ሰዉዬዉ ይህን ሲመለከት በጣም ደነገጠ 'እንዴ ሞቻለሁ አንዴ?' የሚል ነበር ምላሹ። የዚህን ሰዉ ሞት ለመግለፅ በጋዜጣው ላይ 'የተቀጣጣይ ፈንጁ ንጉስ ሞተ (dynamite king dies) እንዲሁም 'የሞት ነጋዴዉ ሞተ (merchant of death dies) የሚሉ ርዕሶች ተሰጥተዉታል።
ይህ ሰዉ ግዙፍ ግድቦችንና ህንፃወችን ለማዉደም የሚያሰችል ተቀጣጣይ ፈንጂን (dynamite) የፈለሰፈ እንዲሁም ጦር መሳሪያዎችን በመሸጥ ኪሱን በረብጣ ዶላሮች መሙላት የቻለ ታዋቂ ባለሀብት ነዉ። ጋዜጣዉ ላይ ስለ እሱ ሞት ሲዘገብ 'የሞት ነጋዴ' ተብሎ የተገለፀበትን ቃል ሲያነብ ዉስጡ ላይ 'እንደዚህ ነዉ የምታወሰዉ ማለት ነዉ?' የሚል ጥያቄ ፈጠረበት።
ከእራሱ ጋር ከተሟገተ በኋላ ከዚህ በኋላ በእዚህ አይነት መልኩ መታወስ አልፈልግም በማለት ስለ ሰላም መስራት ጀመረ። ይህ ሰዉ አልፍሬድ ኖቤል ይባላል። ዛሬ ይህን ሰዉ እጅግ በተከረዉና ስለ ሰላም ለተጉ ሰዎች በሚሸለመዉ የኖቤል ሽልማት አለም ያታወሳል።
እኛስ አንዴት መታወስ እንፈልጋለን በሰዉ ወዳድነት፣ በአክባሪነት ወይስ በጥላቻና በዘረኝነት?
በሰዎች ልብ ዉስጥ የምንናፈቅ ነን? ወይስ... ?
(ከማሕበራዊ ሚዲያ የተገኘ)
👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ
#ZumraTube
ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube