራቸው?

1)
  ወላጆች ለ Digital and Electronic ያላቸውን እውቀት ማሳደግ አለባቸው። ከልጆቻቸው በተሻለ ወይም ቢያንስ የነሱን ያህል ሊያውቁ ይገባል።

2)  ወላጆችረ ለልጆች ጥሩ ምሳሌ ሊሆቸው ይገባል።

3)  እንዴትና ምን ማየት እንዳለባቸው አስቀድመው አይተው ሊወስኑላቸው ይገባል።

4)  የአጠቃቀም ህጎችን ለልጆች ማውጣት አለባቸው

5)  ጥቅሙንም ጉዳቱንም በደንብ በግልፅ መነጋገር አለባቸው::

6) ሌላ ጫዎታዎችን የሚጫወቱበት መንገድ ማዘጋጀት ለምሳሌ በቤት ውስጥ የስእል፡ የሙዚቃ ፡ የተለያዩ  ክሂሎት ሊያዳብሩ የሚችሉበትን መጫወቻዎች በማዘጋጀት : የሰውነት እንቅስቃሴዎችን በማሰራት የስክሪን ጊዜን መቀነስ ይቻላል።

ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው ( ጠቅላላ ሀኪምና ሁለንተናዊ የህፃናት እድገት ባለሞያ)

[ ይኽ መልዕክት @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ዘወትር #ሐሙስ ለወላጆች የሚያቀርብ ትምህርት ነው። ]

t.me/tikvahethmagazine

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:20


Live stream finished (2 hours)

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:20


ልጆቻችንን የፆታ ጥቃት እንዴት እንከላከል በሚል የምናደርገውን ውይይት ይቀላቀሉን።

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:20


Live stream started

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:20


ኑ እንወያይ!
—————————————————
ልጆቻችንን ከፆታ ጥቃት እንዴት እንከላከል?

በዚህ ሳምንት በብቁ ዜጋ ፖድካስት እንዴት ልጆቻችንን ከፆታ ጥቃት መከላከል እንችላለን የሚለውን ከ እናንተ ከ ቤተሰቦቻችን ጋር እንወያያለን ሃሳብም እናንሸራሽራለን።

በዚህ ፖድካስትም ብፅት ኤልያስ እና ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው እብረውን ይኖራሉ። እናንተንም በዚህ ውይይት ላይ እንድሳተፉ እና እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ እና ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው


🗓 አርብ ጷግሜ 1
ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast
@bikuzega

Tik tok:- https://www.tiktok.com/@dr.tumim.getachew?_t=8mDNslc442P&_r=1

telegram:- https://t.me/currrrrrr99

Facebook:- https://www.facebook.com/Drtumim?mibextid=LQQJ4d

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:19


ኑ እንወያይ!
—————————————————
ልጆቻችንን ከፆታ ጥቃት እንዴት እንከላከል?

በዚህ ሳምንት በብቁ ዜጋ ፖድካስት እንዴት ልጆቻችንን ከፆታ ጥቃት መከላከል እንችላለን የሚለውን ከ እናንተ ከ ቤተሰቦቻችን ጋር እንወያያለን ሃሳብም እናንሸራሽራለን።

በዚህ ፖድካስትም ብፅት ኤልያስ እና ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው እብረውን ይኖራሉ። እናንተንም በዚህ ውይይት ላይ እንድሳተፉ እና እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

አዘጋጅ እና አቅራቢ
▪️ብፅት ኤልያስ እና ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው


🗓 አርብ ጷግሜ 1
ማታ ከ3:00 - ከ4:30

#BikuZegaPodcast

@BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:17


🌻🌻አዲሱ ዓመት
80 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለ80 ሰው ግን ጌጥ ነው😀

በዓሉን ወላጆች አብረዋቸው ለማያሳልፉ ልጆች ዛሬ .... አሁን ምላሽ እንስጥ......
😀 ስንት ቲሸርት ይችላሉ?
😆 ዳቦ መድፋት እችላለው?
😃 የአንድ/የሶስት ዳቦ ዋጋ እችላለሁ?
ሌሎችንም መምረጥ ይቻላል😇😇

በህፃናቱ ስም እናመሰግናለን!!🙏👐🙏

ምን ይችላሉ

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:14


ሩዝ በሙዝና በአቮካዶ የሚዘጋጅ ምግብ (ከ6-8 ወር ላሉ ህፃናት)

ግብዓቶች

▪️1 ኩባያ ሩዝ
▪️1/2 አቮካዶ
▪️1/2 ሙዝ
▪️1 ኩባያ የጡት ወተት ወይም የህፃናት ወተት
 
አዘገጃጀት

▪️በመጀመሪያ ሩዙን በደንብ ማጠብና መቀቀል
▪️በመቀጠል ሙዙንና አቮካዶውን በደንብ አጥቦ በትንንሹ መቆረረጥ ፣ በመጨረሻም ተቀቅሎ የቀዘቀዘውን ሩዝ ሙዝና አቮካዶ አንድ ላይ መፍጫ ውስጥ በመጨመር በወተት በደንብ መፍጨትና ማቅረብ።

▪️መፍጫ ከሌለን በማንኪያ ወይም በሹካ በደንብ መፍጨት ይቻላል።

ማሳሰቢያ ፡
- ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት እጃችንን በደንብ መታጠብ ይኖርብናል፣
- የምንሰራበት ቦታና የምንጠቀምባቸው እቃዎች ንጹህ መሆን አለባቸው።


@BikuZega #HealthyCooking

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 23:00


ትንታ

ከ 1 አመት በታች ያለ ልጅ ትንታ ቢያጋጥም ምን ያደርጋሉ?

ትንታ የሚፈጠረው ባእድ ነገር በአየር ቱቦ ውስጥ ገብቶ በሙሉ ወይም በከፊል የአየር ቱቦውን በሚዘጋበት ወቅት ለመተንፈስ የምናደረግው ጥረት ነው፡፡

ትንታ ሲፈጠር ኦክስጅን ወደ ሰውነት በደንብ ስለማይደርስ በህይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያመጣ ይችላል። ትን ያለው ሰው ያለማቋረጥ በማሳል በአየር ቱቦ ውስጥ የገባውን ባእድ ነገር ሊያስወጣው ይችላል፡፡

የትንታ ምልክቶች
▪️የማያቋርጥ ሳል
▪️ትንፋሽ ማጠር
▪️መናገር አለመቻል /መፍጨርጨር
▪️የከንፈርና የእጅ ጣቶች እንዲሁም የሰውነት መጥቆር (ይህም ሰውነት ውስጥ ከፍተኛ የኦከስጂን እጥረት መኖሩን ይጠቁማል)

👉🏼ከ1 አመት በታች

ከላይ በምስሉ ላይ እንደሚታየው☝️
 
▪️ህጻኑን ፊቱን ወደ ታች ዘቅዝቆ እጅ ላይ በማስተኛት አገጭንና ጭንቅላትን በመደገፍ በአንድ እጅ በውስጥ መዳፋችን ጀርባውን 5 ጊዜ መምታት
▪️ህጻኑን ፊቱን ወደ ላይ በመገልበጥ በሁለት ጣት መሀል ደረት ላይ 5 ጊዜ መግፋት
▪️ይህን ባእድ ነገር እስኪወጣ እየቀጠሉ ወደ ህክምና መውሰድ፡፡

አዘጋጅ - ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው
@currrrrrr99

@bikuZega  #BikuZega

BikuZega - ብቁ ዜጋ

20 Jan, 22:50


Live stream finished (1 hour)