ሁላችንም እንደምናውቀው ሴቶች ከሌላው ጌዜ ለየት ያለ ምግቦችን በረመዳን በማዘጋጀት ይጠመዳሉ። እናም ሌሎች የኢባዳ ተግባራትን ለመፈፀም ጊዜ ያጣሉ። ቀኑን በድካም ስለሚያሳልፉ ማታም ሱሁር ለማዘጋጀት ሲሉ በጊዜ ለመተኛት ይገደዳሉ።
እናም ረመዳን የምግብ ሳይሆን የኢባዳ ጊዜ ነው! በማለት ኡለሞችና ሙስሊም ማህበረሰቦች በተለያዩ አጋጣሚ ይመክራሉ።
ሆኖም መዘንጋት የሌለብን ምግብ መስራትም ኢባዳ እንደሆነ ነው። ምግብም ሆኑ ሌሎች የቤት ስራዎች በሙሉ ኢባዳ ናቸው ፤ ኒያችንን እስካስተካከልን ማለት ነው።
ሆኖም ይህ የረመዳን ወር ራስን ለመለወጥና ኸይር ስራ ለማብዛት ምርጥ ጊዜ በመሆኑ ፤ ይህን እድል በአግባቡ ለመጠቀም ብልጥ መሆንና ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ተገቢ ነው።
Tip
1, ለሳምንት ሚሆነውን ተጋግዞ አንዴ ማዘጋጀትና ከፍሪጅ በመጠኑ መጠቀም
2, ስራ እየሰሩም ቁርአን ማዳመጥና ዚክር ማድረግ
3, የሰላት ወቅቶችን በአግባቡ መጠበቅ
4, ጥሩ ልማዶችን ማዳበር
5, መጥፎ ልማዶችን መቀነስና
የመሳሰሉትን እያደረግን ረመዳንን በጥሩ ሁኔታ ማሳለፍ እንችላለን።
በተለይ በስራ ከመጠመድ ውጭ አማራጭ የሌላችሁ እህቶች ይህችን ሀዲስ ሁሌም እያስታወሳችሁ ፤ ምንም ሳታዝኑ ስራችሁን በደስታ ስሩ።
"ስራ ሁሉ በኒያ ነው !!" ቡኻሪ 1:1
አላህ ረመዳንን በአግባቡ ከሚጠቀሙት ያድርገን