Zemedikun Bekele(zemede) @zemedikunbekele Channel on Telegram

Zemedikun Bekele(zemede)

@zemedikunbekele


Zemedikun Bekele(zemede) (English)

Are you looking for a channel that provides insightful information and engaging content in the field of medicine? Look no further than Zemedikun Bekele(zemede)! This Telegram channel, run by the knowledgeable Zemedikun Bekele, is a must-follow for anyone interested in staying up-to-date with the latest developments in the medical world. From health tips to medical breakthroughs, Zemedikun Bekele covers a wide range of topics to keep you informed and engaged. Who is Zemedikun Bekele? He is a seasoned medical professional with years of experience in the field, making him a trusted source of information. What is Zemedikun Bekele? It is a channel where you can find valuable insights, recommendations, and updates related to health and medicine. Whether you are a medical professional, a student, or simply someone who cares about their well-being, Zemedikun Bekele has something for everyone. Join the channel today and start your journey towards a healthier and more informed life!

Zemedikun Bekele(zemede)

24 Sep, 10:58


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 19 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.

Zemedikun Bekele(zemede)

01 Dec, 21:11


ወዳጄ ቀን አይጣልህ !!… ዘጭ እኮ ነው በአንደዜ !!

እጇን ሰጠች አላለም ...

የህወሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊነት ነበራት።

… የጁንታው ጥቅም ይሻለኛል ብላ ወደ መቀሌ የሸሸች ሲሆን ... የተቀራችሁትም እንደ ኬሪያ አዳሜና ሔዋኔ እጅሽን ስጪ ተብለሻል።

… ሴትየዋ የወልቃይት፣ የጠለምት፣ የጠገዴና የራያን ጉዳይ እስከ ዛሬ ቀብራ የኖረችው ሴትዮ ነፍጠኞቹ በነፍጥ ካስመለሱ በኋላ በስተመጨረሻ ኬሪ እጇን ሰጥታለች።

... አሁን እጃቸውን የሚሰጡት ስንት ቀሩ?

ከአንቱታ በአንድ ጊዜ ወደ እጇን ሰጠች ዘጭ።

… በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል... ሉቃስ 1፣ 5–6


https://www.facebook.com/EBCzena/videos/433899024443288/

Zemedikun Bekele(zemede)

23 Nov, 19:41


🤔 በጣም ይገርማል ትህነግ በውሸት ተፈጥሮ፣ በውሸት ኖሮ፣ እስከነ ውሸቱ ሊቀበር ነው። አይናቸውን በጨው አጥበው "በራያ ግንባር 21ኛው ክፍለጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፥ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ጥለናል፥ ሁለት ታንኮችንም አቃጥለናል" ሲሉ መግለጫ ሰጡ።

የሚገርመው አንዳችም በቪዲዮ የታገዘ መረጃ አለማቅረባቸው ነው።

ከትናንት ጀምሮ በራያ ምሥራቃዊ ግምባር ጀግናው የመከላከያ ኃይል የትህነግን ታንኮች ዶግ አመድ እንዳደረጋቸው፣ ምሽግ ስትቆፍርበት የነበረውን ግሬደር እና
ከሰሜን ዕዝ የዘረፈችውን ታንኮች ጥላ እንደፈረጠጠች በምስል የተደገፈ ዜና አይተናል።

ነገርግን ትህነግ ይሄንን ዜና ገልብጣ ደምስሻለሁ፣ ታንኮችንም አቃጥያለሁ አለችን። ለንስሐ ሳይበቁ እንደዋሹ መሞት ይሉሻል ይሄው ነው።

Zemedikun Bekele(zemede)

23 Nov, 07:30


እርግጠኞች ናችሁ
ሮኬቱ ከትግራይ ነው የሚተኮሰው?

• ያሉትን ብቀበል ባምንም እኔ ግን ጥርጣሬ ቢጤ ገብቶኛል !! ምክንያቴንም እንዳስረዳ ኢፈቀድልኝ። አመሰግናሻሎ።

... በሁሉም አቅጣጫ የህወሓትን ጦር ደምስሰን መቀሌን ዙሪያዋን ከበን ጠላትን ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ቆመናል። “ጁንታ“ ብለው የዳቦ ስም ያወጡለትንም የወንበዴ ቡድን የተደበቀበትንም ሥፍራ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ አውቀነዋል። ጁንታውን ከመደምሰሳችን በፊት ግን የመጨረሻ 72 ሰዓታት የእጅ መስጫ ዕድልንም ሰጥተነዋል። ( ከልክ በላይ ነው ግን ያዘኑለት ለጡት አባታቸው ለጁንታው)

… ዕርግጥ ነው የሰሜን ዕዝን ሮኬቶች እና፣ ሚሳኤሎቹን ዘርፈውናል። ሆኖም ግን መሣሪያዎቹን የምንቆጣጠረው ከማዕከል ሆነን ነው። መሣሪያዎቹ ከአዲስ አበባ ስለተቆለፉ ከትግራይ ምድር ወደ የትም ሊተኮሱ አይችሉም። ብሎ ወነጉ መርዳሳ የሚሉት የአየር ኃይሉ ሶዬ ከነገሩን በኋላ ጎንደርና ጎጃም በሮኬቶቹ ሲደበደቡ ወዲያው ወጥተው አሮጌ ሮኬቶች ጠጋግነው ነው እንጂ የተኮሱት አሉን። ወዲያውም እሱም ቦታው ታውቆ ተደምስሷልም አሉን። አልቆየም ወያኔዎቹ መርዳሳ መግለጫ ሰጥቶ ሳይጨርስ ወዲያው ለባህርዳር አስበው የተኮሱት ሮኬት የገበሬ ማሳ ላይ አርፎ በቆሎ ሲጠብስ አመሸ።

... እነሆ ዛሬም ተከበበ፣ ተደመሰሰ፣ ጠፋ፣ ከበባ ውስጥ ወድቆ መቀሌ ነው የቀረው የተባለው ህወሓት ከማይፀብሪ አለመውጣቱ፣ ጠለምትም ላይ እየተዋጋ መሆኑን እየሰማን ነው። ሊሞት እያጣጣረ ነው እየተባለ እንኳ ሟቹ ወንበዴ ለባህርዳር አውዳሚ ሮኬት መላኩን አላቆመም። ጅብን ጭካኔውን አውቆ እግሩን አሳጥሮ፣ ልብም ነስቶ ፈሪ አድርጎ እንደፈጠረው ሁሉ ህወሓት አቅም ያአጣች ፈሪ፣ ደግሞም ገንዘብ እንጂ ተዕውቀት ነጣም ሆና እንጂ፣ ደግሞም ኒዩክለርም ቢሆን አጣች እንጂ፣ በመርፌ፣ በኪኒና ፣ በኤድስና በወባ፣ ብላ ብላ አላልቅ ያላትን ህዝብ ቢቻላት፣ አቅምም ቢኖራት ሙሉ ዐማራን ዶግ አመድ አድርጋ ብትጠፋ ደስታዋ ነበር። የራሷን የአክሱምን አውሮጵላን ማረፊያ በግሬደር ያረሰች፣ ተርሚናሉንም በእሳት ያጋየች፣ ለባህርዳርና ለጎንደር የሚራራ አንጀትም የላትም። ደንታዋ ነው እንዴ ሂዊ?

… በዚህ ወገን ግን ለመቀሌ የታዘነውን ያህል፣ ለዚህ አጥፊ ቡድን የተሰጠውን በነፃነት የመኖር ዕድል ያህል፣ የትግሬ ህዝብ እንዳይሰቃይ የታዘነውን ያህል፣ ሳይራብ ወደፊት ሊርበው ይችል ይሆናልና በሚል የሚታሰብለትን ያህል፣ ለመቀሌ ለከተማዋ የታዘነውን ያህል፣ በቁሙ ኢትዮጵያ ምድራዊ ሲኦል እንድትመስለው የተፈረደበትን ያህል፣ ለዐማራው ህዝብ፣ ለዐማራ ከተሞች ለጎንደርና ለባሕርዳር ያለመታዘኑ ይገርመኛል።

... ወዳጄ አጥፍቶ ጠፊን በጊዜ ካላስወገድከው ይዞህ ነው የሚጠፋው። እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ብለው በድፍረት በአደባባይ ሰልፍ የወጡት የትግሬ ልጆች ሃገራቸው ያልሆነች ኢትዮጵያን አውድመው ለመውደም ለሰከንድ እንደማያመነቱም መታወቅ አለበት። አንድ እንኳ ተቆጪ ሽማግሌ በመሃላቸው ያለመኖሩም ይገርማል። ይደንቃልም።

… ፀረ ህዝብ ነው፣ ፋሽስት ነው፣ ጨፍጫፊ ነው፣ ይሉ ይከሱት የነበረው ደርግ እንኳ ገጠሩን ለቅቆ ከተማ ገብቶ እየተዋጋ ከተሞችን እንዲወድሙ ማድረግ ይችል ነበር። አስመራንም ለሸአቢያ፣ መቀሌንም፣ ጎንደር ደሴ ባህርዳርንንና አዲስ አበባንም ጥይት እንዳይተኮስባቸው፣ የሰው ነፍስም እንዳይቀጠፍባቸው፣ ንብረትም፣ ሃብትም እንዳይወድም ተጠንቅቆ ነው መሸነፉን አምኖ በጊዜ እጁን የሰጣቸው። ምክንያቱ ደግሞ ባንዳ የባንዳ ዘርና ልጅ ስላልሆነ። ኢትዮጵያን ብሎ ለኢትዮጵያ የሞተ ስለነበረ። ለዚያ ነው እንዲያ ያደረገው።

... እነዚህ ግን አውሬ ናቸው። የቆሰሉ ጅቦች። በቃኝ የማያውቁ ጅቦች። ለህዝባቸው የማይራሩ አረመኔ ጅቦች። እነዚህ ባንዳ የባንዳ ልጆች ናቸው። ከትግሬ ማኅጸን ያልተወለዱ አረመኔዎች፣ የሠሩትን ድልድይ የሚያፈርሱ፣ የገነቡትን ህንጻ የሚያወድሙ የቀንም የማታም ጅቦች። ለእነዚህ አውሬዎች አይደለም 72 ሰዓታት፣ 7 ሰኮንድ እንኳ መታገስ ከባድ ወንጀል ነው፣ ንስሐ የሌለውም ኃጢአትም ግፍም ነው።

… እንደ እኔ እንደ እኔ አሁን የዐማራ ክልል በተቻለው መጠን ከተከዜ ሐይቅ በታች ያሉ ነዋሪዎችን ለጊዜው እንዲጠነቀቁ ቢያደርግ መልካም ነው። ከተቻለ ወደ ከፍታ ቦታዎች ቢያሸሽ። ባህርዳርና ጎንደር የሚልኩትን ሚሳኤል እዚያው ተከዜ ላይ ጥለው በጦርነት አላልቅ ያላቸውን በውኃ ሙላት እንዳይፈጁት ነው ስጋቴ። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል ባይ አህያ ከዚህ በላይ ማሰብ አይችልም። እናም ምጥንቃቅ። ሦስቴ ተኩሰው ታርጌቱን ያልመታላቸው ዐቢይ አሕመድ አስተካክላችሁ ተኩሳችሁ አውድሙ እንጂ ብሎ ቀን የሰጣቸው ነው የሚመስለኝ። 4ተኛው ሮኬት ምን ላይ ያርፍ ይሆን?

• አሁን ጄነራል መርዳሳ እስቲ ደግሞ ብቅ ይበሉና በመጠኑ ይበጥረቁብን። ደምሲሰናል። ኬት እንደሚተተኩስ እንጃአባቷ ይበሉና በሳቅ ፍርፍር ያብሉን። ኦሮሙማ ጦርነቱ በአጭር እንዲቋጭ የሚፈልግ አይመስልም። ሰሞኑን 5ሺ የኦሮሚያ ወታደር በወልድያ በኩል ወደ መቀሌ ሄዷል። ዛሬ ደግሞ ፈረንጅ ወታደሮች በወልድያ ወደ ራያ ሲሄዱ ታይታዋል። ዐማራ ሞቶ ነፃ ያወጣውን ምድር በጸሎት ላይ የቆየው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እየሰፈረበት ነው? ወይስ ወደ መቀሌ ሄዶ በዚያ ሊሰፍር ነው?

… ኢትዮጵያ ግን እግዚአብሔር ይሁንሽ !!

Zemedikun Bekele(zemede)

23 Nov, 05:55


የደረሰ ጉዳት የለም‼️ ሮኬቶቹ የወደቁት ባህርዳር በላይ ዘለቀ አየር ማረፊያ በዳር በኩል ነው። ጉዳት አልደረሰም።
መጠነኛ ቃጠሎ ነበር አሁን እሳቱ ጠፍቷል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና አምቡላንሶች እየተመለሱ ናቸው።

ሮኬቱ የተተኮሰው ጸለምት አካባቢ ነው። በአካባቢው ያሉ ሰዎች እሳቱን በአይናቸው አይተውታል። ድምጹን ሰምተውታል።

Zemedikun Bekele(zemede)

22 Nov, 19:12


"ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ነች፣የማንም የሰፈር ወንበዴ እንዲያፈርሳት አንፈቅድለትም። የወያኔ ውሸት የሚያቆመው ስንቀብረው ብቻ ነው ፤ እሱን ደግሞ በቅርብ እናደርገዋለን"

ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ከአድዋ ተራሮች

Zemedikun Bekele(zemede)

21 Nov, 19:47


#ስለአማሮች_አሌክሳንደር_ቡላቶቪች_እንደጻፈው!

አሌክሳንደር ቡላቶቪች ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ሩሲያ በአድዋ ጦርነት ለቆሰሉ ወታደሮችና ሌሎች ዘማቾች የሕክምና ዕርዳታ የሚሰጥ የቀይ መስቀል ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በላከች ጊዜ ነበረ። "ከእንጦጦ እስከ ባሮ" የተባለው መጽሓፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኅትመት የበቃው በ1897 ሲሆን እሱም ከፍተኛ አድናቆት አትርፏል። መጽሓፍም ለሩሲያው ንጉሠ ነገሥት ለዳግማዊ ኒኮላይና ለሌሎች ትላልቅ ባለሥልጣናት ሁሉ እንዲዳረስ ተደርጓል።

ቡላቶቪች ስለ አማራ ሕዝብ አኗኗር፣ አለባበስ፣ ጠባይ ወዘተ በዝርዝር ጽፏል። መጽሐፉን በዶክተር አምባቸው ከበደ በ2005 ተርጉሞ ለንባብ አብቅቶታል። በዚህ መጽሐፍ ገጽ 137-138 እንዲህ ይላል፤

"አማራን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመጠኑ ለማወዳደር ብንፈልግ" ይላል ሩሲያዊ ተጓዥ አሌክሳንደር ቡላቶቪች

'አማራን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመጠኑ ለማወዳደር ብንፈልግ ይህ ሕዝብ የሚገለጸው በሚከተለው መሠረት ነው። እሱም እንደ ፈረንሳይ ልዩ ስጦታ ያለውና አስተዋይ፣ እንደ እንግሊዝ እርምጃ የመውሰድ፤ በሥሩ የሚገኙ ሕዝቦችን የማስተዳደርና የመሪነት ችሎታ ያለው። እንደ ስፔይናዊ ኩሩ፤ እንደ ሩስያዊ ሃይማኖቱን የሚወድ፤ ጠባየ ለስላሳና ታጋሽ፤ እንደ ይሁዳዊ የመነገድ ችሎታ ያለውና በጣም ደፍር ነው" በማለት በመጽሃፉ ላይ አስፍሮት ይገኛል፡፡

እንደገና በገፅ 212 እስከ 213 ላይ እንዲህ ይላል፤

" የአማሮች ጦር የውጊያ መንፈስ በጣም ከፍተኛ ሲሆን እያንዳንዱ ወታደርም የጦርነትን ዓላማ ጠላትን መግደል እንደሆነ ያውቃል። እነሱም በዚህ አንጻር ምንም ማወላወልና ሐሳባቸውን መሸፋፈን አይፈልጉም። የአማራ ወታደር ጦርነት ማለት ሰውን መግደል ማለት መሆኑን ቢያውቅም ወደ ጦርነት ግን የሚሄደው በደስታ ነው። ከዚህም ሌላ ለአማራ ጦርነት ጥሩ ጊዜ የሚያሳልፍበት፣ ገቢ የሚያገኝበት፣ ክብር የሚቀዳጅበት፣ ጀግንነቱን የሚያስመሰክርበትና ሽልማት የሚያገኝበት አጋጣሚ ነው።

"እያንዳንዱ ወታደር ስንት ጠላት እንደገደለ ይቆጠራል። ጀግንነት የፈጸመ ወታደር ወደ ቤቱ ሲመለስ ሕዝቡ እየዘፈነና እየጨፈረ የሚቀበለው ሲሆን እሱም በአለቃው ፊት እየፎከረ የፈጸመውን ጀብዱ ይዘረዝራል።

"በአማሮችና በአውሮፓ ሠራዊቶች መካከል ያለው የሥነልቦና ልዩነት የሚገለጸው አማሮች ጦርነት በአብዛኛው የጥቃት እርምጃ የሚወሰድበት ነው ብለው ስለሚያስቡ ነው። የአማራ ወታደር ወደ ጦርነት የሚሄደው ለመግደል ሲሆን አብዛኛው የአውሮፓ ወታደር ግን ወደ ጦርነት ሲሄድ በልቡ የሚያስው ራሱን መስዕዋት ለማድረግ እንጂ ሌላውን ለመግደል አይደለም።

"አማሮች ውጊያ በጣም ስለሚወዱ የሚዋጉት በደስታ ነው። እነሱም ግልፍተኛ ቢሆኑም ደፋር፣ አስተዋይና የአካባቢን ሁኔታና አጋጣሚን መጠቀም የሚችሉ ናቸው። ዝቅተኛ አለቆችና አብዛኞቹ ወታደሮች ሳይቀሩ የውጊያውን ሁኔታ የመረዳት ችሎታ አላቸው። ከዚህም ሌላ የአማራ ሠራዊት ችግር የመቋቋም ችሎታ ያለው፣ በትንሽ ምግብ የሚኖር፣ ለቁር፣ ለሐሩር በቀላሉ የማይበገርና ረጅም ጉዞ መጓዝ የሚችል ነው" #ሼር

Zemedikun Bekele(zemede)

21 Nov, 17:22


~ ዩቲዩቤን ለማስመለስ
ቢያንስ 5 ሺ ፊርማ እፈልጋለሁ።

… ስሙኝማ ቆዩኝ አንደዜ አድምጡኝ… የጀመርኩትን እመለስበታለሁ። ተያ በፊት ግን አንድ ዜና ጀባ ልበላችሁማ። ይኸውላችሁ የእኔ ፌስቡክና የዩቲዩብ ቻናሌን በደቦ ማዘጋታቸውን ታስታውሳላችሁ አይደል? አዎ መች ይረሳል? ተያ በኋላ ደግሞ ወደ መረጃ ቴቪም ስመጣ ገና ከመግባቴ ወገብ ዛላዬን ቆርጠው አሰናብተውኛል። የእኔ ጦስ ለመረጃ ቴቪም ተረፈው።

… አሁን ግን የመረጃ ቴቪ ይሄን ነገር በዋዛ አልለቀውም። ፌስቡኬን በተመለከተ መልካም ውይይት ተጀምሮ ወደ ፍጻሜው እየቀረበ ነው። ልክ እንደ ልደቱ አያሌው ከፈታነው ምላሱን አንችልም ብለው እንጂ ያጠፋሁት ጥፋት እንደሌለ አውቀዋል። ተረድተዋልም። እናም የማርያም መንገድም ሰጥተውኛል።

… አሁን ደግሞ ሌላ የምሥራች መጥቷል። መረጃ ቲቪ እና በአሜሪካ የሚኖሩ ጓደኞቼ ዩቱዩባችንን በተመለከተ ራሱ የዩቲዩብ ካምፓኒን ለመክሰስ ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ መንገድ ጀምረዋል። ከዚያ በፊት ግን ጠበቆቻችን አንድ ሃሳብ አምጥተዋል። እኔ ዘመዴም ሆንኩ የመረጃ ቴቭ ምን ያህል የህዝብ ድጋፍ እንዳለን ማወቅ አስፈልጓቸዋል። ቢያንስ 5,000 ሰው የፈረመበት ፊርማም ይፈልጋሉ። እናም ለዚህ ሲባል የመረጀ ተቪ ባዘጋጀው የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅጽ ላይ በመፈረም ጎዶኝነታችንን ያስመስክሩ። ተናግርቻለሁ።

… http://chng.it/KHmGxxWf በዚህ
የፊርማ ወረቀት ላይ ስምዎትንና ኢሜይሎትን ብቻ ነው የሚያሰፍሩት። ኔክስት ብሎ በሚመጣው ገጽ ላይ ያለው ዝብዘባ አይመለከትዎትም። ዝለሉት።

… ፍርድ ቤት ከቀረብን በኋላ በአሜሪካ ሕግ መሠረት እንነጋገራለን። እጅ መስጠትንማ መሸነፍን እኔም ከአባቶቼ አልተማርኩም። ለልጆቼም አላስተምርም። ድብቆቹን ከሳሾቼን በአሜሪካ ፍርድ ቤት እስካያቸው ጓጉቻለሁ።

ዳይ 5 ሺ ፊርማ አሁኑኑ … እኔ የጠየቅኩት ጎዶኞቼን ነው። አንተን ካልተመለከተህ ንካው። ካላገባህ ቀይ አብርተህ ታጠፍ። እኚኚ አትበልብኝ። የአንተን ፊርማ አልፈልግም።

ሰምተሃል !!

Zemedikun Bekele(zemede)

20 Nov, 19:28


'94,586 ሰዎች ተፈናቅለዋል'

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በታጣቂዎች የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ 94,586 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

የኮንሶ ዞን ባለስልጣናት ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ እንደገለፁት ነዋሪዎች የተፈናቀሉት ኮልሜ ክልስተር፣ ካራትና በሰገን ዙሪያ ወረዳዎች ከሚገኙ መንደሮች ነው።

ከኮልሜ ክላስተር ቦርቆራ ቀበሌ የተፈናቀሉ አንድ አርሶ አደር ፥ ስለሆኔታው ምንም እንደማያውቁ ተናግረዋል። አርሶ አደሩ ፥ "ንብረታቸው ወድሟል፣ ቤታችን ተቃጥሏል፣ ንብረታቸው ተዘርፏል፣ ብዙ ሰውም ሞቷል፣ ቆስሏል በአጠቃላይ በስቃይ ውስጥ ነን ሲሉ" ገልፀዋል።

የኮንሶ ዞን ባለስልጣናት አሁንም የታጠቁ አካላት በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ትላንትም በሰው እና በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

ለተፈናቀሉ ዜጎች 'የሰብዓዊ እርዳታ' እንዲያገኙ ዞኑ ለደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የድጋፍ ጥያቄ ማቅረቡን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ገልጿል።

Zemedikun bekele (zemede)

Zemedikun Bekele(zemede)

20 Nov, 19:20


ሰበር ዜና‼️ መከላከያ ሠራዊት አኩስምን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አኩስምን፣ አድዋ እና የአዲግራት ዙሪያ ተቆጣጥሮ ወደ አዲግራት ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል።

Zemedikun Bekele(zemede)

19 Nov, 12:21


🤔 ናትናኤል መኮንን የሚባል ሰው ምናለ ብትመክሩት። ከመሬት ተነስቶ እየተቀደደ ሰዎችን ባያሳስት ምናለበት።

በነገራችሁ ላይ በትግራይ #በውቅሮ ስም የሚጠሩ ሁለት ቦታዎች አሉ።

1. ከሽሬ አልፎ በሰለኽለኻ እና በአኩስም መካከል የምትገኘው #ውቅሮማራይ የምትባል ከተማ አለች። ዛሬ መከላከያ የተቆጣጠራት እቺን ውቅሮ ከተማ ነው። በአሁኑ ሰዓት አኩስም ላይ ውጊያው እንደቀጠለ ነው።

2. ከመቐለ ሰሜን መስመር ዛላምበሳና በአዲግራት መስመር ያለችው ውቅሮ ናት። ናትናኤል መኮንን መከላከያ ተቆጣጠራት፣ በቤተክርስቲያን ቦንብ ተገኘ የሚለው በዝችኛዋ ውቅሮ ነው።

በዚችኛዋ ውቅሮ ጥንታዊ የማርያም ቤተ ክርስቲያን እና ነጃሺ መስጅድ ይገኛል። ከመቀሌ 47.1 ኪ.ሜ. ትርቃለች።

አንግዲህ ናትናኤል መኮንን የሚባል ሰው በውቅሮ ጥንታዊ የማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ "መትረየስ ቦንብና ቤኒዝንና ተቀጣጣይ ነገሮች ተገኝቷል" የሚለው የፈጠራ ወሬ ነው። እኔም ጦር ግምባር ከሚገኝ አንድ የጦር መኮንን ይሄን አረጋግጫለሁ።

እግረኛው የመከላከያ ኃይል ውቅሮ አልደረሰም። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ግን በመቀለ ኤርፖርት አቅራብያ ያለውን የኮንክሪት ምሽግ እየደበደበ ነው። ናትናኤል ዝምብሎ ያልሆነውን ሆነ እያለ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መትረየስ ቦንብና ቤኒዝን ተገኘ የሚለውን የፈጠራ ዜና እንዲያቆም ንገሩት።

Zemedikun Bekele(zemede)

19 Nov, 12:15


በጫበጩ አያለሁ። አንዳንዶቹ እንዲያውም ከአሐዱ በላይ አሐዱ ሆነው በመንጣጣት የጨዋታውን ዙር እንዲከር ነው ያደረጉት። ካዋጣችሁ ቀጥሉበት። እኔማ ይመቸኛል። ያውም የሚያዋራኝ አግኝቼ ነው? ተናግሮ የሚያናግረኝ አግኝቼ ነው? ወዳጄ እኔ ዘመዴ እንኳን አፍ የሚካፈተኝ አግኝቼ አይደለም እንዲሁም እንዲሁ በደህናው ጊዜም ክፍት አፍ እኮ ነኝ። ኣ

...በተረፈ የተቃወሙአችሁን በሙሉ መንጋ እያላችሁ በመስደባችሁ ቀጥሉበት። መንጋ የምትሉት ህዝብ አእምሮ የሌለው፣ ተራ፣ የማይረባ አድርጋችሁ ነው የምትቆጥሩት አይደል? እናንተ ያልጋገራችሁት ሁሉ ምግብ አይደለም አይደል? የእናንተ አባል ያልሆነ ሁሉ መንጋ ነው አይደል? መልካም ነው መንጋ ያላችሁት ህዝብ በቁምህ ዘቅዝቁ የሰረቅከውን፣ በቤተ ክርስቲያን ስም የዘረፍከውን፣ ቤተ ክርስቲያን የማታውቀውን፣ በስሟ የዘረፍከውን ሁሉ ታስተፋሃለች። ቱ ምን አለ በሉኝ። እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ፣ የድንግል አሽከር ይሄን ነገር ከጫፍ ያላደረስኩት እንደሆነ ከሰው አትቁጠሩኝ። በማኅበሩ ውስጥ ያሉ የምሳሳላቸው ወዳጆቼ ሁኔታ ይዞኝ እንጂ አሳያችኋለሁ። ጠብቁኝ። በስም እየጠራሁ፣ በመረጃ መነጋገር እንጀምራለን።

... ግለሰቦች በማኅበሩ ስም ያሳተሟቸው መጻሕፍትን ማነው የሚበላቸው? የዶክተር አለማየሁ ዋሴ ድርሰቶች የማን ገቢ ናቸው? ማነው የከበረባቸው? በገዳማት ስም የመጣው ብር የገዳማት ኃላፊዎቹ እንዴት ነው የከበሩበት? ከውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ደም ተፍቶ የሚልከው ብር የት ነው የሚገባው? የገዳማት ኃላፊዎቹ ስንት ሱቅ፣ ስንት አይሱዙ፣ ስንት ውብ የሆነ ቢሮ ነው ያላቸው? ራሴ ወዳጅ አድርገው ያስጎበኙኝን እኮ ነው የምነግራችሁ። የማኅበሩ ነውረኛ አመራሮችን የሚስታቸውን ባንክ ሂሳብ ሳይቀር ብትመለከቱት ታፍራላችሁ። ምድረ ሌባ ሁላ ከሚመጣው መከራ አታመልጣትም። ጠብቀኝ።

… በቀጣይ የፋንታሁን ዋቄን እየዬ እንተነትናለን። ከዚያም የጉራጌዎቹ የአቢሲኒያ ባንክ አራቋች የነበረው የአቶ አንተነህ ሰብስቤና የመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የነበረው የማኅበረ ቅዱሳን መስራች አሁን የአሐዱ ባንክ የአደራጅ ቦርድ ተደርጎ በሂዊ የተሾመው የአቶ ካሳሁን ኃይለማርያም እና የአሐዱ ባንክን የፕሮጀክት ማናጀር አድርገው የሾሙት፣ ዕዳውን ሁሉ በአናቱ የከመሩት የአቶ ነቢየ ልዑልን ጉዳይና ዝርክርክነት እናያለን። ውዝግቡ ጦዟል። እኔ ደግሞ አኞ ነኝ። ከነከስኩ ካላደማሁ አልፋታም። ሁል ጊዜ ከተገፉ ንፁሓን ጎን ነኝ። ሌላህ ስትንጫጫ ውለህ እደር። ለምድረ ነጠላ ለባሽ አስመሳይ ሌባ ሁላ መስሚያዬ ጥጥ ነው።

ከኑመ ጋ ዱቢን !!

Zemedikun Bekele(zemede)

19 Nov, 11:50


ሰበር ዜና‼️

-የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመቀለ ኤርፖርት አቅራብያ ያለውን የኮንክሪት ምሽግ እየደበደበ ነው። አየር ሀይሉ በያዘው ድብደባ የመቀለን ኤርፖርት ሊቆጣጠር የቅርብ ቅኝት ላይ ይገኛል።

-የትግራይ ክልል አመራሮች ለሁለት ተከፍለዋል ተብሏል።
ግማሹ እጅ እንስጥ ሲል፤ ሌሎች እየተዋጋን እንሞታለን እንጅ እጅ አንሰጥም በሚል ጭቅጭቅ ላይ ደርሰዋል።
@endenaendena